የፊደል ሰብል።
„ኃጢያተኞች ሲጠፋ ታያለህ።“
መዝሙር ፴፮ ቁጥር ፴፬
ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Selassie)
26.11.2016 (ሲዊዘርላንድ- ዙሪክ)
·
የኔዎቹ ከተቀመጡ
ለህትምት ካልበቁት ውስጥ ትንሽ የፊደል ውበትን እናነጋግር።
ዝም ብሎ
መሎ
በደበሎ ተመልምሎ።
አዎን ዝም ብሎ
ተዳብሎ።
ሊሉት
ይሆን መኖር?!
ከመከራ
ተድሮ
በፍዳ
ተውግሮ ከቶ አለ ይባልን በቀዬ መኖር?
በምንም
ተዋቅሮ
አለ
ልንል ይሆን ዘር?!
ፈልሶ
ፋድሶ
ተቦድሶ
በግለኝነት
ጢሶ
ቁም ስቅሉን
አይቶ
በበቀል ተቀንጥሶ
ነፃነቱን ተቀምቶ።
ተጣፈ … ጳጉሜ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ሲዊዘርላንድ-ቪንተርቱር
የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