አቅም።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

 

ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 

"ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ።"

(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ቁጥር ፲፯)

 

 


ቅም።

አቅም በግል ህይወት፣ በማህበራዊ ህይወት፣ በፖለቲካ ህይወት፣ በቤተሰባዊ ህይወት፣ በኃይማኖታዊ ህይወት ደሙ ነው።

አቅም አልባ መኖርም፣ ህይወትም፣ ዓላማም ግብም ፍቅርም የለም። አቅም በተለያዬ እርከን፣ በተለያዬ ሁነት ሊሰጥ፣ ሊከፋፈል ይችላል። አቅም ነው ማሸነፍ። አቅም ነው ድልአድራጊነትም።

አቅም በሁለት ልንከፍለው ብንችልም እንደ ፈንጋጣው ሥርጉትሻ ዕሳቤ ሦስተኛም አቅም አለ ብላ ታስባለች። 

1) የሰለጠነ።

2) ያልሰለጠነ።

3) ቅብዓ።

የሰለጠነው ክህሎት የምንለው፣ ክህሎት ግን ምንድን ነው? ጭብጡን ላዘግይ እና ለወል ውል የሚሆኑ ሃሳቦችን ላንሳ።

ራስን መግዛት፣ አዙሮ የማዬት ብቃትንና ጠንካራ ህሊናን ይጠይቃል። አንድ ኃይማኖተኛ ውጪያዊ ረቂቅ ኃይልን እንደሚፈራ ሁሉ፣ የህሊና ጥንካሬ ያለው ሰውም ደግሞ ህሊናው የሚያወግዘውን ተግባር #በመፆም ከራሱ ጋር #መጣላትን በህሊና ቁስል ማሰቃዬት አይፈልግም።

1) ሰለጠነ አቅም።

ፕሮፌሽናሊዝም እንደ ማለት ነው። ከዲስፕሊን፣ ከትምህርት፣ ከተወሰኑ ዓመታቶች ጋር በረጅም ጊዜ ሰልጥኖ ሥራ ላይ ሲውል አቅሙ ሥልጡን አቅም ልንለው እንችላለን።

2) ልሰለጠነ። አማተሪዝም ማለት ነው። ከመኖር፣ ከተመክሮ፣ ከልምድ፣ የሚገኝ እንደማለት።

3) ብዕ፣

በቀጥታ ከፈጣሪ፣ ከአላህ ከተፈጥሮ ፀጋ፣ ከራሱ ተስጥዖ የሚገኝ ሆኖ፣ ከመስማት ወይንም ከበዛ ማንበብ፣ ከብቁ የማድመጥ አቅም የሚመነጭ የፈጣሪ ቅብዓ የሚያመነጨው ልዩ የአቅም ዓይነት ነው እንደ ሥርጉትሻ ዕይታ።

#ማያያዣ

እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ይወለዳል የሚል የግል ዕይታ አለኝ። ይህ ማለት ምን ማለት ነው?

በሰለጠነውም ባልሰለጠነውም አቅም ውስጥ እያንዳንዱ ልጅ ይዞት ሲወለድ የተወለደው መክሊት አብሮት አለ ማለት ነው ብዬ አስባለሁ አነሰም በዛም።

አብዛኛው ወላጅ በጥዋቱ የልጁን መክሊት ከብክቦ በማውጣት እረገድ በሠለጠነውም ባልሰለጠነውም ዓለም እኔ በግል ባደረግኩት ጥናት እጅግ ደካማ ነው።

ዕፁብ ድንቅ መክሊት ያላቸው ልጆች መክሊታቸውን ሳያውቁት አድገው፣ ጎልምሰው፣ አርጅተው ሊያልፋ ይችላሉ። ለዚህ ነው እኔ የወላጆችን ድርሻ ለማሳወቅ ግንቦት 7 ግዞት ቢበይንበትም "ርግብ በር" መፅሐፍን ለወላጆች የፃፍኩት።

