#በዛሬ ውስጥ ነገን አደላድሎ ስለመምራት ይቻል ይሆን። Ja! ይቻላል! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08/04/2023

 

#በዛሬ ውስጥ ነገን አደላድሎ ስለመምራት ይቻል ይሆን።
Ja! ይቻላል!
"አድርገህኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
 

 
!እንዴት ይቻላል?
#መነሻን አክብሮ በመነሳት ይቻላል።
#መድረሻን አክብሮ በማቀድም ይቻላል።
#አገናኝ ድልድይ ዘመናትን አዋዶ በመነሳትም ይቻላል።
#ትናንትን በዛሬ ማድመጥ ነገን ዛሬን አደላድሎ በማበጀትም ይቻላል።
ዊዝደሞቻችን ትናንትን ሳይሞት ያቆዩት እንዴት?
በምን ስሌት?
ትናንትን ሬሳ ክምር ለማድረግ 50 ዓመት ተጉዘን አመድ እና በቀል ተቸረፈሰ። ታስታውሳላችሁ ጦርነቱ ሲወጠን በጦርነት አትራፊነት የለም። አትራፊ አለ ከተባለ #በቀል እና #አመድ ነው ብዬ ሞግቼ ነበር። ዓለምንም በራሽያ እና በዩክሬን ጦርነት ሞግቻለሁኝ። ይህም ብቻ ሳይሆን ጦርነትን የሚፎካከሩ ተቋማት ከመገንባት የፍቅር ተፈጥሯዊ ህግጋት የሚገነቡ #ክፋ ዕሳቤወችን የሚመክቱ ተቋማት እና ፍልስፍናወች ላይ ይተኮር ሌላው በአጽህኖት የፃፍኩት በአማርኛም በጀርመንኛም ነበር። በሌላ በኩልም ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የአገር መሪ አያደርግም፤ ዬአገር መሪ መሆን ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ ያደርጋል ብዬም ጽፌያለሁኝ።
ግድፈቱ ብሄራዊ ብቻ አይደለም ሉላዊ ነው። ዓለም ከአናሎግ ወደ ዲጅታል ስትሸጋገር ጦርነት እና መንስኤወቹን የሚመክት አቅም ሳታበጅ ነው። መመከቻ የሃሳብ አቅም የላትም። ሥልጣኔን ሥልጣኔ ሲያወድም የራሽያ እና የዩክሬን ጦርነት በቂ ነው። በብድር በትውስት ርዮት የተቀመረው ማህበረ ኦነግ የተደራጀን ተቋም በማፈርሰ ኢትዮጵያ ዬተበደረችውን ሳትመልስ ዕዳውንም አመዱንም በማውረስ ለትውልድ ሥልጣኔውን ለአመድ ሲሸለም በአገራችን በኢትዮጵያ በገሃድ አይተናል።
ለምን? እሬሳ፤ በቀል፤ ቂም፤ ቅናት አንዱ ለአንዱ ስጋት የእኔ ብሎ ካለማድመጥ የመጣ ነው። የዩክሬኑ መሪ በአንድ ቃል ይህን ሁሉ ውድመት ማስቆም ይችሉ ነበር። "ራሺያ ዩክሬን ኔቶ ከገባች ስጋቴ ነው ስትል። የራሽያን ኢሊት ትተው ማለቴ ነው ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ እኛ ለራሽያ ህዝብ ስጋት መሆን አይገባንም፤ ስጋታቸው ዬእኛ ልንለው ይገባል። ቢሉ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ባልታዬ ነበር። ቅድስቷ ሲዊዝ የኔቶም የአውሮፓም አገር አባል አይደለችም። ግን ትኖራለች። የጥንት ሥልጣኔወቿን ጠብቃ ዬዛሬውንም ለህዝብ ጠቀም አውላ ማለት ይገባ ነበር ተፅዕኖ ፈጣሪው አርቲስት ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ።
