ሰብዕዊነት ሲበጠስ ትዕግስትም ይበጠስ ...
እንኳን ደህና መጡልኝ።
„በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡
ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽው፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥
ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡
ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡
ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡
ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም። „
(ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫)
ፕ/ለማ መገረሳ ይማሩበት ዘንድ እንደ
አዶልፍ ሂተለር በግሎባሉ ከመወገዛቸው በፊት።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ።
ቃል የእምነት ዕዳ ነበር!
· ቁጥር አንድ ለእኛ በጥቁር።
ዛሬ ሦስት የህሊና ዳኝነት የኦሮምያ ፕሬዚዳንት እና የ ኢትዮጵያ ጠ/ሚር ለማ መገርሳ ይሰጡበት ዘንድ ሦስት ጉዳዮችን ነው እማነሳው። ሦስቱም ተወራራሽ ናቸው። የኢትዮጵያን መንፈስ ሃይልነት እና 21ኛው ምዕተ ዓመትን ጭንቅ ስለሚለው ሰብዕዊነት እና ተፈጥሯዊነት።
የመጀመሪያው ዛሬ „የኔ የነፃነት ቀን #MyFreedomDay“ ነው። በዚህ ቀን 40 ሚሊዮን የዓለም ህዝብ በዘመናዊ ባርነት እንደሚገኝ፤ ከከእነዚህ 40 ሚሊዬን ውስጥም አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት እንደሆኑ፤ የሴቶች ደግሞ በመቶኛ ደረጃው ሲለካ 71% ስለመሆኑ የሲኤን ኤን ዘገባ ይገልጣል። ኢትዮጵውያን ለባርነት መሰናዳታችን ልብ ልንለው ይገባል፤ እኛ ብቻ ሳንሆን ትውፊታችን፤ ትሩፋታችን፤ እምነታችን፤ ሥነ ልቦናችን፤ ባህላችን እና ወጋችንም ...
ሊንኩ ይኸውና።
#MyFreedomDay 2019: Students teach the world about modern slavery
https://edition.cnn.com/world/live-news/myfreedomday-2019/index.html
ይህን አይተን የሰሞኑ የተቀናጡ የግራኝ እምቤትን ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ያወረዱትን ማዕት ደግሞ በንጽጽር አቀርባለሁኝ።
ሊንኩን ብቻ ህሊናም እንዲፈርድ ቡድን ለማም ወደ የትኛው ባርነት እዬወሰዱን እንደሆን መመዘን ነው። ህሊና የተሠራው ለዚህንም አይደለምን?
ይህን ህሊናው ከቦታው ካለ የ100 ሚሊዮን ህዝብ ቃል ከበላው፤ ለአደራ ካልበቃው ኦዴፓ፤ ለዘማናዊ ባርነት ካሰናዳን ከቡድን ለማ የወቅቱ እርምጃ ጋር እንመዝነው። ይህ „የኔ የነፃነት ቀን #MyFreedomDay“ የሚከበረው በት/ቤት ደረጃ ነውና። የእኛዎቹ ባለምጥ ቀንበጥ ህፃናት ደግሞ ምን ላይ ነው ያሉት የሚለውን እዛው መዲናዋ አፍንጫ ላይ ያለውን ብቻ በጨረፍታ እንመዝነው …
ምሽት 12፡00 ዜና ሙዳይ ባሕር ዳር፡ መጋቢት 03/2011ዓ.ም (አብመድ)
„የ5ኛ ክፍል ተማሪው ህፃን በረከት ሃይለመስቀል ከዛን ቀን ጀምሮ ት/ቤት ሂጄ አላውቅም። ምክንቱም ት/ቤት ሄጄ ስመለስ አጣቸዋለሁኝ ብዬ የሚል ፍርሃት አለበኝ። ወንድሞቼም እንደዚህ አቋርጠው እቤት ነው ያሉት። ሰው ጋ ተጠግተው ማለት ነው። ስመለስ አጣቸዋለሁኝ እያልኩኝ እራሱ አፈራለሁኝ።“ የለማ አንጀት ለዚህኛው አይራራም። ስለምን? የእሱ ስላለሆነ።
