እንዴት ይታረቅ?


እንኳን ደህና መጡልኝ።
እንዴት ይታረቅ?
„በሰነፎች መካከል ከሚጮኽ ከገዢው ጩኽት
 ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።“
 መጽሐፈ መክብብ ፱ ቁጥር ፲፯

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.05.2019
ከመነኩሴዋ ሲዊዘርላንድ

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ሁለት ነገር አለ። ይህን ሁለት ነገር ለማስታረቅ እንዴት ይቻል ነው መሰረታዊው ጉዳይ። በአንድ በኩል በሥነ ልቦና፤  በአካል የሚደርስ ጥቃት አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ጥቃት ለመከላከል መፍትሄ የሚሻ አካል ደግሞ ምክክር ሲያደርግ በባህርዳር ሰንብቷል።

ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጦር ሃይሎች ጠ/ አዛዥ ሆነው እንዴት ይህን ሃላፊነት ለምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮነን ለቀቁ? በመርህ ደረጃ ይቻላቸዋል ወይ ምክትል ጠ/ሚሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከአገር እያሉ ለመሰብሰብ። መከላከያ 7ኛ ዓመት ባዕሉን ሲያከብሩ የክብር እንግዳው ሌላ ስለነበር ማለት ነው። ስለምን ሽሽት አስፈለጋቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ? አልገብቶም።

የችግሩ ሁሉ ምንጭ የአማራን ማህበረሰብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ የተረቀቀው ህገ መንግሥት እና እሱን መሰረት አድርገው የወጡ ዬዬክልል ህገ መንግሥቶች፤ እንዲሁም ከእናት ህገ መንግሥቱ የፈለቁ ሌሎች ብሄራዊ ህጎች፤ ደንቦች፤ እና ፖሊሲዎች ናቸው። መቼም ካንሰር በፓናዶል አይፈወስም። ወይንም ኢንፌክሽን በፓናዶል አይፈወስም።

አንድ ችግር መፍትሄ የሚያገኘው የችግሩን መሰረታዊ ጉዳይ ቢያንስ በመርህ ደረጃ መቀበል ሲቻል ነው። የጋዜጣዊ መግለጫዎች፤ የስብሰባ መግለጫዎች፤ የጋራ የፎረም ውይይቶች ሁሉ በሳቢያ ላይ የተሰኩ ከሆኑ ድካሙ የውርንጫ ሆነው ይቀራሉ። 

ለነገሩ የተለመዱ ናቸው ከአራት ወራት በፊት እንዲህ የአማራ ዲሞ ሲኖር ጠ/ሚር አብይ አህመድ ብር ብለው ሄደው ርብ ግድብ ምርቃት፤ ላሊበላ ጉብኝት በዕለቱ ነበራቸው። እናም የሰሞናቱን የምክክር መድረክም እማዬው ከዚህ አንፃር ነው። ማዳፈን የሚፈለግ አቅም ስላለ።

የሆነ ሆኖ ቀድሞ ነገር የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ መንግሥት በአንድ ነገር መሰማማት ይችላል ወይ? ኢትዮጵያ የነበረው ምን ዓይንት የጭቆና ባህሬ ነበረው? የሰላም እና እርቅ ኮሚሽን ትናንት መግለጫ እንደሰጠ ሰምቻለሁኝ እኔ ሰኞለት ለመሆኑ አለን ብዬ ጽፌ ነበር?

