ይድረስ ለአቶ አዲሱ ረጋሳ ካሉበት፤ ቤተ መንግሥትም ከተሆነ?
የእጩ ጠ/ ሚር ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ዘመናይነት።
„ሥጋቸውን መከራ ያስቻሉ በፈጣሪያቸውም አምነው መከራ የተቀበሉ በክፉ ሰዎችም የተነሳ የጎሰቆሉ፤ ፈጣሪያቸውንም የወደዱ፤ ሰዎች ብርና ወርቅን አይወዱም።“ ይሄ በሴረኞች እገታ ውስጥ ላለው ለአብይ ቅዱስ መንፈስ የተጋባው ነው። መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፵፪ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ© ሥላሴ
10.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
አዝናለሁኝ የተለዬ ምልከታ ከቲም ለማ ቡድን እንዳላቸው ባውቅም ግን የሃሳብ ልዩነትን እንደ ወንጀል ስላማላዬው እማከብራቸው ወጣት ሊሂቅ ናቸው አቶ አዲሱ ረጋሳ። እንዲያውም እኔ በአትላንተው ጉባኤ ላይ ሁሉ ቀና ምልክታ ነው የነበረኝ ተሟግቻለሁም። ሰው ሃሳቡን ያውጣ የሚል ዕምነት ነው ያለኝ።
እኒህ ወጣት የፖለቲካ ሊሂቅ ያው በአቶ ጆዋር መሃመድ እንደ ሮል ሞዴል የሚታዩም ናቸው። እኔ እውነት ለመናገር ኢትዮጵያን እንደ ጣዕንት ለሚያ መንፈስ ቆራጣ ጊዜ ማጥፋት አልፈልግም ነበር። ነገር ግን እንዲህ እዬገፋ ከመጣ ግድ ይላል። በአቶ ጃዋር መሃመድ ጠ/ ሚር እንዲሆኑ ይፈለግ የነበረውም እሳቸውን ነው። ከሳቸው ቀጣይ ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን። የሆነ ሆኖ ሳልፈልግ ተገድጄ ለዚህ ጹሁፋቸው መልስ መስጠት ግድ ይለኛል ለአቶ አዲሱ ረጋሳ። ሰሞኑን ብቅ እያሉ መሪነታቸው እያሳዩን ነው።
እራሱ ስለ አዲስ አባባ ስለ ንጉሦች ንጉስ አጤ ሚኒልክ፤ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ስቀደሙት የፖለቲካ ድርጅቶች ወዘተ እምታቀብባቸው ጉዳዮች አሉ። አስፈላጊ በሆነው ሁኔታ ብቻ እንጂ እራሱን አስችዬ የሙግት አውራ አድርጌ አልታገልበትም፤ ስለምን? ባለሙያዎች የታሪክም የሃይማኖትም ሊቀ ሊቃውናታት ስላሉበት።
የሆነ ሆኖ „ምርቱን ከግርዱ እንለይ“ በሚል ከአቶ እዲሱ አረጋ
የጻፉትን አነበብኩት ያው ከቤቴ ከዘሃበሻ። አሁንም እኮ ሌላ መሪ ሌላ ጠ/ ሚር ተቀበሉ እዬተባለ ነው አማራ። አሁንም እንደ ቀደመው በአማራ ትክሻ ወያኔ መንበሩን እንዲለቅ ሙሉ ድምጹን እንደሰጠ አሁን ደግሞ የ አብይን መንፈስ ያገተውን የአትላንታውን ጉባኤ እድምታ አስፈጽም አማራ እዬተባለ ነው፤ እንደ ቀደመው ሁሉ መናጆ ይሁነን ነው እዬተባለ ያለው። አንዲት ብጣቂ ነገር ሳያገኝ። ካለ አማራ የፈለገ ቢታቀድ ፍንክች የሚል ነገር የለም እና። ይህንን ሁሉም አይቶታል። የአማራ የህልውና ተጋድሎ ባይገለል ዛሬ ቄሮ ንጉሥ ሆኖ እንዲወጣ ምቹ ሁኔታ ባልተፈጠረ ነበር። ለነገሩ እምንፈራውም ለዚህ ነው። እንድንጠፋ፤ እንድንከስል የሚፈለገውም በዚኸው ነው። እማችን ግን ይፈለጋል።
ቀድሞ ነገር ኦህዴድ ትእግሥት ነስቶት እዬሠራ ያለውን እቃ እቃ ጨዋታ እና የልጆች ቀልድ ራሱን ቢጠይቅ መልካም ነው። አቅል ነስቶት እዬተክለፈለፈ ነው። ለመሆኑ የት ላይ ነው ያላችሁት ኦህዴዶች? ምንድን ነው አቋሟችሁ? አሁን ያለው የኦሮሞ ወረራ ነው ነው ወይንስ ኢትዮጵያን የማዳን ተልዕኮ ነው? እራሳችሁን አደብ ገዝታችሁ መርምሩት። ታሪክ የሰጣችሁን የቤት ሥራ ትወጣለችሁ ሲባል ቀልብሳችሁ አራት ማዕዘን ሳጥናችሁ ውስጥ ነው ያላችሁት።
ግን ምን ላይ ናችሁ ያላችሁት? መቱ ላይ አብይን፤ ለማን፤ አማራን እንዳትነኩ ያለውን የ10 ሺህ ህዝብ ድምጽ እዬጠበቃችሁ ወይንስ ያን አፈር ድሜ አስግጣቸሁ የአትላንታውን የቻፕተር ሪቂቅ እያስፈጸማችሁ ነውን? ቄሮ ለድል አብቅቶናል፤ ዘመነ ቄሮ ነው አይደል የምትሉት? እንኳንም ብቻችሁን ታግላችሁ ለዚህ በቃችሁ። እንኳን ደስ አላችሁ።
ስለዚህ እኛ ስለምን እናስፈልጋችሁ አለን? እንደጀመራችሁ አጠናቁት።፡ምን ባህርዳር ያስኬዳል። ስለምንስ ሚሊዬንም አዳራሽ ላይ የግዮን መንፈስ አስፈለጋችሁ?
ኦህዴድ አቅሙ እና ፈቃዱ ካለ ከስሜን አሜሪካ መልስ መጀመሪያ መሪውን ከእገታ ያስለቅቅ? መሪው የ ኦህዴድ ሊቀመንበር፤ የ ኢህአዴግ የግንባሪ ሊቀመንበር፤ የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር ታይቶ ተሰምቶ በማያታወቅ ሁኔታ የተፎካከሪ ፓርቲዎች ሳይቀሩ መሪዬ ያሉትን መንፈስ ከእገታ ልቀቁ!
