ቃ! ካላለስ?! // ሥነ - ግጥም
ቃ።
„አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ከአፌ ቃል አትራቁ።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ© ሥላሴ
03.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
በዝምታ ኳኳታ፤ በኳኳታ ዝምታ // ህምታ - ተተፍታታ?
በሁካታ ጸጥታ፤ በጸጥታ ሁካታ // እምታ - ተተፍታታ?
ልቤ በዝንቅንቅ በቅልቅል ሲምታታ
- ድርግምታ
ቃ! እንዳይል በሎሆሳስታ...
ሆታ¡ ሲሆን እልልታ በቃና ዜማ ትክታ … በትክታ …
መቼ ባጅቼ ከንፌስ ለጫጫታ?
ዞገቢስ ነኝ የለብኝም ውለታ!
የሙሉ እድሜ ብክነት በከንቱነት አንደገብያ ለእፍታ ሲፈታ
ተዬት ተገብይቶ ስክነታዊ ገበታ?
ከዬትስ መጥቶ ጌታ ማስተዋል
እርጋታ?
ብቻ ቻቻ ቸበር ምታ፤ በቃ እስክስታ በስክስታ
አንጓ - ተአንጓ የምንቶ ፍሪንባ አቤቱታ …፤
የሥም ወሽመጥ ፍስክታ፤ የህማማት ቋጠሮ ዕድምታ
በቃ! ይኸው ሆነ የሞፈር ቀንበር መፍቻ?!
ሰሚ ሳያገኝ ቤተ - ዋይታ?
በፌስታ ግብይት እንዲህ አንደ‘ልባሌ ይፈታ?
ብቻ … ብቻ ያ መራር እንትን
እንዲህ እንደዋዛ ተረታ?!
ለካንስ ለዚህ ነው የድቅድቅ ግዞት ስንጥር ፈግግታ?
እንዲህ ሲማታ፤ ሲያምታታ
የህቅታ ቬሎ ወበቅታ
የቃል ፍልስ - ምልስ ቅልስ - ጠጠርማ - ቃታ ህቅታ፤
የላቦት ዲሞ ግማዱ በቻቻቴ
ሲፈታ …
ግብዕት ሆነ ተይህ፤ ግብዕት ሆነ ተያ የእንቆቅልሹ ግርምታ፤
የዋንጫው ሩምታ!
ሆ¡ በል አገር --- በትምክህትህ ቃ! በል ሲፈታ
ኪዳን ሲያፋታ ወይንስ ሊያፍታታ?
ገብያ ተውሎ፤ ውሎ ሲፈርስ እንደዋዛ፤ እፍ ብር ሲልም ለአፍታ
የጠብታ ቸርቸር ሳይሰናበት፤ የጅረት ምት አያ እንቶኔ ያ ከርታታ፤
የምትኃት ድርሳነ - ዘንግ ፈርከክ ውሽክታ፤
በፍቅታ - አዜኔታ በኮሽታ
በዝቅታ ንድል ዝቅታ ወይንስ በከፍታ ክፈተት ከፈታ?
የተመጣህ የመጣሁልህ የእቅፍቅፎሽ ትርታ
የውነት መሃንዲስ ልስን ጥፈት ኩነታ፤
መቼ አለፈላት ያቺ ራሄሏ የኔታ፤
ለማታማታ የቀጠሮው ለታ
ንግሥና በፍልሰታ?
ቶሎ በል! ቶሎ በል! ብቻ ጥድፊያ ለከታ
አድርሽኝ አትበል የዙር ቀለበት ጥምልምልታ
ይመጣ ይሆን ዳግም አጤ ጨለምታ?
ያ ክፉ የዘመን ዶፋማ ወለምታ?
ወይስ ተፋሰሱ የፍንደቃ ትዝታ በተዐቅቦ
ግርምታ?
የትምትም ኮለልበል ግርጣታ፤
የኮበለ - ግራምጣ ስርጽታ።
በወጮፎ አልፋ ኦሜጋ፤ የዓይን ልጅ ፉጨታ
ይደላል እንዴ? እንዲህ የቀንስብ ናዳ የሆ¡ በል ፍንዳታ?
ብቻ ትርትር፤ ብቻ ምንትስ ብርብር፤ ብቻ የቅብጥርስ ስክታ -
ክትክታ በክትክታ፤ ስንጥርታ ወይንስ ግጥምታ?
ድገመኝ - ሰልሰኝ - እንዳይመጣ
የስብራት ውልቅታ
በቸለልታ - በግርታ - ገረፍታ፤
መድፊያው እንዳይሆን የኪዳን ቀራንዮስ ሹልክታ
የጎለጎታው አራት እግር - የፍፃሜው ሽልብታ።
- · ተጣፋ አሁን 17.34።
- · ሥጦታ ለአቤቱ ዘመን።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት
ፈተናን አሸነፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