"በዩክሬን እና ሩሲያ የሰላም ድርድር ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት እነማን ናቸው?» BBC. (#ጦርነት እንጂ #የሰላም #ንግግር፤ #የሰላም #ውይይት #ፈጽሞ ሊፈራ አይገባም። Sergute Selassie)
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
"በዩክሬን እና ሩሲያ የሰላም ድርድር ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት እነማን
ናቸው?» BBC.










አሜሪካ፡ ስቲቭ ዊትኮፍ።
አሜሪካ፡ ማርኮ ሩቢዮ።
አሜሪካ፡ ያሬድ ኩሽነር።
ዩክሬን፡ አንድሪ ዬርማርክ (አሁን ከሥልጣን ለቅቀዋል)።
ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ።
ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ።
ሩሲያ፡ ዩሪ ኡሻኮቭ።
ሩሲያ፡ ቭላድሚር ሜዲንስኪ» እነኝህ ከአሜሪካ፤ ከዩክሬን እና ከራሺያ በሰላም ጉዳይ የሚተጉ ሊቀ ሊቃውንታት ናቸው።
ምእራፍ ፲፯
ሰላም አብዝቶ ቅንነትን ይሻል።
ሰላም አብዝቶ ሰብዓዊነትን ይጠይቃል።
ሰላም አብዝቶ አወንታዊነትን ይጠይቃል።
ሰላም አብዝቶ አድማጭነትን ይጠይቃል።
ሰላም አብዝቶ መከባበርን ይጠይቃል።
ሰላም አብዝቶ ታጋሽነትን ይጠይቃል።
ሰላም አብዝቶ አድማጭነትን ይጠይቃል።
• ሰላም አብዝቶ የትውልድ ኃላፊነትን እና ተቀባይነትን የመቀበል ልዩ አርቆ አሳቢነትን
ይጠይቃል።
• ሰላም ናፋቂ ጥርስ ፋቂ አይደለም፤ ጥላቻን ሃራም ባይነት እንጂ። ጥላቻን ከሥሩ
ለማድረቅ ቂም፤ በቀል፤ ግለኝነትንመንቀል የሚችል ብቸኛው ጎዳና የሰላም ሐዋርያነት
ዕድሉን ሲያገኝ ብቻ ነው። ይህን አቃለው፤ ይህን አጣጥለው ሊዩ የሚፈልጉ ሰብዕናወች
ፍላጎታቸው አሳቻ ነው ማለት ይቻላል። ሰላም የትውልድ መዳኛ ነውና።
• የሰላም #ስፍነት ንግግር፤ የሰላም መስፈን ውይይት በሥርዓት ታቅዶ በሚከወንበት
ዓለማችን ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ይህን እንደ ፖለቲካ አቅም ማየት "#ድንቁርና ነው"
ሲባል ስንሰማ ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ዕሳቤው ኩምትርትር፤ ጭብጥብጥ ብሎ ከስሎም
ታያለህ።
በወቅቱ በተከታታይ አብራርቼ ጽፌበት ነበር። አንድ ሰው ቅልጥ ባለ ጦርነት ውስጥ ወደ
አለበት ቦታ አይደለም ስደት ለእረፍት እንኳን አይታሰብም። ሰላም ባላቸው አገሮች በስደት
የምኖኖር ኢትዮጵውያን የምንኖርበት አገር ህዝብ ለሰላሙ የከፈለውን መስዋዕትነት
ቢያንስ ዋጋ መስጠት እንደምን ያቅታል? አንጎልማ ድንቢጥም አላት።
• እኛ የሰው ልጆች #ከድንቢጥ የምንሻለው ህሊና ስላለንም ነው። ህሊና ያለው ሰው
መኖሩን እያኖረ ባለበት አገር ሰላሙ የተጠበቀው አገሬው ቀድምቶቹ አበው እና እመው
በከፈሉት መስዋዕትነት ስለመሆኑ ዕውቅና መስጠት ይገባል። ይህ ዕውቅና መስጠት
ቢታወቅበት በሰላም አገር ተቀምጦ ስለሰላም የሚደረጉ ንግግሮች፤ ውይይቶች እንደ