ኮሚሽኑ ራሱ በዚህ መርህ ላይ ምን ያህል እውቀት አለው? የ66ቱ የፖለቲካ ሊሂቃን የድርጅታቸው መሰረት መርህ ዛቢያ ብሄር ብሄረሰቦች በኢትዮጵያ ጭቆና ነበረባቸው፤ ጨቋኙ ደግሞ አማራ ነው የሚል ነው። ይህን ተሸክመኽ እረቅ ሰላም፤ ፍትህ፤ ርትህ ወዳጅነት፤ መቻቻል ለውጪው ሚዲያ ይሆናል እውነት ለሆነው መፍትሄ ግን እንቦጭ ነው።

በሌላ በኩል ጠ/ሚር አብይ አህመድ "ለአንድ ሰፈር ተብሎ ህገ መንግሥት አይቀዬርም" ብለዋል በአደባባይ። መጀመሪያ ቅቡልነት ስለሌን ቅቡለነት ያለው መንግሥት ሲኖረን አሉን፤ በዛ ተስማማን ከዛ ደግሞ ሲያሰኛቸው በቁጣ መንፈስ "ለአንድ ሰፈር ተብሎ ህገ መንግሥት አይቀዬርም" አሉን።

በሌላ በኩል የሚመሩት ድርጅትም፤ አሁን አገር እዬመራ ያለው አውራ ድርጅትም በቋንቋ ፌድራዚም አልደራደርም ብሏል። ስለዚህ እንዴት ባለ ታምራዊ ሂደት ነው ጸረ አማራ የሆነውን ህጋዊ እውቅና አግኝቶ ሥራ ላይ ሲውል የኖረው ህገ መንግሥት እና እሱን ትራስ አድርጎ የወጡት የዬክልሉ ህገመንግሥቶች ጥሶ ለዚህ ማህበረሰብ  ጥበቃ ሊያደርጉ የሚችሉት? ፈተናው ይሄው ነው።

ህወሃት የተደራጀበት መሰረታዊ አንኳር ጉዳይ እኮ ይኸው የተፋለሰ ፍልሰፍና ነው። የሽዋ አማራ ጨቁኖናል ነው። አይደለም ወይ? ታዲያ በምን ሁኔታ ነው መፍትሄ የሚያገኘው።
በዚህ ማንፌስቶ ሥር እኮ ነው መከላከያው፤ ደህንነቱ፤ የፍትህ አካሉ፤ የፖሊስ አካሉ መንግሥታዊ አካላት ሁሉ የተዋቀሩት። 

በዚህ መንፈስም ነው ፓርላማው የተደራጀው። ላለፈው በደል ካሳው ቀርቶ ነገም በዚህ እቀጥላለሁ የሚል አውራ ፓርቲ ኦዴፓ እያለ እንዴት እና እንዴት ብሎ ነው ይህ ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለው? ሜ/ጄ ከማል ገልቹ እንደገለጹት እኮ በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው ያለው። ሽብርን ስጋትን ወደ ሌላ ቆልሎ ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉ አይቻልም።

በሌላ በኩል ይህ ማህበረሰብ እኮ የህግ ጥበቃም የህግ ከለላም ሳይኖረው ይህን ያህል ዘመን አልበቃ ብሎ አሁንም አማራ ተጋድሎ በማጣው መንበረ ሥልጣን ላይ ተቀምጠው በድፍረት ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ „ለአንድ ሰፈር ተብሎ ህገ መንግሥት አይሻሻልም፤ አይቀዬርም“ ያሉት። ይህ ማለት መንግሥታዊ አካላት ለዚህ ማህበረሰብ ለሚደርስበት ጥቃት ሁሉ ከለለ ለመስጠት አይገደዱም ማለት ነው። ለሚፈጽሙት ጥቃትም ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብም የለም ማለት ነው።

እስኪቀዬር እስኪሻሻል ድረስ እንኳን በምን የህግ አግባብ አንጻራዊ የሆነ ጥበቃ ሊደረገልት ይቻላል ይህ ማህበረሰብ? ይህን ሊያሻሽል፤ ሊቀይር የሚችል ሁኔታ በመንፈስ ደረጃ፤ በቃል ደረጃ፤ በስምምነት ደረጃ ሳይኖር በምን ቀመር ለዚህ ማህበረሰብ እንዴት ጥበቃ ሊደረግ ይችላል ተብሎ ይታሰብ። ለእንሰሳዊ ፍርድ እኮ አይዞህ በርታ ቀጥልበት የማለት ያህል ነው … በሄልተን ሆቴል ጠ/ሚሩ የሰጡት ቃለምህዳን።