መጀመሪያ ኦህዴድ የለማን መንፈስ ገልብጦ የሠራውን እዬሠራ ያለውን አዲስ የጨለማ ቀለበት ይፈትሽ ከሌላ እርዳታ ከመጠዬቁ በፊት። መሥራት ያለበትን ይሥራ። አቶ ጃዋር አህመድን ቀይ ጃኖ አልብሶ ከሚያንገዋልል፤ ኦነግን ተቀበሉ ብሎ ከሚያስገድድ፤ አዲስ የቂም በቀል ሃውልት ተክሎ ነገ ደግሞ የትግራይ ህጻናት አንገት የሚደፋበትን ነቀርሳ በይፋ በአዳባባይ መሰረት ከሚያስጥል። የትግራይ የነገ ህፃናት ኢትዮጵያ ትወልድ አካል ናቸው። አጀንዳችን ናቸው፤ የኛም ናቸው።
ኦህዴድ አዲስ አባባ ፊንፊኔ ናት እዬለ ከሚፎክር፤ መጀመሪያ የታገቱትን መሪዎቹን የምናውቃቸውንም የማናውቃቸውን ያስፈታ። ወይ እሱ እራሱ አግቷቸው ከሆነ ይንገረን። "እናንተ ከረዳችሁን ሁሉም ይሆናል" ያለው አንቦ ላይ አቶ ጆዋር ምን ማለት ነው? ለነገሩ ከአንቦ ውጪ እኮ ሌላ ቦታ የተነጠለ ነው የአቶ ጆዋር መንፈስ፤ አንድነቱን ያመጡት አቦ ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ናቸው።
ስለምን በሌላው ክልል ተብሎ ሲጠይቅ ትግሉ ሙሉ አልሆነም ተብሎ አቶ ጆዋር አህመድ ይቆዩ ብለን አቆይተናቸው ነው ነበር ያለው። ግን አቅሙ ያለው ያው ሽዋ ከተወሰነ አካባቢ ብቻ ነው የነበረውም። ያውም ከዛ ድንቁ ከሎሬቱ መንደር ክህደተ ኢትዮጵያ። ይዘገንናል። ለዚህ ከሆነ ቄሮ የታገለው ያን ድንቅ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን አጽም በግፍ ለመፍጨት ከሆነ።
ለመሆኑ አዲሱ ጠ/ ሚር ማነው? አቶ ጆዋር፤ ፕ/ ህዝቃኤል ወይንስ ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ወይንስ አቶ ዳውድ ኢብሳ? ም/ ጠቅላይ ሚኒስተሩስ ማን ናቸው ለአዲሱ ካቢኔ ይመጥናሉ ተብሎ የተዘረዘሩትስ እነማን ይሆኑ? አሁን እኮ በይፋዊ መስመር አገር እንዲመሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው ዶር ሙለቱ ተሾመ ናቸው። ለሚዲያው ገብያ ማለት ነው።
እኛ ጅሎቹማ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድን ንጹህ መንፈሳቸውን አብጠርጥረን አጥንተን ደገፈን ነበር እኮ። ውጪ አገር ይሁን አገር ውስጥ እናንተ አይደለም የደገፋችሁት። እናንተ አይደለም ቀን ከሌት የታጋችሁለት ለለማ መንፈስ። እናንተማ በOMN የቻላችሁትን ያህል ታገላችሁት እኮ።
ይሆና ተብሎ ሌት እና ቀን እኛ ተገተን በተለይም ጅሉ አማራ ሁሉንም ነገር ሰጠትን ነው እዚህ የተደረሰው። የቄሮ መንግሥት ምስረታውን ቀጥሎ እና ታዩ? አንድ አገር አንድ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አንድ ብሄራዊ መዝሙር ፈጥራችሁ? መጀመሪያ ሰው ስለሚለው ተፈጥሮ ት/ ቤት ግቡ።
ያ የሚሊዮን ድምጽ ለአብይ ቅድስና፤ ለአብይ ሙሴነት ሲመጣ ምን ያህል እብደት እንደ ነበር እኮ ሁሉንም ግራ ቀኙንም እምንታዘብ እኮ አለን። ይህም ሆኖ ቅኖቹ ያን የመሰለ ድጋፍ ሲገኙ ደግሞ በዛ ድጋፍ ትራስነት አሁን ደግሞ በሰላው፤ በላማው በለሰለሰው ማሳ ግብታችሁ ምንን ተቀበሉ እንደምትሉት ራሳችሁን ጠይቁት?
ኦህዴድ ታሪካዊ ድርሻውን መወጣት አቅቶት ቢወድቅ የእናንተ እንጂ የአማራ አይደለም። ከዱከም እሰከ ቢሸፍቱ 80 ኢንደስትሪዎችን ለመገንባት ከቻይና ጋር ስምምነት ስታደርጉ ዝም የምንለው እኮ እንዚያን ቅን መሪዎች ስለመንናከብር ብቻ ነው።
አማራ መሬትማ ወጣት ሴቶች በ300 ብር እንደ ጥንቸል ወጣት ሴቶች አንደ ቀደመው ሁሉ ቤተ ሙከራ ላይ ናቸው። ይህ አያመነም፤ አይሰማንም መሰላችሁን? የእኛ ጀግና አርበኛ ዘመነ ካሴን በምን ሁኔታ ባዕቱ እንደ ተቀበለው እና ንጉሥ ጃዋርን መሃመድን ደግሞ ብኤዴን እንዴት እንደተቀበለው፤ ከቅርቡ ያለው ጀግና ኮ/ ደመቀ ዘውዱ፤ አርበኛ ንግሥት ይርጋ፤ ጄ/ አሳምነው ጽጌ እና መሰሎቹ ያላቸውን ቦታ እያዬን ነው ዕድሜ ለአቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ ሳጅን በረከት ስምዖንን ተከተዋል አሳምረው። ህሊናም ልብም አለን እነስተውላለን።
ምንድነው የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ነጥሎ ወደ ራስ ማስጠጋት። አቶ ንጉሡ እና አቶ አዲሱ ረጋሳ ሰፊ ዕውቅና በOMN ሲሰጣቸው እንደባጀ እኮ ይታወቃል። የውስጥ አድማው የቆዬ ነው። ይህን አቦ ለማ መገርሳም ሆኑ ዶር አብይ አህመድ፤ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሆኑ ዶር አንባቸው መኮነን ለደቂቃ አስበውት አያውቁም ነበር።
እኔ ግን እከታተለው ነበር። በዚህ ሚዲያ አንዲትም ቀን በእነዚህ ቅኖች ላይ የተሠራ በጎ ነገር አልነበረም። BBN፤ ህብርንም በጨማራችሁት አመክንዮ አክላችሁ። የህብር ነገር ይገርመኛል፤ አንደበት እንሱ ሆኖ ነው ቁጭ ነው ያለው። አሁን ደግሞ የቀይ ጃኖ ዘጋቢ። ሁለቱ ራዲዮኖች ጣዕሜ ስለሆነ አብዝቼ እምከታተላቸው ስለነበሩ ስፋታቸው እያዘንኩኝ ነው።
መመርመር መፈተሽ ያለበት ኦህዴድ ራሱን እንጂ አማራ ወይንም ሌላው የህብረተሰብ ክፍል አይደለም። ኦህዴድ ተሸንፎ ኦነግን ተቀበሉ ነው እኮ አደባባይ ላይ ያለው ነገር። 108ቱ የፓርላማ አባላት ድምጽ ኦነግ ይምራኝ ብሎ ነበርን የወሰነው? አሁን ያለው እውነት እኮ ይሄው ነው። ፓርላማው አኮ ፈርሷል። አዋጅችኋዋል እኮ ሚሊኒዬም አዳራሽ ላይ።
