የኦሮሞ የተዋህዶ ልጆች የፈተና መባቻ።

ልባዊነት።
„አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምህ?“
መዝሙር ፲ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
09.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



ቋንቋ ጥበብ ነው። ቋንቋ እውቀት ነው። ቋንቋ ስልጣኔ ነው። ቋንቋ እድገት ነው። ቋንቋ ልሳን ነው። ቋንቋ ሙያ ነው። ቋንቋ ፍልስፍና ነው። ቋንቋን በሚመለከት ያለኝን እይታ በዚህ ፁሑፌ ማገናዘብ ይቻላል።

ቋንቋ ሊቀ ሊቃውንትነት እንጂ መወቀሻ ሊሆን አይገባም።

ከአምስቱ የኦሮሞ ድርጅቶ የመብረቅ ወሳኔያዊ መግለጫ ማንፌሰቶ ወዲህ አማራ ግዕዝን በሁተኛ ቋንቋነት እንዲያጠና ዘመቻ መጀመሬ ይታወሳል። አሁን ዛሬ ከትኩስ መረጃ ዩቱብ አንድ መረጃ አገኘሁኝ። እኔ ግዕዝን የአማራ ህዝብ ማጥናት አለበት ያልኩት ለእኔ ለራሴ የትንቢት ያህል ነው የዛሬን መረጃ ሳገኝ የተሰማኝ።

በወለጋ ብጹዕና አባቶቻችን መሰደዳቸው ብቻ ሳይሆን በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የያሬድ ዜማዊ ቅኝትም፤ በግዕዝ ቅዳሴም እንዲቆም መደረጉን አዳመጥኩኝ። ዝርዝርዝሩን እናንተው ሂዱበት ከሥር ሊንኩን እለጥፋለሁኝ።

ዋና ቁም ነገር ግን ዛሬ የተፈቀደው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግዕዝ እግዳ ነገ ሃይማኖቱም እንዳይቀጥል የመጀመሪያው የክፉ ቀን ደወል ነው። የግራኝ ዋዜማ። የዳውዳውያን እና የጃውርውያን ፍልስፍና ይሄው ነው። „ቀስ እያለ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል“ የሚበለውን ልብ ትሉ ዘንድ በአክብሮት እግልጻለሁኝ።

አሁንም ቅድምም ከኦነጋውያን ጋር ያለው ድርድር ትውፊታችን ላይ የተቃጣ፤ ማተባችን ላይ የተቃጣ፤ በአብሮነታችን የተሳለ ሰይፍ ሊያመጣ ስለመቻሉ የህሊና ዝግጁነት የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

ቅኖቹ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ የሚያካሂዱት የጥገናዊ ለወጥም ቢሆን ከኦነጋውያን፤ የዳውዳውያን ጋር የሚያደርጉት ማናቸውም ስምምነት ጥንቃቄ ሊያደርጉበት እንደሚገባ በአጽህኖት ላስገነዝብ እወዳለሁኝ። በትውፊታችን ድርድር የለም። በሃይማኖታችን ቅኖና እና ዶግማ ድርድር የለም።

ግራኝን እንደገና ተወልዶ መከራ እንዳይመጣ ለጉዳዩ ልባዊነትም መለገስ ይገባል። ኢትዮጵያዊ እስልምናም ቢሆን ፈተናው ተራራ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ይኖርበታል። ይህ ድርጅት ቀስ እያለ ነፃነታቸውን ይነጥቃቸዋል፤ አብሶ  ለአንስት እህቶቻችን። 

  • ·       መረጃው ይህ ነው።

Ethiopian Info - የግዕዝ ቀንቋ እና ያሬዳዊ ዜማ
በወለጋ ጊምቢ ሠሪት /ማሪያም / ተከለከለ

እነዚህን ነው የኤርትራ መንግሥት አቅፎ እና ደግፎ በተሟላ ሎጅስቲክ ሲደግፍ ያኖረው። እስካሁን ስለደረገው ማናቸውም ድጋፍ ሊቆረጥመው ሊያቃጥለው ይገባል። ራሱን የሚንዱትን ጸሮችን ነው አስጠግቶ የኖረው የኤርትራ መንግሥት።

የሆነ ሆኖ እርምጃው የሚያሰዝን የሚያስከፋ ምንም ነገር የለውም። ከዓለም አብያተ ቤተ - ክርስትያን ተልይታ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተለዬ ሥርዓት እና ህግጋትን ነው የምትከተለው። አይጠገበም ሥርዐቷ። ተገልፆም አያልቅም ጥበቧ። ፍጹም እና ዕጹብ ድንቅም ነው። የ ኢትዮጵያ ታሪክ ጸሮች ሃይማኖቱን የሚጻረሩትም አውደ መጠኑ ልዑቅም ረቂቅም ከሃሳብም በላይ ስለሆነ ነው።  

ለወደፊትም ቢሆን በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ ከዚህ ትውፊትን፤ ክብር እና ታሪካችን፤ ትሩፋትን ለማጥቃት ጸር ከሆነ ጥቁር ድርጅት ጋር የ ኤርትራ መንግሥት ያለውን ማናቸውም ግነኙነት ማቆም ያለበት ይመሰለኛል። አሲድ እዬረጨ ነው ያለው ኦነግ እና መንፈሱ - ለኤርትራም ለኢትዮጵያም ለመካከለኛው አፍሪካም ጠንቅ ነው ይህ ድርጅት።

ኦህዴድ /አዴፓም ማሽሞንነሞኑን፤ መለማመጡን ትቶ ለኦሮሞ የቅድስት ኦርቶዶክስ ልጆችም ዘብ ሊቆምላቸው ይገባዋል። ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል።

ባያውቁት ነው እንጂ ዳውዳውያኑ ግዕዝ እኮ ጀርመን ላይ አጤ ነው። ጀርመን ልጆቹን በግዕዝ ያስመርቃል። ለእነሱ ቢቀርባቸው እንጂ ትውፊታችን ምንም አይቀርበትም፤ ምንምም አይጎድልበትም። ብቻ ይህቺ ሽንብራ ካደረች ሆኖ ነገ የክርስትያን ልጆች ደም እዛው ኦሮምያ ላይ እንዳይፈስ ቅደመ ጥንቃቄ ቢወሰድ መልካም ነው።

ኢትዮጵያዊነት ገናና ማንነት!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።