ፖለቲካ ዕሳቤ ሊታዩ አይገባቸውም የሚል ልሙጥ ዕይታ ማቅረብ "#ደንቆሮው" ማን
ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን።
• የሆነ ሆኖ የዩክሬን እና የራሺያን የፋመ እና የጋመ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት
የትራንፒዝም ጥረት አመክንዮ ሳስብ የኢትዮጵያ ፓለቲካ እና ተስፋው እንደሰው በእጅጉ
አሳዘነኝ። ማነው "#ደንቆሮ" ለሰላም በአቅማቸው ልክ ተከታታይ ጥረት የሚያደርጉ
የዓለም ሊቃናት ወይንስ ለሰላም ንግግር ውይይት ማድረግ እንደ አንድ የፖለቲካ ዘርፍ
ሊታይ አይገባም የሚለው ኢትዮጵያዊው ሰነፍ ዕይታ? መዝኑት።
የሰላም ንግግር፤ የሰላም ውይይት፤ የሰላም ድርድር የዕውቀት ዘርፍ ነው። ዓለምንም
በየዘመኑ ከገጠማት የጦርነት ሱናሜ የታደገ ፈዋሽ ፤ ጉልበታም፤ ለሰው ልጆች እና
ለተፈጥሮ የሚያዳላ ልዩ የአቅም ሞተር ነው። ስጦታውም እንደ ክርስትና አማኞች
የአምላካችን ነው። እንደ ተዋህዶ ፈጣሪያችን የውስጡን ሰላም ትቶልን ሂዷል ብለን
እናምናለን።
• #ትራንፒዝም ውድድር ላይ እያለ ነበር የሰላም ሐዋርያ ለመሆን ሲያቀነቅን የነበረው። ምርጫው የተሳካ ድል ሲያስገኝም መደበኛ ትኩረቱ በጋዛ እና እስራኤል የነበረውን ሁለመናን ጨራሽ፤ አውዳሚ ጦርነትን ለማስቆም፤ የታገቱ እስራኤላውያንን ከቤተሰባቸው ይቀላቀሉ ዘንድ፤ በሥጋ የተለዩትም አካላቸው በምድራቸው እንዲያርፍ በማስደረግ፤ በእስራኤል እስር ቤት ውስጥ የነበሩ ፍልስጤማውያን ከእስር መለቀቀ፤ የጋዛ ኗሪ የነበረበትን ሁለገብ የችግር #ዶፍ ደረጃ በደረጃ ለማቃለል ጥረት ለማድረግ በሁለት ምዕራፍ የተከፈለ የድርድር ረቂቅ ተዘጋጄ። ምዕራፍ ፩ ተሳክቶ እንሆ አንፃራዊ እፎይታ የግራ ቀኙ ህዝብ አግኝቷል። ትልቅ ተስፋ ነው። ምዕራፍ ሁለት ላይ የሃማስ ትጥቅ መፍታት ከፍ ያለው ቻሌንጅ ቢሆንም የሰላም አምላክ እርዳታው ቀጥሎ ለስኬት ይበቃ ዘንድ ምኞቴ ነው።
• ሌላው የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት (ኔቶ፤ የአውሮፓ ህብረት) ያካተተው ግዙፋን የሰላም እጦት ለማስታገስም ትራንፒዝም የተለያዩ ጥረቶችን በትጋት ቀጥሎበታል። ይህም ማለፊያ ጎዳና ነው። እኔ ልመናየ ይህ ጥረት በሱዳን የእርስ በእርስ፤ የኢትዮጵያ የእርስበርስ፤ ህንድም ከአጎራባቾቿ ጋር ወዘተ ያለው የታወከ የግጭት፤ የጦርነት ዓውድ ተቀይሮ ቀጣዩ ትውልድ ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን ይረከብ ዘንድ ጽኑ ምኞቴ ነው። ከሰላም በላይ ለሰው ልጅ የሚናፈቅ የተስፋ በር ያለ አይመስለኝም። መድላትም ይሁን መደህየትም የሰላም ማጣት ከገጠማቸው #ትንፋሽ ያጥራቸዋል።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
---------------------------------------------------
• «በዩክሬን እና ሩሲያ የሰላም ድርድር ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት እነማን
ናቸው?» BBC.