ያን ሁሉ የተጋነው ለኦነግ ሥልጣን ነበረን? ያሳፍራል በጣም። እጅግ ያሳፍራል። መጪው ያስፈራልም። እኛ የተጋነው ጥራት ላለው ለለማ እና ለአብይ መንፈስ ነው። ያን ያህል መከራ የታዬው። እንጂ ኦነግማ እንኳንስ እኛ የራሱንም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ሰብሰብቦ ተደምጦ አያውቅም። ባዶውን የቀረ መንፈስ ነው። መርዙ ብቻ ነው ያለው። እኔ ኮፐን ሀገን በ2008 ላይ አይቸዋለሁኝ።
25 አይሞሉም ነበር ለዛውም ከኡጋዴን ነፃ አውጪ ጋር ሆነው። ሁለቱም ዬዬራስ አርማቸውን ይዘው ወዲያ ማዶ ተስፈንጥረው ተሰልፈው ሲያውግዙ ነበር፤ የሄሮድስ መለስ ዜናዊን አስተዳደር። እዚህም አንድም ቀን ስብሳባ ሰምቼ አላውቅም።
በሌላ በኩልም ከአሜሪካን መልስ ቤተ መንግሥት ያለውም ሁኔታ ኦነግ አሸነፎ ድል አድርጎ የገባ ይመሰል ያን ያህል አሰረሽ ምቺው ምን የሚሉት ቅልጣን ነው? 1ሚሊዮን ህዝብ ሜዳ ላይ ወድቆ።
ለመሆኑ አቦ ለማ መገርሳ ኤርትራ ገቡ ታላቅ ዜና ነበር፤ ሲመለሱ ደግሞ ዜናው የውሃ ሽታ ሆኗል። አቶ ወርቅነህ ገበዬሁ እስረኛውን ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ጋር አጃቸው የስልክ መሥመር ያለው ይመስል በምን ሁኔተ ግንኙነት እንዳለ ተመልክተናል። አስተውልናል።
ለመሆኑ ኦቦ ለማ መገርሳ ከኤርትራ ተመለሱን? ከተመለሱስ የት ነው ያሉት? መቼም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በነፃነት ውስጥ ናቸው ብላችሁ እንደማትነገሩን ተስፋ አደረጋአለሁኝ? ነፃነታቸው ተቀምቷል። ታስረዋል።
ሥልጣኑን ሰውር ሃይል እዬመራው ነው ያለው። አሁን ኢትዮጵያ ጠ/ ሚር የላትም። የተፈለገው በሳቸው ሥም፤ በሳቸው ህሊና ባፈራው ቅምጥ ሃብት ኦነግን መጠቀም ነው። ኦነግን ከብክቦ ዙፋን መስደፋት ነው። ይህ በምዕራቡ ዓለም እንዳይታወቅ ደግሞ ፈርማዋል የታገቱት ጠ/ ሚር። በስተቀር ልጆቻቸውን ያጣሉ።
ሌላ መፈንቀለ መንፈስ እዬተካሄደ ነው። ትግሉ እኮ አንድ አንባገነን ነቅሎ ሌላ አንባገነን፤ አንድ ጸረ አገር እና ወገን ነቅሎ ሌላውን ለመትከል አይደለም። አንድ የጎሳ ጽንፈኛ ተወግዶ ሌላ ለመተካት አይደለም።
ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት ብሎ ያን ያህል ሲያብድ የነበረ መንፈስ አሁን ቀይ ጃኖ አልብሶ ቀልዱ ይቁም። ተረበኞች ናቸሁ። በሙሉ አቅም እና ቁመና ብቻችሁን ተነጥላችሁ እንድተበቅሉ ያደረገው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። አማራን ያከሰመ መስሎት።
አማራን እዬነቀለ እናንተን ሲተክል ቆዬ ወያኔ ሃርነት ትግራይ። ጊዜ ሲገኝ በቃ ከላይ ከላይ በተተኪ ተሞላ ቦታው ሁሉ። ስለዚህም አቅም ያለው ይምራ ሲባል ኦረሞይተከል፤ ይጽደቅ፤ ይለምልም፤ ያስብል የተባለው ሌላው ከስሞ ስለቀረ ነው። ኦሮሞ ሁሉ አነግ ነው የሚል እምነት ማንም የለውም። አምላኪዎች ግን ኦህዴድ ውስጥ እራሱ አሉት። ኦነግ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ነው ያለው። ያሳበዳችሁም ይሄው ነው።
ኦነግ አይወደነም። ጸረ አማራነቱም የተፈጠረበት ነው፤ ለድርድርም አይቀርብም። ለዚህ ደግሞ አዲሱ ጥላሁን ግዛው፤ አዲሱ ዋለልኝ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሆነው ቀርበዋል። ያገኙትን ፍቅር እና አክብሮት በራሱ እዬደረመሱት ነው። ሚናቸውን ለይተዋል።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሥልጣን ሲወገድ አምሳዬውን እንዲተካ ፈቃዳችን አይደለም። ኦህዴድ ዕድሉን እያሾለከው ነው። በሌላ በኩል ከለማ እና ከአብይ መንፈስም እዬወጣ ነው። ኦህዴድ አፈንግጧልም። ይህ በይፋ ግልጽ ሆኖ ሊወጣ ይገባል። አብይ እና ለማ እንጂ ሌላው መንፈስ እኛን እንዲገዛን፤ እንዲያሰተዳድረን አንፈቅድለትም። በአማራም በኩል ቢሆን የገዱ እና የአንባቸው መንፈስ ብቻ እና ብቻ ነው የሚፈቀድለት።
ያን ያህል ሌት እና ቀን የባከነው እኮ ለኦነግ ነፃነት አይደለም፤ እኛ የታገለነው ለኢትዮጵያ ነፃነት ነበር። ኢትዮጵያ አዲስ ጨለማ ውስጥ ናት። ጠ/ ሚር አብይ አህመድም የቁም እስረኛ ናቸው። ጠላትም ወዳጅም ይህን ይወቀው። የቁም እስር ማለት ህሊናህን መሰጠት ማለት ነው። አብሶ ለትግራይ ንጹሃን ይህ እጅግ አስጊ መነገድ ነው።
የአቶ ንጉሱ ተነጣይ መንፈስም ቢሆን ያው ሁሉማነው ካስረከበ በሆዋላ ወያኔ ሃርነት ኦሮሞን እንዳረገፈው ያራግፈዋል። እንኳንስ እኛን ሰብዕናችን መንፈሳችንም አይፈልገውም። ከክርስትና እምነት ጋርም ያለ ያልተነካም አመክንዮ አለ። ይሄ ብንፈራውም፤ ብንተዎውም የማይቀር ነው። አማራነት በግማሽ ብቻ ሳይሆን ክርስትናም ተፈርቷል።
አውስትራልያ ያ እጅግ የማከብራቸው፤ የምሳላቸውም ጋዜጠኛ አቶ ካሳሁን ከሦስት ሊቃናት ጋር ግሩም ውይይት አድርገዋል። የአብይ መንፈስን በዘላቂ ለመደገፍ። ቅንነታቸውን አከብረዋለሁኝ። ቃለ ምልልስ ተጠያቂዎች አቶ አዳሙ ተፈራ፤ አቶ አያሌው ሁንዴሳ እና አቶ ዘመድኩን ወርቁ በSBS ነበር። በነገራችን ላይ አቶ ዘመድኩን ወርቁን ጋዜጠኛው አቶ ካሳሁን ሲያስተዋውቁ እንደ ተማላ ሰው አድርገው ነው።
