#ነገረ #ራያ።

 

"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ ራያወች በህወሃት ምክንያት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው እዬተንገላቱ ስለመሆኑ ቢቢሲ የአማርኛው ዘገባ መረጃውን ሰጥቷል። ለእነኝህ ተፈናቃዮች ሁነኛ #ባለቤት የተገኜ አይመስልም። እርዳታ የሚያደርግላቸውም አላገኙም። በውነቱ #ባለቤትም ያገኙ አይመስልም። 
 
ሚኒስተር በለጠ ሞላ ምን ያስባሉ (ዶር)???? ሃይቅ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የሚኒስተሩን ሥም አጉልተው ሲያነሱ የሚያስደስት ከሆነ ኃላፊነትን በቀጥታ በሚመለከት ጉዳይ ፋይዳ ያለው ተግባር ተፈጽሞ ቢሆን መልካም ነው። መግለጫ ለ60ሺህ ግፋዓን አፍ ማርጠቢያ ስለማይሆን። ለነገሩ ማህበራዊ መሠረት አልቦሽ የመሆን ሁነት ነው ያለው። 
 
የአማራ ክልል በወዘተረፈ ችግር እየተጣደፈ ነው። የራሱን ችግር ማስተዳደር ያልቻለ ክልል፤ ተጨማሪ ብሄራዊ ግዴታ ሲታከልበት ለራሱ የውስጥ ችግር መብቃት ያቃተው ሌላ ሃላፊነት #የሚያስቃስት ነው የሚሆነው። 
 
በዚህ 8 ዓመት በዕድሉ ጨምቶ እየተጠቀመ ያለው #ሱማሌ ክልል ነው። የወደፊቱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሚዛንም ወደዚህ እንደሚያደላ አስባለሁኝ። ከታች ጀምሮ የአወቃቀሩ ስታይል ብቃት ባላቸው ወጣቶች የተገነባ ነው። ሰላምም ነው። በሲዳም የተበራከተ ስሞታ አልሰማም። ደቡብም እንዲሁ። የጠቅላይ ሚር #የአትኩሮት አቅጣጫም #ደቡብ - ገብ ነው። 
 
የሆነ ሆኖ ነገረ ራያ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን #ቢያቀኑለት ስል በትህትና አሳስባለሁኝ። ለነገሩ በደባርቅ #ከሱዳን የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳሉም ሪፖርተር ላይ በዚያ ሰሞን አንብቤያለሁኝ። ደብረብርሃን የገዘፈ #የተፈናቃይ ችግር ነው ያለው።
የኔወቹ እንዴት አደራችሁ፤ አረፈዳችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ
 
ኑሩልኝ። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።