ልጥፎች

ኢትዮጵያ ባላባራ ጦርነት ተበልታለች፤ በቃትም!

ምስል
አውሬነት? "በውን ጽድቅን የሚጠላ ይሠለጥናልን?" መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፲፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 13.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። መነሻ ምርኩዝ። https://www.youtube.com/watch?v=6vi9PgOzwEQ Ethiopia ዶ / ር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ያደረጉት ሙሉ ንግግር ሰላም የጽድቅ መንገድ ነው።! ·        እፍታ። እግዚአብሄርን አመስግኜ ልነሳ። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ዶር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋዋላ እንደ ዜጋ ፓርላማን እንዲህ በመደበኛ እምከታተለው። በቀደመው ጊዜ ስለምን ይህን ያህል አገለልኩት ብዬ ሳስብ፤ ግብረ ምላሹ ውስጤ ባይታዋር ነበር ማለት ነው።  ውስጤ ባይታዋር ለሆነበት ጉዳይ ጊዜ አላጣፋም። የመስማት አቅሙም ስሌለኝ። ሰሞኑን እህቴ የሳጅን በረከት ስሞዖን መጽሐፍ ተለቋል እና አንብቢው ስትለኝ ሴራ ት/ ቤት ለመግባት አላነበውም ነበር ያልኳት። የዶር አብይ አህመድን የቀደመውን ንግግር አብዛኛውን ቃል በቃል አውቀዋለሁኝ ስለምማርበት። ·        የወ ግ ገባታ።   አሁን የጹሑፌ ታዳሚዎች ለምን ስለዚህ፤ ስለዚያኛው ድርጅት አትጽፊም ይሉኛል። ስሰማው ነው ያን ድርጅት ወይንም ቃለ ምልልስ ያን ውይይት እምሞግተው ወይንም ደግፌ እምጽፈው። ጹሑፍም ሲሆን ሳነበው ነው ሞግቼ ወይንም ይጠናከር፤ ወይንም በትርጉም ይቃና ብዬ እምጽፍለት። የፖለቲካ ድርጅቶች ደግፎ መጻፍ መስዋዕትነቱ አይደለም ክፋቱ እንሱም እዬደገፋችሁዋቸው ግን ማህበራዊ መሰረታችሁን እርቃኑን ያስቀሩታል በጎን። ይህ የግንቦት 7 ካድሬዎች ሌጋሲ ነው። ለዚህ ነው እኔ ኢሳትን ከጅምሩ ሳልቃወመው ግን ምንም ጊዜ ላባክንለት ያ

ደጉ አቶ ዮሴፍ ገብሬ፤ ተባረክ!

ምስል
የማስተዋል አንበል። „ደግ ሰው ግን ለሞመት በደረስ ጊዜ በ ዕረፍት ይኖራል።“ መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·          መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=9ndpRVHlBG8 „Jossy In Z House የአዲስ አመት ዘመድ ጥየቃ ከኢንጅነር ስመኘው ቤት“ ደግነት ለራስ ቢሆንም ትውልድን በማነጽ እረገድ ተቋም ነው። የደግነት ተፈጥሮ ሰላምን ይሰጣል። መጀመሪያ ሰላም የሚሰጠው ለራስ ነው። ሲቀጥል ለቤተሰብ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ በመንፈስ ታለቅሳለች - ሲከፋት። በመንፈስ ታናባለች - ሲጨልምባት። በመንፈስ ትሰጋላች - አዬሩ ሲታወክ። በመንፈስ ሰላሟ ይታወካል ልጆቿ - ሲበተኑባት። ኢትዮጵያ ልጆቿ ሲጠነክሩ እሷም - ትጠነክራላች። ልጆቿ ሲዝሉ እሷም - ትዝላለች። ልጆቿ ተስፋ ሲኖራቸው እሷም - ተስፋ ይኖራታል። ልጆቿ ተስፋቸው ሲደርቅም እሷም - ክው ትላለች። ልጆቿ ቅስማቸው ሲሰበርም እሷም - እንኩት ትላለች። እናት እኮ ናት - አገር። አንጀት ናት የትወልድ ባዕት። ህሊና ናት የነፍስ ባድማ። ልክ እንደ ሰው ነው ጠረኗ። እንዲህ ደግሞ በክፉ ቀን፤ ሰው በጠፋ ቀን፤ ቀን ፊቱን ባዞረ ዕለት፤ አዬሩ በከፈው ማዕለት፤ ተስፋው በራቀ ዕለት፤ ስጋቱ አገር ምድሩን በረቂቅ ባከለለው ሰዓት አንድ እንደ ወልዴ የዛን የበርሃ ከልታማ ቤተሰብ ሄዶ መጠዬቅ ምን ይባል? አለሁላችሁ፤ አይዟችሁ ከአዘቦቱ ቀን ይልቅ ይህ ቀን ወሳኝ ነው። በምን መስፈርት ይህ ደግነት ይተርጎም? በምን ሜትር ይህ ቸርነት ይለካ? በምን ደረጃ ይህ ማስተዋል ይመዘን? ይገርማል እጅግም ይደንቃል። ይህ ቅን ወ