አርበኛ ዘመድኩን ወርቁ ጀግና ሰው ነው፤ ሥራ ዓለምም እንዲሁ ሲታይ እና የሚፈጸመው ግን የተለዬ ነበር። አለቃውን እራሱ አይፈራውም በብዙ ሁኔታ ይዳፈረው ነበር። ካለመነበት አለቃ ነው ብሎ ተነስቶ አይቀበለውም። "ልፍስፍስ" ነው የሚለው የበላይ አለቃውን። የወጣለት ደፋር ነው። ወኔውን አውደዋለሁኝ።
ጀግና ነው አቶ ዘመድኩን ወርቁ ማለት። ዶክትሬቱን ሰርቶ ይሆናል ብዬ ነበር ግን አቶ እንደሆነ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊገባ ሽግግር ላይ እያለ ይመስለኛል አፈንግጦ ከደርግ የሸፈተው፤ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስልጣን ሲይዝም በጎጃም እና በሽዋ አዋሳኞች በትጥቅ ትግል ሲያርበተብተው የነበረ፤ በጋዜጣ በሚዲያ ሲፈለግ የነበረ፤ በፖለቲካ ሳይንስ የተማረ የሠራ፤ እግሩን ስለታመመ ነው ከትግል ሜዳ ወጥቶ ወደ አውስትራልያ የሄደው። ከገባ በኋዋላ በዓለም አቀፍ ቢዝነስ ይመስለኛል በማስተርስ ደረጃ፤ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ዕውቅና ካለው ዩንቨርስቲ ነው የተመረቀው።
የሚገርሙ ሁለገብ ብቃቶች ያሉት ሰው ነው፤ ዛሬ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለወርቅ ተሸላሚ ተማሪዎች እንደሚያድርጉት ሁሉ በሚኖርበት ኪዊንስላንድ ውስጥ ባለማዕረግ ተመራቂ ኢትዮጵውያንን በራሱ ወጪ ልዩ ዝግጅት አድርጎ ሽልማት የሚሰጥ፤ አካባቢውን ለመጎብኘት ተደራጀተው ለሚሄዱ ኢትዮጵውያን ጥግ እና ከለለ የሚሆን፤ ወላጆቻቸው ታግለው የተሰውባቸውን ሰብሳቢ ላጡት ስፖንሰር በመሆን የሚችለውን ሁሉ የሚያደርግ። ከባህል ከእሴት ከትውፊት የወጡ ማናቸውም ነገሮችን በፍጹም ሁኔታ የሚጸዬፍም ነው።
ይህም ብቻ ሳይሆን ፍጹም ይሉኝታ ያለው ሰው ነው። ለትግል በተንቀሳቀሳባቸው የሽዋ ገጠር ከተሞች ያሉ ወገኖቹን ያረሳ፤ ልጃቻቸውን ልጆቼ ብለው ወደ አውስትራልያ ወስዶ፤ ቤት ያከራዩትን ልጆችንም እንደ ልጁ አድርጎ ያሰተማረ ለቁም ነገር ያበቃ። የማር ልጆቹ ከልጆችም በላይ ናቸው ለእሱ። ለእነሱ የሚሆነው ነገር ፍጹም ሰዋዊ ተፈጥሯዊም ነው። ቸርነቱን ልክ ደንበር የለውም።
አገር ቤት ላሉት፤ በችግሩ ጊዜ ለረዱት፤ ጥግ ከለላ ለሰጡት አራሶችን ገንዘብ በመላክ ያረሰ፤ የታመሙትን ያስታማመ፤ ቤተቸው የፈረሰውንም የጠገነ ነው። ይሄ የነፃነት ፍለጋ መንገዱ ጀግንነቱ ይሄ ነው አይባልም ቁምነገሩም እንዲሁ።
ብሄራዊ ፍቅሩን እኔ መለኪያ ወቄት የለኝም፤ ማህበራዊ ኑሮን በሚመለከት አገር ቤት ሀዘን ደረሰበት ለተባለ ሁሉ እዬደወለ በነፍስ ወከፍ የሚያጽናና የሚችለውን የሚያደርግ። የተበተኑ ጓዶችን ለማሰባሰብ ጥርት የሚያደርግ ሰው ነው። ማህበራዊነት ከፖለቲካዊ ህይወት ጋር አጣምሮ ለመምራት የሚያደርገው ጥረት እጅግ የምወድለት ነገር ነው። ለዚህ ነው ኢሳትን ስሞግት ብዙ ጀግኖች አሉ ዕዱሉን ስላላገኙ ነው እንጂ የምለው። ቃለ ምልልሱን ራሱ ማዳመጥ ይቻላል። ሳተናው ላይ አለ። https://www.satenaw.com/ethiopian-australians-support-for-abiy-ahmeds-ethiopia-sbs-amharic/Ethiopian-Australians Support for Abiy Ahmed’s Ethiopia – SBS Amharic
በሳል ቃለ ምልልስ ነው ያደረገው። አንድ የአርበኞች ግንባርም ነበረው፤ አፍሪካ ውስጥ ኮማንድ ፖስት ነበረው፤ ጀርመን እና ኖሮዬ ቅርንጫፍ ነበረው። ከውጪ አገር የነፃነት ታጋዮች ጋር ሰፊ የሆነ ግንኙነት ነበረው በተለይ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሁሉ። ከአገር ውስጥ በተለይ ከጋንቤላ ድርጅት ጋር በጣም ቅርበት እንደ ነበረው አውቃለሁኝ።
ስለዚህ ለነፃነት ትግሉ አዲስ ገብ አልነበረም ብዙ የደከመ፤ በማደረጃት የቆዬ፤ በመምራት በቂ ልምድ ያካበተ፤ ውጪ አገርም አጫጫር ኮርሶችን የወሰደ፤ አገር ውሰጥም በፖለቲካ ሳይንስ ዲፕሎማ የነበረው፤ በእውቀት ላይ የተመረኮዘ አቅም ያለው ሁለገብ የፖለቲካ ሊሂቅ ነው። አርበኛም ነው። የወጣለት ጀግና ነው ጫካ ለጫካ ክልትምትም ያለ።
ስለዚህም የአብይ መንፈስ ስለመጣ የነጻነት ታጋይ የሆነ አይደለም። ብዙ መክሊቶች አሉት። ሲታይና በመሆን ውስጥ ያለው መስተጋብር ልዩ ነው። የመሪነት ብቃቱ፤ የማስተዋል፤ የማሰባሰብ፤ የማቀፍ፤ አዳዲስ ሃሳብ የማፍለቅ፤ የመፍጠር አቅም አለው። ቅራኔዎችን የደፈር፤ የመሞገት ክህሎት ሁሉ አለው። የሴቶችን ብቃት በማጥናት አረገድ ደግሞ የተለዬ አቅም አይቸባታለሁኝ።
ስለዚህ ቢያንስ አርበኛ አቶ ዘመድኩን ወርቁ መባል አለበት ነው። የፖለቲካ ሊሂቅ እኮ ነው። ብቁ ነው በአማራርም። ብዙ ጊዜ እጽፈዋለሁኝ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን ስጽፍ „አብርሃም“ እያልኩ እምጽፈው እሱን ነው። ይህን ሥም ስለሚወደው። እናም ፈቃዱን ስላልጠዬቅኩት። ድፍረቱ የወንድነት አቅሙ ወኔው ኮስታራነቱ በላይ ዘለቀ ምስጋን ይነሳው።
አገራዊ ህልሙ ከድንቅ በላይ ነው። ብስጭቱ እራሱን አውድለታለሁኝ ጠረኑ የቀደሙት ዓይነት ስለሆነ። ነፃነቱን ለሚገፉት ማናቸውም ሁነቶች ብስጩ ነው። ሰው ለመርዳት ደግሞ እጅግ ፈጣን ነው። ተላላም ነው። ግን በትግሉ አልቀጠለም? ስለምን?