የዓለም ልጆች ይህን ቀን ሲያከብሩ አቻ ምንዱባን እነ ታዳጊ ወጣት ተማሪ ሃይለመስቀል በረከትን እና መሰሎቹን ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሜዳን አምነው ተማምነው ያሉት ሚሊዮን ልጆች ምንዱብ ልጆችንም አሰብው ነው።
ይህ ቀን „„የኔ የነፃነት ቀን #MyFreedomDay“ ማዕት አውርድ ብሎ መሬት ለሚደበደበው ለፕ/ለማ መገርሳ ቡድን ታላቅ ትምህርት ይመስለኛል። ከሰብ ተፈጥሮ ውጭ የሆነ ዲዛይነር ስለሆኑ። ፎቷቸውን ሳስተውለው ውስጣቸው ሞቶ ነው የሚታዬኝ። ለነገሩ አቶ አዲሱ አረጋ ደህና አድርገውም አፍርሰዋቸዋል።
አውሮፓም በጊዜ ካልነቃ ያ የሚፈራው የሚሊዮን ስደት ዳግምያ ትንሳኤ ያደርጋል። አሁን ለለማዋብይ ካቢኔ ብድግ ቁጭ የሚለው ከዚህም አንጻር ስለሆነ ያን የስደት ማዕበል ያስቆምልኛል ብሎም ስለሆነ። የዚህ ገመና ፍሬ ነገር እዛ ግልጥልጥ ብሎ የቀረበ ቀን ሁሉም ይሰበሰባል። ፊቱንም ያዞራል።
ስለዚህም ኦነጋውያኑ ቅጥ ያጣውን ያበደ መንፈስ ኢትዮጵያን ቀብሮ ኦሮሞን ለማንገሥ ትልሙን መቅጣት እና ማረቅ ይጠበቅባቸዋል። በሁሉም ዘርፍ ራሱን ማረቀም ይጠበቅበታል ያበደው መንፈስ። ይህም ማለት በመሸወድ ሳይሆን በግልጥ በግንባር። በሌላ በኩል ክብር ሲገባው ልጣጭ የተለገሰው … ቁልፍ ቦታዎች አስረክቦ ቅራሪ ልመና ላይ ያለው ብአዴንም ልብ ሊገዛ ይገባዋል። በቁመናው ሥረ ትውፊቱ እዬተጣሰ ነው።
· ቁጥር ሁለት ጥቁር።
የገመና ቋት የኢትዮጵያ አዬር መንገድ እና የታሰበለት የሞት እርምጃ።
„ክምታደርገው ይልቅ የምትናረው ብዙ ርቀት ይጓዛል (ይኄይስ አእምሮ)
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94303“
„የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ላሉት ክፍት ቦታዎች 350 ሠራተኞች ተመልምለው እንዲሰለጥኑና እንዲቀጠሩ የሚመለከተውን ክፍል ያዛል አሉ – ከሁነኛ ምንጮች የሰማሁት ነው፤ በሚዲያም ተገልፆ ከሆነ አላውቅም፡፡ ትዕዛዙ የደረሰው ክፍል በአጭር ጊዜ ውስጥ ምልመላውን አካሂዶ የ350 ሰዎችን ስም ዝርዝር ያቀርባል – የሰውነት ደረጃችሁን ያልሳታችሁ ጤናማ ወገኖቼ እንዳትደነግጡ እነዚያ ሰዎች ሁሉም ኦሮሞ ናቸው፡፡ የበላይ ማኔጅመንቱ ውስጥ የሰው ሽታ ያላቸው ጥቂት ርዝራዥ አሳቢ ሰዎች ኖረው መሆን አለበት “አይ፣ በዚህ የለውጥ ጊዜ ይህማ እንዴት ሊሆን ይችላል? አየር መንገዱ እኮ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው፤ ከሁሉም ዜጎች በአዲስ መልክ ምልመላው ይካሄድና ይምጣ” ተብሎ ይመለሳል፡፡ እንዲያም ሆኖ ተሻሽሎ በቀረበው ዝርዝርም ከ350ው ከ170 በላይ የሚሆኑት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የገባንበትን አረንቋ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ፡፡“ አሜን ብለናል።
ያው ተለማድናል አይደል ሰላምታ መዘግዬቴ … እንዴት አደራችሁ፤ ዋላችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በዚህ በረራ አደጋ በተሎ መንፈሴ አያገግም። ዜናም አበክሬ ነው እምከታተለው። ትናንት ማታ ሲኤንኤን ስከታተል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕ በተረጋጋ መንፈስ አዲስ መግለጫ ሲሰጡ ሰማሁኝ። „USA Orderers Grounedinge 737 max 8 & 9“
