ልጥፎች

አክብሮት የፍቅር ተፈጥሮ እንደምን ሊሆን ቻለ?

ምስል
  አክብሮት የፍቅር ተፈጥሮ እንደምን ሊሆን ቻለ? #በርግጥም አክብሮት የፍቅር ተፈጥሮ አካል ነው። #ስትወደው ታከብረዋለህ። #ስትወደው ትንከባከበዋለህ ያከበርከውን ሰብዕና፤ ማህበረሰብ፤ ተቋም አመክንዮም። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ"     ** መነሻ በር። አቨይ አባቴ መምህር እና የቤተ መፃህፍት ሰው ነበር። የዝምታ ንጉሥ ነበር። የአበይን የበቃ ሳቅ አይቼ አላውቅም። የበሞቴ ልዕልቴ የእሽታ ንግሥቴ የእቭዬ ሰብዕና ደግሞ ጠሐይ ነው። ሳቂተኛ ናት። እንዲያውም እናቷ ጢጢዬ አፍሽ የሰፋው ከሳቅ ብዛት ነው ትላታለች። እኔም የሁለቱን አጣምሬ ይዣለሁኝ። ያልሳቅኩበት ፎቶ የለም። ከልቤ ከሆነ ጎረቤቶቼ አብዛኛውን ጊዜ እረፍት ሄዳለች ብለው ስለሚያስቡ ከሩሜ የፀጥታ ግርማ ብዛት፦ ሳቄን ስለቀው ደግሞ ያን ያህል አውዳቸውን አለች ያሰኛቸዋል። ድሮ ድሮ በሩቅ ሰው ሳይ እስቅ ነበር። ዛሬ ዘመኑ አስተማረኝ። ወደ ፍቅር ተፈጥሮም እንዳዘነብል ዬረዳኝ ይኽው ነው። ድሮ ባቡር ውስጥ ሆነ አውቶብስ ውስጥ ባዶ ቦታ ካገኜሁ አስፈቅጄ መቀመጥ ነበር። ዛሬ እንደዛ ዬለም። ሰው የሌለበት ወንበር ፈልጌ እቀመጣለሁኝ። የእኛ ቀለም ያላቸው ሁሉ ዕይታቸው ያስፈራል። አያስጠጋም። ይገፈትራል። ልጅ እያለን እናታችን "እጃችሁን ዘርጉ" ትለናለች። እንዘረጋለን። ከዛ "ጣታችሁን እዩ" ትለናለች። እናውቀዋለን እንላለን። "አታውቁትም" እዩት ትለናለች። እሺ ብለን መዳፋችን አገላብጠን እናያለን። ከዛ "ምን አያችሁ ብላ ትጠይቀናለች።" ጣት መዳፍ እንላታለን። ሌላስ ሌላ ምንም እንላታለን። ወይ ቀድማ የነገረችን እናስታውሳታለን። እሷ ጣቶቻችን እያሻሸች ትንሽ እጣ የቀለበት እጣት ጠቋሚ እጣት አውራ እጣ የሚዛን እ

#ተግባር ትጥቁ ተግባር - ተግባር ስንቁ ተግባር - ተግባር ትንፋሹ - ተግባር ነው! ከሥርጉተ ሥላሴ 19.07.2015 /ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ/