በዚህ ዘርፍ የሲዊዝ ሪቷል እጅግ ደካማ ነው ለተፈጥሯዊ ፀጋ አትኩሮቱ ያን ያህልም ነው። ሲዊዞች የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሠጡት ለቀለም ትምህርት ነው። መክሊት፣ ተሰጥዖ ትርፍ ነገር ነው። ልጆችም እጅግ ቁጥብ እና የበዛ ዲስፕሊን ያላቸው ናቸው። በቀለም ትምህርታቸው የበረቱ የሰከኑም ናቸው። ሲዊዝ መኖርን በማኖር ጥበቡ ቁጥብነት ነው።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ማናቸውም ሥጦታ ያላቸው ወጣቶች ሄደው የሚወዳደሩት እና ዕድላዊ በር የሚያገኙት ጀርመን ውስጥ። ሲዊዝ ውስጥ ማንኛውም ልጅ በቀለም ዕውቀት ፕሮፊ መሆን አለበት በሙያ ይህ ግዴታ ነው። ሲዊዞች ሲበዛ በጣም ሲበዛ ዓይን አፋሮችም ናቸው።

ህሎት (skill)

ክህሎት የሚገኜው ተሰጥዖን በማዳበርና ስሜትንና ህሊናን በማሰልጠን ነው። ከአለው የዓለም ዝብርቅርቅ ውስጥ አንዷን ዘለላ እውነት ስሜት የሚሰጠንን አውጥተን መግለፅ ስንችል። ማዳበር፣ ማፋፋት፣ ማለምለም ሲቻል።

ያቺ ዘለላ ለህይወት ትርጉም የሚሆን ብልጭታ ተግ ብሎ የማይጠፋ መሆን አለበት። ይህን አነጣጥሮ ነጥሎ ማዬት ሲቻል፣ የዐዕምሮ ስልጠና ይሆናል። ከዚህ በኋላ ነው ቴክኒካል Skill የሚተባው።

ቅም አስተዳደራዊ አቅምን ይጠይቃል።

 

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚፎርሸው ከዚህ ነው። አቅም በግልም፣ በግብርም፣ በወልም በውልም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ህይወት ባለቤት የሌለው፣ አጀንዳም ያልሆነ ጉዳይ ነው።

አቅም ሲዋጣ ለዛውም በነፃ ከጉዳይ ጥፎ ዕውቅና መስጠት ዳፍንት ነው። ለተሰጠው የአቅም መዋጮ ዲስፕሊን መገዛት አይቼ አላውቅም ድንብልብል ነው። 

ከዜሮ ለመነሳት እንኳን የፈቀደ ቀንጣ ነፍስ ገጥሞኝ አያውቅም። ወደፊት አገኝ ከሆነ እፀልያለሁ። ነገ አዲስ ቀለማም ቀን ነውና።

በእኔ የግል ህይወት የደረሰውን ከፍ ባለ ደረጃ ብሄራዊ አድርጌ ሳዬው ከውስጤ ነው የማዝነው። የውድቀቶቹ ሁሉ አናት የአቅምን ስጦታ ዕውቅና ከመስጠት፣ በቅጡ ከማስተዳደር፣ ዲስፕሊኑን ከመሸከም ግድፈት ጋር የሚመነጭ ነውና።

አንድ ፀሐፊ፣ አንድ ጋዜጠኛ፣ አንድ የህግ ባለሙያ፣ አንድ ባለተስጥዖ፣ አንድ ኢኮኖሚስት፣ አንድ ገር ደጋፊ ወዘተ ማለት ያለውን ፀጋ አከለልህ፣ ጨመረልህ ማለት ነበር ለልባም ባለህሊና ሰብዕና።

እማዬው አራባ እና ቆቦ ነው። መውደቅ ለእኛ ሲያንስ ነው። መድፋት ስለሆነ ሱሳችንም፣ አዳራችንም። አፍሶ መልቀም፣ ለቅሞ ማፍሰስ።

ገናናት ያስገኜው አቅም ጥለህ ስትወጣ ስንት ነገር በአፍ ጢሙ እንደሚደፋ፣ ስንት የአቅም ክምችት እንደ ሹግ እንደሚነድ አታውቀውም። ዕውቀቱም ልምዱም የዝና አርኬቡ ነውና።

ይብቃኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

 

ቅኖቼ ሆይ!

ኑሩልን ለእኔም ለአላዛሯም ኢትዮጵያም።

መሸቢያ ጊዜ።

ቸር ወሬ ያሰማን።

አሜን።

ለሁላችንም የመፅናናቱን አቅም ፈጣሪ ይላክልን።

አሜን።

በጣም ተሰቃይተናልና።

 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

23/03/2021

ክትረ ቢስ ዕውነት የሆነ የዕውነት አርበኛ ይናፍቀኛል።

ዕብለት ስንቃቸው የሆኑ መሪ ገለሙኝ! ጎፈነኑኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።