ኢትዮጵያ ባላባራ ጦርነት ተበልታለች፤ በቃትም!
አውሬነት?
"በውን ጽድቅን የሚጠላ ይሠለጥናልን?"
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፲፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
13.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
- መነሻ ምርኩዝ።
Ethiopia ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ያደረጉት ሙሉ ንግግር
ሰላም የጽድቅ መንገድ ነው።!
- · እፍታ።
እግዚአብሄርን አመስግኜ ልነሳ። ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ዶር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋዋላ እንደ ዜጋ ፓርላማን እንዲህ በመደበኛ እምከታተለው።
በቀደመው ጊዜ ስለምን ይህን ያህል አገለልኩት ብዬ ሳስብ፤ ግብረ ምላሹ ውስጤ ባይታዋር ነበር ማለት ነው።
ውስጤ ባይታዋር ለሆነበት
ጉዳይ ጊዜ አላጣፋም። የመስማት አቅሙም ስሌለኝ። ሰሞኑን እህቴ የሳጅን በረከት ስሞዖን መጽሐፍ ተለቋል እና አንብቢው ስትለኝ ሴራ
ት/ ቤት ለመግባት አላነበውም ነበር ያልኳት። የዶር አብይ አህመድን የቀደመውን ንግግር አብዛኛውን ቃል በቃል አውቀዋለሁኝ ስለምማርበት።
- · የወግ ገባታ።
አሁን የጹሑፌ ታዳሚዎች ለምን ስለዚህ፤ ስለዚያኛው ድርጅት አትጽፊም ይሉኛል። ስሰማው ነው ያን
ድርጅት ወይንም ቃለ ምልልስ ያን ውይይት እምሞግተው ወይንም ደግፌ እምጽፈው። ጹሑፍም ሲሆን ሳነበው ነው ሞግቼ ወይንም ይጠናከር፤ ወይንም በትርጉም
ይቃና ብዬ እምጽፍለት። የፖለቲካ ድርጅቶች ደግፎ መጻፍ መስዋዕትነቱ አይደለም ክፋቱ እንሱም እዬደገፋችሁዋቸው ግን ማህበራዊ መሰረታችሁን
እርቃኑን ያስቀሩታል በጎን። ይህ የግንቦት 7 ካድሬዎች ሌጋሲ ነው።
ለዚህ ነው እኔ ኢሳትን ከጅምሩ ሳልቃወመው ግን ምንም ጊዜ ላባክንለት ያልፈቀድኩት።
በተደጋጋሚ
ደውለው ጠይቀውኝ ነበር። ቅንጣት ደቂቃ አላጠፋሁም፤ ስውሩ የሴራ
ድር በዚህ በእግረኛ ወታደር አስልፎ አንተን እያነደደ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጉልበታችሁን ገንዘባችሁን ምጥምጥ አድርጎ ይበላል። በጎን
ደግሞ የጠላት ማምረቻ ካንፓኒ ዓላማ ያደርግሃል። ይህን ሳያውቁ የሚተጉ ቅኖች እንዳሉ አውቃለሁኝ። ብቅ ብለው፤ አቅም አግኝተው
መወዳደር አይደለም ሥማቸው ከፍ ብሎ ፓል ላይ ደረቅ አበባ ሲበተንላቸው እንኳን ደም የሚለብሱ አውሬዎ መንፈሶች አሉበት። ልክ እስረኛ
ስለምን ተፈታ እንደሚሉት የአውሬዎች ማህበር መንፈሶች ማለት ነው።
ስለዚህም እራሴን እያጠፋሁ፤ ድካሜ መና የሚያስቀር የሥም አጥፊ አስተባባሪ ባለበት አቅም እምጠፋበት፤ ተጋድሎ በውስጥ ገብቼ እምዳክርበት ስውር ሴራ እንዲያከስመኝ መፍቀድ፤ አንድ ጊዜ ሊሆን ይችላል ማንኛው ነገር ሲወጠን ሁሉንም በቅንነት መመልከት ሰውኛ ስለሆነ፤ ለድጋሚ
ጥቃት ግን ጅልነት ነው። ለዛውም ለጎንደሬዋ ሥርጉትሻ እቴጌ!
በሌላ በኩል ዕድሜ ለቅንጅት ብዙው ወጀብ ባመጣው የፖለቲካ ማዕበል የተቀላቀለ ሊሆን ይችላል፤ ሥርጉተን ግን ገና
በቀንበጥነቷ ፓርቲዋ ሙሉ ጊዜ ሰጥቶ፤ አሰልጥኖ፤ ዓይነህ ጥርስህ ብሎ መንፈሷን ኮትኩቶ፤ ገርቶ በተገባው ልክ ቀርፆ ሰፊ ኃላፊነትን አምኖ ላዘ ዕድሜ ሰጥቶ ዕውቅና ሰጥቶ አብቅሎኛል። መቼም የአንድ የፖለቲካ ድርጅት የክ/ አገር የሙያ ማህብራት እና የ የህዝባዊ ድርጅቶች
ጉዳይ ሃላፊ በዛ ዕድሜ፤ ለአንዲት ቀንበጥ ሴት ወጣት ኃላፊነት መስጠትን ያህል ቁም ነገርም ደፋር እርምጃም የለም።
ስለሆነም ፓርቲዋ ኢሠፓ እማታፍርበት ድርጅቷ በተመክሮ አብስሎ ያሳደጋት እንጂ በሁኔታ፤ ባጋጠሚ ጎርፍ የቆለለት አይደለችም። ሂደቱን ጠረኑን ከሩቁ ነው የምታሸተው
እናም የዛ አስኮባ መሆንን አትፈቅድም። ለጠራጊነት ወይንም ወጥ ለመቀቀል? እእ። ወጥ ቅቀላውን ለእመቤቴ ደጀሰላም፤ ሎሌነት ለእመቤት
ቤተ እግዚአብሄር ከዛ በመለስ ግን አይሞከረም - አልተሞከረም።
ያለውን የበዛ አቅም ጎልቶ እንዳይወጣ
በስውር ዲስክርምኔሼን ጠንቅቃ ታውቀዋለች። የዲያስፓራ የፖለቲካ አቅም ተቀናቃኝ ሪክርድ ሰባሪ ቢበላ ግንቦት 7 ነው። አሁን ተመስገን
ነው እኛን ለቀቅ አድርጎ ኦህዴድ ላይ ጉብ አለ። ያ አልሆን ሲል ደግሞ አሁን አብን ላይ ሰፍሯል። ይህ ያልተገለጠው የግንቦት
7 ወኪሎቹ የውስጥ ለውስጥ ህግ ነው። ሙኒክን
አይጨምርም። ሙኒክ ያሉ የተግባር አንበሶች ንፁህ የነፃነት መንፈስ ነው ያላቸው።
የሆነ ሆኖ የግንቦት 7 አጠቃላይ ነፍሱ
ማጥቃት እና መቅጣት ነው፤ እንዲህ ላለ የቅጣት ተውኔት ፈቅዶ ማገዶነት በጥናት ሊመሰረት ይገባው ስለነበር ዘው አላልኩም በቤተ - ኢሳት።
ጠብታ፤ እፍታ፤ ማዕዶት፤ ቃናም፤ የወግ ገበታም የሥርጉትሻ መንፈስ በ20006 እ.አ.አ የተፈጠሩ ናቸው። ግን ተዘርፈዋል። ጠያቂ የለም እና። እንዴት አሻቅበን ንጉሦቻችን እንጠይቃለን?
