ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?
ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?
የተከበረው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን "አህያውን ፈርቶ መደላድሉን" እንዲሉ ብሄራዊ ሆኖ ግን የእስረኛ ፍቺን አስመልክቶ፤ የአማራ ክልል ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከሩ ግርም አለኝ። #አዝኛለሁም። በእድሜ ዘመኑ የ365 ቀናት በራሱ አቅም የመንቀሳቀስ ምንም አቅም የሌለውን አልቦሽ ክልል ላይ ሃሳቡን ማቅረብ በራሱ ኮሚሽኑን ግምት ውስጥ ይጥላል።
የሆነ ሆኖ አጠቃላይ የፖለቲካ እስረኞች የእስር ፍቺ #በብሄራዊ ደረጃ ቅድሚያ ተሰጥቶት፦ በበኽረ ጉዳይ አጀንዳነት ተይዞ ሊሠራበት ሲገባ እንደ ተራ #ተለጣፊ ጉዳይ፦ የአማራ ክልል እስረኞች ብቻ እንዲፈቱ መጠዬቁ ኮሚክ እሳቤ ሆኖ ነው ያገኜሁት። ቀድሞ ነገር የህወሃትን መንበረ ሥልጣን እንዲለቅ ምዕራብውያንን ያሳመነው መሠረታዊ አንኳር ጉዳይ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ነበር። ያንጊዜ ተደማሪ፤ #ተጠማኝ፤ ተዋህጂ ስስ ስለነበር በዬትም ሁኔታ የሚደመጠው ድምጽ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ነበር የትግሉ ሞቶ። እናም አሳካን።
የሆነ ሆኖ የአማራ ጉዳይ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የአብይዝም መንግሥት በቆራጥነት ሊወስዳቸው ከሚገቡ መቅድመ እርምጃወች ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የፖለቲካ እስረኞችን #ያለምንም #ቅድመ ሁኔታ መፍታት ለቀጣዩ የፖለቲካ ንግግር ይሁን ስምምነት በር ከፋች ይሆናል።
እንደ እኔ ምኞት እና ተስፋ በኢትዮጵያ ምድር ማንም በአስተሳሰቡ፤ በምልከታው፤ በፖለቲካ #አቅሙ እና #አቋሙ አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊታሰር፤ ሊንገላታ፤ #ቤተሰቡ #ሊጉላላ አይገባም። በእስር ምክንያት የመኖር ተስፋው ሊዘረፍ፤ ወጣትነቱን ሆነ የቤተሰብ ኃላፊነቱን ካቴና ቅርጥም አድርጎ ሊበላው አይገባም። በታወቀም ይሁን ባልታወቀ ሁኔታ በቁም እስርም ጭምር ያሉ ወገኖቻችን ከእስር ይፈቱ ዘንድ የሁሉም አጀንዳ ሊሆን ይገባል። አይደለም ለምክክሩ ኮሚሽን።
እስር ጭካኔ ነው ለእኔ። የምክክር ኮሚሽኑ ጭካኔን ሊያበረታታ አይገባም። በድሮን የንጹኃን ጭፍጨፋም የምክክር ኮሚሽኑ ምንም ሲል አይደመጥም። መጀመሪያ የምክክክር ኮሚሽኑ ሰው የመሆንን ሚስጢር ሊቀበል እና በዛም ሊተጋ ይገባል ባይ ነኝ። እስር ሳይለንት ዲስክርምኔሽን ነው - ለእኔ። እስር ሳይለንት ኔግሌሽን ነው - ለእኔ። ከፍ አድርገን ስናስበውም ለምን #ሰው #ሆነህ በዚህች ምድር ተፈጠርክም ነው። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተለመደው ሥልጣን ላይ ያለ ኃይል ሁሉ ሃሳብን #ሲፈሩ ካቲናን የዜጎች ቀለብ ማድረግ የተገባ አይደለም። #ኢትዮጵያም ነው #አብራ የምትታሠረው።
ስለሆነም የተከበረው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ኢትዮጵያን ከእስር ያስፈታ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁኝ። ትውልድ ስጋት ላይ ነው ያለው። ትውልድ ፍርኃት ላይ ነው ያለው። ፍርኃት እና ስጋት ደግሞ የሥነ ልቦና ችግር ያመጣል። ይህ ደግሞ ለአገር፤ ለተስፋ፤ ለአደራ ለማግስት #ጠንቅ ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፥ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/04/2025
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