በባዕላት ከብር ለሚገባው ክብር መስጠት ዕንቋችን።

ምስል
ማለፊያ! „አድርገህልኛል እና ለዘላላም አመሰግንሃለሁ።“ መዝሙር ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.09.2018 ከጭምረቷ ሲዊዘርላንድ። በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን! ኑሩልን! ·        መነ ሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=CLDYosWqMXQ „ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ በመሆን በአንድት የአዲስ አመት በዓል ሲያሳልፉ የሚያሳይ ልዩ የበዓል ዝግጅት“ ከእንግዲህ „ሁለቱ ሲኖዶስ“ የሚለው ቃል ራሱ መታረም ያለበት ይመስለኛል። በቅደስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብጽዑን አባቶች ባዕለ ቅዱስ ዮሖንስን ሲያከበሩ ሊባል ይገባል። ቀድሞውንም ዶግማው አንድ ነው የነበረው።  ቅድስት ቤተክርስትያነችነን ጊዜ ፈተነ፤ ዲያቢሎስ ሲረታ ደግሞ አህቲ ቤቴክርስቲያን እንደ ተፈጥሯዋ ሆነች።  የሆነ ሆኖ እጅግ የሚመስጥ የበዓል ጠረን በቅደስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብፁዕን መኖሪያ ቤትም መከወኑ ዘገባው ያመልከታል። ለእኔ በቅድስት ፓትርያርክያት ደረጃ እንዲህ ባህላዊ ትውፊት ሳይጓደልበት ሲከበር የመጀመሪያዬ ነው። እንዲህ ሲከበር አይቼ አላውቅም። ቡናው እየተቆላ እንደ አባት አዳሩ መሰናዶው ተሟልቶ፤ ቤት ያፈራው እንደዛ ኑብኝ ኑብኝ አያለ፤ መዘምራን እዬወረቡ ቅኔው እዬተዘረፈ እፁብ ድንቅ ነው። ይህ ትውፊታችን፤ ትሩፋታችን ያከበረ አያያዝ የዛሬ 10 ዓመት ብዬ ሳስብ ዘመኑም፤ ታሪክም፤ ትውፊትም፤ ትውልድም፤ አገርም የሚካስበት አዲስ ስዕል ዲዛይን ሸልሞኛል። በሌላ በኩል ድርጊቱ  የአብይ ሌጋሲ ታሪክንም እዬጻፈልን ነው። ታሪኩ ደግሞ የ አላዛሯ ኢትዮጵያ አንጡራ ሃብቷም ነው። የነገ ደግሞ ትውፊቷ። ውርስ ቅብብል እንዲህ እያለ ከትወልድ ወደ ትውልድ