ቀደም ሲል በነበረው ዜና ቦይንግ ባለው ሙሉ በራስ የመተማመን የእርግጠኝነት አቅም ሰለባ ሆኖ የነበረው የፕሬዚዳንቱ ቢሮ በቲተር ገፃቸው ሳይሆን ይፋዊ የሆነ እገዳ ነበር የጣለው። መግለጫውን ሲሰጡም ፕሬዚዳንነቱ እርጋታቸውም ከወትሮው የተለዬ ሆኖ ነው ያገኘሁት። አደብ የሰፈነበት ነበር ማለት ያስችለኛል።
Boeing 737 Max 8 planes grounded after Ethiopian crash
ከዛ በፊት ይህ አውሮፕላን ሌላ አገር ተከስክሶ ነበር። በህዳር 28 ቀን በ2018 የእነዚህን ቅዱሳን የ189 ሰዎችን ሲቀጠፍ በኢንዶንዢያ አዬር መንገድ ደቂቃውም ልዩነቱ ተቀራራቢ ነው። አማካኙን ብንወስድ ከሩብ ሰዓት በፊት ቀድሞ ማለት ይቻላል።
ነገር ግን ያን ጊዜ ዓለምን እንዲህ አቋም አላስወሰደም። ቦይንግም ሱባኤ አላስገባም። ደረቱን ነፍቶ ተግባሩን ቀጠለ እንጂ። እንዲያውም Max 9 ትልም እንደነበረው ነው ከዚህ ሰበር ዜና ከፕረዚዳንት ትራንፕ ፍንጭ ያገኘሁት።
የሆነ ሆኖ ወደ ዕድምታው ሚስጢር ስናመራ … አደጋው ነገረ ኢትዮጵያ ሲሆን ግን እንዲህ ዓለምን ሱባኤ አስገባ። ልዩ ትኩረትም ተቸረው። የሚገረመው ይህ አደጋ ሌላ አዬር ክልል ቢሆን ብዙ የተወሳሰቡ ችግሮች ይገጥሙ ነበር። ታዳፍኖ ሊቀር ይችል ነበር። የአብራሪ ስልጠና ችግር ሊባልም ይችል ነበር፤ ልክ እንዳለፈው የቤይሩት አደጋ ጭራሽ ተቀብሮም ሊቀር ይችል ነበር። ቀዝቃዛው ጦርነት የውሳኔ አቅጣጫ ጠቋሚ አሸናፊ ገዢው ዓለም እንጂ ደሃው ዓለም አይሆንም ነበር።
ለመወሰን እራሱ አደጋው የደረሰበት መብት እንጂ የአውሮፕላኑ ባለቤት አይሆንም ነበር። የኢትዮጵያ አምላክ የፈጣሪ ሥራ መከራውም በጥበብ የተቀመረ ነው። ይህ የሆነው መታበይ በዛ፤ ጥጋብ በዛ። ምርቃቱን ወደ ሬት ቀየረው እራሱ ኦደፓ። ራሱን ነው እንደ ኢሠፓ ያከሰመው። መንፈስ ከስሟል። መሃከነ?
ግን ዶር/ ገመቺስ ደስታ ነፍሳቸው አለችን? የት ናቸው ያሉት? ያው እሳቸውም ከመንፈሱ አብረው ስላሉ። የባዕለ ሲመቱም በልዩ ሁኔታ ነበሩ። የክህነት መለኪያው ይኸው ፈተና ነው። ፈጣሪ ሰውን ሲፈጥረው በአምሳሉ ነውና?
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ አቅም ሰጪው አምላክ ድርብ ድምጽ ኢትዮጵያ እንዲኖራት አደረገ። አደጋው ያው ፕ/ ለማ መገርሳ እና ቡድናቸው ማዕት አውርድ ብለው መሬት በመደብደባቸው እና በማስደብደባቸው በፈጣሪ ቁጣ የመጣ ቢሆንም የኢትዮጵያን ታላቅ ሃያል አምላክ እንዳለት ግን በጣምራ አስተምሯቸዋል እሳቸውን እራሳቸውን ጠ/ሚር ለማ መገርሳን። ግር አይበላችሁ የ ኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በሳቸው መዳፍ ውስጥ ነው። ወንበሩ ባዶ ነው። በመንፈስ ያሉት ደግሞ ዶር ለማ መገርሳ ናቸው። መንትዮሹ እስቲ እንይ
1) አንደኛው ወታደሮቻቸው መታበይን እዮር ቁጣ በዓይናቸው አሳይቷል እዮር። ለዛውም በፍጥነት። አገር እንገዛለን እያሉ የኮንዲሚኒዬም ቤት ትርኪ ምርኪ ላይ ሲወራከቡ …
2) ሌላው ከዚህ ቀደም አደጋው እንደ ማንኛው አደጋ እንጂ ቦይንግን ሱባኤ ያስገባ አልነበረም። ፕ/ ለማ መገርሳ በሰውኛ በሁሉም ዘርፍ ዛሬ እሳቸው ናቸው ወሳኙ። ይሁን የሚሉት የሚሆን አይሁን የሚሉት ደግሞ የሚሻር። ከሳቸው የላቀ መሪ ደግሞ ኢትዮጵያ አላት ፈጣሪ። ይቀጥላል የሚለው አዋጅ ነጋሪታቸው … በምለሰት ሲታብ … ሲመዘን … ይህ ሰቅጣጭ አደጋ እና ሂደቱ ደግሞ አቅል ላለው፤ እድምታው እዮራዊ ነው … የካህን እርዳታ ስለሚያስፈልጋቸው ነው ዶር ገመቺስ ደስታን የጣፍኳቸው። ጠበልም ካስፈለገ እርጫ እርጫ... ቤቱ እዬረከሰ ነው ፍቅር በገፍ፤ ምርቃት በገፍ ከ እዮር የረበበት ...