አርበኛና የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ ሊሂቁ አቶ ዘመድኩን ወርቁን አሳምኖ ወደ ለውጡ ያመጣ መንፈስ ምን ቢሆን ነው ብዬ ራሱ እራሴን ጠይቄዋለሁኝ? እሱም ቃለ ምልልሱ ላይ ትርጉም እንዳጣለት ሲገልጥ አዳምጫለሁኝ። በጠበቅኩት ብቃት ልክ ስላገኘሁት ባጋጣሚው አመሰግነዋለሁኝ። የእሱ እንዲህ በነለማ አብይ ገዱ መንፈስ ይህን ያህል መመሰጥ በእጅጉ ገርሞኛል። ለቅንጅትም ቀና ምልከታ ነበረው።
ለዛውም የዛን ጊዜ የእሱ ድርጀት እሱ የሚመራው ጠንካራ በነበረበት ጊዜ። እውነት ለመናገር እንደ መኢሶን ቅን ነው። የታምር ያህል ነው ያዬሁት ይህን ለውጥ የተቀበለበት መንገዱን። ምክንያቱም አቋሟን፤ አቅሙን፤ ድፍረቱን፤ ጅግነቱን ስለማውቀው። ማንም ሃይል ሊደፍረው አይችልም። ኮ/ ደመቀ ዘውዱ መሰሉ ነው። አንበሳ ነው የወጣለት!
እኔም አንዷ ሞገደኛ ነኝ። በጅ አልልም፤ አልጨበጠምም። ማንም ሰው ከእጃችን ገብታላች ብሎ እንዲፎክር አይፈቀድለትም። እና ቀድሜ የለማን ቡድን የተቀብለኩት ደግሞ እኔ ነኝ። እንደ እኔ ደፍሮ ለማውያን ነኝ ብሎ የወጣ እስከ አሁን አላዳመጥኩኝ። በውነቱ ኦህዴድ እድለኛ ነበር ግን መንገዱን እዬሳተ ነው። ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢል ሥርጉተ ሥላሴ ኦነግውያን ልሆን አልችልም። በፍጹም!በዚህ አጀንዳ እራሱ እምጽፈው ተገድጄ ነው። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊነትን ከሚጸዬፍ ጋር ጊዜ ማባከን አልሻም። እምሟገተው ለጠረኔ በጠረኔ ውስጥ ላለ ብቻ ነው።
ደግሞም ነገሬያቸዋለሁ እነ አቦ ሌንጮ ለታ አገር ሲገቡ መግባታቸውን አድንቄ፤ ኦህዴድ ግን የዓላማ ለውጥ ካደረገ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታሰር ተነጥዬ ብቻዬን ጥቁር እንደ ለበስኩት ጥቁር እለብሳለሁኝ ብዬ ነበር። አሁንም ለብሻለሁኝ። ኦህዴድ ተሸንፏል በኦነጋውያን አንጃዎች።
ስለምን ያ ቅን የአብይ መንፈስ በማዕቀብ ዕገታ ውስጥ ስለመሆኑ አሳምሬ ስላማውቀው። ነገ ቅዳሜ አሜሪካን አገር በሚኒያ ያለፈውን የሚያካክስ ስብሰባ እንደለ ተደምጧል፤ የቄሮ ብሄራዊ ምክር ቤት እንደሚቋቋም ሃሳብ እንደቀረበም በፎርም 65 ቃለ ምልልስ ሰምቻለሁኝ፤ የነገው ስብሰባ ምን ሊሆን እንደሚችል ባለውቅም አማራ ከብት አይደለም በአሞሌ ጨው የሚታለል። ኦህዴድን ግልብጠው ኦህዴድ ውስጥ በበቀቀሎ ኦነጋውያን ድል ስላደረጉ ነገ ድሉን ያወራርዳሉ። ግን መስሏቸው ነው ድሉ ወገሚት ነው።
- · ምልሰት።
አሁን ደግሞ ኦቦ ለማ መገርሳም ከኤርትራ መልስ ይመለሱ አይመለሱ ምን ይሁኑ? ምን አይሁኑ አይታወቅም። ከዚህ ቀደምም አቶ ለማ መገርሳ የቁም እስር እንደ ነበሩ ግዮን ድምጽ የአማራ ራዲዮ ዘግቦ ነበር።
ያን ጊዜስ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው። አሁን ግን ያው የራሳችሁ የኦህዴዶች ኦነጋውያን ገመና ነው። ኢጓችሁን ደርምሱ እና እንያችሁ። እነ አቶ አዲሱ ረጋሳ። ይህ የ አገር ጉዳይ እንጂ የአሻቦ ገብያ አይደለም!
ኦህዴድ ኦነግ ነው ወይንስ ኦህዴድ? የሥም ለውጥ የዓርማ ለውጥ ሳይሆን የመንፈስ ለውጥ ያስፈልጋል። አገር በማትባል አገር ውስጥ እንደ ወያኔ ሃርነት እናንት ደግሞ ለስንት አመት ትዘናከቱባት ይሆን?
