ውሃ በቀጠነ ቁጥር መበርገግ አያስፈልግም።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

ውሃ በቀጠነ ቁጥር
መበርገግ አያስፈልግም
„ፈራህ አትፍራቸው።“
ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20.02.2019
ከእም ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።


·       መንፈቀ ሌሊት - አንድ።

እንዴት አላችሁልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ አንድ ህልም አዬሁኝ። አንድ የተዘጋ በር ተከፈተ። ከዛ የተዘጋ በር ሲከፍት ሜዳ አለው። ሜዳው ላይ ትንሽ ሳር በቅሎበታል። አንድ ሰው ከአቶ ሃይለማርያም ደስለኝ ጋር አለ። ያ ሰው ግን ግርዶሽ ጥሎበታል። 

እናም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳሩን ገፋ ገፋ አድርገው ከሉት። አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ሳሩን ገለጥለጥ ሲያደርጉት በሰው ቁም ልክ የሆነ ጉድጓድ ተከፈተ። ከዛም አንድ ብረት በብረት የሆነ የተቆለፈ ትልቅ የብረት ሳጥን ወጣ። እንደወጣ ቀረብ ብዬ ላይ ስፈልግ በሌላ አቅጣጫ ከአንገቱ ላይ ራፊ ያደረገ አንድ እርቃነ ነፍስ የሆነ ከ9 እስከ 11 ዓመት ዕድሜ የሚሆን ታዳጊ ወጣት መለመላውን መጣ። ታዳጊ ወጣቱ ያልተገረዘ ነው። ታዳጊ ወጣቱ ዕብድ ነው። 

እሱ ሲመጣ እኔ ፈርቼ ቦታውን ለቅቄ ወጣሁኝ። ስወጣ ያ ሳጥን ሳይከፈት ነበር ... ህልሙ የውነት ነው። ፍቱት… ኢትዮጵያ መንፈቀ ሌሊት ላይ ነው ያለችው።

·       ንፈቀ ሌሊት - ሁለት።

ያው የማለዳ ቁርሴ የሳተናው ድህረ ገጽ ነው። በርከት ያሉ ጹሑፎች አዬሁኝ። ትንሽ አነበብኩኝ። ስለ ጠ/ሚር አብይ አህመድ „ካህዲነት“ ጠንከር ያለ ጹሑፍ ወጥቷል። ሰለ ወዮልሽ አዲስ አባባም እንዲሁ። አሁን መፈናቀሉ ደግሞ ማህሉን እያመሰው ነው። ይህ በዚህ እንዳለ ትናንት ማምሻ ላይ ኦዴፓ አንድ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል። በዚህም በዚያም ብሎ ኦዴፓ እና መጪው የኢትዮጵውያን ዕጣ ፈንታ አደጋ ውስጥ እንደሉ አመላካች ስለመሆኑ ጸሐፍት ጽፈዋል።

እኔ ደግሞ „ነገር ከሥሩ ውሃን ከጥሩው“ ይሉ ዘንድ ሳይበረግጉ ጥርት ያለ፤ ረጋ ያለ፤ ትንፋሽን የሰበሰበ፤ ፍተሻ እና የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብን ነው እምመርጠው፤ ኢላማ በተተኮሰ ቁጥር ከግቡ አይደርስም፤ ኢላሚው እና ታላሚው ሲገናኙ ነው ድል ጉሮ የሚባልለት …

በዛች ቀዳዳ እና መስመሯን ተከትሎ ከታለመለት ጋር ለማገናኘት ማስተዋልን ብቻ ሳይሆን ሃሳብን ሰብሰብ በመድረግ ወኔን መፈተሽን ይጠይቃል። ይህን ተኩስ የተለማመደ ሁሉ ያውቀዋል። ዓውሎ በመጣ ቁጥር ወጀቡን ዞር ብሎ ማሳለፍ እንጂ ፊት ለፊት መጋፈጥ ያብጠለጥላል፤ የያዙንት ያስጥላል፤ የተጠጉበትንም ይንድ እና ራስንም ይጠርጋል። እናስተውል ለማለት። ኢትዮጵያ መንፈቀ ሌሊት ላይ ነው ያለችው ለእኔ። ለነገሩ የጠ/ሚሩን ሹመት ያዳመጥነውም በመንፈቀ ሌሊት ላይ ነበር።