ከሁሉ የሚገርመው እና የሚደንቀው የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ነው ቀድሞ በቦይንግ 737 ማክስ ስምንት ላይ ጊዚያዊ እገዳውን የጣለው። ይህም አቅም ለጋዜጠኛ አበበ ገላው በሄሮድስ መለስ ዘናዊ ሰማይ ጠቀስ መታበይ እስከ ፓታርያርኩ እዮር ፍትህ የሰጠበት፤ ለዶር አብርሃም አለሙ መንፈስ ቅዱስ የሰጠውን አቅም የጠ/ሚር ለማ መገርሳን የውስጥ ምህንድስና እና የውጭ አገራት ጫማችን ላሱ መታበይ የተናደበት መስመር፤ የአንዲት በቀወስ ውስጥ በምትናጥ ደሃ አገር ያለ አዬር መንገድ አሜሪካን ያህል ታላቅ አገር የምርት ውጤት መገዳደር ሙሉ አቅም የሰጠው እዬር ነው።
ውሳኔው የተባረከ ስለሆነም ደጋፊም፤ አጋዥም አገር ፈጠረለት። ቻይናም ትባረክ። ታላቅ ባለውለታ ናት ውሳኔውን መከተሏ። የአንበሶች አገር ሲንጋፓሩ ደግሞ ገድል ነበር የወሰነው፤ በቀጠናዬ ድርሽ እንዳይል ይህ አውሮፕላን ዘር ነው ያለው።
የኢትዮጵያ አምላክ እንዲህ ነው። እናፈርሳትአለን ሲሉ የሚያፈረስ። ከሁሉ በላይ ለካንስ የሰው ልጅ ሰው ሰራሽ ከሆነው ከጫማ የአነሰ አቅም ነበረን የሚያሰኝ ነው ይህ አደጋ። የሰው ከሚመሰለው ቅሪት ይልቅ ቁሶች ነው ተሽለው የተገኙት። ይህን እኔ ያዬሁት በጀርመን ዊንግ አውሮፕላን ከአልፐስ ተራራ ጋር ታቅዶ ግጭት በገጠመው ጊዜ ነበር። 15 ቀን ሙሉ ነበር በሃዘን የታደምኩበት። ይህን ኢትዮጵውያን እንዲዩም በእለተ መጋቢት ልደታ ሆኗል። ስለ ኢትዮጵያ ብቸኝነት እንተጋ ዘንድም ... ከወንበር ውጪ ኢትዮጵያ የሚለው ድሃው ብቻ ነው። ሥጋ መልበስ ግን ስንሞት እንኳን እንዲህ ነው።
የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ አዬር መንገድ በቀሪዎቹ ላይ እገዳውን ሲጥል ከባድ ውሳኔ ነበር። ደፋርም ውሳኔ ነበር። ፍጥነቱ እና ድፈረቱ ግን የመንፈስ ቅዱስ አቅም ነበር። በውሳኔው ሌላው አገር ላይከተል ይችል ነበር። ዓለምን እዬተገዳደረች ያለችው ቻይና እንድትከተል ያደረገው መንፈስ ቅዱስ። መንፈሱ የእሱ ስለነበር ራሱ መደበኛው ተግባሩ ያልተስተጓጎለም። ስክነት አለው አዬሩ።
አስደሳች ዜና የተከሰከሰውን አውሮፕላን አስመልክቶ ከአቶ ተወልደ አውን የተሰጠ መግለጫ
እነ ጠ/ሚር ለማ መገረሳ የናቁት የኢትዮጵያ አምላክ ይህን ያህል አቅም አለው። አቅም ይሰጣል። ጉልበት ይሰጣል። ይህ የማይደፈረው የኢትዮጵያ አምላክ አሜሪካ እንኳን አሻፈረኝ ብላ እንዳትቀጥል እንሆ አደረገ።
ይህ በውነቱ ኢትዮጵያ ምንም አይኑራት፤ ማንም አይኑራት አላዛሯ ኢትዮጵያ የዓድዋ ድል ቤተኝነቷ ዘላቂ እዮራዊ ሚስጢርን ያብራራል። በዚህ በተመሳሳይ ቀን ነው የፊኩ ስብሰባ በቤተመንግሥት የፈጣሪ ታምራት የተገለጠበት በባልደራስ አዳራሽ የተካሄደው።
የፌኩ ሰብሳቢ በባንድ መንፈስ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ የቅዱስ መንፈስ ስብሰባ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ። የሚገርመው ከዛ ደቂቃ በፈጠነም ከተማ ላይ አደጋ እንዳይደርስ ያደረገው ፈጣሪ። ይህም ምክንያት አለው።
መስከረም ላይ በግፍ በጃዋርውያን የፈሰሰው የአዲስ አባባ 5 ወጣቶች ሰማዕት ቅዱስ መንፈስ ነበር ደቂቃውን ያራዘመው፤ እንጂ ከ6 ደቂቃ ቢቀድም እዛው መዲናዋ ላይ ነበር የሚሆነው። መከራውን ያቺ የአላዛር መሬት እንዲችለው ብቻ ማሳ አንዲወጣው ሆነ።
8 ሜትር መቆፈሩስ? ተሰምቶ እኮ አያታውቅም? በምን አቅሙ ነው ብጥስጥስ ካለ በኋዋላ ደግሞ ያን ያህል መሬት የመሰንጠቅ አቅም የኖረው?