በሌላ በኩል ደግሞ የሲዊዝ መንግሥት አሳምሮ የሚያውቃቸው የራሴም የጸጋዬ ድህረ ገፅ እና የጸጋዬ ራዲዮም በራሴ በጀት የሚተዳደር አለኝ። ቅንጣት 05 ሳንቲም መዋጮ ያልተጠዬቀበት። የትውስት ጹሁፍ እና መንፈስ ቀርቦበት የማያውቅ።
ሁለቱንም ማጠቅላል ያሰኛቸው ሳይችሉ ሲቀሩ አንድ ጊዜ ኦነግን የሚበረታታ ነው፤ ሌላ ጊዜ ተዋህዶን የሚቀድስ ነው፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ
አንድነት ፓርቲ ልሳን ነው በማለት ያደረጉትን አድርገዋል። ከሰውኛልም። ከብዙ ትግል ክስ በሆዋላ ክሱን የሎሬቱ መንፈስ አሸንፎልኝ ቀጥዬ ነበር።
ነገር
ግን በመጨረሻ ራዲዮኑ የተስተጓጎለው ግን „ለአንቺ ነው ኢትዮጵያን“ ስለምወደው ስለማዘወትር ነው። ለዚህም ሲቆም የሥርጉተ ሞገድ
ሲስተጓጓል ጮቤው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ይልቅ ግንቦት 7 ደስ ይላቸዋል። ሥርጉትሻ ድምፆዋ ተዘጋ። ግን የሚዘመረው የእነሱ ላንቺ
ነው ኢትዮጵያ ነው። የግንቦቶች ስብሰባቸውም ሄጄ እምቆዬው መዝሙሩ በጋራ እስኪዘመር ነው። ከዛ ጥዬው ነው ወደ ቤት እምመለሰው።
እኔ መዝሙራቸውን በመደበኛ በራዲዮ ፕሮግራሜ እዬሰራሁ፤ ስለ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ እዬሞገትኩኝ
ጸረ ግንቦት 7 እያሉ እዚህ ያሉ ወኪሎቻቸው ደግሞ ያሳድዱኛል። እዚህ ብቻ አይደለም በኔት በመላ ዓለም ነው፤፡ ጉግልን ሊንክ ማድረግ
አልችልም። አንዲት ቀንጣ መንፈስን እንዲህ የሚታገል ኢትኦጵያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓለማ ለብሶ … ለ ኢትዮጵያ ነጻነት ተስፋነት ... እሱ ይሁነው።
የሆነ ሆኖ እኔ የሃሳብ እንጂ
የድርጅትም፤ የሊሂቅም ጸር የለኝም። ወደፊትም እምታገለው ሃሳብን ነው። ብቻ የፈለጉት ተሳክቶላቸዋል የጸጋዬን ሌጋሲ ማስቀጠል ሲዊዝ
ውስጥ አልተቻለም። እንደ አጀማመሩ የወጣቶች የህሊና ግንባታ ማዕከል ሁሉ መመስረት ይቻል ነበር። መቼም የጸጋዬን ሌጋሲ እዬታገሉ
ኢትዮጵያዊነት ትርጉም አልባ ፍጥረትነት ነው ለእኔ።
- · ቀንበጥሻ።
አሁን ፈተናው ተግ ቢል ብዬ ብሎጌን „ቀንበጥ“ አልኩት እንጂ እኔ ከሎሬቱ መንፈስ ውስጥ ነፍሴ አዬር ያጥራታል። እንኳን
እኔ ቤተሰቦቼም። እህቴ ገጣሚ፤ ጋዜጠኛ እና የፈጣራ ባለሙያ የሆነውን ፍጹሜ አሳፋውን ሰፍ ብላ ነው የምትወደው። ለምን እንደሆን
ታውቃላችሁ በጋሼ ጸጋዬ ምክንያት።
አሁን ስለ አቶ ታከለ ኡማ ለእህቴ ነግሬያት ስለነበር ደግማ ደውላ ግን እውነትሽ ነው የሎሬት ጸጋዬ የአንቺ ታቦት የሥጋ ዘመድ ናቸው አለችኝ። አዎና አልኳተኝ። ይህን ያህል ተጽዕኖ የሚፈጥር መንፈስን ነው የሚታገሉት። ጸጋዬ ማለት እኮ
ኢትዮጵያም አፍሪካም ማለት ነው። ቅኔም ጥበብም ማለት ነው። ማን መተርጎም ይችላል የሎሬቱን መንፈስ ቀድሞ ነገር። ማን አቅም አለው ለማመሳጠር?
- · የትውስት ክብር ይቀፈኛል።
ብቻ የሥርጉተ ፕሮጀክት በማንም ሥር መሆን አይፈቅድም። የትውሰት ክብርም አያሻም። የሥርጉተ
መንፈስን መጠቅለል አይቻልም፤ ፋክት እንጂ ሥርጉተን የሰው አምልኮ አያስደገድጋትም። ወረቀትም አምላኪ አይደለችም። ሃሳብ ለዛውም ቅን ከሆነ ሸፍጥ እና ሴራ የሌለበት ከሆነ ብቻ።
ለዚህም ነው የግንቦት 7 ካድሬዎች ባለበሌለ
ኃይላቸው እዬታገሉኝ ኤርትራ አመራሩ ሲገባ ፈትኑን ተብለው በወያኔ
ሃርነት ትግራይ፤ ሌሎች የጎረቤት አገሮች እንዳይጠጉ መንገድ ተዝግቶ ኢትዮጵያና ኤርትራ በነበራቸው የጦርነት ቁርሾ እና በቅንጅት
ቁርሾም የተነሳሱባቸውን አክሎ ህዝብ እንዳይደግፋቸው፤ እርምጃውን እንዲጸዬፈው ዘመቻ ሲካሄድ
ደግሞ ከድርጅት አባላቶቻቸው፤ ከሚዲያዎቻቸው፤ ከተንታኞቻቸው በላይ እጅግ በላይ በትጋት ጭብጨባ፤ ከንቱ ውዳሴ፤ የጎርፍ ድጋፍ ስንቋ ያልሆነችው
ጎንደሪት ሥርጉተ ሥላሴ ወጥታ ሁሉንም ሞግታለች ሃሳቧም እረቷል።
የግቦት 7 ካድሬዎቻቸው ኦህዴድ ሲመጣ ነው መጻፍ የጀመሩት፤ በአቅም ኦህድድ የሚበልጣቸው መሆኑን
አሳምረው ያውቃሉ። መንገድ ላይ ለማስቀረት ብዙ ተሞክሯል። ያን ጊዜ ግንቦት 7 በግራ በቀኝ ሲፈሰፍስ ትንፍሽ የሚል አልነበረም። ደግሞም
አልነበሩም። ራሱ ግንቦት 7 ሲመሠረት ችቦ ለኮሿ ሥርጉተ ሥላሴ ነበረች። ግን መንፈሱ አቅምን በቅጡ ማስተዳደር የማይችል ስለሆነ፤
የራሱን አቅም ራሱ ሲደርምስ ውሎ ስለሚያድር ጠላት እና ወዳጁን የመለዬት ክህሎቱ ስላልተሰጠው ሞገዳማ አቅሙ ባክኖ ተኖ ቀረ … አሁን ባለው ቀዝቃዛ ስሜት አንድ አመት ቢቀጥል ይታይ ነበር ጉዱ …
ግንቦት 7 የአማራ ተጋድሎ ሲነሳ ደግሞ በሳተው መርህ ብቻ ሞጎቼዋለሁኝ። እራሱ ከኢትዮጵያ አርበኞች
ጋር ሲዋህድ እዚህ ያሉ ወገኖቼ ደውለው ተደስተን ሲሉኝ እኔ በዬትኛውም ሁኔታ ውህደት ሲፈጠር አላጨበጭብም፤ ጀንበር ስታዘቀዝቅ
የሚመጣውን ጣጣ አውቃለሁኝ እና። የቅንጅትም ጊዜ በልክ ነው የነበርኩት። ነገር ግን ተቃውሜ አልነሳም።
እንዲያውም ተቃውመው የሚነሱትን
እሞግታለሁኝ። በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር የውጭ አገር ተወካዮች አብረሽን ሥሪ ብለው ጠይቀውኝ ነበር። አልፈቀድኩኝም።
እኔ ሰው እንጂ ሮቦት አይደለሁኝም። ሚዛናችሁን ነው የሚያሳጣው አንድ መንፈስ ብቻ ጥገኛ ስትሆኑ።