እና እኔ አሁን የባህርዳሩ ስምምነት ም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ የሰበሰቡት ማለቴ ነው የሚያፈስ ነው የሚሆነው ውሳኔውን። ምክንያቱም ከቁንጮው ያልታመነበትን ነገር እውን ለማድረግ ለሰራዊቱም፤ ለክልሎችም እጅግ ፈታኝ ስለሚሆን። በዚህ ላይ መዋቅራዊ ሰንሰለቱ ያለው መስተጋብር ሲሰላም ያን ያህል ጥብቅ አይደለም።

ዛሬ ገብቼ ሳረጋግጥ ተሰርዟል ሌላም በዚህ ዓመት የጎበዝ ተማሪዎች ምርጫ ላይ ያለውን የጠ/ሚር ጽ/ቤት በአማራ ላይ ያለውን አግላይ ዕድምታም የሚገልጽ ጹሑፍ ወጥቶ አንቤያለሁኝ። ጹሑፉ ቢነሳም በመንፈስ ያለው የነገ ጸረ አማራ ሁኔታ ግን አይተነዋል። እያዬነውም ነው ያለነው።

የቁጥሩ ዳታ መረጃው የትኛው ትክክል መሆኑን ባለረጋግጠም ከ45 አስከ 55 ሺህ ተማሪዎች በማዕከላዊ ጎንደር የአንድ ዓመት ትምህርታቸው መስተጓገል አሁን በጠ/ሚር ጽ/ቤት ፈቀድ ተነሳ ከተባለው ጋር በስሜት ይገናኛል። ይህም ማለት አማራው  ለአዲስ መከራ የተሰናዳለት ዲል ያለ ድግስ እንዳለ ነው። ለዚህ ነው እኔ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ቀጣይነትን አብክሬ እማስገነዝበው።

በሳቢያው ላይ ሳይሆን ለሰባዕዊ መብት የሚታገል ማንኛውም ንጹህ መንፈስ ያለው ባለህሊና ማሰብ እና ማስተዋል ያለበት ይህ መከራ በደርበቡ ሊታይ እና በዛም ሊዳኝ የማይችል መሆኑን ነው። ይህ እንዲቀጥል የሚሹ አካላት ናቸው አብን ላይ ጦር የሚዘምቱት፤ የሚያዘምቱት።
https://www.youtube.com/watch?v=Kduoc4DeE_w


ሀገር ተረጋግቶ እንዳይቀጥል እያደረገ ያለውን መሠረታዊ ምክንያት ቃኝቶ መመለስ እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

እኔ የም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን ንግግር አዳምጫዋለሁኝ። ግን በመርህ ደረጃ ይቻላል ወይ? እሳቸውስ ይህን የማስፈጸም አቅም አላቸው ወይ? ቆሞስ ኢነጂነር ሰመኘው ከዚህ አለም ከሞት ሲለዩ እሳቸው እያሉ ቀብር አድናቂዎቻቸው ተነፍገዋል፤ አዲስ አባባ፤ ቡራዩ፤ ለገጣፎለጋዳዲ እዛው አፍንጫ ሥር ያሉ ሰቆቃዎችን እንኳን ለማስቆም አልተቻላቸውም ስለዚህ እኔ ተስፋዬ ጥንዙል ነው።

ሃላፊነት ሙሉ ስልጣን ሲኖረው እንጂ በዚህ መልኩ ከሆነ ጋዳ ነው። ከንቲባው ስብሰባውን ይፈቅዳሉ፤ ፓሊስ ጥበቃውን አያደርግም፤ ቄሮ መጥቶ ያግዳል። እንዲህ ዓይነት ሥርዓት አልበኝነት በወርርስ የትም አገር አስተናግዶ አያውቅም። 

ከሥም ውጪ፤ ከፕሮቶኮል ውጪ ሥልጣኑ አለ ለማለት እኔ አልደፍርም። ሚና የለሽ ወንበር እኔ ፋይዳው አይታዬኝም …ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ አዲስ አባባ እና አካቢቢው በዴሞግራፊ ፍልስፍና አውን ሲሆን ሙሉ ካቢኔው፤ ምክትል ጠ/ሚሩ የትኛው ፕላኔት ላይ ናቸው ያሰኛል?