ተጽዕኖ ፈጣሪነት አገር መምራት ሊሆን አይችልም እምላችሁ ለዚህ ነው። ራሺያም እኔ ለዩክሬን ሉዓላዊነት ስጋት ከምሆኑ እሷን ከሚያሰጋት ጉዳዮች እታቀባለሁኝ። ዬዩክሬን ህዝብ ስቃይ፤ መከራ ስጋት የእኛም ነው ቢሉ በቃ ይህ ሁሉ ቋያ በሰማይም በምድርም አይወርድም ነበር። ሁለቱም አገሮች ራሽያ እና ዩክሬን ቢያንስ ሁለተኛው የዓለም ጦርነቱን የህሊና መተግበሪያ፤ መግሪያ የፍላጎታቸው ሚዛን ማስጠበቂያ ሊያደርጉት ይገባ ነበር።
ወደ እኛ ስመጣ ስመ ጡር ፀሐፊ እና አስተዋዩ አቶ በሪሁን ከበደ በአብረንታት ገዳም ላይ በፃፋት ኢትዮጵያ ከ4ሺ ዘመን በላይ የሚዘልቅ ታሪክ እንዳላት ዋቢ አቅርበው ጽፈዋል። የተጋሩ ኢሊቶች መነሻቸውን ክደው እራሳቸውን በእራሳቸው የሚያጠፋ ዘመን፤ ሰነድ አበጁ። ዛሬ ከፈጠሯቸው ከኦህዴድ፤ ከአቶ አባ ዱላ ገመዳ ዕሳቤ በታች ሆነው ምህረት እና ፍርፋሪ ይለምናሉ።
ዛሬ ገዥ ነን ዬሚሉትም በተሠራ አገር ላይ ዬተረከቡትን ማስቀጠል ሲገባቸው ትናንትን፤ ከትናንት በስቲያን ተጠይፈው እንዲያውም እዬነቀሉ፤ እዬደረመሱ ትቢያ እያለበሱ ጣሪያ በሌለው ድንኳን ውስጥ ይታያችሁ ይሰማችሁ #በሌለ ዛሬ ነገን እንሠራለን ብለው ሲደናበሩ አስተውላለሁኝ። የቆሙበትን መሬት የአጥንት የደም ዋጋ የተከፈለባት ናት። እነሱ ሳሉም ባሉኑሩበት ዘመንም። ግን ያን አገናኝ ድልድይ ደርምሰው መጭ እያሉ ነው። በዚህ ውስጥ #ቁጣው - አመጽን፤ #አመጽ - ቂምን፤ #ቂምን - በቀልን እያዋለደ እያጣፋ ዛሬን #እሬሳ አድርጎ ነገን ያከስማል።
ከማይጨው፤ ከአንባላጌ፤ ከአድዋው፤ ከካራማራው፤ ከባድመው ያልተማረው የተጋሩ እና የኦሮሞ ሊቃናት ዘመን በሰጣቸው የዕድል በረከት እና ልዕልና በዛሬ ውስጥ ነገን ማበጀት ተስኗቸው አልፈው ሄደው ትናንትን በበቀል እና በማንአህሎኝነት አፈለሱት። አሁን ህወሃት በአማራ እና በአፋር ክልል ሠራሁ ያላቸውን ፀፅቶት አመድ አደረገው፤ ኦነጋዊው ኦህዴድም አጣዬን 10 ጊዜ፤ ሽዋ ሮቢትን፤ ዝዋይን፤ ሻሸመኔ፤ አርሲ ነገሌን ደጋግሞ ዬአመድ አፓርትመት ሠራበት። በዚህ ውስጥ ትናንት አቶ ጎልጉል አቶ ሽመልስ ሸገር አዲስ አበባን ጨፍልቃ ናዝሬትን የአፍሪካ መናህሬያ የፖለቲካም የኢኮኖሚም እናደርጋታለን። ይህን እዬሠራነው ነው።
ጠላቶቻችን ገብቷቸዋል። የእኛወቹ አልገባቸውም። እኛ ግን ለ20/30 ዓመት እዬሠራን ነው። ይላሉ ዛሬ እንዴት እንደ ተገኜ ተዘሏል። ጠላቶቻችን የሚሉት የአማራ ውክል ብአዴን ሙሉ 45 ድምፁን አሽሮ ነው ለዚህ ዬተበቃው። በሎቢም ጠንካራ ሥራ ተሰርቶ። እነሱ በዛሬ ውስጥ ነገን የሚመሩት ትናንትን አፍርሰው ነው። የቆሙባት መሬት ግን ዬትናንት ጥረት እና ስኬት ነው። ይህን አንድም የተጋሩ ልሂቅ ልብ አይለውም። እንዴት የፈጠሯቸው እፋኝት አመድ እንዳደረጓቸው አይረዱም። በትናንት በቀደመው ውስጥ ተጋሩ፤ ሱማሌ፤ አዳል፤ አፋር፤ ጉራጌ፤ አማራ ወዘተ አሉበት።
