#ውሃዬ………

 

#ውሃዬ………
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
ኢትዮጵያ ~አገሬ
ስስቴ ~~ናፍቆቴ
የእኔ ~~~መጠሬዬ
ክብሬ እና ~~~~ኩራቴ
ንባቤ ~~~~~ትርጉሜ
መንፈሴ ~~~~~~ሚስጥሬ
ቀደምቷ ~~~~~ግርማዬ
ጠይሟ ~~~~ዕንቁዬ
ቡኔዋ ~~~~ቡናዬ
እናት ~~~ሃይማኖቴ
#ዓናቷ ~~ሐሤቴ
ውድዬ ~ህብረቴ
ቅኔዬ ~~ድጓዬ
ኢትዮጵያ ~~~አገሬ
የአፍሪካ ~~~~ፊደሌ
መዝሙሬ ~~~~ሃናዬ
ኃይሌና ~~~~መክሊቴ
የእኔ ~~~~~ስጦታዬ
ንባቤ ~~~ማዕረጌ
ማርዳዬ ~ውበቴ
ናርዶሴ ~~ሳባዬ
መንዙማ ~~~ህብስቴ
ሁሉዬ ~~~~~ዕውቀቴ
አንች ነሽ ~~~~መንገዴ
ፍልስፍና ~~~~ማዴ
ሉሲዬ ~~~ዝናዬ
ውዳሴ ~~ድርሳኔ
ቅንዬ~ ´መቤቴ
የተስፋ ~~መርከቤ
የህቅታ ~~~ምግቤ
የመኖር ~~~ቋንቋዬ
ስዋሰው ~~~ውሃዬ
ጠሐዬ ~~~~ብዙዬ
ዘውዴ ~~~~~ጉልላቴ
እቴጌ ~~~~ልዕልቴ
ህብስቷ ~~~~ሥህኔ
የእኔ ~~~የእኔ!
የዕውነትም ~~ገዴ
ለመርህም ~ቅርቤ
የዕድምታ ~~ክቤ
የአቋም ~~~ተቋሜ
የሞራል ~~~~ዘቢቤ
የጽናት ~~~~ግማዴ።
 
ፈጣሪዬ ሆይ! የማንነት ቀውስ ድርሽ እንዳይልብኝ በሙሉ የራስ መተማመን ሰብዕናዬን ገንብታ ያሳደገችኝ ልዕልት ኢትዮጵያን ጠብቅልኝ። አሜን።
 
ተፃፈ ~ ዛሬ 06/04/026
ሰዓት ~~ 08.20
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
Selassie©Selassie.
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።