· የፈታው የላይኛው መንፈስ።
ጠለቅ ብዬ ደግሞ ስለምን እንዲህ የአሜሪካ መንግሥት ይህን ውሳኔ አሰወሰነው፤ ወይንም የቀደመውን በራስ የመተማመን ጉዳይ ምኑ ሸረሸረው እና ድንገተኛ አቋም አስወሰደው ብዬ አሰብኩኝ።
አሜሪካ ሁለት ቡድን ነው የላከችው። በነገራችን ላይ ቦይንግ 737 ማክስ 8 ብቻ ሳይሆን የ9 ፕላንም ላይ ነው ገደብ የተጣለው። ይህ የሆነበትን ሚስጢር ደግሞ እኔ እንደ ገሃዱ ዓለም ሳይሆን እንደ መንፈሳዊ ዓለም ስለሆነ እማዬው … እንዲህ አሰብኩት።
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት /ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመጋቢት ወር ቀድሞ ታቅዷል። አሁን ክቡርነታቸው ሲመጡ እኛ የምንጠብቀው ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባባል ይደረግላቸዋል ብለን ነበር። ይህን አደጋ ሳንስብ ማለት ነው። የሆነው ግን በንጉሥ እና በቅዱሱ ላሊበላ መንፈስ የተቀደስ ነው። የመጡበት ወቅት ደግሞ በአውሮፕላን አደጋው የሀዘን ቀን ብሄራዊ እወጃ ነው። ይህ ሰው ሰራሽ ሊባል ይሆን? እንዴትስ ተገጣጠመ? አቅም አለን ይህን የምንተረጉምበት? የትስ ነው የሚገኘው ይህ ኪናዊ የመንፈስ ቅዱስ ህንፃ? ማነው የተካደው?
ይህም ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ድርብ ድሏን ይዛ ማለትም አውሮፕላኑም የራሷ ነው፤ አደጋው የደረሰውም በወሰኗ ክልል ነው፤ ሰሪው አሜሪካም አንድ ድምጽ ይዞ ብላክ ቦክሱን ማን ያንብብ በሚለው ላይ የኢትዮጵያ ዝንባሌ አውሮፓ መሆኑ ሌላው ታማራዊ ውሳኔ ነው።
ይህ ታማራዊ ውሳኔ በዚህ መልክ ነው የሚታዬው … የፈረንሳይ ቅዱሳን ቦታ ጉብኝት እና የኢትዮጵያ የሚስጢር ቋት ታማኝነት ለፈረንሳይ …። ፈረንሳይስ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ትወጣው ይሆን በታማኝነት? ሁለት ሃያላን መንግሥታትን በእዮራዊ ድሃ አገር ዕድምታ ….እንዲህ አብረው ታደሙ። እንዳለ ዜናውን አቅርቤዋለሁኝ … እንዲህ ማን ይህን ያስበዋል?
Ethiopian plane black box flown to Paris
An Ethiopian delegation led by the accident investigation bureau has flown the black boxes from the Ethiopia plane crash from Addis Ababa to Paris for investigation, Ethiopian Airlines says. Sunday's crash killed all 157 people aboard and has prompted the grounding of Boeing 737 MAX 8 jet airliners across the world.