አሁን የእውቅ ሰዎች ችግር ይኸው
ነው፤ ትናንት ግንቦት 7 ዛሬ ደግሞ አብይ ሆኗል ጨዋታው። አብይን ገዱን ደግፉ። እም! ነው። ያ ምርጫ መጥቶ የግንቦት 7 ካድሬ
እና ፊታውራሪ የነበሩ ሰዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ማዬት ናፍቆኛል።
የሆነ ሆኖ የአማራ የህልውና ተጋድሎ ሲመጣ አቤቶ ግንቦት 7 የመንፈስ ዘረፋውን አና ብሎ ሲመጣ
የማከብረውን ድርጅት ወጥቼ ሞግቼዋለሁኝ። አውቀዋለሁኝ እና ያ መንፈስ የአማራነት ብቻ እንጂ የማንም አጀንዳ ተለጣፊ አለመሆኑን፤ የራሴ ጉዳይ ነው። አጀንዳዬም ነው አብሶ ወልቃይት እና ጠገዴን በሚመለከት።
በተሰቦቼም ያውቃሉ ውጪ ያሉት። ይህ የነፃነት ተጋድሎ ከመጣ ግንባርቀደም እንደምሆን።
በሌላ በኩል ግንቦት 7 ለአማራ
ህዝብ ያለው ስውር፤ ረቂቅ ጉዳይንም የተቀነባባረ ጥላቻም ሆነ መሰሪ የሴራ አግናባትን እረዳለሁኝ። ቅንነት ብቻ ነው እኔን የሚሸውደኝ
እንጂ ብልጥ እና ጮሌነት አብሶ ሌብነት እኔን መግዛት እና መንዳት አይቻለውም፤ አይታሰብም።
ከዛ የቀጠለው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር መዋጡ በህብር ራዲዮም ይፋ ሆነ። "አልተለዬነም አብርን ነን" ሲሉ እነ አርበኛ ማዕዛው ጌጡ ከብት ጠባቂ ሲሆኑ፤ እነሱ በቻፕተር አውሮፕላን ስቲዲዮም ቅብጥ እና ቅልጥ ሲሉ ደግሞ ነበር።
ለዚህም ነው እኔ "አርበኞች" የሚለውን እያነሳሁ ግንቦት 7 እያልኩ ስጽፍ የነበረው። አብረን ነን እያሉ ሲሞግቱ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባላት እና አርበኛ አበጀ በለው ክብር የመሥራቾቹ
ደግሞ እንደ አሞሌ ጨውነት ሟሙተው ታይተዋል። ይኽው ነው ግንቦት 7 ማለት።
ሠራዊት የተባለውም ሲመናመን ሲመናመን አሁን ያን ያህል ስሜን እዝ፤ ምስራቅ እዝ፤ ደቡብ እዝ
በንፈስ ሠረጋላ አጠቃ እዬተባለ ሞገድ ላይ የተደራጀው ብርጌድ ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጀምሮ ሰፊ ክብርና ሞገስ የተሰጠው ድርጀት
ሠራዊት 300 አለሞላም። ለዛውም የአማራ ሠራዊት ብቻ ነው። ለዚህም ነው አማራ መሬት ላይ እንዲቀመጥ የተደረገው። ከላይ እስከታች
የቢሮ የሚኒስተር መ/ቤት ሰዎቹ ነጭ ለማቦሾች ደግሞ እነማን ተሰልፈው እንደ ነበር ይታወቃል። እግረኛው አማራው እዛው ወደ ከሞፈሩ ነገ ይሸናል። ምን አልባት አስከ ምርጫ ድረስ ቀለብ ይሰፈርለት ይሆናል ...
- · የአፍታ ሙቀት በጥንግ ድርብ …
አሁን ኢትዮጵያዊዬ ሆነናል እያሉ ነው ግንቦቶች። አብይ ካቢኔን ለመሞገት አፍታ አይቆዩም -
ሲሾልኩ። የሆነ ሆኖ ኤርትራ መሄዳቸው፤ የትጥቅ ትግል መጀመራቸው በአማራ መንፈስ ውስጥነት አቅም ሙቀት ብቻ እና ብቻ ነው። ዘሃቸው፤
ፈትላቸው ሠራዊት እያሉ የሚንኮሹበት ያው አማራ ነው።
ያን ተማምነው ብቻ ነው ትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡት። እግረኛው አማራ ነው። ይሄው ሄዶ የተቀመጠው ሰራዊታቸው
እኮ ባህርዳር ነው። አንዲት ሃባ ጉራጌኛ የሚናገር ሰው አይኖራቸውም። በግንቦት 7 ቁልፍ መዋቅር ለቤተመንግሥቱ የሚ/ሮች ምክክር
ውሳኔ ሰጪ ደግሞ ማን እንዳለ ዝርዝሩን ገባ ብሎ ማዬት ነው። አሁን ፊት ለፊት የሆኑት ህብረብሄር ነን ለማለት ነው።
ቆዩ የተባሉ ሊሂቃኑ እንደ ዶር ታደስ ብሩ ያሉ ባለ ሙሉ አቅም ሞጋች ሊሂቅ የጉራጌ ግንቦት 7 እንዳይባሉ
ለሸውዳ በሚያመች መልኩ ከሚዲያ እንዲሰወሩ
ተደርጓል። ቆይቶ ግን ካርታው ይወጣል። ግንቦት 7 በተቆጣጠራቸው የዲያስፖራ ሚዲያዎች፤ በሊሂቃን ጉባኤ ላይ ቁልፍ ቦታ
ማን እንደለ ዛሬ ዛሬ ሁሉም ደፍሮ እዬተናገረው ነው።
የአሁኑ ንግዱ ደግሞ ከአገርዊ
ንቅናቄው ፍርሰት ማግስት ደግሞ የኦነግን ዓርማ ተሸክሞ መዞሩ አብቅቶለት ትንዳኤና ህይወትነትም አክትሞ፤ ኢትዮጵያዊነት ተሁኗል። ግንቦት 7 በውነተኛ ማንነቱ የኢትዮጵያዊነትን መከራ መሸከም አለመቻሉን ታሪኩን፤
አካሄዱን መፈተሽ ነው መጎጎል ነው … ጉጉልሻ ይዘረጋግፈዋል ….። ምን አልባት ለሌላው ይመች ይሆናል፤ ብቃት ላላቸው በዬትኛውም ሙያ ዘርፍ ላሉ አማራዎች ግን ተነግሮም አያልቅም። ጦርነቱ ማጥቃቱ መስወገዙ ...
ቀስተደመና፤ ቅንጅት፤ ግንቦት 7 ኢትዮጵያ አብሰንት ናት። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ጋር ተዋህድኩ ሲል። ሥሙ ከነመንፈሱ
ተከልቶ "አርበኞች ግንቦት 7" ተብሎ „ኢትዮጵያ“ ተጎመደ። ተስፋውም እንደዛው። እጅግ በጣም በርካታ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።
እንዴት አግላይ ድርጅት እንደ ሆነ። አግላይ መሆኑ ባልከፋ ዜጋን ስደት ላይ የሚያሰድድም፤ ማህበራዊ መሰረቱን የሚበትን፤ የውስጥ
ሰላምን የሚያውክ ነው። አዝነን እንድንኖር የበዬነብንም ነው።
ተነግሮ እንኳን አባላቱን ለመቅጣት አለመፈለግ ውስጠ አካሉን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ለዚህ
ነው ፈተናው ለሁሉም የተፎከካሪ የፖለቲካ ድርጅት ነው የምለው። መሬት እራፊ እስኪያገኝ ድረስ ሰላማዊ ነው ግንቦት 7። ከዛ እዬፈረፈረ እዬፈረፈረ
ባዶ ያስቀራል። አብሶ ብአዴን በዚህ አያያዙ ያዬው ሰው ነገን?