  እንደገና ሥራ ስላስጀመሩን "ሀ" ብለን ለመታገል ፋይል፤ ፎቶ ቪዲዮ ሳስስ ያገኜሁት ነው። ለዛሬም ይጠቅማል። መሪም አቅጣጫ ቀያሽም ለሌለው ትግል ዬተደከመበት ማሳ። በ2015 እንደ አውሮፓውያን የተፃፈ ነው። #ተግባር ትጥቁ ተግባር - ተግባር ስንቁ ተግባር - ተግባር ትንፋሹ - ተግባር ነው! ከሥርጉተ ሥላሴ 19.07.2015 /ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ/   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ / ምሳሌ 16 ቁጥር 9/ #የተግባር ግብ ተግባር ነው! #ተግባር ስርክራኪ የለውም። #የተግባር አሰር የለውም። #ተግባር አቮል ነው። ተግባር በኽር ነው። #ተግባር ዓይነታ ነው። #ተግባር የነጠረ ንጡህና ፃድቅና ፀዲቅም ነው። #ንጡህና ጻድቅ ደግሞ ልክስክስ የሆኑ ጉድፎች ክፍሉ አይደሉም - አይሆንም። #ስለሆነም ተግባር፣ ተግባርን ጸንሶ ተግባርን ይገላገላል እንጂ ተግባር ክፋትን - ቂም በቀልን ጸንሶ ዬእንግዲህ ልጅን - አይገላገልም። #የተግባር ሩኹ ብሩኽ - ራዕይ ነው። #ብሩኽ ራዕዩን ለማግኘት በሠርግና ምላሽ አለመሆኑን ጠንቅቆ - ይገነዘባል። #ተግባር መከራን ለመቀበል፤ ፍዳን - ለመሸከም፤ አሳርን ለማስተናገድ የተዘጋጀን ጀግና - ይደግፋል፤ ይመራል - ያስተዳድራል። #የተግባር ድፍረቱ የሚመነጨው ከተነሳበት እውነተኛ ህዝባዊ ዓላማና ካስገኘው ውጤት - ይነሳል። #አዎን ! የተግባር መነሻው ተግባር ነው። #የተግባር መድረሻው ተግባር ነው። #ተግባር ሁልጊዜም አሸናፊ ነው። #ተግባር ሁልጊዜም ድል ላይ ነው። #ተግባር እንኳንስ እሱ ሊሸነፍ ተሸናፊዎችን ሳይቀር በነጠረ ጭብጥ በመሆኑ - ነፃ ያወጣቸዋል። የተግባር መሳሪያው ተግባር ብቻ ነው። የተግባር ጠበቃው ተግባር ብቻ ነው። የተግባር መከላከያው ተ

#በአማራነት #ቃሉ ኢትዮጵያዊነት ነው።

  #በአማራነት #ቃሉ ኢትዮጵያዊነት ነው።    የአቅሙ ጣዝማም ኢትዮጵያዊነት ነው። ጉዞው የመስቀል የሆነውም ለዚህ ነው። መስቀል ስል የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቼ አይክፋችሁ። ጉዞው መከራን መሸከም ነው ለማለት ነው።   ኢትዮጵያዊነትን ያዋህደ ተፈጥሮ #ለአናርኪዝም ቦታ አይኖረውም። ፈጽሞ። የዓለም ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አዩ፣ አዩ አንድም ቦታ በአማራ ተጋድሎ አናርኪዝም፣ ጭካኔ፣ አረማዊነት አጡ። እናም #በባዶ #ከሰሱ ።   ማይካድራ ላይ አይደለም የአማራ ፋኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊም መብት የላቸውም። ከለውጡ በፊትም ሆነ በኋላ በአፓርታይድ አገዛዝ ትውር የሚል የለም ትግራይ ውስጥ። ስንት ዓይነት መሰናዶ፣ ሰልፍ እንደባጄ ታይቷል። የአሁን እኮ ነው። የአማራ ህዝብ በሚበደለው ልክ አፀፋ ልመልስ ቢል አይደለም ኢትዮጵያ መካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ህውከት ይሆን ነበር። የአማራ ህዝብ የመቻል አቅም ኢትዮጵያን አፅንቷል ትናንትም ዛሬም።   ሌላው ቀርቶ ተፈጥሮውን ሳይቀር ያቃጠለ መንፈስ እንደገና እርዱኝ ብሎ ከእጁ ሲወድቅ የአማራ ህዝብ #በሰማያዊ #ፃድቅ አቅሞ እዬተቀበለ እያስተናገደ ነው። በታሪክ አማራ ወደ ትግራይ ለትምህርት ካልሆነ ተሰዶም፣ ሃብት አፈራለሁ ብሎ አይሄድም። ሃቁ ይህ ነው። የአማራ ህዝብ 50 ዓመት ሙሉ በደሉን ችሎ #ችሎቱን #በአልማዝ አፅፏል። ይህ ህሊና ላለው ሁሉ ዩንቨርስቲ ነው። ዓለምን በሚመለከት ድርጅቶች አሉ ተብሎ እንጂ ተናጠላዊ ተጋድሎ በማድረግ ዝበቱን ማረቅ ይቻላል።   ህወሃት እኮ ቅራቅር ድረስ መጥቶ ሲዋጋ ጥሶ ጎንደር እገባለሁ፣ ባህርዳርን አጋያለሁ ሲል ከዕለተ ማክሰኞ እስከ ቅዳሜ የተፋለመው ህዝብ ነው። ዛሬ እነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚበጠረቁበት ገመና ይህ ነው። ሠራዊቱ የደረሰው ቅዳሜ ነው። ይህን የሚ