·       ንፈቀ ሌሊት - ሦስት።

እኔ ደግሞ እላለሁኝ። የጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቢኔ ሰሜን አሜሪካ ከመውጣቱ በፊት በነበረው ቁመናው ልክ መቀጠል እንዳይችል ማዕቀብ እንደተጣለበት ነው የሚገባኝ። ለዚህም በህልሜ እኔ አማኝ መሆኔ ነው። እሳቸው ወደ አሜሪካ ጉዞ የጀመሩ ዕለት ነበር እኔ ወንበሩ ባዶ ሆኖ የተመለከትኩት ያው በተለመደው መንፈቀ ሌሊት። 

በዬዕለቱ ያን ወንበር ሰው ተቀምጦበት አየዋለሁኝ እያልኩ ስጠብቅ ህልሙ ምልሰት አላረገም። ስለዚህ በእኔ እምነት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሚሰጣቸው መመሪያ ልክ በመጠራቅቅ መንቀሳቀስ ግድ እንዳላቸው ስለማስብ እሳቸውም ፈተና ውስጥ እንዳሉ ይረዳኛል።

ለምሳሌ በምን ታምር እሳቸውን አብዝተው የሚጸዬፉት፤ ሊዮዋቸውም የማይፈቅዱት ሰው የኢህአዴግ ጉባኤ መግለጫ አንባቢ ሊሆኑ ቻሉ? ስለምን አቶ ገዱ እያሉ እሳቸው አደራዳሪ ሆኑ? የብአዴን ጉባኤ ላይ አቶ ደመቀ መኮነን እንዲነሱ ስለምን ተፈለገ? አሁን በመጨረሻ የጠ/ሚር አብይ ካቢኔ ንደበት ስለምን የጃዋርውያን መንፈስ ተሾመ? ይህንም ፍቱት … ለዛውም አቶ ካሳሁን ጎፌ እያሉ።

ጠቅላላ የሚታዬው የሚደመጠው ምስቅልቅ እንዲሆን የተፈለገ ጉዳይ ነው።  የአብይን አቅምን አሟጦ ተጠቅሞ ገዝግዞ የመጣል ትልም እንዳለ ነው እኔ የሚሰማኝ። ህወሃት ህውሃት አትበሉ ስል ባጅቻለሁኝ። 

ለውጡን የሚፈልጉ የጠ/ሚር አብይ አህመድን አመራር በጽኑ የሚቃወሙ በአቅማቸውም በክህሎታቸውም በተቀባይነታቸውም ብን ብለው የቀኑ የራሳቸው ሰወች አሉ። ከላይ እሰከታች የእነዛ ቅኝት ነው ቦታውን ተቆጣጥሮት የሚገኘው። እሳቸው አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ያሉት ብዬ አስባለሁኝ።

እኒህን ሰው እኮ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚ/ር ሆነው ዓለም አይቷቸዋል። ያን ጊዜ በሙሉ አቅማቸው የገነቡት ተቋም አሁንም የመልካምነት ተምሳሌት ነው በሁሉም ዘርፍ።  የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ሠራተኛ እረፍቱም ቤቱም መዝናኛውም የሥራ ቦታው ነው ዛሬ። አንድ ትልቅ ማህበረሰብ ፈጥረዋል። የፈቀደ ድርጅቱን ሄዶ ማዬት መጎብኘት ነው። ህልማቸው ለኢትዮጵያም ያ ነበር። ግን አጨናጎሉት እነ ጃዋርውያን … ይህ ቅናት የሚሉት ነገር ምን ያህል ግብረ ሰይጣን እንደሆን ከዚህ ዘመን በላይ መስካሪ የለም።

ይህ ሁሉ የጎጀመበትን የእሳተ ነበልባል ቦታውን ቢለቁላቸው እሳቸው በተባበሩት መንግሥታት ቁልፍ የሚባለውን ቦታ ዓለም እጃቸውን ስሞ ይወስዳቸዋል። የሚለካ፤ የሚሰፈር፤ የሚወሰን አቅም አይደለም እኒህ ሰው ያላቸው። ብቁ ናቸው። ቅብዕም አላቸው። ያሰቡትን ለመሳካትም በፈተና ውስጥም ሆነው እንኳን ይሳካላቸዋልም።