አሁን እኮ እንኳንስ ለአማራ ለኦቦ በቀለ ገርባ፤ ለዶር መራራ ጉዲናም አስጊ ነው እንኳንስ ለዶር ለማ መገርሳ እና ለዶር አብይ አህመድ ቀርቶ። ቀደም ብዬም ተናጋሬዋለሁኝ። የእነ ኦቦ በቀለ ገርባ እና ዶር መራራ ጉዲና እስር አጀንዳ የሚሆነው ለማናጆነት አቅም ለማዋጣት እንደነበረ። ለነገሩ እነሱም ዘመድ ከዘመዱ እንዲሉ ነው የሆኑት። ዘመን ጥሩ ነው ሁሉን አሳይቶናል።
የሚያሳዝነው ሁለቱ ባንድ ላይ አሜሪካ መሄድ አልነበረባቸውም። የሁለቱ ጣምራ ጉዞ ያመጣውን አምጥቷል። ቀጣዩ ታጋች ደግሞ ም/ ጠ/ ሚር ደመቀ መኮነን ይሆናሉ። ያለው ዕውነት ይሄው ነው።
ለዚህም እንዲመች ነው ሁለቱም ሲሄዱ ልዩ ቡድኑ እግራቸው ከመውጣቱ የሠራውን የሠራው።
ጊዜ የሚሰጣቸው፤ ተከድነው የሚቀመጡ ጉዳዮች ስላሉ ነው ዝም የምንለው። የሆነው ሁሉ ስለምን እንደሆነ አሳምረን እናውቀዋለን። ሰውሩ መንግሥት ሥራውን የት ላይ እንደ ጀመረ እነ ዶር አብይን ሸኝቶ ይታወቃል።
ቁልጭ ባለው አገላለጽ ኢትዮጵያ ወደ አልታወቀ ጉዞ እዬሄደች ነው … እኔ ደግሞ ለዚህ ላልታወቀው ጉዞ ጥርት ያለ መንገድ መኖሩን እስከ አረጋግጥ ድረስ አልጮኽም። በተደሞ እና በአደብ መቆዬቱን እመርጣለሁኝ። ውጥኑ ውጥን ሆኖ እንደ ኩሬ ወሃ ታቆቶ እንዲቀር ስለተወሰነበት በራሱ በ ኦህዴድ አንጃ ኦነጋውያን።
ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለ ተጋድሎ ሌላ እጅ ውስጥ ወድቋል። ለውጡ ምን አልባትም በቀጣይነት ከ ኦነጋውያን እጅ ወጥቶ በሌላ ሃይልም መቀልበሱ ግድ ይላል። ሦስተኛ ማለት ነው። አያያዙን ኦህዴዶች ስላለወቃችሁበት። ምርቃቱ ይነሳል። አብይን ያን ድንቅ መንፈስ ስታገሉት፤ ስታግቱት፤ ልተግድሉት መንፈሱን በተደጋጋሚ ስትሞክሩ? መሬያችሁን ገላችሁ ወይ አግዳችሁ በምስል ቀን እንገፋለን ነው ሂሳቡ። ግን መርከቡም ሹፌሩም አብሮ ይሰምጣል።
ከእንግዲህ ሞኛችሁን ፈልጉ። ከአማራ ቆራጥ ተስፋ ይገኛል ብላችሁ አትሰቡት። ዶር ገዱ አንድአርጋቸውም ሆነ ዶር አንባቸው መኮነን ከመታገታቸው፤ ወይን በመርዝ እንደ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ከመጥፋታቸው በፊት ራሳቸውን ለማዳን መትጋት አለባቸው። መቅደም።
በምልሰት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ከOBN ጋር የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ማዳመጥ ይቻላል። ድፍን ነበር ድንብልብል። በዛ ቃለ ምልልስ አንዲት ጊዜ እንኳን
„ ኢትዮጵያ“ ለማለት እንኳን አልደፈሩም ነበር። „አገሪቱ አገሪቱ“ ነበር የሚሉት። በዛው ሰሞን ዶር ነገሬ ሌንጮ ያደረጉት እና አቶ ንጉሱ ጥላሁን ያደረጉት ቃለ ምልልስ በፍጹም ሁኔታ አይገናኝም ነበር፤ ምን ሆነው አኮረፉ እስክል ድርስ። ዶር ነገሬ ሌንጮ በቃ በኢትዮጵያ ተጀምሮ በኢትዮጵያ ነው የተጠናቀቀው።
የጠ/ ሚር አብይ አህመድ የባህርዳር እና የጎንደር ጉብኝት ሚዲያ ላይ የነበረው ሳቦታችጅ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው። ግን እውነት ለመናገር ዳግሚያ አባ ኮስተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ መንፈስ ውስጥ ነበሩን?አሁን ካለውስ ሰውር መንግሥትስ ጋርስ አሉበትን? ግድ ይላል አማራን ለመያዝ። መናጆነት። ግን ተንሳፎ ነው የሚቀረው። ጡጦ የሚጠባ ስሌለ።
አሁን እንደማዬው በራሱ በለውጥ ሃይሉም ውስጥ ሌላ አዲስ የቅናት መንፈስ እንደ ተፈጠረ እና ሌላ አፈንጋጭ ቡድን እንደ ተከሰተ ነው። እርግጥ የቀደመ ነው። ፍጥነቱ ግን የአብይ መንፈስ ማዕበል አሰጋው እና አሱም እራሱን በተለያዬ ሁኔተ ገለጠ። ይህም የአንድዬ ጥበብ ነው።
ያ ፍንጋጣ አሁን የተፈጠረ ሳይሆን የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድን እና የልጅ ጃዋር አሃመድን ቃለምልስ ማዳመጥ ነው። በሳል የፖለቲካ ሰዎች ውጭ ያሉት ማለቴ ነው ግልቡን ከመሄድ ቁጭ ብለው የተፈጠረውን ነገር ተወያይተው እልባት ሊሰጡት ይገባል። ምንም ነገር ከመጀማመራቸው በፊት። አብይ እስከ ዲካ የለሽ አቅሙ ታሥሯል። አብይን እንስፈታ! ቀዳማዊ ነገር አብይን ነጻ እስከቤተሰቡ መንፈሱን ካጋቾቹ ማሰልቀቅ ማውጣት ነው።
ኦቦ ለማ መግርሳ ዕውቅና እያገኙ፤ ተቀባይነት እዬአገኙ ሲመጡ ቢቢኤን ይህን ሠራ።
"News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa"
„ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?
– ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል“
የለውጥ ጉዞው ለእኔ የሚሰጠኝ ውስጡ ተገልብጧል። መፍንቅለ መንፈስ ተደርጓል። የመንፈስ ኩዴታ ነው የተደረገው። በለመለመው መንፈስ ውስጥ ኦነግን ማኮፈስ። ለውጡን የሚመሩት ሃይሎች ለጊዜው በሰውር እዬመሩት ነው። የአትላንታው ጉባኤ መንፈስ ነው እኔ እማዬው። ይህ የግድያ በሉት የመርዝ ቅንብር ከዛ ከሰውር ሃይሉ ጋር በሚጋባ የተያያዘ ነው፤ ከዚህ ቀደም እኮ አቶ ተስፋዬ ጌታቸውን አጥተናል፤ ምን አዲስ ይሆንብናል።
