«#UnitedByMusic” ይህ የእምዬ ሲዊዘርላንድ ለዓለም የላከችው የመንፈስ ስጦታ ነው። #Stolz!

 

• «#UnitedByMusic” ይህ የእምዬ ሲዊዘርላንድ ለዓለም የላከችው የመንፈስ ስጦታ ነው። #Stolz!
"ጥበብ ቤቷን ሠራች፤
ሰባት ምሰሶም አቆመች።"
 
79ኛው የዓውሮፓ የሙዚቃ ውድድር ትናንት በባዝል ከተማ በእምዬ ሲዊዘርላንድ #ኦስትሪያ ያሸነፈበት መሰናዶ በስኬት ተጠናቋል። በ2024 እምዬ ሲዊዘርላንድ አሸናፊ ስለነበረች የ2025 አዘጋጅ ቅድስቷ ነበረች። አንድ ሳምንት ቀድሞ መስተንግዶ የነበረ ሲሆን ተሳታፊወች በተመረጡ ከተሞች በነፍስ ወከፍ ግብዣ ነበራቸው። ህሊናቸው #ቤተሰባዊነትን ይዋህድ ዘንድ የነበረው ቅድመ መሰናዶ እጅግ ሳቢ ነበር ለእኔ።
 
ዘመናችን የዲጅታል ሆነ እና ሰውኛ ጸጋችን እዬተጫነው ስለሆነ የእኔ ማሽን ጄኔሬሽን አስመልክቶ ስጋቴ እጅግ የላቀ ነው። ለዚህም ነው ዓለማችን የፍቅር ተፈጥሮን በትምህርት ደረጃ #ካሪክለም ነድፋ ልትሰጥ ይገባል በማለት የዛሬ 15 ዓመት #ለተመድ እና #ለአውሮፓ ህብረት መሻቴን በክብር የላኩት። እነሱም የተከበሩ ስለሆኑ ለእኔ አንዲት ባተሌ ብላቴና አክብረው መልስ ሰጡኝ።
 
ይህን ያነሳሁት የነገ ጉዳይ ውስጤ ስለሆነ የኦስትርያ፤ የሲዊዝ የጀርመን እና የኢትዮጵያን የትውልድ ቀረፃ መሰናዶወችን ከውስጤ ሆኜ ነው እምከታተለው። ጭንቅላቴን የሚመራውም ይህ ትጉህ ሰውኛ የተስፋ ብርኃናማ መንፈስ ነው። ሰዋኛ! ሰውኛነት! ተፈጥሮ! ተፈጥሮኛነት! ቢፈቀድላቸው በዓለማችን ያለው የስጋት ዳመና ተወግዶ #ቤተሰባዊነት ይነግሥ ነበር።
 
የሆነ ሆኖ ዊዝደም ያበቀለው የአውሮፓ የየዓመቱ የሙዚቃ ድግሥ የዬዓመቱን ቴክኖሎጂ፤ የየዓመቱን የሳይንስ፤ የዓመቱን የሞድ፤ የየዓመቱን የሙዚቃ ምርት ዕድገት፤ የያዓመቱን የሚዲያ ክህሎት፤ የየዓመቱን የኮስሞቲክ ሥልጣኔ ብቻ ሳይሆን የየዓመቱን የፖለቲካ ክስተትም ገረፍ አድርጎ አቅፎና ደግፎ ለዕያታ ያቀርባል። ለምሳሌ ራሺያ ለሦስት አመት እግድ ነው። ራሺያ ያሉ ታዳጊ ወጣት የጥበብ ባለጸጋወች በፖለቲካው መታመስ ምክንያት ከኢሮቪዥን ኮሚኒቲ #ንጥል ናቸው። ይህ ማለት አውሮፓ አንድ አካሏ የተሳትፎ ተሳትፎ የለውም ማለት ነው። የራሺያ ትውልድ አለመሳተፍ የራሺያ ህብራዊ ማንነት ለኢሮቪዥን ቤተሰብ ይጎድልበታል ማለት ነው። 
 