ሌላው ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና መሪነት ተዳብለው የትውልድ ተስፋ እና መሰረት የሚሆኑት ባልተፈቀደ የአመራር ባዕት አናርኪ በሆነ ሂደት የአመራር ተዋረዱ ውጥንቅጡ በወጣ ሁነት ዬሃሳብ ሬሳን ማሸከሙንም አስተውያለሁኝ። በዛሬ ውስጥ ነገን መምራት የሚቻለው በሽምጥ ግልቢያ አይደለም። አገናኝ ድልድይ ክፍተትን አሟልቶ እና አጣጥሞ፦ ሥርዓት ተከትሎ የአስተዳደር ዬአመራር ወሰኔን ሳይጥሱ ትንንትን፤ ከትናንት በስቲያን እንደ ፒላር ሊያቆም ይችላል ዬተባለው መንፈስ ራሱን ችሎ የወጣ የአማራ ፖለቲካን ጥገኛ አድርገው አይሆኑ አድርገው አስመቱት። አንኮላሹት።
ከቲም አንባቸው ሰማዕትነት ጀምሮ ይህ ያልተገባ ጉዞ ያመጣው ጦስ ነው። ተፅዕኖ ፈጣሪነት በተሆነበት አመክንዮ እንጂ በመሪነት ሊሆን አይችልም። ኢብን ፖለቲካ ሳይንስ ቢጠና እንኳን መሬት ላይ ፋንክሽነሪ ሆኖ የመሥራት ዕድሉ ከሌለ የእንቧይ ካብ ነው። ሌሎች ሲመሩ የገደፋት በተንጠራራ ፍላጎት በዛለ አቅም ያ ሁሉ ተስፋ ረገፈ። ሁሉም ነገር ከሙት መሬት ጋር ተቃቀፈ። ተው ስንል እንኳን ሰሚ አልነበረም።
በዚህ ሁሉ መዳኛ ፈውስ ይሆናል ዬሚባለው የኢትዮጵያኒዝም በትረ መንፈስ ደቀቀ። እራሱን ችሎ መውጣት ተስኖት የህወሃት እና የኦነግ ደጋፊ ባለፈም ኤርትራን ጥሪኝ በሚሉ #በተዥጎረጎሩ ዝልኝ እና ዝርክርክ ፍላጎቶች ዛሬ ኢትዮጵያ ነገን ማበጀት ሳይሆን የትናንት እና የትናንት በስትያዋን ማህለቅም እንድትስት በወጀብ እዬተናጠች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ዬከበደችው ለኦነግወህወሃት ብቻ አይደለም። ለኢትዮጵንይዚም አራማጁም ነው። አያውቋትም አታውቃቸውም።
#ሰብሰብ አድርጊ ሳቀርበው።
1) መነሻን ማወቅ አክብሮ መቀበል።
2) መሪነት ለሥርዓት ስለመገዛትን መልመድ። ለዴሞክራሲ መታገል እራስን ለስርዓት ከማስገዛት ይነሳል።
3) ዬአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሲነሳ በግሎባሉ ዕውቅ ሳይንቲስት መሪነት ትውልድ ባልተካቸው በፕሮፌሰር አስራት ወልደዬስ ነው። ይህ ልብ ሊባል ይገባል።
#ዕውቀት ዬተፈጥሮ ከፀጋ የሚገኝ፦
#ከቀለም ትምህርት የሚገኝ እና ከማህበረሰቡ የሚመነጭ ነው። ይህን ያጣመረ ልዑቅ የመራው ተጋድሎ ዛሬ የአገኜ ያሻውን እንዳሻው ሲወራኝበት ንዶም ሲሾልክ አያለሁኝ።
#ዕውቀት #ዕብደት #ሊሆን #ከቶም #አይችልም። ከወፈፌ እርግጫ እና ፍጥጫ፤ ከአቲካራ እና ከምልልስ አታሞ ወጥቶ ክፍት የሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊሞላ የሚችል አማራዊ ስኩን ፖለቲካን ርጉ ተናዳፊ ያልሆነ፦ ግጭት ናፈቀኝ የማይል፦ ልቆ የሚፈልቅ አዳኝ ሃሳብ ይሻል።
ከዚህም ከዚያ ሲባዝኑ የባጁ ነፍሶች ለትግሉ አይሆኑም። ከዜግነት ወደ አማራ ፖለቲካ፤ ከዞግ ወደ ዜግነት፤ ከዛው ከአንዱ ዘውግ ድርጅት በመዘዋወር በውራጅ እና በትውስት ፍላጎት ተቀይጦ የፈለገ ቢጽፋ የፈለገ ቢያነቡ ለግብ አይበቃም።