የዶር ገዱ አንዳርጋቸው ከሥልጣን መቆዬትም አጠራጣሪ ነው የሚተኳቸው ደግሞ ለአቶ ጆዋር መንፈስ ምቹ የሆኑት አባ ኮስተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ይሆናሉ። ይህን ካለደረገ ብአዴን መቀጠል አይችልም፤ አርማውም እንዲቀዬር ቢደረግ በኦነግ መንፈስ ነው። ሂደቱ ወያኔያዊ ግልባጭ ነው።
አብሶ ዳግሚያ አባ ኮስትር አቶ ንገሡ ጥላሁን በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እርቀ ሰላም በዘለቄታ ስለማይወርድ እሳቸውም ማጓጓዣ መሆናቸውን አውቀው አቋሟቸውን በማይታይ፤ በማይዘልቅ ስውር ተስፋ ላይ ከማንጠልጠል ይልቅ ጥርት ብሎ የወጣውን የለማ የአብይ የገዱ የአንባቸው መንፈስ የእውነት እና የሃቅ ጎን መቆሙ ብቻ ነው የሚያዋጣቸው። ሞትም ካለ ታሪካዊ ሞት ይሙቱ፤ ኢትዮጵያን ባላተወቀው መንገድ ላዳግም እርድ ከሚያቀርቧት። የተገባላቸው ቃል ኪዳን ሊኖር ይችላል ሐውልት እስከ ማቆም ግን በክህደት ውስጥ ክብር ማፈሪያነት ነው።
መጽናት ነው መልካም ነገር። በማተብ መቆም ነውአውነት የአማራ መለያው ደሙ ከኖረ፤ አማራነቱን ከተቀበሉት። ነጋዴ አለመሆን ለነፍስ ቢያንስ የረዳል ሃይማኖቱ ካለ። የመንፈስ የሸቀጥ ቤት መክፈት ለትወልዱ ኪሳራ ነው። ወጣቱ አማራ ደግሞ እንዲህ ከነገረነው የፈረመበትን እንደሚሰርዘው ይታወቃል። ስለዚህ ብአዴን ሾልኮ ይቀራል።
ከዚህ ጋር ሌላ ያልተጠበቀ ሃይል ደግሞ አለ። ድርጁ ነው በሁሉም መስክ። ጥምረቱ የመንፈሱ በርቀትም ይኖራል ብዬ አስባለሁኝ። ሊንክ ስላለ እንደ አቶ ሃብታሙ አያሌው ዓይነቶች ለዚህ የተሰናዱ ናቸው። መቼም አቶ ሃብታሙ አያሌው ሌላም ጣምራ ግዳጅ እንዳለበት ማወቅ ይገባል። ባለ ማህያም ነው። ይህ ወጣት ለኢትዮጵያም ዘላቂ ደህንነት አደጋ ነው። አዛውንቶቹ ሲያረጁ ተተኪው እሱ ነው።
ቀልደኛ።
ሌላው አቶ አዲሱ ረጋሳ በጣም ጨዋታ ያውቃሉ። በሰንደቅ አንጣላ ይላሉ። ያ ሁሉ ዘመን ጦርነት የነበረው በሰንደቅ እንጂ በሌላ አይደለም። ታሪካችን የቆመው አገራችን የቆመችበት፤ እራሱ በትምህክት የእኛ የብቻችን እያሉ የሚነግሩን እኛን መጤ አደርገው የቆሙባት መሬት የቆዬችው በዛ ሰንደቅ ሃይል እና ግርማ እና ሞገስ ነው።
ያ የእኛ ፊንፊኔ መሬቴ የሚባልለት ቀዬ በዛ ሰንደቅ ሃይል እና መንፈስ ነው የኖረው። አይደለም ትናንት የባድመ ጦርነት አሰባሰባቢው ይሄው ሰንደቅ ነው። ባድመ ላይ አሁንም የሚውለበለበው ሰንድቅ ዓላማ ይሄው ነው። ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ። ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ቅደስት ክርስትናም ይፈራበታል። ይህ ግልጥ ብሎ ሊታወቅ ይገባል።
መቼውንም ለባንዳ መንፈስ ዝቅ ብለን እምናደገድገበት ምክንያት የለንም። ሰንደቃችን የሚጻጻር ባንዳ ብቻ ነው። መንፈሳች ቅኝ እንዲገዛ መቼውንም አንፈቅደም። የትውስት መንፈስ እንዲመራን አንፈቅደም!እኛ ሰው እንጂ እቃ አይደለንም፤ በጎደለ ቁጥር ለማሟያ የምንፈለግ።
ከዚህ በላይ አጀንዳ ለኢትዮጵያ ህዝብ የለም። የኦነግ እኮ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ዓርማ እንጂ ብሄራዊ አርማ አይደለም። ለሌላ የመንፈስ ወረራ ፈቃደኞች አይደለነም። ኦህዴድ ውስጥ ያለው ሰውር ሴራ በግልጥ ፍርጥርጥር ብሎ መውጣት አለበት።
መጥራት ያለባችሁ እናንተ እንጂ እኛ አይደለነም። በማተባችሁ የማትገኙ፤ ፍቅርን የምትገፉ፤ ክብር የማይዋይድለችሁ ናችሁ። ይህ የታምር ያህል ነበር የረበበው ፍቅር። ከእግራችሁ ሥር ወደቃለችሁ እኮ ያ ቀን ከሌት ሰንደቁን ይዞ ሲተጋ የነበረው መንፈስ በአደባባይ።
አማራ ውስጥም የራሱ መከራ ላይበቃ ለገዱ መንፈስ ሌላ ተቀናቃኝ መንፈስ የፈጠራችሁለት እናንተው እራሳችሁ ናችሁ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ የኢህአፓ ዝንጣፊ አማራ ሁን ብሎ እንዳደረገው፤ ያ ተገልብጠህ ኦነግውያን ሁን፤ ጃዋራውያን ሁን ነው የአሁኑ ትግል። ሞት ይሻለዋል ለአማራ ይህን መንፈስ ከሚቀበል።
ብቃት አገር ለመምራት አትችሉም የሚሏችሁ ምዕራባውያን እዬሆነ ነው። በክርስትና ላይ በጎነት የለም ለሚለውም በሌላ ሴራ ምክንያት ቢሆንም እናንት በምትገዙት፤ በምታስዳድሩት መንበር ሥር ነው በአንድ ሳምንት ስንት አብያተ ቤተክርስትያንት የተቃጠሉት። ነገ በክርስትና አማንያን ምን ሊታወጅ እንደሚችል ሁሉ አይታወቅም። ለመካካለኛው ምስራቅ ሰላም እና መረጋጋት ኤርትራን ጨምሮ አደጋው ሰፊ ነው።
በእናንተ በምትገዙት ዘመን ይሄን ያህል የኦርቶዶክ ተዋህዶ አብያተ ቤተክርስትያናት፤ ማህበረ ምዕመናን መንደደ ከግራኝ አህመድ ዘመን ምን ተለዬ? ድሉ የቄሮ ብቻ ነው እያላችሁ በምትፎክሩበት ዕለት ይህ አሰቃቂ ነገር ሲፈጸም ልታፍሩበት ይገባል። መሪውን ባታግቱት ይህን ያህል ጥፋት አይመጣም ነበር።
ስለዚህ ሳይውል ሳይድር የለበጣውን ጉዞ አቁሞ ያገታችሁትን መሪዎቻችን ከእስር ለቆ የጠራ ጉዞ መጀመር ግድ ይላል።
እንግዲህ ቤተሰቦቻቸውም እስረኞች እንደሆኑ ይሰማኛል። ቅድመ ሁኔታው ይሄው ነው ቦሌ አውሮፕላን ማርፊያ የተፈጸመው ድርድር። የተፈረመበት። ይህን ግልጽ በሆነ በሚዲያ ፍርጥርጥር አድርጎ አንዱን መምረጥ ነው። ወይ እኛን ወይ አቶ ዳውድ ኢብሳን እና ግብጽን።
ወይ መቀልበስ ወይ ደግሞ መቀጠል። እኛ ኢትዮጵያዊውን ለማ እና አብይ መንፈሳቸውን ነው የምንፈልገው። ወንበሩ መስሏችሁ ነው እንጂ እኔ ያዬሁት ግማሽ ፊት የሌላ ሰው ነው። እኒያ የፖለቲካ ሰው እርግጥ ነው የድርጅት ሊቀመንበር ገጽ ነው።