ፈረንሳይ በዚህ የተባ ልምድ እንዳላት ቢታወቅም ይህን የቀዝቃዛው ጦርነት ልብ ቀዶ ጥገና እንድታደረግ ዕድሉን ማግኘቷ የፕሬዚዳንቱ ኢማኑኤል ማክሮን የላሊበላ ጉዞ እና ከመንፈሱ ጋር መዋህድ አሜሪካን አዲስ ውሳኔ እንድትወስን ያስገደዳት ነው ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ።
ተስፋ ነበራት አሜሪካ። ሁለት የተለያዬ ቡድን ስትልክ። ሶፍት ዌሩ ያለው እዛ ስለሆነ እድሉን አገኛለሁ ብላ አስባ ነበር። ከዛ ቢሆን ንባቡ እንደ አንቀጽ 17 የውጫሌ ውል ይሆን ነበር። በጣም ጥምር የሆኑ የእድመታ ሚስጢራት ነው ያሉበት። ወቅቱም ሱባኤም ነው። በዚህ ውሳኔ አሜሪካኖች ራሱ ጋዜጠኞች ድባባቸው ከፍቷቸዋል።
አገሮችንም በዚህ ላይ የወል አቋም ያስወሰደው የኢትዮጵያ አምላክ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያን ቀዶ ለመጠገን የተሰለፈው የርዕሰ መስተዳደር እና የጠ/ሚር የለማ መገርሳ ዲዛይንን እንዲህ አድርጎ ከሥሩ በላልቶ እንዲያው አየር ላይ ያወጠው የኢትዮጵያ አምላክ ነው።
ወደ አሜሪካ ብላክ ቦክሱ የመሄድ ውሳኔ ኢትዮጵያ ቢኖራት አሜሪካ ውሳኔውን እንድትወስን አትገደድም ነበር። ከመዳፏ ሲጋባ በራሷ መንገድ እንደሚሆን አድርጋ ግዙፉን ድርጅቷን የማዳን ተግባር ትከውንበት ነበር። ይህ የዓለም ፖለቲክ የሚመራበት ነው …
ኦደፓዎች አማራ በሰጣቸው ያልተጠበቀ ዕድል እነሱ ባለጊዜ ሆነው አማርኛ ቋንቋን ኢትዮጵያዊ መልከኑ ለማክሰል ውስጥ ለውስጥ እንደ እባብ ሲሄዱ፤ ለዚህም ደቡብን ኢላማ ሲያደርጉ፤ ቡራዩ ላይ ጋሞን ሲያስለቅሱ፤ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ፓን አፍሪካን ታሪክ ሊበርዙ ሲታታሩ፤ ኢትዮጵያን መናህሪያ መዲና አልባ አድርገው የ እነሱ ምጽዋተኛ ለማድረግ ሲታትሩ ግሎባሉን ሱባኤ ያስገባ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውሳኔ ጎን ያስቆመ የአዬር መንገዱ የዛ የሚፈሩትን የዓድዋ ድል እንሆ ተደገመባቸው።
አዲሱ የቦርድ አባል አቃቢ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ እንደሆኑም አዳምጫለሁኝ። የኢትዮጵያ አምላክ ግን አይተኛም አያንቀላፋም … የኢትዮጵያ አዬር መንገድን የባለቤትነት ጉዳይ ለመክፈል ጥናት የተጀመረበት ሁኔታም እኔ እማስበው እማዬው ከዚህ አንጻር ነው … በርታ በርታ ያሉ ኦነጎች የምክክሩም አባል ናቸው … ስለዚህ ይህም በቅጡ እንደገና ሊፈተሽ ይገባዋል። ኦነጋውያን የኢትዮጵያ ብሄሬዊነት የሚገለጽበት ማናቸውም ነገር ያናውጣቸዋል። የበታችነት ስሜቱ ይሰቅዛቸዋል።
ደሃ አገር ግን የመንፈስ ሃይል የማይበገር የፈጣሪ ድጋፍ ያላት አገር ኢትዮጵያ የአሜሪካን መንግስት ውሳኔ በቀናት የሚያስለውጥ አቅም እንሆ አገኘች። አድዋም እንዲህ ነበር። ካራማራም እንዲህ ነበር። በነገራችን ላይ የካራማራም የዓደዋም ድል አቋቋም ቅኝት እንዲህ መወድሱ የጎረበጣቸው ሃይሎች ሲረባረቡበት፤ እንሆ በማግሥቱ ደግሞ ለቀዝቃዘው ጦርነት ወሳኝ ቦታ መራጭ እና ወሳኝ ኢትዮጵያን አደረጋት።
አደጋው ውቅያኖስ ውስጥ ቢሆን? ብላክ ቦክሱ አይገኝም ነበር። አደጋው ሌላ አገር የአዬር ክልል ቢሆን ኢትዮጵያ ይህን ዕድል አታገኝም ነበር። ለዚህ ነው ሥርጉተ ሥላሴ ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር የምትለው። ቃለእዬሱስ!
