#ዛሬም???

 

 May be an image of heart and text
 
"#ከማይረባ እንጒርጒሮ ተጠበቁ፡ ከሐሜትም አንደበታችሁን
ከልክሉ ቀስ ብለው የተናገሩት ነገር በከንቱ አይነገርምና እንደ
ፍላፃም የሚወጋ አሰት የሚናገር አፍ ሰውነት ይጐዳልና።"
(መጽሐፈ ጥበብ ፩ ቁ፲፩)
 
አምላኬ ሆይ! እራሴን እምገስጽበት አቅሙን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁኝ። አሜን። ከዘለለው ጋር እንዳልዘል፦ ከጎረፈውም ጋር እንዳልጎርፍ #ሃግ በለኝ አደራ አማኑኤል ሆይ። እንደጠበቅከኝም አውቃለሁኝ። 
 
ዕውነትህ ይመራኛል። ዕውነትህ ያጽናናኛል፦ ዕውነትህ ያፀናኛል ዛሬን እንዳይ ከዛሬ ጋር እወያይ፦ እነጋገር ዘንድ ጌታዬ እና አምላኬ ስለፈቀድክልኝ ክበርልኝ። ቅድስቷ በዕቴ ሲዊዚሻም ከርህርህናሽ ጋር ኑሪልኝ። አሜን። መመኪዬ እቴጌ ኢትዮጵያም አለሽልኝን ልበልሽ አዘውትሬ። ኑሪልኝ። አሜን።
 
 ቅኖቹ የአገሬ ልጆችም የተጓዝንበትን ሂደት በቅጡ ገምግሞ እራስን በማረም የፊት ረድፈኝነቱ እንዳያመልጣችሁ ተሽቀዳደሙ። ብዙ በጣም ብዙ ግድፈት ካለ ስኬት ተጓዝን። ዛሬ በድህነት ለመኖር ሰላሙን የተቀማ ህዝብም ኖረን። መለቀስ ካለበት በከንቱ አፍሰን ስንለቅም፦ ለቅመን ስናፈስ ለኖርንበት ዘመን ይሁን። ፖለቲካ ግን ለማን? ስለማን? ስለም ይሆን ድካሙ? ሰላምን ሆዱን ማሙላት፤ ጥሙን ማርካት ካልቻለ ግን ፖለቲካ ምንድን ይሆን???? 
 
#ምልሰት ይሁን።
 
ህም። ዛሬም ለፖለቲካ ድርጅት መሪወች፦ ለተጽዕኖ ፈጣሪወች ብላችሁ ሰላማችሁን ታጎሳቁሉትአላችሁን? ማህበራዊ ኑሯችሁን ታስከፋላችሁን? ከእኔ በላይ ዘመኑን ሁሉ የተማገደ የለም። ብላሽ ድካም። የውርንጫ ልፋት ሆኖ ፈሶ ነው የቀረው። የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሆነ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሰናፍጭ ታክል አትኩሮት የላቸውም።
 
በብላሽ ላፈሰሳችሁት ጊዜ ዕውቀት ርቁቅ መስዋዕትነት ግድ አይሰጣቸውም። የትናንቱ የትሜና ተጥሎ ዛሬም ለማገዶነት ሲሿችሁ ቆራጣ ይሉኝታም የለም። ለሰከንድም ስለምትሰጡት ገንቢ ዕይታ ዋግ አይሰጡት። ከጉዳይም አይጥፋት። ዛሬ ዛሬ ሳስበው ልብ ገዝቼ ማለት ነው የማለቅለቅ ያህል የሚዩት ይመስለኛል። ይህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሁሉም መለያ ነው። ስለሆነም ማገዶነቱ ለገራገሩ የኢትዮጵያ ገበሬ ርትህ እና ለደጉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለሩህሩሁ ታሪክ፤ ትውፊት እና ባህል።
 
ለእኔ ቢጤ ትዳር፤ ትምህርት ኑሯቸውን በትነው ካቴና ላይ ላሉ እና ለሞት እራሳቸውን ላሰጡ ይሁን። በተረፈ ሁሉንም ግጭት ሳትገቡ በጥንቃቄ ከውኑት። ስለማንም ለመመስከር እርግጥ የሚያደርገው በራስ ሰብዕና ብቻ ይሆናል። ተጽዕኖ ፈጣሪ ይሁን ፖለቲከኛ ባህሪያቸው መዳፋችን ላይ የለም። ኑሮም አያውቅም። አናውቃቸውም። ዕውነቱ ይኽው ነው። ቅንነታችን ቢደፋም በግፍ የውስጥ ሰላማችን ተመርቆት ይኖረዋል። ብልህነት መርህ ይሁን። በመርህ ስለዕውነት ሞግቱ ግን በራሳችሁ አቅም ልክ በአቋማችሁ ዙሪያ ብቻ።
 
ምዕራፍ ፲፫ በዚህ መሰል የውስጥነት ሃዲድ ትኩረት ያደርጋል። ወቃሽ ብቻ ሳይሆን ተወቃሽነታችን ደፈር ብሎ ይቀርባል። አሰር፤ አረም፤ የጓጎለ ሁሉ ይታረም ዘንድ ወራስ መዝመት ይገባል። 
 
ሥርጉትሻ አገልጋይ።
2024/05/16
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።