ግን ከአማራም ከኦሮሞም ውጪ ነው። በትንሹ ኦሮሞ ደም ሊኖርባቸው ይችላል። እናንተ ግማሽ አማራ የሆነ፤ ለዛውም ክርስትናን የተቀበለ፤ አማራ አገባ እያላችሁ በዶር አብይ አህመድ እንደዛታችሁ፤ እንደዘመታችሁ እኮ አሳምረን እናውቃልን።
የሚረብሻችሁም ይሄው ነው። እናንተ ሰትወራካቡ ዕድላችሁን ያውም በዘመነ የሚሊዮን መንፈስ ዲታነት የሌላ ሲሳይ ይሆናል። ወንበሩ አሁንም ባዶ ነው። ያዬሁት ህልም አስቀድሞ የነገረኝ ያንን ነው።
ሥውር የመንግሥት ግልበጣ ተካሂዷል። ኩዴታ ነው ይሄ። አብይን እናንተ ቅድመ ሁኔታ ሰጥታችሁ ብቻ እንጂ ከዛች ውልፍት ቢል የአብይ መንፈስ አንዱን ይመርጣል። ትጨርሱታላቸሁ።
አላወቃችሁበትም። ስላላወቃችሁበትም በጊዜ መንፈሳቸውን የሚሰበሰቡ ነፍሶች ይኖራሉ። ይህን ያደረገው ደግሞ የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሄር ነው።
መታመን ቢያንስ ለራሳችሁ በትረ መንግሥት እንዴት ይነሳችሁ? በውነት ህሊናን ይፈትናል? ምዕራባውያን ምን ቢያጠኑ እንደዛ ሊሉ እንደቻሉ ሁሉ ይገርማኛል? „አገራዊ ራዕይ የላችሁምን“ ይሄ ሊጎረብጣችሁ ይገባ ነበር። ኦነግንማ የፈለገ ካባ ብትደርቡት አይደለም እኛ ምዕራብውያንም አይቀበሉትም። ጥብቆ ነው።
ለመሆኑ ለማ የት ነው? ለለማስ ፈቅዳችሁለታልን? ለአብይ ያዬነውን አይተናል ያው ግማሽ አማራ አይደለምን? "ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይስላል" ቅኔው እኮ የሄው ነው። ጤናውንም አጉድላችሁ ጥውልግ መንፈስ አስረክባችሁናል። ይህም አልበቃ ብሎ ገመምተኛው አብይ እሰረኛ ነው። ዕውነቱ ቢመርም ይሄው ነው።
ግንቦት 7 ልብ ይስጣችሁ፤ አገር እንገባለን ብላችሁ ሰምጣችሁ እንዳትቀሩ። ፈርትን አንሸሽም ማለታችሁን አዳምጫለሁኝ። እንግዲህ ከሰውሩ መንግሥት ጋር ውል ካላችሁ መሄድ ትችላላችሁ፤ አቶ ሃብታሙ አያሌው ካላዳናችሁ በስተቀር፤ ግን አገር ቤት መግባትን ልታስቡት አይገባም። ብትሄዱም እናንተም አይቀናችሁም ዝም ብዬ አይደለም ይህን የምለው ህልም አይቻለሁኝ። ከገባችሁ።
ለነገሩ አትሰሙም፤ ራሳችህን ለማድመጥ ብቻ ነው የተፈጠራችሁት።
ሥልጣኑ ሳይሆን መኖራችሁ ነው ብልሁ ነገር። ጉዞው ተስተጓጉሏል ቤንዚኑም መኪናውም … ታግቷል። ነገ ሌላ ቀን ነው። በጎ ለማስብ ሁኔታውን በጥሞና አጥንቶ ለሚመለከታቸው ሃያላን አገራት ማሳወቅ ነው። ለእነሱም ነገ ሊፈጠር የሚችለው ነገር ስለማይታወቅ ኢንባሲዎቻቸው እዛው ነው ያሉት፤ የቻለ አገሬው ትንሽም ቢሆን ስንቁን መቆጣጠር ይገባል። አደጋው ለሁሉም ነው። ጦርነት ህግ የለውም።
ጦርነት የእናት ልጅ የለውም። ጦርነት ጨካኝ ነው። አሁን የታጠቀው ሃይል በማን እጅ አንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።
ኦህዴድ አረሙን መንቀል ያለበት ራሱ ነው። ትተዋወቃላችሁ። መቼም የኢትዮጵያ ህዝብ ጃዋርውያን ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው ተረብ የውርንጫ ድካም ነው … የኢትዮጵያ ህዝብ አብያውያን ነው። ይህን ደግሞ አይታችሁታል። ያሳበዳችሁም ይሄው ነው።
በአጭሩ ቆርጣችሁ ሥልጣኑን እንቁጣጠር ያሰኛችሁም ይሄው ነው። ሸግግሩን ሲጨርስ እንፈነግለዋለን ስትሉ ነው የነበረው። ነገም ይህ አብይ መንፈስ አሰፈራችሁ እና ያደረጋችሁትን አደረጋችሁ። ድብብቆሹን አቁሙ። የ108 ያ ድምጽ እንደገና የሰጠውን ድምጽ ይርምርም። እርግጥ አሁን እረፍት ላይ ነው። የመረጠው መሪም የቁም እስር ላይ ስለመሆኑ ይወቅ። ይሄው ነው።
ሌላው የአማራ አክቲቢስቶች ግን ከአብይ እራስ ውረዱ። መከረኛ ነው። ሲኖርም መከረኛ ነው። በግራቀኝ ተሰቅዞ ነው ያለው። ትንሽ እንደ ሰው እዘኑለት። ትንሽ እንደ ሰው እንደ አገር ልጅ እሰቡ።
አብይ ንጹህ ሰው ነው። መቼውንም ዘመን እማናገኘው። እንዲህ ዓይነት ሰው በ200/300 ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጠር ነው። እግዚአብሄር ሰጠን ምርቃቱ ይነሳል እያልኩ ስጮኽ ባጀሁኝ የሆነው ይሄው ነው። ለአማራ አብይ የሰማይ ገነት ነበር። ግን አክቲቢስቶች፤ ጋዜጠኞች፤ ተንታኞች የባጃችሁበትን ታውቁታላችሁ …
የኔዎቹ ከልብ ብሎ የእኔ ብሎ ሁኔታዎችን፤ ዜናዎችን፤ ምስሎችን፤ ሂደቶችን፤ ዘገባዎችን መከታተል ይገባል። ወያኔ ወያኔ ብቻ አትበሉ። እነሱም በእድሉ አልተጠቀሙም።
የአብይን መንፈስ ተፃራሪ ሆነው ነው የቀረቡት፤ አላወቁበትም፤ ታገሉት አሁን ሁሉም የሚሰምጥበት ጊዜ ነው … ኦህዴድ ውስጥም ቅኖች እንዳሉ ግን ማሰብ ይገባል። ጠንካሮችም አሉ። በድምሩ እነሱንም ማውገዝ አይገባም። ግን ሥልጣኑን በስውር አዬመራ የያዘው ኦህዴድ ውስጥ ያለ የኦነግ አንጃ ነው … እርግጥ ነው ወያኔያውያንም ይኖሩበታል።
ዘመን እንደገና ይሞት ወይንስ ይነሳ ይሆን? ውጪ ያሉ ሊሂቃን፤ ብልሆች የአብይ መንፈስ ማህበርተኞች መትጋት ያለባቸው እገታውን መጀመሪያ ማስነሳት ነው … ተቀምተናል! እርማችሁን አውጡ። ስለዚህ አቅም ማዋጣት ያለብን ቤተሰባቸውን እና እሳቸውን ነፃ በማውጣቱ ላይ ነው። እግዚአበሄርም ይርዳን! እንጸልይ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
አዱኛዎቼ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