ባዶ አስቀርቶም እሱ ቢበጅ፤ ተስፋን ለድል ቢበቃ ምንም ባልነበረ አብሮ መውደቁ ነው ክፋቱ።
ጦርነት የመሳሪያ ብቻ አይደለም የመንፈስ ጦርነቱ አሁንም ቀጥሏል። „ሲጠሉም እስከ ንፍጥ እስከ ልጋጉ፤ ሲወዱም እስከ ንፍጥ ልጋጉ
ነው።“ አማራን ጠልተህ፤ አማራን ተጠልለህ እና ተጠግተህ አይሆንም። ለዛውም ነፍሱን በሸልንግ እዬገዛህ። የሚብጠለጠሉት የ አማራ አባት እና እናት የወለዳቸው ናቸው።
የትኛውም ድርጅት ይሁን ካለ አማራ መንፈስ አይሳካለትም፤ ለዚህ ነው አሁን ጫና በጫና አማራ
መሬት ላይ ያለው፤ በመንግሥት ደረጃ እራሱ … የአማራ አቅልን ማግኘት
ብቻ ነው ኢትዮጵያን ከነክብሯ ማዘለቅ የሚችለው። ይህን ኦህዴድ ራሱ አይቶታል። የዘመን ታሪክ አይደለም እምናገረው። በተጨባጭ ያለውን
ዕውነት ነው። ግን አሁንም ኦህዴድ ለመንፈሱ ከድል ማግሥት ተጠንቅቆለታል ወይ ሲባል ምንም ነው ...
- · ጦርነት እና እኛ።
እውነት ለመናገር ግንቦት 7 ጦርነት ናፋቂ ድርጅት አልነበረም። በተለያዬ ቃለ ምልልስ ይህን አዳምጣለሁኝ። ተገዶ ነው ጦርነት ውስጥ የገባው። እንዲያውም በዚህ መልክ የሊሂቃኑን የሰለቻቸውን የኤርትራ ኑሮ እና አዬር
ላይ የተቦረቀቀው ተስፋ መኖ ስለቀረ ተገላግለዋል፤ ዕድሜ ለቄሮ እና ለአማራ ታገድሎ።
ከማንም በላይ አትራፊ ነው ግንቦት 7 በዚህ ለውጥ። በቃል ብቻ ስንት ዘመን ይኖራል? ምክንያቱም በራሱ በዴያስፖራው አንድ ዓመት የሚያስቀጠል
የመንፈስ ቅምጥ ሃብት አልነበረውም። ለዚህ ነው እኔ በ2016 ተግቼ
የሠራሁት ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል እያልኩ ግን ሰሚ አልነበረኝም።
አሁን አውሮፓ ላይ የነበረው ስብሰባ እጅግ የቀነሰ ነበር፤ ሆላንድና ጀርመን የሆነ ሆኖል። ልዋጋ
ቢልም አይችለውም። ለማስፈራሪያነት ሠራዊት አለኝ አለ ይህም ታዬ። ድርጅታዊ የፖለቲካ አቅሞ የሞባይል ጽ/ቤት ነበር፤ የጸና የፖለቲካ አቋም፤
የጸና የሃሳብ እቅድ የለውም። ካቀደው ላይ መዳበል ብቻ ነው ነፍሱን ለአደራ ሰጥቶ። ያ ያን ዕቅድ አቃጁ ሲሰበስብ መሃል ላይ ይቀራል
ግንቦት 7። ብቻ በአውሮፓ ህብረት እና በምዕራባውያን ፈቃድ ነበር ቀይ ምንጣፍ የታሰበው ለማ እና ገዱ በቆረጣ ገብተው ጉድ ሠሩ።
ቀድሞ ነገር --- ዘመኑ አይፈቅድም በሽምቅ ውጊያ ድል ማሰብ፤ ይህንንም በ2013/14 በሚገባ ዘርዝሬ
ጽፌዋለሁኝ። ይህን ስል ጀግንነት ያነሰዋል ማለቴ አይደለም። ቀደም ባለው ጊዜ የእክሌ ተከሌ ተብሎ አይለይም አገር የቆዬችበት ጥበብ።
ህብራዊ ተጋድሎ ነው ኢትዮጵያን ያቆያት። ጀግና
የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ነው። ወደፊትም
ጀግንነት የአንዱ ብሄር ብሄረሰብ መለያ መግለጫ አይደለም። የኢትዮጵውያን ደም ጀግና ነው ኤርትራን ጨምሮ።
- አሁን?
የአልጀርሱ ስምምነትን ወደ ተግባር ለማሸጋጋር ደፈር ውሳኔው ሲወሰን እኔም ጽፌበታለሁኝ። አይሳካም ላለው ለጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ትንብያ መልስ ሰጥቼበታለሁኝ። እንደሚታወቀው
የሁሉ ዓይነት የጦርነት ቀጠና የነበረው በኤርትራ በኩል እንደ ነበር ይታዋቃል። የመንፈሱንም፤ የሚዲያውንም ሞገድ አክሎ።
የአልጀርሱ
ስምምነት ውሳኔ ማግኘት ትሩፋት ተዘርዝሮ አያልቅም። ይህን የስምምነት ሂደት ያልተገባ ነው ሲሉ በ2010 በፓርላማው ጠ/ ሚር አብይ
አህመድ ጥያቄው ተነስቶ የሰጡት መልስ ነበር። አሁን ደግሞ በ2011 ድጋሚ ተነስቷል። ያሳፍራል። ቀድሞውንም የራሳቸው ውሳኔ ነው የ ኢህአድጎች። ሲቀጥል መልስ ተሰጥቶበታል፤ ሲሰለስ
መሬት ላይ ታምር እዬታዬ ነው በመንፈስ ትርፋማነቱ፤ የዓለምም ዕምደኛ ሆኗል ሂደቱ።
ጥያቄው በድጋሚ የተነሳበት አግባብ ኤርትራን ምሽግ ያደረጉ የነፃነት አርበኞች የትጥቅ ትግልን አቁመው አገር
እንዲገቡ ግድ ይል ነበር። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም መሆናቸው የኤርትራ መንግሥት ሊወስድ ይገባው የነበረው ቀዳሚው እርምጃ ያስታጠቃቸውን
ትጥቅ አስፈትቶ፤ ቢፈልጉ ኤርትራ መኖር ቢፈልጉ ኢትዮጵያ ገብተው እንዲታገሉ መፍቀድ ነው።
ይህን ደግሞ እኔ እራሴ የኤርትራን መንግሥት ጠይቄዋለሁኝ። ትጥቅ እንዲያስፈታ። ውሳኔው ሲወሰንም
አመስግኜ ጽፌያለሁኝ። ይህን የመሰለ ዕድሏ ኢትዮጵያ ሊታቀብባት ስለማይገባ። አሁን አላዛሯ ኢትዮጵያ ትንታግ ሙሴ አግኝታለች። ኢትዮጵያ
ብቻ አይደለችም አፍሪካም ጭምር። ዓይነ ገብ፤ ህሊና ገብ፤ መንፈስ ገብ ብጡል አህጉራችን መሪ አላት።
ስለዚህ የትጥቅ ታጋዮች ምርጫ አልነበራቸውም። ይህ ማለት መፎከሪያ መሬት የላቸውም። በጀቱም
እንዲሁ ይታጠፋል ወደ አትራፊው ጉዳይ። ሌሎችን የጎረቤት አገሮችን ቢሆን ብልሁ የአብይ ሌጋሲ ቀድሞ መሰመር አስይዞታል። ስለዚህ
ጠቅለል ብለው መግባት ግድ ሆነባቸው እና እዬገቡ ነው። ይህ መቼም ጉሮ ወሸባያ አያስብልም። ትጥቅ ፈቶ ገብቶ ጉሮ ወሸባዬ አስፈለጊ
አልበረም። ድል እንኳን ቢሆን ቀስ አድርጎ መያዝ ይገባል። መብሰል፤ መሰልጠን፤ ነገን አርቆ ማዬት ያስፍለጋል። መስከን!
ሌላው የአማራን ገበሬውን አስታጥቄ ነበርም እያሉ ገበሬውን በገንዘብ መግዛትም ለአብይ ለልሁቅ መንፈስ የማይመጥን ነው። እንኳን ይህን ሌላ ያውቃል መንፈሱ። የነፍስ
ሌብነትን ደግሞ በአጽህኖት ይጸዬፋል - ሙሴው። ሌብነት ሲባል የሁሉም ዓይነት ሌብነትን ነው።
በሌላ በኩል የምስራቁ፤ የማሕል አገሩ፤
እና የደቡብ እዝ የሠሩት ካለም ቢዘረዘር ወሸኔ ነበር። በተጸዬፍከው ማህበረሰብ ላይ ድርብ ጨዋታ ያ ሁሉ ግፍ በአንተ
ስም፤ በሌለበት ተቀብሎ አሁንም አይጥን ድመት ገድላ የምትጫወትበት ያህል ከሥልጣኔ በታች የሚያደርግ ጉድ ነው የሚደመጠው አዲሱ ትዕይነት ደግሞ። ለዛውም የአብይን የለማን መንፈስ ለመሸወድ ማሰብ?
