ሰው'
ሰው።
„አሁንስ ተስፋዬ ማነው?
እግዚአብሄር አይደለምን?
ትዕግሥቴም ካንተ ዘንድ ነው።
መዝሙር ፴፯ ቁጥር ፯“
ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute©Selassie)
26.11.2016 (ሲዊዘርላንድ- ዙሪክ)
·
የኔዎቹ እስቲ ከተቀመጡ
ለህትምት ካልበቁት ውስጥ ትንሽ የፊደል ውበትን እናነጋግር።
ሰው
ሰው
ሰው
በቃሉ የተፈጠረ
በቃሉ ዩነጠረ
በታዕምሩ የነጠረ
ለታምሩ ያደረ
በፍቅሩ የቀለመ
ለፍቅሩ የተተለመ
ነበር በደሙ የታተመ።
ሰው
ሰው
ሰው
በመቅደሱ የታጠነ
እሱን ያመነ፤
በአምሰሉ የተኳለ
ነበር ለመስቀሉ የተኮለመ።
ለምን ይሆን ለተንኮል ያደረ?
እኮ! --- ለጥላቻ አንደምን ቸኮለ?
በግለኝነት
የተማሰለ?!
እኮ!!! ሰው? ? ?
ሰውነቱን ለምን፤ ስለምን እንዴትስ ተወ?!
·
የተጣፈ …. ጳጉሜ 5 ቀን 2003 ዓ.ም ~~ ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር
የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