ይህን መሰል ሁለገብ አቅም እና ችሎታ በ27 ዓመት ቀርቶ በ50 ዓመት ውስጥ ዕድሉ ነበር ቢባል ኢሚንት ነው። ብዙ ነገር አላቸው። እንዲያውም እንደ እኔ በህይወት መኖራቸው ስለሚያሳሳኝ እኛ ወግ ደርሶን ልንጠቀምበት ካልቻልን ሉላዊው ዓለም ቢጠቀምበት ስለሚሻል የነፍስ አምላክ ቢጠብቃቸው እና ያን አጓጊ ቅንነት እና ክህሎት ሉላዊው ዓለም ላይ ቢውል ምርጫዬ ነው።

አይናገሩትም እንጂ እሳቸው እራሳቸው ፈተና ውስጥ ናቸው። ፈተናው ደግሞ ሰኔ 16ቱ ያመጣው ጣጣ ነው። ያ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ ፈጽሞ አያስፈልግም ነበር። ያን ያህል ተቀባይነት ባጠረ ጊዜ ውስጥ ይኖራል ተብሎ አልተገመተም ነበር። ያ ዱብ እዳ ሰውን ሁሉ አሳብዶታል። ዶር አብይ ንጹህ ሰው ናቸው። 

በወጣትነት የጠፋ የጎደፈ ነገር ይኖራል። ወጣትነት ሳተናነት ስለሆነ። ወጣትነት ከማገናዘብ ጋር ብዙም እርቀሰላም የለውምና። የሆነ ሆኖ ስህተትም እንደ ሰውኛ እንጂ እንደ መላክኛ ማዬት የተገባ አይደለም። መላዕክታን ራሳቸው እኮ ይሳሳታሉ ይለናል መጸሐፈ ሄኖክ። እንዲያውም እኩይ የሆኑ ሰብዕናቸው የዛ ተወልጆዎች ናቸው ነው የሚለን መጸሐፈ ሄኖክ።

·       ና ስንቅነት።

ኦፌኮን ከአረና ጋር ወግኖ የተጽዕኖ ፈጣሪ መንግሥት አሁኑን እያለን ነው። ኦነግ ከህወሃት ጋር ወግኖ በመንፈሰም በአካልም መደርመሱን አና ብሎታል። የአራት ወንበር ህልመኛውም በራሱ መንገድ ሸሩን ይሸርባል። ነገርዬው ከሁሉ ሳይሆን ወልቆ ከቀረ ኢትዮጵያ በመከራ ሌሊትነት ትቀጥላለች። መንፈቀ ሌሊት ...

ወደ ቀደመው ስመለስ ትርምስ ከዛም ከዚህም ያለው አብይ አልቻለበትም በአብይ ትክ ሌላ ሰው ይመራ እንዲባል ነው። ይህ ደግሞ መንገዱ ወደ አልታወቀ ጉዞ የሚያመራን ነው። ኢትዮጵያ እኮ ጠላቶቿ ቀናተኞቿ የራሷ የማህጸን ፍሬዎችም ናቸው። 

ኢትዮጵያዊነት ዳግም መምጣቱ እንቅልፍ የነሳቸው ነፍሶች አሉ። ለዚህ ኦነጋውያን እና ህዋህታውያን የቅናት ባህታውያን ናቸው። ሌላ ምን ሥራ አላቸው ይህን ሲፈትሉ ነው ውለው የሚያድሩት።

ደጋግሜ እለዋለሁኝ አቶ ጃዋር መሃመድ ሳያሽነፍ አይተኛም። ፈጽሞ! አሁን አገር ምድሩን የሚመራው የእሱ መንፈስ ነው። እሱ የፈቀደው ብቻ ነው የሚሆነው። እሱ ሽፋን የሚሰጠው ብቻ ነው ይለፍ የሚሰጠው።

·       ንሽ ልብ ቢሸምት።

ሌላው ስለተ ቢስነት ነው። "በምርጫ አንዘርረዋለን" ብሎ ነገር ብልህ ፖለቲከኝነት አይደለም። ሌላ ፍዳ እና መከራ ለመከረኛው አዲስ አባባ ህዝብ መናፈቅም ነው። ሆድ ብዙ ነገር ይችላል።

