ቢራቢሮ ሥነ - ግጥም። የምወዳትም።
ቢራቢሮ ...
***
„የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፤
እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤
እኔንም የጣለ የላከኝን ይጠላል።“
የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
15.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
ቢራቢሮ።
ነይ እሰኪ ዘንድሮ
አለፈልግም ከርሞ
የለኝም አርምሞ
ሁለመናዬ አሮ
በበቀል ተነክሮ
ቀለም የለሽ ኑሮ፣
ቋሳ ተዘርሮ
መብቴ ተዘሮ
ሁኛለሁ ደንቆሮ።
አንቺ ቢራቢሮ
ሕይወት ቢራቢሮ
ኑሮ ቢራቢሮ
ነፍሴ ቢራቢሮ
ተስፋ ቢራቢሮ
አትሁኝ በረሮ
አታፍቅሪ ጦሮ።
ነጠብጣቤ አሮ
ዓይኔም ተማርሮ
ቢራቢሮ ... በበላህሰቦች እንዲህም ተወሮ
ከምሾ ተድሮ
ከዋይታ ተዳብሎ።
አንቺ ቢራቢሮ
ሕይወት ቢራቢሮ
ኑሮ ቢራቢሮ
ነፍሴ ቢራቢሮ
ተስፋ ቢራቢሮ
አትሁኝ በረሮ
አታፍቅሪ ጦሮ።
ገሳ ተንተርሶ
ሞረሽን ተንፍሶ
በቀልን ተቋድሶ፣
ዛሬ ተቀልብሶ
እህህን ተለብሶ።
አንቺ ቢራቢሮ
ሕይወት ቢራቢሮ
ኑሮ ቢራቢሮ
ነፍሴ ቢራቢሮ
ተስፋ ቢራቢሮ
አትሁኝ በረሮ
አታፍቅሪ ጦሮ
ፍሬ ዘሬ ሁሉ ...
.... በምጣድ ታምሶ
አመድ ተነስንሶ
ትብያ ተበስብሶ
ድንጋዩን ቀልብሶ፣
ተቀበረ ተምሶ
ታ ም ሶ።
አንቺ ቢራቢሮ
ሕይወት ቢራቢሮ
ኑሮ ቢራቢሮ
ነፍሴ ቢራቢሮ ቢራቢሮ ...
ተስፋ ቢራ ቢሮ
አትሁኝ በረሮ
አታፍቅሪ ጦሮ።
ክርም ተበጥሶ
ጅማት ተጠናብሶ
ማትብ ቢሆን ጢሶ፣
ፍዳ ተሰልሶ
ክብር … የአሳር ትቢያ ተለብሶ።
አንቺ ቢራቢሮ
ሕይወት ቢራቢሮ
ኑሮ ቢራቢሮ
ነፍሴ ቢራቢሮ
ተስፋ ቢራቢሮ
አትሁኝ በረሮ
አታፍቅሪ ጦሮ።
ሥርዓት ተጥሶ
ፍትህ ተገርስሶ
ጭንጋፍ ተኮፍሶ
ርኩም ተፈውሶ፣
ብዙሐኑ አንሶ
መጠጊያ ተውሶ።
አንቺ ቢራቢሮ
ህይወት ቢራቢሮ
ኑሮ ቢራቢሮ
ነፍሴ ቢራቢሮ
ተስፋ ቢራቢሮ
አትሁኝ በረሮ
አታፍቅሪ ጦሮ።
ስልቻ ቃልቻ
ብልቻ ጉልቻ
አንተ አለህ መፍቻ፣
ቢራቢሮ ... መድሕን አንተው ብቻ
ሰልችቶናል ግቻ
የ እ ን ጉ ቻ ች ር~~~~~ ዛቻ።
· ተጣፈ ጥቅምት 11 ቀን 2001 ዓ.ም ዙሪክ አውሮፕላን ማረፊያ፤
· ተስፋ መጽሐፍ ከገጽ 15 ጀምሮ እስከ 17 ለህትም የበቃ።
· ቢራቢሮ እጅግ በጣም ከምወዳቸው ግጥሞች ዋነኛዋ ናት። የጻፍኩበትም ሁኔታ የወያኔ ሃርነት ተጋፊዎች መኖሪያ ቤቴን አስለቅቀውኝ ሰላም ፍለጋ ዙሪክ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ሆኜ እዛውም ስጽፍ አድሬ ከኮለምኳቸው ግጥሞች የበኽር ናት። በድምጽ በጸጋዬ ራድዮ፤ በፀጋዬ ድህረ ገጽ በስፋት ሰርቸበታለሁኝ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ። ዛሬ የፍቅራዊነት የቱብ ላይ ምዕራፍ ሦስት ኮንፓክቱን ሰርቼ መለጠፍ አለብኝ፤ ስለዚህ በዚህው ሥነ - ግጥም በጎ ነገሮችን ተመኝቼ እለያችሁ አለሁኝ።
መሸቢያ ጊዜ። ብሩክ ቅዱስ ሁኑልኝ ኑሩልኝ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