የሆነ ሆኖ ማክሰኞ በመክፈቻው እና ማጣሪያው እንዲሁም ሃሙስም በማጣሪያው የእምዬ ሲዊዝ የመስተንግዶ ድባብ በሁለት ሞደሬተሮች የተመራ ነበር። ባክስቴጅም እኒሁ ሁለቱ ሞደሬተሮች ነበሩ የሚመሩት። የማጠቃለያው ውድድር ግን ለሦስት ነበር የተመራው። ሙሉዑ ነበር። መክፈቻው በእንግሊዘኛ፤ በጣሊያንኛ፤ በጀርመንኛ፤ በፈረንሳይኛ፤ ወደ ሲዊዝ ጀርመንኛ ባደላ ጀርመንኛ ቋንቋ ነበር። ሙሉ ፕሮግራሙን የመራው ግን ዓውራው ቋንቋ እንግሊዘኛ ነበር። 
 
ይህ መሰናዶ ከራሽያ ውጭ ያሉ የአውሮፓ አገሮች ብቻ ሳይሆን አውስትራልያ፤ እስራኤል ሙሉ ታዳሚወች ናቸው። ቻይና ሙሉ ፕሮግራሙን በሚዲያቸው ይተላለፋል። በ13 ሰዓት ወደ 11 ሚሊዮን ተመልካች አግኝቷል የማጠቃለያው ፕሮግራም። ይህ ማለት ይህ የሙዚቃ ውድድር ዓለም ዓቀፍ የሆነ ተወዳጅ፤ ተናፋቂ እና #ተከባሪ መሰናዶ መሆኑን ያመለክታል።
 
በዘንድሮው የአውሮፓ ዓለም ዓቀፍ የሙዚቃ ድግስ የ37 አገሮች ዳኝነት፤ የህዝብ ድምጽም ታክሎ አራተኛው የዓለም የዲፕሎማቲክ ድንቅ አገር #ኦስትርያ አሸናፊ ሆኗል። በ2014ም ኦስትርያ አሸናፊ ነበር። ለዓለም ልዩ #ክስተት ነበር። በዓመት ውስጥ 500 ቀጠሮ አሸናፊው ነበረው። አውስትራልያ ልዩ የኦፔራ መሰናዶ ነበራቸው ለኦስትርያ አሸናፊ። ኦስትርያወችም ለዕድላቸው የሰጡት ክብርም ፍጹም ልዩ ነበር። የመክፈቻ ሥርዓቱ በህፃናት እና በሦስት ሞደሬተሮች ከህሊና በሚታተም ዝማሬ ነበር። 
 
ኦስትርያወቹ አሁን ድጋሚ ዕድል አግኝተዋል ቀጣዩ ዓመት ታምር እናያለን። የሚገርመው የአሸናፊው ነገር ሳርፕራይዝ ነበር ማለት ይቻላል። ፋክክሩም በጣም የተፋፋመ ነበር። ነጥብ መሰጠት ሲጀምር ያለው ድባብ ሊንኩን ለጥፌዋለሁኝ። እጅግ የሚመስጠኝ ፓርቱ ስለሆነ። የየአገሮች ዳኞች ስሜታቸውን ለማዬት ሂደቱ ራዲዮሎጂ ነውና።
 