ዝም ማንን ገደለ? ከ1ሺህ በላይ ጦላይ የተወረወሩ ዜጎች፤ 5 ወጣቶች አዲስ አባባ ላይ የተረሸኑበት ምክንያትን የልቤ ማለት ያስፈልጋል። የቡራዮን ባለቤት አልቦሽ ሰቆቃንም። አንድ በዛን ጊዜ አደጋ የደረሰበት ወጣት ካሳውን አግኝቶ በሰኔ 16 መከራ ቤቱን ከእነ ህትምት መሳሪያው በሳት ነው ያጋዩት። አሁን ሜዳ ላይ ነው እስከ ልጆቹ። ራማ ሚዲያ ላይ ይህን አሳዛኝ ዜና አዳምጫለሁኝ። 

በቀሉ በነፍስ ወከፍም አና ብሎ ተይዟል። ስለምን አብይን ደገፍክ ነው ጉዳዩ። ይህን ደግሞ የጃዋርውያን ቡድን እንጂ ህውሃት አይደለም ያደረገው። ህውሃት ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ላይ ነው ያለው …

የሆነው ሁሉ የሚሆነው ሁሉ ታቅዶ ነው የሚከወነው። ይህ ታቅዶ ለሚከውን ነገር ደግሞ በተደራጀ መንፈስ መመከት እንጂ መበርገግ አያስፈልግም። ኦነጋውያን የተለሙትን ትልም ለመስበር በሃሳብ ልቅና በልጦ መገኘት ብቻ ነው መፍትሄው።

 በሌላ በኩል ሙያ በልብ እንጂ እንዲህ በዬሜዳው እንደ ቄጠማ የነገን ድርጁ ፍላጎትን እዬበተኑ መሆን አይገባውም ነበር። እማዬው ግን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ገና ለግንቦት 2012 ለሚሰጥ ድምጽ ከአሁን ጀምሮ እርግጠኛ ሆኖ ዓዋጅ ማስነገር የተገባ ብልህነት አልነበረም። ፈጽሞ የተከለከለ መንገድ ነው ይህ ለብልህ ፖለቲከኞች። የግንቦት 7 ኪሳራ እኮ ይህ ነበር። ደጋፊቹን አስደስትኩ ብሎ ስልቱን ስትራሪጂውን በመጸሐፍ ጽፎ/ በመግለጫም፤ በሚዲያውም ይበትናዋል በበተነው ልክ ንጹሃን ዋጋ ይከፈሉበታል። አሁን ያ የአቀባባል ፕሮግራም የተገባ አልነበረም። ሁሉንም ነገር በልክ መያዝ ያስፈልግ ነበር።

ያን አቀባባል እናካክሳል ሲል ኦነጋውያን ተባባረው ሌላ ትዕይንት ፈጠሩ፤ ያ ሁሉ ሰቆቃ ዳግም ተከሰተ። ውድድሩ ግን የሁሉም የሰኔ 16 የአብይ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ ጋር ለመፎካካር ያን ለማስናቅ ነበር። በመሃል ንጹሃን ተገበሩ። ነገም የሚጠብቅ ሌላ ደመራነት አለ። ለህዝብ ሰላማዊ ኑሮ፤ ለቁርሾ እንዳይጋለጥ ማንም አያስብም። ጭብጨባ እኮ የሳሙና አረፋ ነው ጤዛ። ትልቅ ዓላማ ላለው መንፈስ አጀብ ምኑን ባልሆነ ነበር ግን ኢጎ እያለ … 

ያሰቡትን፤ ያለሙትን ጠብቆ መያዝ እንዴት ያቅታል?

·       ጎን ለማዬት መሰወር።

ሌላው ጥቅልል አድርጎ ሁሉንም ቆሻሻ ውስጥ መጨመርም ደግሞ የለመደብን ጉዳይ ነው። በተጋድሎው ልክ የተገኙ እጹብ ድንቅ የሚባሉ የመንፈስ ምህረቶች አሉ። የሰው ልጅ በታፈነ ተፈጥሮን በነፈገ መከራ ውስጥ ኖሮ ሌላው ቀርቶበት መጸዳጃ ቤት በፈቀደው ሰዓት መሄዱ እራሱ ትፍስህት ነው። 

