ከቆዩት የሥነ ቃል ውበቶች አንዱን ... ስለ ዱር አውሬ።
የዱር አውሬ።
„በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ።“
መዝሙር ፴፯ ቁጥር ፴፰
ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Selassie)
26.11.2016 (ሲዊዘርላንድ- ዙሪክ)
·
የኔዎቹ እስቲ ከተቀመጡ
ለህትምት ካልበቁት ውስጥ ትንሽ የፊደል ውበትን እናነጋግር።
አለቀ~~~~~~~~ቀ ~~~~~~ቀ ~~~~~~~ ቀ ~~~~~~ቀ ቀ ቀ።
ያ … መጋኛ፣ አላልቅ ብሎ
ተ------- ድብልብሎ
--------- ተቸንክሮ------ ተወሮ------- ተማሮ ----- በቀበሮ
----
እህህን ቀለበ ----- አሮ ----------------ተኮማትሮ
ተጨማትሮ
------ የሀገሬ ሰው
የዱር አውሬ
------- ተቀራምቶ አመሰው።
-------- በራህብ አረሰው።
ቆረሰው ----
አደራ በላው
------- በጥፋት ደረመሰው-------
ትናንትን ቀነሰው
አደራን ወቀሰው
--------- ማተበ --- ቢሱ፤ ባልወለደ አንጀቱ ደቆሰው------------
ነገን አስቀድሞ ---- አጠንዝሎ፣ አዝሎ ጠበሰው።
ተጻፈ፤ ጳጉሜ 5 ቀን 2005 ዓ.ም ቪንተርቱር ሲዊዘርላንድ
የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