ምክንያት ፦፦፦ ከቀደመ ማንነታቸው ጋር ስለሚጋጭ፤ ብአዴን ዬአማራ ነው። አመሰራረቱ ለአማራ ተጋድሎ እና ህልውና አይሆንም፤ ዬተነሳበት የሶሻሊስት የሰው ዘር ይሆናል ነው። የዜግነት ፖለቲካ አራማጆቹም አይሆኑትም ለአማራ ማንነት እና የህልውና ተጋድሎ። ለምን ተጋድሎ የራሱ ባህሬ፤ የራሱ ማንነት ስላለው። ግጭቱ ይህ ነው። በዚህ ውስጥ ዬተወለደው አናርኪ ብዙ በጣም ብዙ ነገር አሳጥቷል።
4) ተጋድሎውን ያኮሰሰው ተጋድሎውን ተሻምተው አቅሙን ለአቅመ ቢሱ ለዜግነት ፖለቲካ እናደርጋለን ያሉትም እራሳቸውን ማዳን ሳይችሉ በቁማቸው እያሉ ሃሳባቸው ፈርሷል። ደመ ነፍሳቸውን ካለ አድራሻቸው ያልተፈለገ መገበርን ዬእኔ ብለው ዬእኛ በሉልኝ ሲሉ አያለሁኝ። ክብር በተለይ ሰው ተስፋ ያደረገው ክብር እንደ ብርጭቆ በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባል። ወርቅ ከፈሰሰ አይታፈሰም። ሁሉ ቢቻልም ሁሉ ግን አይሆንም መጥኖ ካልተነሱት። ሌላው ሶስት ቀን መጠሞን ያቃተው 360 ቀንን የሚፈቅደው ሲወድቅ ነው። ፈጣሪን ስታመሰግነው የማድመጥ ጊዜ ሰጥተኽው ነው። ይህንንም በአጽህኖት ነግሬያለሁኝ። አልሆነም።
ባለመሆኑም በምርጫው አዲስ አበባ ላይ አንድ ቀንጣ ነፍስ ኦነግን አሸንፎ ሊወጣ አለመቻሉን አይተናል። የአማራ ተጋድሎ እና የማንነቱ ሰማዕትነትም አዲስ አበባን ትቶ አስረክቦ በፈቃዱ አማራ ክልል ብቻ ተወዳደረ። ይህን ያስደረጉት አማራ ይደራጅ ለቡና ተርቲም ነው እንጂ ለፖለቲካ ሥልጣን ሊሆን አይገባም ብለው ካራገፋት በኋላ ለአጃቢወቻቸው በግልጽ አደባባይ ወጥተው ይናገራሉ።
ጉልበት አወጣልን ብለው ያሰቡትን በስል ገብተው የሚከስሙትን አራግፈው የሚያጎሉትን ካደመቁ፤ ዬተተረተረውን ኢህአዴግ የጫጉላ ሽርሽር ማግስት። ይህ መንፈስ ነው ልዩ ኃይል፤ ሚሊሻ ፈርሶ የአማራ ህዝባዊ ኃይል ስትራቴጅስት የነበረው። ህወሃት አቅም ቢያገኝ አጋዥ እንዲሆንም ይመስላል። ጥንስሱ። ብቻ እነ ማሞ ቂሎን መልምለው ሃሳቡን አመድ ካስጋጡ በኋላ ከአልባሌ የሃዘን ሰሞናት ወደ ገበርዲን ሽር ብትን እያሉ ነው። በያንዳንዱ መስመሩን በሳተ ሂደት በዛሬ ውስጥ ነገን ለመምራት ሳንክ የሚሆኑ አመክንዮወችን እዬነቀስኩኝ ሞግቻለሁኝ። ዛሬ እኔ ከኮሽ አይሏ ሆኜ ትርምስምሱን አስተውላለሁ።
5) በቅድሚያ የአማራ ዬማንነት እና የህልውና ተጋድሎ በደራሽ የድል አጥቢያ አዝማቾች ቅጥ መጠኑ ጠፍቶ ህዝባችን ለበለጠ በቀል እና ለበለጠ ጥቃት ተዳርጓል። መሪዬ ስትል ትናንት ነበር ወይ በዚህ የትግል ባህሪ ውስጥ ብሎ ተግ ብሎ ማድመጥ ይገባል። ሰማኑን ከሚኒሊክ ሚዲያ ጋር የተፈጠሩ ሰብዕናወችን ጀግናዬ ሲባልም አዳምጫለሁኝ። ከሌለ፤ ካልነበረ የት ያመጣዋል። ልጥፍ ነው የሚሆነው።
