ልጥፎች

"በሽምግልና ስም የፖለቲካ ተልዕኮ ነው" - አርቲስት መላኩ ቢረዳ በጉራጌ ዞን ተቋቋመ ስለተባለው የገዳ ስርዓት

ምስል

"ትናንት የበደሉንን ሕሊናችን መርሳት ባይችልም መጭው ትውልድ ግን የተሻለ ያስፈልገዋል" - አርቲስት መላኩ ቢረዳ

ምስል

የጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ አባት አቶ አህመድ አሊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተደመጠ።

ምስል
„መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ“ የጠቅላይ ሚ / ር አብይ አህመድ አባት የ ዕድሜ ባለጸጋው አቶ አህመድ አሊ በ 105 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ አሁን ዜና ዘሃበሻ አዳምጥኩኝ። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር። አሜን! ወቅትን መሻማት ከጸጸት ይታደጋል። ሁላችንም እንማርበት ዘንድ ፈጣሪ ይህን የትምህርት ተቋም በብሄራዊ ደረጃ ከፍቶልናል። መቅደም ያለበትን እናስቀድም ዘንድ። ጠ / ሚር አብይ አህመድን ጨምሮ ለልጆቻቸው፤ ለቤተዘመዶቻቸው፤ ለመላ ቤተሰባቸው ሁሉ መጽናናቱን ፈጣሪ ይስጥ። አሜን ! አቶ አህመድ አሊ ቀደም ባለው ጊዜ እንደተረዳሁት ለህዝባዊ አገልግሎት መሬታቸውን በፈቃዳቸው የሚሰጡ ለአገር እና ለህዝብ አሳቢ እና ተቆርቋሪ እንደሆኑ አንድ ቃለ ምልልስ ላይ አዳምጫለሁኝ። ስለሆነም በዕድሜያቸው ለአገራቸው የሚገባውን በማድረጋቸው በሥጋ ቢለዩም በነፍስ ግን ዘላለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። እጓጓ የነበረው አንድ ቀን በቤተ መንግሥት ደስ ብሏቸው ለማዬት እፈቅድ ነበር። ብቻ ሰው ካሰበው እግዚአብሄር ያሰብው ሆነና የተመኘሁትን አላገኘሁም። እኔ እንዲህ በዕድሜያቸው የገፉ ሰዎችን ሐሤት፤ ተስፋ፤ ሰናይ ማዬት በእጅጉ የሚናፍቀኝ ነገር ነበር። * ፎቶ ከቢቢሲ አማርኛው ዝግጅት የተወሰደ። ፈጣሪ በምንማርበት መስክ ሁሉ ጠቃሚ ትምህርትን ህሊናችን ይፈቅድ ዘንድ ይርዳን። አሜን ሥርጉተ ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

የአሉታዊው የዴሞግራፊ ዕሳቤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዎሎጂ ነው። {የወግ ገበታ 17.06.2019}

ምስል

አቶ ያሬድ ኃይለማርያምን እና መሰሎቻቸውን የሚሰማ መንግሥት ከወዴት አለ?! MP3 {በጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ...

ምስል

የጢስ ፖለቲካ ጦሱ ... የአሉታዊ ዴሞግራፊ ቤተኝነት ነው።

ምስል
ተስፋ ዝልቅ ተስፋ ልቅ ተስፋ ፍልቅ ነው።  እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   የአሉታዊ ዴሞግራፊ ዕሳቤ   ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዲዎሎጂ ነው። „የሰዎች መፈጠር በበጎም ብክፉም ነውና።“ መጸሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 15.06.2019 ከእመ   ዝምታ   ሲዊዘርላንድ። ·        መቅድም። የኢትዮጵያ ጌጦች እንዴት ናችሁ። ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ የጢስ ፖለቲካን እናያለን። ·        መነሻ።   „ መረጃ   ሳይኖረን   የማንንም   ስም   አላጠፋንም፦   ትርጉም   በአብርሃም   ዓለሙ  ( ዶ / ር )“ April 1, 2019 | Filed under:  ነፃ   አስተያየቶች  | Posted by:  ዘ - ሐበሻ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94532#respond https://www.satenaw.com/amharic/archives/65399 „ ነጋዴ   በኦሮምኛ   ካልሸጠ   አትግዙ  –  አቶ   በቀለ   ገርባ “ March 23, 2019 ·        እፍታ እንዴት ናችሁ የአገሬ ፈርጦች ? ደህና ናችሁ ወይ ? ጢስ የዕለቱ ዕርዕሰ ጉዳዬ ነው። የአሉታዊ ዴሞግራፊ ዕሳቤ በብሄራዊ ደረጃ ሲታሰብ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የጨፈገገው  ጢ ስ እንደታዘዘባት ነው እኔ አማስበው። ስለሆነም የጢስ ፖለቲካ ዛሬ  በመጠኑ  ይፈታተሻል።   የአብይወለማ ድፍን አይዲወሎጂ እያራመደ የሚገኘው ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ቀለሙ የጢስ ፖለቲካ ነው። ጢሱ ሲበረታብህ ዓይንህ እንኳን የሚሆነውን ነገር