እኔ እሰከዛሬ ድረስ ታማሚ ነኝ በዚህ መከራ ውስጥ ስላለፍኩኝ። ኩላሊት ከተጎዳ በኋዋላ እንደ ሳንባ እንደ ጉበት በቀላሉ የሚያገግም አይደለም። አብሶ ለሴቶች ብዙ የተፈጥሮ ቀውሶች ነው የሚያስከትለው።

ስለሆነም ለዛ መብቃት እራሱ ትልቅ በረከት ነው። የሰው ልጅ ለመኖር ነፃነት ያስፈልጋዋል። በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ነፃነት አለ። ያ ነፃነት ደግሞ በመብት እና በግዴታ መጋባት ይኖርበታል። „መብቴን እጠቀማለሁ ግን ግዴታ የለብኝ“ የሚል ሁሉ ነጋሪት አነባለሁኝ። መብቱን የሚጠይቅ ግዴታውን መፈጸም ግድ ይላዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ አስካሉ ድረስ ደግሞ ህጎችን ማክበር ግድ ይላል። ህግ ትናንት በማን ላይ ተፈጻሚ ሆነ ዛሬ በማን ላይ የሚለውን ትዝብታቸውን ያጋሩን አቶ ምህረቱ ዘገዬ ጹሑፍ ግብረ ምላሹን ቢገልጹልንም፤ እኛም በሰኔ 16ቱ፤ በቡራዩ መካራ፤ በሻሻመኔው ፋሽስታዊ ምግባር፤ በ አዲስ አባባው ጭፍጫፋ፤ በቆመስ እንጂነር ስመኘው ሞት ብንመለከትም ምንጊዜም ማንም ይሁን ማን ሰብዕ ከህግ በላይ ላለመሆን መትጋት ይኖርበታል። ሌላው አይሁን ግን እራስን ገርቶ በዛ ልክ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል። 

·       ዓለም ጆሮዎች እና ዓይኖች እንሆ ተከፍተዋል።

የÄugen farbe ምስል ውጤት

አሁን ከቀደመው ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ላይ የዓለም ሚዲያ እና የዓለም የፖለቲካ ሊሂቃን ዓይናቸውን ስላሰረፉ በተሞገሰው ልከ አውራው ፓርቲ ኦዴፓ ቀዳዳውን ሁሉ የሚፈትሹ ብዙ ዓይኖች ደግሞ አሉበት። ይህ መታወቅ ይኖርበታል።

አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ ውጭ አገር የለም የሚል ነገር ተደጋግሞ ይደመጣል። ምን ፓርቲ ለመመሰረት እኮ የአንድ ቀን ተግባር ነው። አሁንም ያፈነገጡ ነገሮች ከተከሰቱ ለውጡን የሚቀናቃን ሌላ የተቃዋሚ ድርጅት ሊፈጠር ይችላል። በሎቢም አቤት የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ። ምን ለማለት ነው ይሄ መፍትሄው „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውና“ መተገበር ነው አዋጪ መንገድ የሚሆነው። ለኦዴፓ የሚጠቀመው ይኸው መንገድ ብቻ ነው። እንደተከበረም የሚያዘልቀው።  

ለምሳሌ የ5 የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች የአቀሟም መግለጫ ሲወጣ ኦዴፓውያን በመንፈስ የሉበትም፤ አልነበሩበትም የሚል ከኖረ ሶሻሊዝምን አያውቀውም ማለት ነው። ራሱ የሰሞናቱ የሠራዊቱ የ7 ኛ ዓመት ክብረ ባዕል የሰደደው መልክት በዝም ብሎ የሚታይ አይደለም። ደጀንነት የትግል አጋርነት የውል እደሳ ማህተም ነበር። 

መልካምነቱ እንጂ ጥፋቱ አልተጠቀሰም የሠራዊቱ። ስለምን? ሌላው መንግሥት እሱም ነውና። እሱ ካመጸ ኦዴፓ ያበቃለታል። ስለዚህ በግራ በቀኝ ጫን ያለ የክብር የሙገሳ ቀን እንዲሆን ነበር የተደረገው።