እኔ ኦስትርያወቹ የመሰናዶ ግራውንዳቸው፤ የአቀራረቡ ሂደት ሁልጊዜ ስለሚስበኝ ዓለም ዓቀፌ የእግር ኳስ ጨዋታ እና ኢሮቪዥን ሶንግ ኮንቴስትን ከመጀመሪያው የመክፈቻ ዕለት ጀምሬ እስከ ፍፃሜው የምከታተለው የኦስትራሹን #ORF አንድን የቴሌቪዥን መሰናዶ ነው።
ትናንት ሦስት ጎረቤታማ #የጀርመንኛ ቋንቋ ቤተሰባዊ አገሮች ውህደትን አመላካች ልዩ ስቴዲዮ በባዝል ነበራቸው። ለሲዊዝም ሶልዳሪቲ ነበር። የጀርመኑ እና የኦስትርያው ታዋቂ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በአንድ ነበር መሰናዶውን በጥምረት የተከታተሉት። የሦስቱም አገር ተወዳዳሪወች ፎቶም ጊዜያዊ ስቴዲዮ ላይ ተለጥፎ ነበር። ለእኔ የውስጥነት ስሜት ይሰጠኛል ይህን መሰል ማዕደኝነት። ለዓለማችን ተስፋ መቀራረቡ፤ መጠጋጋቱ፤ መተቃቀፋ ብቻ መፍትሄዋ እንደሆነ በጽኑ ስለማምን።
 
በዚህ ዓመት ውድድር እምዬ ሲዊዝ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ነበር መስናዶዋን ይዛ የቀረበችው፤ ብዙ አገሮች በራሳቸው ቋንቋ ሲሆን ቀላል የማይባሉ አገሮች በእንግሊዘኛ ያቀርባሉ። ከቀረቡት ውስጥ ሲዊዝ፤ እስራኤል፤ ግሪክ፤ ሆላንድ፤ ኦስትርያ፤ ፈረንሳይ፦ ስፔን ወዘተ ምርጫወቼ ነበሩ። ምክንያቴ ቀስ ያሉ መሆናቸው ብቻ እንጂ እኔ በሙዚቃ ጥበብ ዕውቀቱ የለኝም።
 
እምዬ ሲዊዝ ከ1 - 5 ዕድል ይኖራታል ብዬ ነበር። በተጨማሪም ቡኔ ቀለምን አድምቆ ያቀረበው የሆላንድ መሰናዶም ዕድል ያገኛል የሚል ተስፋም ነበረኝ። ብቸኛው ቡኒ ዕንቁ የሆላንድ አርቲስት ነበር።
 
የኦስትሪያው ተወዳዳሪ እና አሸናፊ ፎጣ ለባሽ ዓይነት ነበር። ከወጀብ ጋር የሚታገል ህይወትን ያመሳጠረ ቀለል - ፈካ - ደልደል - ያለ ወጣት ነው። እኩለ ሌሊት አልፎ ነበር የፕሬስ ኮንፈርንሱን የተቀላቀለው። በነገራችን ላይ ኢሮቪዥን ሶንግ ኮንቴስት ላይ #ከ200 በላይ ጋዜጠኞችም ይታደማሉ። ዓለም ዓቀፍ ጉልህ የጥበብ ማዕዶት ነውና። 
 
በ2025 ኢሮቪዥን ሶንግ ኮንቴስት ኦስትርያ አሸናፊ በመሆኑ ትክክለኛ ዳኝነት ነው ብዬ አምናለሁኝ። ፖለቲካ ነክ ውሳኔም ነው ብዬ አላምንም። ብቁ ብቃት ስለነበር። ይገባቸዋልም። በዚህ ጉዳይ ላይ የሚተጋው ጋዜጠኛ ሚስተር ኢሮቪዥን ሶንግ ኮንቴስት ብለው ነው የሚጠሩት። ኦስትርያወች ለኢሮቪዥን ሶንግ ኮንቴስት አቅላቸው እና አቅማቸው ልዩ ነው። ለቀጣዩ ዓመት ለዛ ካበቀና፤ መኖሩ ከተገኜ ጣዕሙ እና ቃናው የሚመስጠው የኦፔራ በዓት ኦስትርያ የቆንጆወች አገርም ነውና በ2026 ከድንቅ ውብ ማራኪ እና ዘመኑን በመጠነ መሰናዶ እናገኜዋለን የሚል ተስፋ አለኝ።
 