ቅኝተ ኦነጉ ኦዴፓ በጫና ኢትዮጵያን ለማፍረስ፤ በቅድመ ሁኔታ ሊያስር ቢተጋም እዮር ግን ኢትዮጵያዊነት ምን ያህል አቅም እንዳለው እያሳዬው ነው። አንድ የቀረ የመለያችን ግማድ የተሸከመው እሱ ብቻ ነው።
መንፈስ ቅዱስ በአዬር መንገዳችን አድሮ እሱም ይኸው ታማራቱን ገለጠ። ወደ ግል በከፊል ለማዛውር ሲታሰብም እኔ አይሆንም ቅዱስ መንፈስ አይሰጥም ብዬ ጽፌ ነበር። ኢትዮጵያ አዬር መንገድ ነው የሚለው ሥያሜን አልቀዬረም። በዛም ነው ጥንካሬው እየጎለበተ የሚሄደው።
አሁንም የበለጠ በጥልቀት እንዲታሰብበት መግቢያ ላይ የለጠፍኩትን ደግሜ ለጥፌዋለሁኝ። ደጋግመን፤ ደጋግመን እናስብ ዘንድ። ውስጣችን እያስበረበረን ብቻ ሳይሆን ፈቅደን እያስቦረበርን ስለሆነ ተግ እንል ዘንድ ደግመን፤ ደጋግመን ሁኔታውን ከስሜታዊነት በራቀ ሁኔታ ማጥናት ይኖርብናል። ጥንቃቄ የሚደረገው ግን በሊቃናቱ ግድፈት ከወገኖቻችን ጋር የቅንጣት የመንፈስ ልዩነት እንዳይፈጥርብን ስሜታችን መጠንቀቅ አለብን። እኔተ ጢቾ ሰርቼ ስላዬሁት ህዝቡ ወተት ነውና።
„ክምታደርገው ይልቅ የምትናረው ብዙ ርቀት ይጓዛል (ይኄይስ አእምሮ)
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94303“
„የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ላሉት ክፍት ቦታዎች 350 ሠራተኞች ተመልምለው እንዲሰለጥኑና እንዲቀጠሩ የሚመለከተውን ክፍል ያዛል አሉ – ከሁነኛ ምንጮች የሰማሁት ነው፤ በሚዲያም ተገልፆ ከሆነ አላውቅም፡፡ ትዕዛዙ የደረሰው ክፍል በአጭር ጊዜ ውስጥ ምልመላውን አካሂዶ የ350 ሰዎችን ስም ዝርዝር ያቀርባል – የሰውነት ደረጃችሁን ያልሳታችሁ ጤናማ ወገኖቼ እንዳትደነግጡ እነዚያ ሰዎች ሁሉም ኦሮሞ ናቸው፡፡ የበላይ ማኔጅመንቱ ውስጥ የሰው ሽታ ያላቸው ጥቂት ርዝራዥ አሳቢ ሰዎች ኖረው መሆን አለበት “አይ፣ በዚህ የለውጥ ጊዜ ይህማ እንዴት ሊሆን ይችላል? አየር መንገዱ እኮ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው፤ ከሁሉም ዜጎች በአዲስ መልክ ምልመላው ይካሄድና ይምጣ” ተብሎ ይመለሳል፡፡ እንዲያም ሆኖ ተሻሽሎ በቀረበው ዝርዝርም ከ350ው ከ170 በላይ የሚሆኑት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የገባንበትን አረንቋ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ፡፡“ አሜን ብለናል።
እርግጥ ነው አሁን ከጃዋርውያኑ ጋር ሌላ ውጊያ አለበት የኢትዮጵያ አዬር መንገድ፤ የቦርድ ሰብሳቢው እነሱው ስለሆኑ፤ አባልነቱም በገፍ ቦታ ቦታ ተይዟል። ውስጡንም ለመመረዝ እዬተጉ ስለሆነ። ግን በጥዋቱ ምልክት እዮር ሰጥቷል። የሚገርመው ያ ከንቱ መንፈስ አዬር መንገዱንም በክብር እንዲጎበኝ ተደርጓል።
አንድ ጊዜ አሜሪካን የሚናውጽ ንፋስ ነበር፤ ያ ንፋስ ከኢትዮጵያ የመጣ ነበር። እና ይህቺ አገር የሚያሰኝ ዕድምታ ነበረው። ዛሬም የሆነው ይኸው ነው። ለዚህ ነው እኔ ሲጀመርም በሰውኛ አትዩት ያልኩት አደጋውን ያልኩት። በሰውኛ ትርጉሙም በአደጋው ዋዜማ ጠ/ሚር አብይ አህመድ አማራ ክልል ነበሩ ምሽት ላይ። ተመልሰው ፕ/ ኢማኑኤል ማክሮን የጠበቁት ደግሞ በሃዘን ድባብ ሆነው እዛው ክልል ነው።