·       ልብያልተባለለት አመክንዮ።

ምንም የአገሪቱ እንቅስቃሴ ከሀምሌው ዝምታ ካወጣው መሪ ውጭ አትከወንም። እስኪ ከሀምሌው ዝምታ በኋዋላ ያሉ የጠ/ሚሩ የውጭ ጉብኝት ተመልከቱ ከኦዴፓ ሰዎች በስተቀር እኮ ሌላ ሰው ትውር አይልም። እራሱ ጠ/ሚር አብይ አህመድን አምነው ብቻቸውን አይለቋቸውም። ይህን ልብ ያለው የለም።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በማይነግሩን ዛሬ፤ ወደፊትም ሊነግሩን የማይችሉት ብዙ የተከደኑ ጉዛቸው በብዙ መሰናክሎች ውስጥ ነው ያለው። ስለዚህ መበርገጉን ተገስ አድርጎ፤ እርስ በእርስ ከመቦጫጨቅ፤ እርስ በእርስ ከመፈራረጅ ወጣ ብሎ ራቅ ባለ በረጋ እና በሰከነ አኳኋን ውስጥን መመልከት የሚገባ ይመስለኛል። ቀድሞውን ሲጀመርም ጸረ አብይ ሆነው የተነሱ የየትኛውም ማህበረሰብ ክፍሎች መቼውንም አብይን ጎሽ እንደማይሉ ማሰብ ይገባል።

በተፈጥሯቸው ሁሉንም ነገር የሚቃረኑ አሉ። በተፈጥሯቸው በጎውን በጎ ለማለት የሚቸገሩ አሉ። በተፈጥሯቸው አመሰግናለሁ ለማለት የማይደፍሩ አሉ። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ እራሱ ቃሉ ወይንም ስንኙ ወይንም ሐረጉ ለመንፈስ ተስፋ መጋቢ ነበር። ተናጋሪው ላያደርገው ይችላል። ዴሞክራሲ የሚለን ነፃነት እያለ የሚጮኸው ሁሉ ነፃነቱንም ዴሞክራሲውንም ሰጥቶን ስላላዬን ግን ነገር ግን ቃሉ በራሱ የመንፈስ ቴራፒ ነው። 

የሰው ልጅ በተስፋ ነው የሚኖረው። የሰው ልጅ ተስፋ ሲያልቅ በቁሙ ይሞታል። አሁን ስለ ህውሃት ብዙ ሰው ብዙ ይላል። ባለቀ ተስፋ የሚጠብቀው የፊት ለፊት ጉዳይ ሞት ነው። 

በሰሞናቱ ፎቶ አቶ አባይ ጸሐይ ስትመለከቷቸው መላዕከ ሞት ነው የሚመስሉት። ስለምን? ተስፋቸው አለቀ … አይሆኑ ሆኖ ደቀቀ እንጂ የሚበሉት፤ የሚጫሙት፤ የሚመነዝሩት ዶላር አጥተው አይደለም …  

„ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ እርግጥ ነው ደግመን አልሰማነውም፤ እንደናፈቀን ነው የቀረው። ነገር ግን በዛ ውስጥ በርካታ ነፍሶች ጤናቸው ተመልሷል። አንድም ቀን ዕድሜ ነውና። የተበተነው መንፈሳቸው ለምልሟል። አገር አለኝ ለማለት አስችሏቸዋል። 

አንድ ዓመት ይህን ሰንቆ መቀመጥ መልካም ነው። በዚህ ተስፋም ነው ልቅምቅም ብለው ፖለቲከኞች አገር የገቡት። እነሱም የናቁትን መንገድ ውረሰኝ ንዳኝ ብለው ዳግም „ኢትዮጵያዊነትን እናወድሰው“ እያሉን ነው … እኛም ተመስገን ብለናል ከልባቸው ከሆነ ሰሜን መለስ ካለሆነ ምኞቱ ሆነ ፍላጎቱ...