በመኖር እና በመሞት መካከል ያለው ልዩነት የመተንፈስ ይሆናል። ማስተዋል ያለብን #እዬተነፈሰም #ተገድሎ #የሚኖር ህዝብ ሊኖር እንደሚችል ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ

 በመኖር ውስጥ ያለ መከራ ቃልህን ጦርነት ከፍተህ ስታወድመው ይሆናል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09/04/2022  ብትን አፈር ያጣ ህዝብ እና መተንፈሻ ያለው ህዝብ እኩል ሊታይ አይገባም። የአፋር እና የአማራ መከራ ከሁሉም የበረታ፣ የከፋ ነው። አያያዙም አስተዳደሩም ብልህነትን ይጠይቃል። ሥርጉተ©ሥላሴ  በሞቅታ፣ በለብታ፣ በግርግር፣ በሁካታ፣ በአፍላ፣ በግንፍልፍ ፖለቲካ አገር ፀኖቶ አያውቅም። አገር በዕውነት፣ በተፈጥሮ ማስተዋል እና ትጋት ብቻ ይፀናል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  ባለቤት ለሌለው ህዝብ ባለቤት ይሰጠው ዘንድ መፀለይ #ትርፍ ሥራችን ሳይሆን #መደበኛ ተግባራችን ሊሆን ይገባል፣ በተለይ አቅም ያላቸው አቨው ሱባዬ ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  09/04/2022  የጭንቅ ዘመን የሰጠው ህዝብ ቢያንስ የመቻል ፀጋውን ማዘረፍ አይኖርበትም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09/04/2022   በመኖር እና በመሞት መካከል ያለው ልዩነት የመተንፈስ ይሆናል። ማስተዋል ያለብን #እዬተነፈሰም #ተገድሎ #የሚኖር ህዝብ ሊኖር እንደሚችል ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09/04/2022  የፈጣሪ ታምር ኢትዮጵያን አይረሳትም ብዬ አምናለሁ። በተለይ እሷን የመሰጠሩ ጠፍተውም አይጠፋም፣ ደክመውም አይደክሙም። ከመልካም ቀን ጋር መገናኜታቸውም አይቀሬ ይሆናል። ሥርጉተ©ሥላሴ  በዚህ ዘመን ያዬሁት የጽናት ተቋም የአማራ እና የአፋር ህዝብ የሰጡን #የፅናት #ሽልማትን ነው። ተመስገን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09/04/2022    የአማራ እና የአፋር ህዝብ መከዳት ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ጽናትን በዕውን እናይ፣ እንማርበትም ዘንድ ፈጣሪ አላህ ፈቀደልን። ተመስገን። ሥርጉተ©ሥ

Sergute Selassie Talent Biographies.

ምስል
                                                      Mein Talent Biographies.       Sergute Selassie Talent Biographies.     The honorary heavenly grace, In the first instance I want to thank you very much for your willingness to look at the multi-purpose information that I am going to provide, and not only this but because you have willingly allowed me to receive my application in an urgent manner, thus it is not I myself who thank you but it is the wisdom king God almighty that give you the grace of wisdom. When I was filling my application form, I gave a brief and even unclear answers for the basic questions that I have been asked.   The reason was even to pass the first turn clearance I have been imprisoned by the language to give a detailed narrative. I should have gone with the time. Accordingly I will provide in the following manner in detail the two basic things and my future hope. I give my thanks beforehand for the time you scarify for my information.     1.