«አሜሪካ፡ ዳን ድሪስኮል
አሜሪካ፡ ስቲቭ ዊትኮፍ
አሜሪካ፡ ማርኮ ሩቢዮ
አሜሪካ፡ ያሬድ ኩሽነር
ዩክሬን፡ አንድሪ ዬርማርክ (አሁን ከሥልጣን ለቅቀዋል)
ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ
ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ
ሩሲያ፡ ዩሪ ኡሻኮቭ
ሩሲያ፡ ቭላድሚር ሜዲንስኪ»
«የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም በሚደረገው ስምምነት ላይ የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር ወደ ክሬምሊን አቅንተዋል።»
«ጉዞው በዩክሬን ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ውስጥ የቅርብ ጊዜው እርምጃ ነው።»
«ከሁለት ሳምንታት በፊት አሜሪካ ለሩሲያ ያደላ እንደሆነ በሰፊው የተነገረ 28 ነጥብ ያለው የሰላም ዕቅድ ለኪየቭ አቅርባለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጄኔቫ እና ፍሎሪዳ የአሜሪካ-ዩክሬን ውይይት ተደርጓል። ነገር ግን በውይይቱ ውስጥ የተሳተፉት ቁልፍ ተደራዳሪዎች እነማን ናቸው?»
• አሜሪካ፡ ዳን ድሪስኮል
«የ39 ዓመቱ ድሪስኮል በታሪክ ትንሹ የአሜሪካ ጦር ዋና ፀሐፊ እንዲሁም የምክትል ፕሬዝዳን ጄዲ ቫንስ የቀድሞ የክፍል ጓደኛ እና የቅርብ አጋር ናቸው። የአሜሪካ የሰላም ዕቅዶች ሾልከው ከወጡ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፤ ባለፈው ወር በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ በተደረገ ልዑክ ውስጥ በድንገት ከተካተቱ በኋላ ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረገው ድርድር ውስጥ ማዕከላዊ ሰው ሆነዋል።»
«ድሪስኮል የወደፊት የአሜሪካ የመከላከያ ፀሐፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነግሯል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው መጀመሪያ ላይ የጦር ሠራዊት ፀሐፊ አድርገው ሲሾሟቸው፣ "የለውጥ ወኪል ሆነው ለማገልገል ከፍተኛ የልምድ ጥምረት እንዳለባቸው" ተናግረዋል።»
• አሜሪካ፡ ስቲቭ ዊትኮፍ
«የትራምፕ የሪል ስቴት እና የጎልፍ አጋር የሆኑት ዊትኮፍ መጀመሪያ ላይ በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሹመዋል ነገር ግን የአሜሪካ ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ድርድር ቁልፍ አካል ሆነዋል። ጦርነቱን ለማስቆም የሞስኮን ጥያቄዎች ቅድሚያ በመስጠት ትችት ይቀርብባቸዋል፤ እና በዚህ ዓመት ወደ ኪየቭ ሳይሄዱ የሩሲያ ዋና ከተማን ብዙ ጊዜ ጎብኝተዋል። ይህ ፑቲንን ለማግኘት ወደ ሞስኮ ያደረጉት ስድስተኛ የታወቀ ጉብኝታቸው ነው።»
• አሜሪካ፡ ማርኮ ሩቢዮ
«የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአገሪቱ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሩቢዮ በጄኔቫ የአሜሪካን ልዑክ መርተዋል፤ የቅርብ ጊዜው የሰላም ዕቅዱ ረቂቅ ማሻሻያዎችን አድርገዋል። በታሪክ ውስጥ በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች ይልቅ ሩሲያን የበለጠ የሚተቹ ናቸው ይባላሉ።»
በፍሎሪዳ በተካሄደው የሰላም ድርድር ቅዳሜና እሁድ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ የቅርብ ጊዜው የዲፕሎማሲ ዙር "ጦርነትን የሚያቆሙ ውሎችን ብቻ አይደለም" ብለዋል።
"ለዩክሬን የረጅም ጊዜ ብልጽግና ውሎችም ጭምር ነው... ዛሬ በዚያ ላይ እንደሰራን አስባለሁ፣ ግን ብዙ የሚቀር ጉዳይ አለ።"
• አሜሪካ፡ ያሬድ ኩሽነር
«ኩሽነር የትራምፕ አማች ሲሆን በፕሬዚዳንቱ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን እንደ ከፍተኛ አማካሪ ቁልፍ ሰው ነበር። በዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነቶች እና በንብረት ልማት ይታወቃል። የ44 ዓመቱ ሰው በዚህ ጊዜ በትራምፕ አስተዳደር ውስጥ ኦፊሴላዊ ሚና ባይጫወትም፣ በዚህ ሁለተኛ የሥልጣን ዘመን በዋይት ሐውስ የዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች ወቅት እንደ አማካሪ ሆኖ ያገለግላል። በቅርቡ በዩክሬን የሰላም ድርድር ውስጥ እየተሳተፈ ነው።»