ብቻ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የማይመቸው የትጥቅ ትግል አራማጅ ውስጥ የግንቦት 7 እና የአማራ
ዴሞክራሲያዊ ኃይል የሚባለው ነበር። ሰራዊታቸው የሁለቱም የአማራ ነው። ሊሂቃኑ የግንቦት 7 አማራ መደራጀት የለበትም ለኛ ዘበኛ፤
ቀቃይ፤ አንጣፊ፤ ጎዝጓዥ መሆን ብቻ ነው ባይ ናቸው።
እንዲያውም የተደራጁበት ጊዜ አግባብ አይደለምም ባዮች ናቸው። እስተዚህ ድረስ የአማራ ሊሂቃን
ጨምሮ ሁሉም ሊሂቃን የሚያስማማ ጉዳይ ነው። በዚህ አቋም እከሌ ተከሌ የሚባል የለውም። ስለምን ያ የነጠረው አማራ አቅም ለግለግ ብሎ ከወጣ ለመሪነት መወዳደሩ አይቀሬ ነዋ። በሌላ በኩል
ጠረኑን ጠረኑ ይመርጠዋል። ይህም ሥጋት አለ። ደጋፊ ዞግኛ ህብረ ብሄር የሚባለውም ያው ዞግኛ ነው ወስጡ ለቄስ ነው።
በሌላ በኩል የግንቦት 7 ሊሂቃን በታወቀም ባልታወቀም ምክንያት ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር
የውስጥ ለውስጥ ቀዝቃዛው ጦርነት አለባቸው። ይህ በቁጥር ማንስ የሚመጣ እሰጣ ገባ መሰለኝ።
አሁን እነሱን ግንቦቶቹን ማለቴን ነው በሚሊዬነም አዳራሽ ማዬት የመሰለ የሽንፈት ሽንፈት የለውም ለወያኔ ሃርነት ትግራይ
ሊቃናት። ሽንፈት ግን አልነበረም። ያው አውራው ፓርቲ እኮ ኢህአዴግ ነው። ያለው መንግሥትም የ ኢህአዴግ ነው። ጡንቻው መቀነሱ ነው ልዩነቱ።
ብቻ ... አዎን ብቻ ... ዛሬ በፓርላማ የተነሳው ጥያቄ ምንጩ ከዚህም ነው። አሁን ለሥልጣን ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት የአብይን መንፈስ ማሸነፍ ከባድ
ነው ለሁሉም ሊሂቃን እከሌ ተከሌ ሳይባል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሌጋሲ አራማጆች ለምዶባቸው ነው እንጂ … በዚህ ለውጥ እኮ የበለጠ
ተጠቃሚ የሚያደርገው ወያኔ ሃርነት ትግራይንም ጭምር ነው፤ በዛው በግንባራቸው ቤተኝነታቸው።
- · አልጀርስና ወያኔያዊ መንፈስ።
በቅድሚያ በኤርትራ በኩል „ከአክራሪነት ደጋፊነት" ጋር የነበረው መሞዳሞድ ቅስሙ ተሰብሯል። በዚህ ዓለም
አቀፍ ድጋፍ እና ተቀባይነት ኪሳራ አለበት አቤቶ ወያኔ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምምነት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ህልም
አይደለም። ሌላ ቦታ ቀውስ፤ ጦርነት ይካሄዳል፤ በዚህም ካለነሱ ሰላም መረጋጋት እንደማይችል የዓለም ማህበረሰብ ድጋፍ ይሰጠናል ብለው
ያምናሉ።
ይህም ቢሆን ሰፊ ወገን ቢፈናቀልም፤ አሁን ጥበበኛው የወሰደው እርምጃ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር አፈታት ታሪክ በኢትዮ
ሱማሌ የታዬው ብልህነት እና ልቅና ተስምቶ አይታወቅም። ረቂቅ እና ሩቅ ነው።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንታት የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነት ሌላ ስጋትም አለባቸው፤
ደሴታቸውን ሰላም ለማስጠበቅ ተብሎ የኢትዮጵያ አሉ የሚባሉ የአገር መጠበቂያ ጥሪቶች ሁሉ ትግራይ ላይ ስለተከዘኑ ማዕከላዊ መንግሥት
ወደ ማጠናከር ይዙር ሲባል የትግራይ ልዕለ ኃያልነት ይሸረሸራል። ይህም ትልቅ ስጋት ነው።
በሌላ በኩል ሲቆፈር የሚውልም አገልጋይ የሠራዊት አባልም አይጠፋም። ያም መንግሥት ይከፍለዋል ለውትድርናው ነገር ግን ትግራይን ያለማል። ይህም ሌላው
ፈታኝ ጉዳይ ነው። ሌላው ይዳራል፤ ይኳላል፤ ይማራል፤ የሠራዊቱ አባላት ደግሞ ቀበሮ ጉድጓድ ላይ አቧራ ለብሶ፤ በበርሃ እዬተቃጠለ
የትግራይን ልዕልና ማስከበሩን ይቀጥል ነው ፍሬ ሃሳቡ።
ወይ ሰላም የለም ወይ ጦርነት የለም ግን ትግራይ አንበርክካ ታስገብር ነው። ሌላው የአገር የመዋለ ንዋይ
የመንፈስ ጥሪት ኪሳራ ጉዳያቸው አይደለም። የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦርነት በቀዝቃዛው ጦርነት ውስጥ ብቻ ተማክሎ እንዲቀመጥ የተደረገበት
አውራ ምክንያት ይህ ነው። ማድቀቅ።
እኒያ እንደዛ የምናከብራቸው የዓለም አቅፍ ህግ ሊቀ ሊቃውንት ዶር ያዕቆብ ኃ/ማርያም እኮ ዋናውን መርህ ላይ ማተኮር
ሲገባቸው ታች ወርደው አፈጻጸም ላይ ነበር ያተኮሩት። ተደናቅፎ ወይንም እሽሩሩ እዬተባለ በታመሰ ፖለቲካ ኢትዮጵያ እንድትታመስ
ነው የሚፈለገው የነበረው። ኤርትራን ያህል አገር ተገንጠይ ስትባል፤ ኢትዮጵያ ወደብ አያስፈልጋትም ተብላ አስብ ተገፍቶ ሲሸኝላት
ብቻ ነው ለግንበት 20ዎቹ ድል ነው።
„ዶር ያዕቆብ ኃይለማርያም
የባድመ ጉዳይ እንዴት ይሆናል Dr Yakob“
ሌላው የወያኔ ሃርነት ትግራይ
አማራን ለመንቀል፤ የውስጥ ሰላሙን ለመንሳት አብሶ ጎንደርን ለመበቀል የግንቦት 7 የአሸባሪ ድርጅት እያለ ዘር ማፍለስ፤ ማሰቃዬት፤ ማንኮላሸት፤ በዘር ማፍሪያ
ሽቦ ልኮ አረመኔያዊ ድርጊት መፈጸም፤ ጥፍር መንቀል አይቻልም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ካወረዱ።
የቁርሾ መጋገሪያው ለግራ ቀኙ
አማራ ነበር። ያ ትክክል ነበር እያለ ነው አሁን ግንቦት 7 መሳሪያ የገበሬውን እዬገዛ ያስታጠቅኩትን፤ አስፈታሁ የሚለው። 5 ሺህ
ቀርቶ 500 ሠራዊት አልነበረውም። ይህን የኤርትራ መንግሥትም አሳምሮ ያውቀዋል።
በሌላ በኩል እሳቱ የሚነደው አማራ መሬት፤ አብሶ ጎንደርም የጦርነት አውድማነቷ ያከትማል። ስለዚህ ህዝብ
ህሊናውን ሰብሰብ አድርጎ ሰላማዊ ኑሮውን ሲቀጥል ይህ እረፈት አይሰጠውም ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ጸረ አማራ ማንፌስቶው። ከመቃብር
