ግድግዳ እና እኔ ሥነ ግጥም።

ግድግዳ እና እኔ።
„ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሄር እኔ ፈርጄ አጠፋዋለሁ ብሏልን
 ከምጽዕት በኋዋለ ግን ለዲያቢሎስ ሥልጣን የለውም“
መቃብያን ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
15.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ


  • ·      ወግ ቢጤ።

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት አላችሁልኝ። ትናንት ብቅ አላልኩም፤ ሚስጢረ አዲስን ገለጥለጥ ለማድረግ ፈርቼው አይደለም።  እኔ የሥላሴ ባርያ ከፈጣሪያ በታች እምፈራው ህግ ብቻ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ከፖለቲካ ውጪም ህይወት አለ። ነፍስም አለች። መኖርም አለ በዛ ተከርም መሥራት ያስፈለጋል።
የሆነ ሆኖ ዕውነት በሌለችበትም ስለ እውነት ጮኼለሁኝ። አትኩሮት ሊሰጣቸው በሚገቡ ወገኖቼንም ቢሆን እንደ እኔ ደፍሮ የሚጽፍ የለም። ስለ ወገን ደግፍሮ በቅንነት፤ በትጋት እና በተከታታይ መጻፍ አንዱ የመጻፍ ባህሌ ነው። ይህ ደግሞ  በእኛ የለም።
ስለ ሌላው ወገን መመስከር፤ ስለ ሌላው እውቅና እንዲሰጥ ማድረግ የሚፈራ አምክንዮ ነው። ለዚህ ነው ቃለ ምልልሶች በመቁኑን፤ በደንበር፤ በወገንተኝነት፤ ወይንም አቋሙን ለማጋለጥ ሲታሰብ ብቻ ታቅዶ ሲከውን የምታዩት።
ከእኔ በላይ የሚበልጥ መፈጠሩን መመስከር ወይንም ስለዛ ነፍስ መሞገት አውቀን የተውነበት ምክንያቱ ድምቀትን፤ እውቅናን ከራሳችን አልፎ እንዳይሄድ ስለምንሻ ብቻ ነው። የኢጎ እና የምቀኝነት እስረኞች ነን። በእኔ ቤት ግን ይህ የለም። ወደፊትም ካለምንም ተዕቅቦ ለእኔ ዕውነት ነው በምለው አምክንዮ ዙሪያ ይጣፋል።
ያልተጣፈበት ምክንያት አቀባበሉን ድምቀት ከልብ የሚፈቅደው  የኢትዮጵያ መንግሥት፤ የአዲስ አባባ የከንቲባ ቢሮ በተለዬ ሁኔታ እና ወገኖቼ ፈቃድ አላቸው የኦነግን አንድ ክንፍ አቶ ዳውድ ኢብሳን ለመቀበል። የፈቀዱትን እስኪከውኑ ክብሪት መሆን አልሻም። ሞልቶ ለተረፈው ቅዳሜ ... ምን ያጣድፋል?
የሆነ ሆኖ የግንቦት 7 አቀባበል እና ኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍና ድርጅቱ የመሸከም አቅሙን በሚመለከት ከደማቁ አቀባበሉ በኋዋላ ነው የሚሰማኝን የጻፍኩት። ለሞላው ቀን እሚያጣደፍ፤ የሚያስቸኩል ትቅማጥ ነገር የለም። በሌላ በኩል ይህ ይሆን ዘንድ ፈቃደ እግዚብሄርም ነው ብዬ አምናለሁኝ። ይህንም ማክብር ይጠይቃል እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ። „ከሆነው ሁሉ ያለ እርሱ ፈቃድ አንዳችም የሆነ የለም“ ይላል ቃሉ።
በተረጋጋ ሁኔታ ሳላቆላምጥ፤ ሳላባብል ህሊናዬ የሚለውን እጽፋለሁ። ከሁሉ በላይ ልዑል እግዚአብሄርን የምለምነው ሥርዓቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ ብቻ ነው። ከመኪና አደጋ ሆነ ከሰው ሰራሽ ችግር ልዑል እግዚብሄር ጠብቆ ነፍስ በሰላም ውሎ ይግባ የ እኔ ዋና ጉዳይ ይህ ነው። እኔ የድምጽ አላባ ኢትዮጵያ እናቶች ተቆርቋሪ ነኝ።
ሰላም ሲኖር ነው ፉከራውም፤ ቀረርቶውም፤ መሳቃውም፤ ዝናውም፤ ሹመት ሽልማቱም፤ ቅስናው ሆነ ሐጅነቱ ሊኖር የሚችለው። የእስከ አሁን ይበቃል የኢትዮጵያ እናቶች 50 ዓመት ሙሉ ቋት ለማይገፋ የፖለቲካ አቅም ሲያለቅሱ ኖረዋል። ዞሮ ዞሮ ተጎጂዎች እነሱ ናቸው።
ብቻ ውዶቼ ዛሬ የሥነ ግጥም ቀን ስለሆነ እነሆ …

ግድግዳ እና እኔ
      ***
ይመለከተኛል እንደ መልካም ወዳጅ
ፍቅሩን ሳልፈልገው፣
... እሱ ነው አስገዳጅ።

ሚስጥሩን ሊነግረኝ ሲኮለኩለኝ
ሊጠጋኝ ሲከጅል ከሱ ሸሸሁኝ።

ደግሞ በማግስቱ አፋጦ ያዘኝ
እኔ ነኝ የብቻሽ ... ተጠጊኝ አለኝ።
ኧረ ባክህ ተወኝ አልሻም ብያለሁ
ቀን ሰጠኝም ብለህ አትበል
... አለሁ - አለሁ።

ከአንተ ሚስጢር የለኝ፣

.... አንተም ከእኔ የለህ፣
ብትለቀኝ ምን አለ? አቻህን ፈልገህ ...
ስለምን ቀፈቀፍክ .. ቅርንጫፎቼን
ጠሀይነሽ ስትመጣ .... የሚያድጉልኝን።

ጥፈጠፍህ ባዝቶ፣
... አስመርሮኛል
ያልፋልን ስጠብቅ
... እሱ ያዘልባል።
ከአንተ ጋር መሆኔ ጥግ ላይሆንኝ
አርፌ ልቀመጥ አትበጥብጠኝ

አንተ ምን አለብህ?
... የደላህ በጥባጭ ነህ
እሬቱን ለውሰህ መላ ቅጥ ያሳጣህ።
አልሻም! ብያለሁ ...  አትገጥግጠኝ
እሱ ባለው መጥቶ  እስኪ ገላግለኝ።

አፋጠህ አትያዘኝ ብያለሁኝ በቃኝ
የሰጠኝ ይበቃል አትቀጥቅጠኝ።
በቃኝን! አታውቅም በቃኝን እውቅ!
የመጣብኝ ለታ ንዳትወቀ!

ጅማሮ ምንድን ነው? የምን ታቱ ዥግራ?
ወፌ ቆመች ቀርቶ ስባል በውጅግራ።
ውርድ ከራስህ ነው ከራሴ ውረድ
ቆራጣ ሰንጣራ አንተ ድልዝ ጉርድ
                                                                 
·        ተጣፈ ሚያዚያ 16/2001 ሄርሽን ሆቴል
·        ተስፋ መጸሐፌ ላይ ገጽ 10 እና 11 ላይ ይገኛል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።