የም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ ሞኮነን ንግግር አጽናኝ ቢሆንም የማስፈጸም አቅሙ ግን ልበሙሉ ነው ለማለት አያቻልም። በጣም የሚገርመኝ እና የሚደንቀኝ ነገር ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንዲህ ባሉ ችግሮች እሳቸው የማይጋፈጡ መሆናቸው እና ለሌለው ጠቅለልው የሚያሸክሙ መሆናቸውን ነው እኔ በአንድ ዓመት ውስጥ ያዬሁት።

እሳቸው ሙገሳ፤ ውደሳ፤ ሐሤት ላይ ብቻ ነው መገኘት የሚሹት። የአብይ ካቢኔ ዕንባ ሲያምረው ወ/ሮ ሙፍርያትን ካሜልን፤ የኳስ ምህንድስና ሲሻው አቶ ለማ መገርሳን፤ ጃኖ ሲያምረው አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን፤ ሽሽት ሲያምረው አፍሪካ ቀንድ፤ መታመን ማህተም ሲሻው ፕ/ ብርሃኑ ነጋን፤ ርህርህና ሲያምርው የቀዳማት እመቤትን ቢሮ፤ ጫና ሲያምረው ፕሬስ ሴክርተርያትን፤ ለ አማራ ማህበረሰብ ጠብሰቅ ያለ ኩርኩም ሲያስፈልግ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን  ወዘተ አሰልፎ በአለዝበኝ፤ በአለስልሰኝ ጉዞ በራሱ ውስጥ የፈለገውን ከማድረግ ሳይታቀብ ይኸው ዓመት አለፈ …

ትንሽ ልቀጠል መሰል... ትዝብቴን፤ መከራን መሸከም ሲሳነው አቶ ደመቀ መኮነን፤ ሙገሳ ድንቅነት ሲያምረው ወ/ሮ አዳነች አቤቤን፤ ድግስ ሲያምረው ኢንጂነር ታከለ ኡማን፤ ሎሌ ሲያምረው ብአዴንን፤ ሹመት ሲያምረው ኦዴፓን፤ ማጠፊያ ሲያጥረው ኦሮማራን፤ ስብከት ሲያምረው ማይንድ ሴትን፤  እንዲህ በወረፋ እያሰለፈ መንፈስን ወደ አሻው አቅጣጫ እዬቀያዬሰ የሚያሻውን እሽት እዬያደረገ ቀጥሏል።

ሀገር ተረጋግቶ እንዳይቀጥል እያደረገ ያለውን መሠረታዊ ምክንያት ቃኝቶ መመለስ እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡


https://www.youtube.com/watch?v=WCOKJALO2Y8
#Amhara_Mass_Media_Agency #Demeke_Mekonnen #Dr_Ambachew

Amhara TV | ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለተፈጠረዉ ግጭት መግለጫ - አቶ ደመቀ መኮንን - ዶ/ር አምባቸዉ

Published on Apr 30, 2019
ምንም ዓይነት ለውጥ፤ ምንም ዓይነት ተስፋ፤ ምንም ዓይነት ራዕይ፤ ምንም ዓይነት የህግ ማሻሸያ ከማዕቀፉ አይወጣም። ከህወሃት ማንፌስቶ … ከዚህ ሲኦል መንፈስ እርቅም፤ ሰላምም፤ ፍቅርም፤ መቻቻልም፤ ታማኝነትም፤ ፍትህም፤ ዴሞክራሲም፤ ቃልም መጠበቅ እብንነት ነው።


የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ፀንቶ ተጋድሎውን መቀጠል ይኖርበታል።
አማራነት ተወዳጅ ማንነት ነው!
ፍቅር ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።