በታችም ይህ ያባንነዋል የዚህ ማንፌሴቶ ማህበርተኛን።
- · ሌሎችም ቢሆኑ …
ሌላው ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የፃፈውንም፤ አቶ ነዕምን ዘለቀ የጻፉትንም ልብ ብላችሁ መርምሩት፤
እርቀ ሰላሙ የመሳካቱን ምኞት እና ዕድምታው ምን ያህል እጁ አዎንታዊነት ነበረው ብለን ማሰብ አለብን።
ሲሳካ ደግሞ ግንቦት 7 ሳያፍር ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ እኛ አለንበት አለ ያው እንደ ለመደበት።
የሚገርመው ታሪክ ግንቦት 7 መንግሥት ሳይሆን ከሌላ መንግሥት ጋር ተደራደርን ማለት በፖለቲካ ፍለስፍናዊ አቅሙ በራሱ የወደቀ ነው። የፖለቲካ አቅሙም አይፈቅድም። ቢፈቅድ አኮ የዲአስፖራው ተቃዋሚ ድርጅቶች አንድ ማድረግ፤ ማህበረሰቡን አንድ ወጥ መንፈስ ይፈጥር ነበር። እንደ በተነን እኮ አገር የገባው። ሙሴ ሲገኝ ደግሞ ስሜን አሜሪካ ገድል አተይቷል። እኛ ቀድመን እንገኝ ጉባኤውን እንምራም አለበት ... ዕውነቱን ማወቅ ይጠቅማል። ጎንደሬዎች "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ።
ለዛውም አመራሩም ካድሬዎቻቸውም አይሳካም እያሉ እዬሞገቱ፤ ከተሳካም ተብሎ ወደ ኋዋላ ጎታች መንፈስ
በታኝ ጹሁፍን እያሰራጩ። መቼም በዚህ የአብይ ሌጋሲ ብቻ ሳይሆን ኦህዴድም ጉድ በል ጎንደር ሳይሉ አይቀሩም።
ምዕራባውያን እንኳንስ ይህን ሉላዊ ትርፍ ቀርቶ ቅንጣቷን
ሁሉ እዬተከታተሉ ስላሉ እነሱም ይገርማቸዋል። ብቻ ቃሉ ከግምት በታች የወረደ ጉድ ነበር - እኔ ራሴ የማልጠብቀው።
ይህ ቢሆን
እማ የኤርትራ መንግሥት ባነሰ ግምት ለአርበኛ አቶ አንዳደርጋቸው ጽጌ
እንደ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ያህል የአክብሮት አቀባበል ያደርግ ነበር። ጓዶቻቸው ብቻ ነው የተቀበሏቸው። ሆዴ እስኪረበሽ
ድረስ። ሌላው ግን መጠለፍም ከጥንቃቄ ጉደለት ስለመሆኑ ለፖለቲካ ክህሎቱ አቅም ተጠዬቅ ማለቱ አይቀርም። ትልቅ ጥቃት ነበር ለሁላችንም።
ሌላው ለቢቢሲ የትም ቦታ የትጥቅ ትግል አላደረኩም ብለህ ደግሞ የባለቤቱን መሳሪያ ገዝተህ ትጥቅ
አስፈታሁ? ለመሆኑ ብአዴን የት ነበር ይህ ክሽፈት ሲከወን? ውጥንቅጥ የሆነ ጉድ። ማለት ብአዴን ነፍስ አለኝ ካለ፤ ስንቀሳቀስ
ስመራ ነበር ካለ ክልሉን ይህን አመክንዮ አንድ ሊለው ይገባል።
የሆነ ሆኖ የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ጉዳይ ይፈለግ የነበረው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ እንጂ ከውስጥ የሆነ የህዝብ ሰላም፤ ሳቅ ፍለጋ አልነበረም
ማለት ይቻላል ጭብጡ ሲተረጎም።
በአብይ ሌጋሲ ግን ሲጀመርም በቅንነት ነው። አካሄዱም ቅንነት ነው፤ ውጤቱም ቅንነት ነው። እዛ
መሬት ላይ የሚኖረው ህዝብ አዬነው የራማ ህዝብ ካለምንም ቅደመ ሁኔታ፤ ካለምንም አዛዥ ራሱ በእግሩ ሄዶ ወገኑን አገኝቶ ተቃቅፎ
ተሳስሞ ተምለሷል። እኔም „ትግራይ ካለገመ“ ብዬ ጹሁፍ ጽፌያለሁኝ።
መጀመሪያ በፓርላማ የወሰኑትን ውሳኔ እንደ አዲስ ወደ ተግባር ከተገባ በኋዋላ ጥያቄ ሲቀርብ ጉዳዩ ልጅ ስለሆነ ይባል፤ አሁን ትርፉ
እዬታዬ ነው። ምን ይቀርብናል ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ ሆነው አብረው ቢሠሩ። ቢረዳዱ። ቢተባባሩ። ፍቅር ምኑ ይሆን የሚጠላው?ከፍቅር በላይ አትራፊ የለም። ከፍቅር በላይ ትውልድ አሻጋሪ ክስተት የለም። ፖለቲካዊ ተጫኝ ካልሆነ ግንኙነቱ ማለቴ ነው።
እኔ ስሞግተው የነበረው የ ኤርትራን መንግሥት የፖለቲካ የበላይነቱን
ነበር። ድሮ እኔ በደርግ ጊዜ ኤርትራውያን ነበሩ በመንግሥት፤ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ዘርፍ ወሳኝ እና የበላይ አሁን
ያን የሚፈቅድ ኢትዮጵያዊ አይኖርም። ዳይናሚክ የሆነ ትውልድ ተፈጥሯል እና።
ነገር ግን ዓለም አንድ በሆነችበት ዘመን ኤርትራ እና ኢትዮጵያ አንድ መሆናቸው ቢጠቅም እንጂ
የሚጎዳው አንዳችም ጉዳይ የለም። ለዛውም ምናችን ይሆን ልዩነታችን? ለሰሚው ግራ እኮ ነው።
ለማህበራዊ ኑሮ ደግሞ እኔ ጎንደር ያደግኩት እመሰከራለሁኝ አብነት ናቸው ኤርትራውያን። ተግባቢ
ናቸው። ሥልጡን ናቸው። ጽዑዱም ናቸው። እንዲያውም ቤተሰቦቼ ክፍሎቻችን ናቸው ይላሉ። ይህንንም ስሞግት በመነበረበት ጊዜም ጽፌዋለሁኝ።
ሌላው ለውጡ እንዳይቀለበስ ለተፈለገው ግብ እንዲደርስ የሚፈለግ ከሆነ፤ የኤርትራ መንግስት አዎንታዊ አቋም በእጅጉ ለአብይ ሌጋሲ ያስፈልገናል። ረቂቁ ሚስጢር ይህ ነው።
ደግሞ ሁልጊዜ እንደምናገረው የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ቀላል ሰው አይደሉም። የሠራ አካለታቸው ዓይን ነው። የሠራ አካላታቸው የደህንነት
ሠራተኛ ነው። እና የአሁኑ ቅናዊ - ንጹሃዊ - ልባዊ ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ ጠቃሚ ኦክስጅን ነው።
በሌላ በኩል ደንበራችን ቀይ ባህር ነው እንላለን፤ ደግሞ ኤርትራውያን ለምን ይመጣሉ፤ ስለምን እነገናኛለን እንላለን።
ይህ የማይገጥም ነገር ነው። የቸርነት አንበሉ አቶ ዮሴፍ ገብሬ አንድ የቤተሰብ አፈላላጊ ፕሮግራም ጀምሯል፤ መቼም የተባረከ ልጅ
ነው። ከመንግሥት ያላነሰ ዕውቅና ሰጥቶ መሬት ላይ ሥራ እዬሠራ ነው።
ሁላችንም ወንድሞቻችን የወለዱት / የወለዷት ልጆች ይኖራሉ ብለን ፕሮግራሙን በተስፋ እዬተከታተልን
ነው። እህቴ እዚህ ነይ ስላት ሥራዬን መልቀቅ አልፈልግም ትላለች፤ የሃይልዬ የወንድማችን ልጅ ቢኖረው እና እኛን ቢፈልግ ምን ታስቢያለሽ
