ቤልጀም ብራዚልን አንገት አስደፋ።

ቤልጄም ብራዚልን 
አንገት አስደፋ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
„የሚለምኑትን ሰዎች ልመናቸውን ይሰማል።“
(መጸሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፳፯)



                               ዛሬ ቤልጀሞች ማልዶ ነው የቀናቸው። 
                              ጨዋታው ግን የሞት የሽረት ያህል ነበር። 

ኳስዬ ተደልቃም አሽካክታም ተወቃቅታም የሰናይ መሰረት ናት። ኳስ ፍቅር ነው። ኳስ መሻት ነው። ኳስ ደስታ ነው። ኳስ ሰላም ነው። ኳስ ኪዳን ነው ኮስ ጥበብ ነው። ኳስ መቻቻል ነው። ኳስ መከባባር ነው።  ኳስ ዕውቅና መስጠት - መቀበል - ማግኘትም ነው። ኳስ ተስፋ ነው። ኳስ ድል ነው። ኳስ ትጋት ነው። ኳስ የድካም ሥራ፤ የልፋት ውጤት ነው። ኳስ የማሰብ ችሎታ ነው። ኳስ የእግር ሥራ ሳይሆን የጭንቅላትም ነው።

ኳስ ልዩ መክሊትም ነው። ኳስ ህግ  -ዳኝነት - ችሎትም ነው። ኳስ ትውልድ ነው። ኳስ የፈጠራ ሥራ ቤተሰብ ነው። ኳስ ሳቅ  ነው። ኳስ ማስተዋል ነው፤ ኳስ መልካም ነገርን መመኘት ነው ተስፋን። ኳስ ጊዜ ነው።  ኳስ ክውን ያለ ንጡህ መንፈስ ነው። ኳስ ምጥን ያለ ዕቅድ እና ግብ ያለው የመሆን ሁነኛ ነው። ኳስ ነገ ነው። ኳስ ሃብትነቱ ለማህበረሰቡ የማህበረሰቡ አንጡራ ሃብት ነው። ኳስ ዘመናይ ኢንደስትሪ ነው። ኳስ ሲታስብ ዓለም ደንበር ወስን የሌላት ሆና ህሊናን በሰውኛ እንዲጠበብ ያደርጋል። ሁሉም በአንድ መንፈስ ይከትማል በፍሰሃ እና በሰናይ።



አሁን አውሮፓ ብቻ ቀረ። አውሮፓውያን ሁሉንም አህጉራት ሸኝተው አንድ ለአንድ ዋንጫው ላይ አስፍስፈዋል። ድንቁ ነገር ያልታሰቡት ቡድኖች ስለሆነ የቀሩት ጨዋታውን ብቻ ሳይሆን ዘመኑንም ልዩ ያደርገዋል።

እኔ እራሴ ሶስት ቡድኖች የልቤ ናቸው ፈረንሳይ፤ እንግሊዝ እና ቤልጄዬም። የዳኑት ለምን መሰላቸው ሬሳ ሃሳብ ለመሸከም ባለመፍቀዳቸው።

አብሶ ፈርንሳይ እና እንግሊዝ የወሰዱት ወሳኝ እርምጃ ለዚህ ብቃት እና ቁመና አብቅቷቸዋል። እንግሊዝ ካሸነፈ ዕድል ከጠይም ዕንቁ ጋር ይጋባል።

ቀደም ባለው ጊዜ የነበሩት በሥም በግነት በኮከቦች ኮከብነት የሚመረጡት አንቱዎች ጨዋታ ላይ ደግሞ የረባ ሚና ሳይጫወቱ ለሽንፈት ይበቁ ነበር። አሁን ያን የሬሳ ሃሳብ ድሪቶን አሽቀንጥረው ሦስቱም አገሮች በዚህ መስመር በመጓዛቸው ጨዋታውንም አዬሩንም የታህድሶ ቤተኛ አደረጉት። ዓይን አዲስ ነገር ይናፍቀዋል።

 በአዲስ ተስፋ ዕድሉን ለወጣቶች ሰጡ ይህው እዚህ ደረሱ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታም ይህን የመሰለ ዕውነት የማይመስል ትንግርት እዬታዬበት ያለውም የሬሳ ሃሳብ ባይረሶችን ገፋ አድርጎ ድግንቴውን ትዕይንት የእኔ ስላለ ነው። ቅርጥምጣሚ ሃሳቦች ቢወናጨፉም ቋት አይገፉም። በተሟጠጠ ዕድል ነው ትርምሱ።

በቃ ውሳኔ ከእርምጃ ጋር ለድል ያበቃል፤፡ ዘንድሮ የ2014 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ከነ አምልኮ ጀርመን፤ ሆላንድ፤ ጣሊያን፤ የራሞሱ ስፔን፤  የ2014 የአውሮፓው ዋንጫው ባላቤት ፖርቹጋል የሉም እኮ።


እንግሊዝ እኮ ሲረታ የኖረው አንድ የኳስ ንጉሥ ነበረው እሱን አሽኮኮ አድርጎ ይመጣ እና ሲያንጎባልል በቃ በጥዋቱ ይሰናበት ነበር። አሁን መልካም ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው። በለስ ቀንቶት ከዚህ የደረሰው ግን ለእኔ የሲዊድን ቡድን ነው።

የሆነ ሆኖ ዛሬ የጠይም ዕንቁ ጥምር መንፈሶች ድል በድል ሆነዋል። ብራዚልን ኡራጋይን ሸኝተዋል ባይ ባይ ለቀጣዩ 2022 ብለዋቸዋል።

እኔ የቤልጄም እና የፈረንሳይ ጨዋታ በርጋታ ነው የምጠብቀው። ስለምን? ሁለቱንም እኩል ስለምወዳቸው በአሸናፊውም በተሸናፊውም እኩል ስሜት ነው የሚኖረኝ።

እብሶ ብራዚሎች በአፍሪካ እግር ኳስ ሰፊ የሆነ ንቀት ስለነበረባቸው ዛሬ በመውጣቸው ደስ ብሎኛል። እንሱም ጠይም ሆነው ግን አፍሪካን የተመለከቱበት የጨዋታ ሞራል እጅግ አሳንሰው ነበር። በአፍሪካ ቡድን ተሸንፈው ቢሆን ያብዱ ነበር እስከ ማራዶናቸው ድርስ።


ኳስ የወደፊት መኖር የተስፋ ሐዋርያ ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።  


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።