ስለዚህ በቃል ውስጥ ባለ ተስፋ ማደሪያ ጥግ ማግኘት በራሱ መልካም ነገር ነው። ይህን ራሱ ቃሉን መስማት ያልፈቀዱ ሰዎች ዛሬም ከዛው አቋሟቸው ላይ ቢሆኑ አይደንቅም። ምክንያቱም ዛሬ የሚታዩ ዘንበል ቀዳ ያሉ ገዳዳ ማጠናከሪያ ነገሮችም ስላሉ። ከጥዋቱም ያልጣመ መንፈስ አይጥምም „እንኳንም ዘንቦብሽ … „ስለሆነ።

የሚበልጠው የሚሻለው ግን በጥሩ ነገር ውስጥ እኔ የድርሻዬን እንዴት ላግዝ፤ በተዛባው ጉዳይ ደግሞ እኔ የድርሻዬን እንዴት ልወጣ ማለት ይገባል። ተጋኖ በወጣው ዘመኑ የኛነው የሚለው አስፈሪ ሥነ -ልቦና ያን ሲከበክቡ የነበሩ ነፍሶችም አሉበት። ለዚህ አቅም እና ጉልበት እነሱም የበኩላቸውን የተወጡ ናቸው። አሁን የካቡትን ለማናድ የቤት ሥራው ደግሞ የጋራ የወል ሆነ።

ቀደም ባለው ጊዜ ለውጡ እንዳይቀለበስ በሚል አቅም ማዋጣት ይገባ ነበር። አሁን ግን ኦዴፓ መከላከያውንም፤ የአዬር ሃይሉንም፤ የኢትጵያ አዬር መንገድንም፤ ምዕራባውያንንም በመዳፉ ያስገባ ስለመሆኑ ተረገጡን ግብረ ምላሹ ሹክ ብሎናል። እነሱም ነገርውናል። ስለሆነም የሚያመነን፤ ጎደለ የምንለውን ነገር ሳይፈሩ ሳይቸሩ መግለጽ ይገባል። እውነት እውነቱን የሚያበላ የሚያበላውን።

አንድ ነገር ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሙሉ አቅማቸው በፈቀዱት ልክ ባለሙት ልክ ብቻቸውን የሚወስኑት አንዲት ቅንጣት ነገር የለም። ትእዛዝ የሚቀበሉበት ሰውር አካል አለ። ለዚህም ነው እኔ ወንበሩ ባዶ ሆኖ ብህልሜ በሐምሌ ላይ ያዬሁት። ከዛች ድርድር ፍትልክ ቢሉ የጦስ ዶሮ መሆን ነው እስከ ቤተሰባቸው።

ጥንካሬያቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው። ምንም እንዳልተፈጠረ፤ ምንም እንዳለሆነ ሆነው ከአዲሱ ማንነታቸው ጋር ተዋህደው የሚችሉትን ለማድረግ መጣራቸው እራሱ ልባምነት ነው።

 … በቃላቸው ልክ መሄድ ባይችሉም ሙካራቸው እና ተጋድሏቸው ግን እያዬን ነው። ቢያንስ በሚችሉት ደልዳዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የሚፈጽሙት መልካምነት ከወገናዊነት የጸዳ እኩላዊ ፍትሃዊ እርምጃ ነፍስን የሚታደግ ነው። በዚህ መስመር ያለው ጥንካሬ ይበል የሚያሰኝ ነው። በውንም „ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ ህልሙ እውንነት የኖኽ መርከቡ የቀዳማዊት እመቤት ቢሮ ነው ለእኔ።  

ስክነትን ብንሰንቅ ያለንን አቅም ሁሉ ለስክነት ብንቀልብ እኛ ብዙ ነን። አቅም ደግሞ አለን። አቅማችን ለሁለማናችን ለማዋል በቅንነት ብንነሳ የሚያቅተን አይኖርም። ግን እኛም እንደ አይዋ እንቶኔ ውስጣችን ሌላ ውጪያችን ሌላ ሆኖ በጥምር ማንነት ስለሆን ያለነው ፍሬ ለማስበል የሰበለ እንዲያፈራ ለማደረግ አቅም ጠፋ።

አሁን ሁሉም በአብን ላይ ይረባረባል። 81 ፓርቲ ባላት አገር ልብም፤ ዓይንም ህሊናም ቁርጥማት የሆነው ለሁሉም አብን ላይ ነው። ስለምን ቢባል? በቅሎ ማዬት አስብሎ ማዬት በሽታችን ስለሚያመጣው። ይህን እንኳን በውል አልገባን ብሎ ጫናውን በዚህ ለጋ ቀንበጥ ድርጅት ባልወለደ አንጀታች ስንከምርበት ውለን እናድራለን። ይቅር ይበለን አማኑኤል። አሜን!

የተደራጀ መንፈስ ውሃ በቀጠነ አይበረግግም!

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።