ስላት ፕሮግራሙ ሳያልቅ ትኬት ቆርጭ ከአሜሪካ ኤርትራ እገባለሁ ነበር ያለችኝ።
ይህ የመንፈስ ስኬት - ናፍቆት ዋጋ የለውም በፖለቲከኞቻችን፤ በጸሐፊዎቻችን፤ በተንታኞቻችን፤
በሊሂቃኖቻችን፤ በጋዜጠኞቻችን፤ በፓርላማ ተመራጮቾች። ቀድሞ ነገረ የፓርላማ አባልነት ማን መረጣችሁ ቢባሉ ማን ሊሉ ይሆን? የባድመ
ውሳኔ ለህዝብ ይቅረብ የሚሉት ለህዝብ እነሱ ቢቀርቡ እኮ አሁን ባለው የነፃነት ሞገድ አንድ ሰው አይመርጣቸውም። በላተመረጡበት
ወንበር ላይ ተቀምጠው እዬወሰኑ፤ እዬፈረዱ መኖራቸው ላይበቃ፤ አሁን ደግሞ ዘፍዝፈውት የኖሩት የመከራ ተራራ መፍትሄ አገኜ ብለው
ፍዳ ያያሉ። ጦርነትን ይናፍቃሉ … ድንቄም ለአገር ተቆርቋሪነት። ዕድሜ ለአብይ ይበሉ ...ያ በታጣፊ አልጋ ሲያንጎላች የነበረ ፓርላማ ይኸው ለመደመጥ በቃ።
ቀድሞ ነገር በድፈረት እምናገረው እኮ በዓለም የእርቅ ታሪክ አፈፃፀም ውስጥ ይህን በመሰለ መልኩ
በጥበብ ተፈጽሞ አያውቅም። ውስጥህ ተቀምጦ ሪፈር እያደረክ ደስታህን የምታጣጥመበት እፁብ ድንቅ ብልህነት ከማስተዋል ጋር በፍጹም
ቅንነት የተፈጸመ ነው። ብዙ አልጻፍኩበትም እንጂ ድፈረቱ፤ ሂደቱ፤ ቅደምተከተሉ፤ አክብሮቱ፤ ይሁናታው፤ ትስስቡ፤ ፍሬማ ጅምሩ፤ የመንፈስ አቀባበሉ፤ አፍረካዊነቱ የሊቀ
ጳጳስ ወይንም የሐጂ ያህል ነው።
አንድ ሰው ስቆ ሲያድር ስለምን ይከፋናል? አንድ ሰው ፍሰሃን ተስፋ ሲያደርግ ስለምን ይጨንቀናል?
ያ እኛ ስናምሰው በኖርነው ሴራ ተከዝኖ ህዝብ በማቅ ይኑር ብሎ መፍረድ አውሬነት ነው።
እንዴት ተብሎ ጦርነት ይናፈቃል? ከጦርነት እኮ አመድ ብቻ ነው ትርፉ። ከስጋትም ስነ - ልቦናው
የተሰለበ ትውልድ ነው የሚፈጠረው። ሥነ ልቦናው የተሰለበ ትውልድ ደግሞ ራሱን መሸከም አይችልም። የዛለ ነው የሚሆነው።
ጦርነት
የተፈጥሮ ጸር ነው። በዬትኛውም የጦርነት ሂሳብ አትራፊ የለውም። አትራፊው ቂም ብቻ ነው። አሁን የኢትዮጵያ የፓርላማ አባል የሚሉን
ቂም እንቆፍር ነው። ቂምን እንደ ገና እንውለደው ነው። አለመታደል። እርግማንም።
ቂምን የሚያስተናግድ ህሊና የለንም። እኔ ጦርነትን እዬተካሄደ አይቻለሁኝ። የሰው ልጅን ጭንቅላት ውሻ ይዞ ሲመጣ በዓይኔ በብሌኑ አይቻለሁኝ። ተገደው ምርጫቸው ላደረጉት ምንም አልልም። እግዚአብሄር በቃችሁ ሲለን
ግን ሊናፈቅ የሚገባው አይደለም አውዳሚው ጦርነት።
አብዝቼ እኔ እምጸልዬው ለትግራይ ገና ላልተፈጠሩት፤ በሃሳብ ላልታሰቡት ህፃናትም ጭምር ነው።
ወልጋዳው የትግራይ የፖለቲካ ሊሂቃን አስተሳሰብ ከመፈጠራቸው በፊት ዕጣቸውን እንኩት አድርጎ እዬሰበረው ስለሆነ።
ጦርነት ለኢትዮጵያ መመኘት በውነቱ ዲያቢሎስነት ነው። ህዝብ ሲስቅ የሚያመው ፍጡር ፓርላማ ላይ ተቀምጦ ድምጽ ሰጪ ሆኗል።
ይከረፋል። ዴሞክራሲ ይህንም መፍቅድ ቢሆንም ሁልጊዜ እዛው ላይ እንደ ኩሬ ውሃ መቆም ግን ትውልድንም ሥልጣኔን ወደኋዋላ ይጎትታል።
ሌላው ይቅር እንዴት ህፃናት ይረሳሉ። ህፃናት ስለነገ ሞት አጀንዳቸው ሆኖ እንዲያድግ ስለምን
ይፈለጋል?ስለምን ጦርነት ይውረሱ ይባላል? ህፃናት ስለነገ ሰግተው እንዲያድጉ ለምን ይፈለጋል? ስጋት እና ፍርሃት እንቀድ ይባላልን። ደመነፍሰነት።
ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ህዝብ
ትክክል አይደለም ካለ በነበረው እንቀጥላለን ብለዋል። ህዝብ ሞትን ቢፈቅድ ኖሮ ከኤርትራ ይሁንታ ማግስት አሳቸውን ደግፎ ሞቱን
ይቀበል ነበርን? ሚሊዮኖች እኮ ፕሮፓጋንዲስት ሳያስፍለጋቸው ነበር የተመሙት፤ የልብ ነፍስ አብይን አድርገው። የአላዛሯ የንስሃ
አባት ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አብዩ ነው ዛሬ።
እሳቸውን የደገፈው እኮ በዬትኛውም ጊዜ እንዲህ ሆኖ በፈቃድ የተወደደ መሪ በዘመናችን አላዬነም።
የሚገርመው የሲዊዝ ራዲዮ የዘገበውን ማድመጥ ነው። ለዛውም ገለልተኛዋ ሲዊዝ።
የሆነ ሆኖ እኔ እንደ ሥርጉተ ኢትዮጵያ አይደለም ጦርነት ስለጦርነት ፊልም ሊታይባት የሚገባ አገር መሆን እንደሌለባት ነው የምፈልገው። ጦርነት ብቻ አይደለም የወንጀልም፤ የስርቆትም፤
የሴራም ፊልሞች መታገድ አለባቸው ባይ ነኝ።
ክፉ ነገርን ስለሚያበረታቱ፤ መልካምነትን ስለሚዋጉ። መቀራረብን ስለሚፈታተኑ። ጀርመን እኮ ማህበራዊ
ሚዲያን የሚመራ ህግ የደነገገችው ናዚዝም ከፍ ባለ ሁኔታ እንደ ገና ተወልዶ መንፈስ የመምራት፤ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም እያገኜ
በመሄዱ ነው፤
ጦርነት
ኢትዮጵያን በልቷት ኖሯል። ከእንግዲህ አንፈልገውም። የምንፍለገው ፍቅርን እና ሰላምን ብቻ ነው። የፈለጉ
ኤርትራዊ ይሁኑ ደንበር አካባቢ ያሉት፤ የፈለጉት ደግሙ ኢትዮጵያዊ ይሁኑ። ኤርትራም ቢቀመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚወስድባቸው
ሊኖር አይገባም፤ ኢትዮጵያም ቢቀመጡ ኤርትራውያዊነታቸውን አይወሰድባቸውም።
አሁን እኔ ሲዊዝ እኖራለሁ፤ ለሰከንድ ከኢትዮጵያ መንፈሴ ወጥቶ አያውቅም። እኔ ብቻ እንዳይመስላችሁ
ሃኪሞቼ፤ አማካሪዎቼ ሁሉ ሳይቀሩ እኔን ካገኙ የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ኢትዮጵያ
እንዴት ናት ነው። ህመሜን ትቼ ስለዛ ዜና ነግሬ ነው ወደ ሄድኩበት አጀንዳ የምገባው።
ሌላው አሁን እዚህ ሲዊዘርላንድ
እኮ በኤርትራ ሥም መኖሪያ ፈቃድ ያገኙት እነ ተጋሩ ኤርትራዊ ተብለው ነው የሚኖሩት። ልጆቻውም
ሲፈጠሩ ኤርትራዊ እዬተባሉ ነው የሚያድጉት። ይህ ከሆነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለስለላ ተግባር የሚያሰማራቸው ሺ ተጋሩ ስለምን የኤርትራን
ዜግነት ይዘው ወረቀት ይጠይቃሉ? ይህን ጥያቄ እስኪ ፍቱት የፓርላማ አባል ተብዬው?