አዲስ ገቦችን እንደ አመጣጣቸው ተቀብሎ ቀደምቶችን መሪነቱን በዕውቀት በሥልጣኔ በአክብሮት እንዲመሩት ማድረግ ሲቻል ነገ በዛሬ ውስጥ ይበቅላል፤ ነገ በዛሬ ውስጥ ይመራል። በውራጅ ፖለቲካ፤ በጥገኝነት አቅም ህልውናን ማትረፍ አይቻልም። ለመሆኑ ቀደምቷ ዬአማራ እናት ክብርት ዶር አበባ ፈቃደ ዬት ሄዱ። መነሻን ስቶ በዛሬ ውስጥ ነገን መምራትም፤ ማግኜትም አይቻልም። ፈጽሞ።
6) ፕሮፖጋንዳ እንደ ትግል ፖሊሲ የማዬት ሂደት። ፕሮፖጋንዳ #አሉታዊ እና #አወንታዊ ተብሎ ይከፈላል። ተምሬውምአለሁ። ከንግግር ጥበብ ፔሬድ ጋር። ፕሮፖጋንዳ የፖለቲካ ትምህርት ክፍለ አካል ነው። አሉታዊም ይሁን አወንታዊ ፕሮፖጋንዳም ብቁ አስተዳዳሪ ይሻል። በአሉታዊ አዶልፍ ሂትለር እና ቤንቶ ሞሶሎኒን ማንሳት ይቻላል። የወጣላቸው ተናጋሪም ፕሮፖጋንዲስትም ነበሩ። ብዙ ጊዜ ፕሮፖጋንዳ ለጦርነት ወቅት እና ለደራሽ ጉዳዮች መካች ሊሆን ይችላል። ለህልውና ተጋድሎ ግን #ጥንቃቄ ይሻል። ዛሬ ማህበራዊው ሚዲያ ዘውድ የደፋ የራሱ ንጉሥ እና ፓርላማም ነው።
የአማራ ትግል #የህልውና ብቻ አይደለም። የአማራ ትግል #የማንነትም ነው። መነሻው ይህ መሆን ይገባል። ሁለቱንም አጣምሬ እምታገለው እኔ ብቻ ነኝ ማለት እችላለሁኝ። ሁለቱም እራሳቸውን የቻሉ፦ የገዘፋ ሲቻል በተናጠል፤ ሲቻልም ተጣምረው በትግል መስመር ውስጥ ተዋህደው በቂ ዕውቅና ሰጥቶ መንፈሳቸውን ማታገል ካልተቻለ ለዛሬ 20/30 ዓመት ለአማራ ትውልድ ሳንክ ይሆናል።
በማንነት ውስጥ ህልውና፤ በህልውና ውስጥ ማንነት መኖራቸውን በአጽህኖት አዋዶ መወጠን የሚቻለው እራስን በዚህ ውስጥ ለማግኘት ፍለጋ መጀመር ሲቻል ብቻ ነው። በስተቀር አንዱን ይዞ ሌላውን አንጠልጥሎ ይሆናል። ያ ደግሞ ከቀንበጥ ተስፋ መቀንጠስ በቀር ያተረፈው አንዳችም ነገር የለም።
በዛሬ ውስጥ ነገን ለመምራት የትግሉን ጭብጥ ባህሬ ከማወቅ፤ ከመቀበል ይመነጫል። ዛሬ እኮ ለዚህ ጨካኝ ዘመን የምርጫ ዕውቅና ላይ ታች በዬሚዲያው ሲሉ የነበሩ ናቸው የአማራን ግሎባል መንፈስ ሲመሩት እማዬው። በዚህ ውስጥ ነገን የመምራት ቅንጣቢ ተስፋ ማድረግ አልችልም።
ፖለቲካ ሰው ነው። ሰው ደግሞ የምሽት ፍጥረት አይደለም። ፖለቲካ ተለዋዋጭ አቋም የሚይዝበት እና የማይዝበት አመክንዮ መለያት ያስፈልጋል። በአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መንፈስ ዶክተሪን ላይ እንደ ሽንብራ ቂጣ የሚገላበጥ ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ አያስፈልግም። መሪም አጋርም አያስፈልግም። ግልጽ እና ቀጥተኛ ጽኑ እና የጠራ አቋም ይጠይቃል።
ጥቂት የተመረቁ፤ ጥራት ያላቸው ዕውነቶች በዛሬን ውስጥ ነገን ሊያበጁ፤ ሊሠሩ፤ ሊመሩ ይችላሉ። አቅማቸውን አስክነው ከቁጣ፤ ከግልምጫ፤ ከጥላቻ፤ ከቂም በቀል፤ ከህግ መተላለፍ እና ከአናርኪ ጉዞ ታቅበው። ነገን ዛሬ መምራት የሚቻለው በዚህ ጥበብ ብቻ ነው። ይቻላልም።
#ዛሬን ለመምራት የተሳነው የአማራ ፖለቲካ ነገን እንዴት?