እናቱ፤ እምዬ ሲዊዝም በበቃ፤ በነቃ፤ በፍቅር፤ በሰውኛ፤ በተፈጥሮኛ የድርጊት ጸጋዋ የተሞሸረው ዓለም ዓቀፍ #ዓይነ - ገብ፤ #ደመ - ግቡ መሰናዶዋ በተሟላ ስኬት ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ፍፃሜውን በስኬት አግኝቷል። የመክፈቻው ሥርዓት፤ በመሃሉ ቆይታ፤ የፍፃሜው የተደራጄ ድባብ የተጎናጸፈው መስተንግዶ እና የጥበብ ልክ በብቃት፤ በልቅና እና በልዕልና ተከውኗል።
 
የጥበብ ዓውደ- ምህረት ለሰውኛ፤ ለተፈጥሮኛ፤ ለትውልድ ተስፋ እና አደራ በሚያመች ሁነት መከወኑ በራሱ ተቋም ነው። ለዚህ ተምሳሌነት ደግሞ እምዬ ሲዊዝ #ልክ ናት።ሚሊዮኖች ከዓለም የቀውስ፤ የጭንቀት፤ የጦርነት ድባብ ለአፍታም ቢሆን #እፎይ ብለው በአዲስ ማንነት እና ተስፋን ነገን በበጎ ያጩበት መሰናዶ በሐሴት በሰላም ተጠናቋል። 
 
እግዚአብሄር ቢፈቅድ እና ቢወድ በቀጣዩ ዓመት የራሺያ እና የዩክሬን፤ የጋዛ እና የእስራኤል፤ የእስራኤል የቤይሩት እና የኢራን፤ የህንድ እና የፓኪስታን፤ የአፍሪካ #ቀንድ ውጥረት ታግሦ መኖርን የሚያኖር አዲስ፤ ንጹህ መቻቻል ፈጣሪ ይመርቅልን ዘንድ ምኞቴ ነው። በዚህ ዓመት በዚህ ሁሉ ጭንቅ ሆነው የእስራኤል ተወዳዳሪ በሁለተኝነት ነበር ያጠናቀቀችው። ገርሞኛልም።
 
ለአውስትራልያ ሙሉ ምኞት ነበረኝ። ምክንያትም ለጥበብ ፍቅር የሚከፍሉት መስዋዕትነት ድንቅ ስለሆነ። ከአውሮፓ ጋር ተዋህደዋል ማለት ያስችለኛም። የዘንድሮው ካለፈው ጋር ሲነጣጠር ዝቅ ብሎብኛል። ለወደፊቱ በብዙ ነገር ተገዳዳሪ ሆና የወጣው ቻይናም በተሳትፎ ደረጃ ፈቃዱን ቢያክል መልካምነት ይፋፋ ነበር። ውጥረቶችን ለማርገብ ብቻ ሳይሆን ግሎባላይዜሽንን ትንፋሹን ያለመልም ነበር። ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ጥቂት ሊንኮች አክያለሁኝ።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/05/2025
 
"#United By Music."
ሰውኛነት ይለምልም። አሜን።
Eurovision Song Contest 2025
“The Grand Final of the Eurovision Song Contest 2025 will take place in St. Jakobshalle, Basel, on Saturday 17 May with Semi-Finals on Tuesday 13 and Thursday 15 May, after it was selected by Host Broadcaster SRG SSR and the European Broadcasting Union to host the 69th edition of the Contest.”
Basel 2025 - Eurovision.tv
https://eurovision.tv › event › basel-2025
JJ – Wasted Love (LIVE) | Austria 🇦🇹 | Grand Final | Eurovision 2025
The jury results of Eurovision 2025 | #UnitedByMusic 🇨🇭
Public Vote - The Televote Results of Eurovision 2025 | #UnitedByMusic
Eurovision Song Contest 2025 - Grand Final - Livestream | #Eurovision2025
11,034,620 (13)
Eurovision Song Contest 2025 - Grand Final - Livestream | #Eurovision2025

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?