- · የዱባ ጎረዳ።
ሌላው የማይገባኝ ግን የኢትዮ ኤርትራ ዜና ሲመጣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚያስተዳደረው ሚዲያ
ካርታቸው ተከትፎ ነው የሚቀመጠው። ጸሐፍትም እንደዛ አድርገው ይጽፋሉ። ብቻ ልክ እንደ ምን ልበለው እንደ አቦካዶ እና እንደ ብረቱካን። ወይንም እንደ
ዱባ። ዩክሬን እና የራሺያ ዜና ቢኖር የቀደመው ካርታ ነው ዜና ላይ
የሚመጣው።
ሌሎችም የይጉዝላቢያ ነባር አገሮች የተከፋፈሉት ዜና ሲመጣ የኮራዚ እና የአዘርበጃን ሊሆን ይችላል
ሉላዊ ካርታው ነው የሚመጣው። የኢትዮ ኤርትራም ሲመጣ በውጭ አገር ዜና እንዲሁ አትላስ ነው የሚታዬው። ኢትዮጵያ ላይ ሲመጣ ግን
ባልሰለጠነ ሁኔታ ነው፤ ከሉላዊ ዓለም የተለዩ ሁለት ደሴት የማይቀራረቡ አገሮች ተደርገው ነው።
ሊሆን የሚገባው ግን እንዲህ ነው።
ማን አሁን ወደዛ ወደ አለፈ ነገር
ሄዶ ይደክማል። አይተውታል መነጠል ማለትን? ስላዩትም ነው አሁን ቅን መንፈስ ሲያገኙ ካለሸፍጥ ፖለቲካ ልባቸውን ቧ አድርገው ፏ ብለው ሰናያቸውን እያጣጣሙ ያሉት።
ቅዱስ ዮሖንስ በጋራ ማክበር
እኮ የቀን አቆጣጠሯን ለቀዬረች ለኤርትራ ትርጉም እሰቡት። በመንፈስ ወደ ጸጋዋ እዬተመለሰች ነው እትጌ ኤርትራ። ተመስገን!
„Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!“
ይህ ፈቃድ ይህ ምኞት አሸነፊ ሆኗል። ኤርትራ ከራሷ ከውስጧ የወጣችበት የቀን
አቆጣጠር ከዘመኑ የዲጅታል ስልጣኔ በላይ ስለመሆነ የገለጹበት ዕድምታ ነው ዶር አብይ አህመድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ። አብዩ ማለት እንዲህ ነው። የእኔ በመሆኑ ራሱ ፈጣሪዬን
ሙሉ ቀን ሳመሰግነው ውዬ አድራለሁኝ። የእኔ አብይ ስላት እህቴ የእኛም ነው ትለኛለች። /ይህ ማለት በሃሳብ አልሞግተውም ማለት
ግን አይደለም/
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ማንም እኮ ያውቃል ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ሁለት ሉዕላዊ አገሮች መሆናቸው።
ወይ ሉላዊን ካርታ ማምጣት፤ ወይ አህጉራዊ ካርታውን ማምጣት ወይ ደግሞ የቀደመውን የኢትዮጵያ ካርታ ማምጣት የደንበር ክልሉን ግን
ጎላ ባለ ቀለም መለዬት እንጂ ሁለት ጉልቻ አድርጎ ማምጣት የኤዲቲንግ ችግር ይመስለኛል።
ይህን እነ ዶር መራራ ጉዲና አባል የሆኑበት የብሮድካስት ኮሜቴ ማስተካከል አለበት። በሌላ በኩል
የድህረ ገጽ አዘጋጆችም እንዲሁ ቢያሰተካክሉት ፍላጎቴ ነው። ሳናውቀው በመንፈስ እዬከፈል ነው ሚዲያው ራሱ። በዚህ ይገነባል በዚህ
ይፈርሳል መንፈሱ።
ይህ በራሱ አሁን ያለውን የሰላም፤ የፍቅር፤ የመታሳሰብ አቅም ይተረትራል። ይፍልጣል። ይሰነጥቃል።
አመጣጡ ስሜቱ የማይገናኙ ከመቃብርህ ከመቃብሬ የተባባሉ አዬነት ነው።
ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮችን ሁሉ ኤዲት ማድረግ ያስፈልጋል።
መሬት ላይ ሥራ ጀመረ ብዬ የመናገርለት ሚዲያ ጄቲቪ ብቻ ነው።
ወደ ቀደመው ስመለስ የሰለችኝ፤ ምንም መስማት የማልፈገው ነገር የጦርነት ነጋሪት ነው። ያስደሰተኛ ነገር
ደግሞ እኔ እንዳለብኝ ስጋት ሳይሆን እናቴ ከምትለው አታውለኝ፤ ሚስቴ ከምትለኝ ዓይነት ሆኖ የፈለገ ድርጅት ሊሂቅ ይሆን ኢትዮጵያዊ
ሊሂቅ አንድ ነገር እንዲሆንብኝ አልሻም።
ብቻ ይህ ነው ያለተመቻቸው ህዝብ ሳይመርጣቸው ባለወንበር የሆኑት የፓርላማ አባል ስለምን ጦርነት
አይቀጥልም ብለው እዬሞገቱ ያሉት። ድሮሞ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሞክሩኝ ፈትኑኝ አሉ፤ እሺ ብለው ሲወጥኑት ደግሞ አሸባሪ ብለው እስከ
ሞት የሚያደርስ ፍርድ ፈረዱ። መከረኛ አማራም ታጨደበት በማያገባው አጀንዳ። አሁን ይህን የሰላማዊ ጥረት አልተመቸነም እያሉ ነው
የፓርላማው አባል።
ይልቅ አካሎቻቸውን ስለምን ዘረፊዎች የወሰዱትን ገንዘብ ይመልሱ፤ ያሸሹትን ያምጡ፤ ከህግ በላይ
የተሆነበት አሰቃዮችም ፍርድ ይሰጣቸው ስለምን አይሉም? ጥያቄው ራሱ ትውልድን የሚጠፋ ሃሳብ ነው። አውሪነትም ነው። ለአፍሪካዊነትም
ጠንቅ ነው።
አሁን ህዝብ ጦርነት - ስጋት - ፍርሃት ሲቀር፤ ጦርነት ይታወጅልን ስጋት ይናጠን ብሎ ጥያቄ
አለን? ለነገሩ ኢትዮ ሱማሌ ላይ ያደረጉትን አስደርገው አሁን እሱም እፁብ ድንቅ በሆነ ብቃት መፍትሄ ሲያገኝ ማጣፊያው
አጠረ እና መታመስ ሆነ። ብቻ
እንዲህ መሰል ዲያቢሎሳዊ አውሪያዊ ህሊና እያነሰ፤ እዬከሰመም የሚመጠበት ዘመን ፈጣሪ ይስጠን“ አሜን!
ሰላማችን እንዲቀጥል በአጽህኖት እንፈልጋለን፤ እንጸልያለንም!
ሰላማችን ሩሃችንም ሃይማኖታችንም ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