!ይቻላል።
#በመዋቅር ብዛት?
#በውዳሴ ክምችት?
# …በአጃቢ ብዛት?
#በሠራዊት ብዛት?
እእ! በዚህ አይደለም። ይህ ማህበራዊ ሚዲያ እጅግ ዘመናዊ፤ እጅግ ሥልጡን፤ እጅግም ፈጣን፤ እጅግም ቅን እጅግም ሩህሩህ፤ እጅግም አቀራራቢ ነው። አህዱ ብንለው --- ክለቱ --- ሰለስቱ --- አርባዕቱ እራሱ መስመሩን ይቀይሰዋል። ብቻ አወን ብቻ እራሳችን ቀጥተን፤ አርቀን፤ ገስፀን እንነሳ።
አንድ ምሳሌ ላንሳ ……
በአሁኑ ወቅት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ዕውቅና ያላቸው የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። እሳቸው የሰላም መሪነት አባትነት ለሉላዊው ተሸልመዋል። ሽልማቱ እስኪነሳ ይህ ክብር አለ። ፈጣሪ ፈቅዶ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን እስኪለቁም ድረስ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው። መሪነቱ ለኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለች። አገሬ ኢትዮጵያ ያለ ማንኛውም ዜጋ እናቱን አክብሮ ሊነሳ ይገባል። ክብሩ ለሰብዕናው አይደለም ለቦታው ነው። ይህን መምራት ማስተዳደር ማለት በነገ ውስጥ ዛሬን መምራት ማለት ነው።
ህግ ተላላፊወችን ስትጠዬፍ አንተም ተላላፊ ስትሆን እራስህን አነውረህ ሊሆን ይገባል። ከፊት ከኋላ በሰብዕናው አፈፃፀም ሂደት ጠንካራ ሥሞችን መጨመር ይቻላል። በአሉታም በአወንታም። የኢትዮጵያዊነት ዬአክብሮት ክብር ግን ከጫፋ ድርሽ ሊባልበት አይገባም።
በጀርመኖች የአክብሮት ሰዋሰው አለ። ለሴት እህት sie ብጠቀም ለአክብሮት Sie ኤስ በትልቁ ይፃፋል። እጅግ ነውር ነው አንጠልጥሎ ዘንጥሎ መጥራት። የጥበብ ሰው ጋዜጠኛ ከተሆነ ግን አንቺ ነው። ይህን በራዲዮ ጋዜጠኛም፦ በቲያትርም ኮርስ አይቻለሁ፤ በኮንፒተር በቋንቋ ኮርስ ግን መምህሮቼ እርስወ ብለው ነው የሚጠሩኝ።
ኢትዮጵያም ዬአማራ ህዝብም አክብሮት ተፈጥሯቸው ነው። የአማራ ገበሬ በሬውን በሬ ሆይ! አንተ ሆይ! እያለ አክብሮ እኮ ነው የሚይዘው። ከዚህ ዬሞራል ልዕልና ካልወረድን በዛሬ ውስጥ ነገን መምራት እንችላለን።
በነገራችን ላይ አክብሮት የፍቅራዊነት ተፈጥሮ ምንጭ ነው። እንዴት በቀጣይ እንገናኛለን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08/04/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
በዛሬ ውስጥ ነገን መምራት ይቻላል!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።