• ዩክሬን፡ አንድሪ ዬርማርክ (አሁን ከሥልጣን ለቅቀዋል)
«ባለፈው ሳምንት በፀረ-ሙስና ዘመቻ ከተደረገ በኋላ ከሥልጣናቸው ከመልቀቃቸው በፊት፣ ዬርማክ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ የረዥም ጊዜ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የአገሪቱ ዋና ተደራዳሪ ነበሩ። የጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ እንደመሆናቸው መጠን፣ በመንግሥት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከፍተኛ ሥልጣን ነበራቸው እና ወሳኝ የሰላም ድርድሮችን እንዲመሩ በዘሌንስኪ ተሹመዋል። ባለፈው ሳምንት የፀረ-ሙስና መርማሪዎች በኪየቭ የሚገኘውን ቤታቸው ከወረሩ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የፖለቲካ ስራቸው በድንገት አክትሟል።»
• ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ
«ኡሜሮቭ የዩክሬን ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ኃላፊ ናቸው። ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በፍሎሪዳ በተካሄደው ውይይት የዩክሬን ዋና ተደራዳሪ ሆነው ዬርማክን ተክተዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ የሰላም ድርድር ልምድ አላቸው እስካለፈው ሐምሌ ወር ድረስ የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስትር ነበሩ። ኡሜሮቭ በውይይቱ ዬርማክን መተካት ለኪየቭ የሚኖረው አስተዋጽዖ አሉታዊ ነው ወይስ አዎንታዊ የሚለው ግልጽ አለመሆኑን የቢቢሲ የዩክሬን ዘጋቢ ጄምስ ዋተርሃውስ ተናግሯል።»
• ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ
«ዲሚትሪቭ ትራምፕ ሁለተኛውን የፕሬዚዳንትነት ዘመን ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የአሜሪካ እና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አካል ናቸው። ከዚህ በፊት በአሜሪካ ሰርተዋል፤ ኖረዋልም፤ እንዲሁም ከውጭ ዲፕሎማሲ ወይም ከወታደራዊ ኃይል ይልቅ በንግድ ስምምነቶች የበለጠ ልምድ አላቸው።»
«ከአብዛኛዎቹ የፑቲን አባላት በተለየ መልኩ፣ በአሜሪካ የቴሌቪዥን ስቱዲዮ ውስጥ ቃለ መጠየቅ ለመስጠት አያመነቱም። የትራምፕን የዲፕሎማሲ ክህሎቶች በማመስገን ለምዕራባውያን ተመልካቾች የሩሲያ መንግሥትን ትረካ በራሳቸው ቋንቋ ይሰጣሉ። ባለፈው ወር የወጣው የሰላም እቅድ ረቂቅ የመጣው በማያሚ ዲሚትሪቭ እና ዊትኮፍ ለሦስት ቀናት ከተገናኙ በኋላ ነው።»
ሩሲያ፡ ዩሪ ኡሻኮቭ
«ኡሻኮቭ እአአከ2012 ጀምሮ ቭላድሚር ፑቲንን በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ሲያማክሩ ቆይተዋል፤ ከ1998 እስከ 2008 የሩሲያ የአሜሪካ አምባሳደር ነበሩ። ብሉምበርግ ኒውስ እንደዘገበው ከዊትኮፍ ጋር ባደረጉት እና ሾልኮ በወጣ የስልክ ጥሪ ትራምፕ ድርድሩን ለማስቀጠል ከፑቲን ጋር እንዲነጋገሩ ፍላጎት እንዳላቸው ታይቷል። ባለፈው ሳምንት በሞስኮ "የአውሮፓ ዕቅድ፣ በመጀመሪያ ሲታይ... ሙሉ በሙሉ ገንቢ ያልሆነ እና ለእኛ የማይሰራ ነው" ብለዋል።»
• ሩሲያ፡ ቭላድሚር ሜዲንስኪ
«ከፑቲን ከፍተኛ ረዳቶች አንዱ የሆኑት ሜዲንስኪ፣ የዩክሬን ሙሉ ወረራ በ2022 ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የሩሲያ የድርድር ቡድን ቁልፍ አባል ናቸው። የቀድሞው የባህል ሚኒስትር ለጦርነቱ አሳማኝ ምክንያት እንዲኖር የረዱ ጠንካራ ሰው በመባል ይታወቃሉ። በማዕከላዊ ዩክሬን በምትገኘው ስሚላ ከተማ ነው የተወለዱት»
• ፎቶግራፎቹ በሙሉ ከBBC የአማርኛ ፔጅ የተወሰደ ነው። ቅደም ተከተሉም BBC
እንደሰራው ነው የተቀመጠው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