ብአዴን ምንጊዜም ክህደት የሚፈጸምበት ድርጅት ነው። ለ11 ወራት በክህደት መጪ ሲል የባጀው ኦዴፓ ድሉን ያበሰረው በጣና ኬኛ ነበር። አሁን ደግሞ ፈጣሪ ደግሞ ይማርበት ዘንድ ይህን ተወራራሽ አምከንዮ ከእዮር ልኮለታል፤ ሹምሽሩ እኮ ከታቀደ የቆዬ ነበር። ግን ስለምን አሁን? ይህም ሌልኛ ነው።
አሁን ምዕራብ ጎንደርን በጃዋርውያኑ በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሲያስምስ የነበረው ኦዴፓ ደቡብ ላይ ላይ ደግሞ ሌላ ጦር ሰብቋል። እራሱ ብአዴን በሰጠው አቅም ነው ይህ ሁሉ አገራዊ ንደት እዬተከወነ ያለው። ሱማሌ ላይ በቅርቡ የነበረውም እንደዛ ነበር።
ደቡብ ያለውን አቅም ለመበተን ታጥቆ የተነሳበት ምክንያት ኦዴፓ ምንድን ነው ብላችሁ ስታስቡት ልክ ህወሃት ኦሮሞዎችን ከአማርኛ ቋንቋ ጋር እንዳይገናኝ 27 ዓመት የነገደበትን ሴራ አሁን ደግሞ ደቡብ ያን ይከተል ዘንድ አስደማሚ አቅሙን እና አድገቱን፤ የቱሪስት መናህሪያ ሆነ የተባለላትን አዋሳ ለመበትን እዬተጋ ነው። ተራ ምቀኝነት ተራ ቅናት።
ከዛ በላይ በፌድሬሽን ምክር ቤት ያለውን A+ አቅም ሽባ አድርጎ የደቡብን የኦሮምያን አገርነት የአሮሞን የበላይነት የኢትዮጵውያነትን ባርነት ለማሳወጅ ነው እዬተጋ የሚገኘው ኦዴፓ።
ይህ ሁሉ ሲደመር ፕ/ለማ መገርሳ እና ምህንድሳቸው በፈጣሪ ዘንድ ምን ያህል ቅያሜ መከፋት እንዳስከተል መታወቅ ይኖርበታል። የሳቸው ምህንድስና ኢትዮጵያን የሚያጠፋ ነው። ለመካካለኛው ምስራቅ አፍሪካም ጠንቅ ነው። ጃዋርውያኑ ኬኒያ ላይ ሚዲያ ሲከፍቱ በስዋህልኛ እና በሱማልኛ ለመስጠት ሁሉ አሰበው ነበር። ኦዴፓም ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ ገዳን አፍሪካዊ ኦሮማማን አፍሪካዊ አደርጋለሁ ነበር ህልሙ።
ስለሆነም ታማራቱን ተከትሎ ያለው ነገር በአደብ በጥሞና ስለ የቆምንበትን መሬት መመርመር ይገባል። ለዚህም የመንግሥትን ሚዲያ OBN በምን ዓይነት አመራር እንደሚመራ ማስተዋል ይገባል። በጀቱ የኢትዮጵውያን ግብር ነው፤ የሚሠራው ደግሞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ነው።
ቤተሰቦቼን ጨምሮ አንዳንድ ወዳጆቼ ጨክንሽባቸው ይሉኛል፤ ወትሮም ክብር የሰጣሁት ስለ ኢትዮጵያዊነት ነበር፤ አሁንም ክብር እምነሳው በኢትዮጵያዊነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከእኔ በላይ ነውና። እንሱም ሊከፉ አይገባቸውም ከስንት ሚሊዮን ህዝብ ተነጥላ ሥርጉተ ብቻ ዕጣ ነፍሷን ነበረች ለማውያን የሆነችው። ያው ቅንነትን ቢቀዱትም፤ ንጽህናን የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቢያደርጉትም።
የለማ መገርሣ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ትርክትና የመሐመድ አዴሞ ሹመት
ይህን ዜና ጎልጉል ሲሰራ ሌላ አልፃፍኩኝም እኔ። እም! ነበር ያልኩት።
· ቁጥር ሦስት።
ሌላው ፕ/ ለማ መገርሳ እንዲያስተውሉት እንዲመረምሩት መንገዳቸውን እሚያስፈልገው የኢንግሊዟ ጠ/ሚር ወ/ሮ ትሬዛ ማይ ከአውሮፓ ህብረት እንግሊዝ የመውጣት ወሳኔ ጋር ነበር ወደ ሥልጣን የመጡት።
የቀደሙት ጠ/ሚር ዴቢድ ካሜሩን ይህን የማስፈጽመበት አቅም የለኝም ብለው ነበር በፈቃዳቸው በድንገት ጠ/ሚር ቦታቸውን የለቀቁት። ትናንት የዘለገ ጉባኤ ነበር በታላቋ ብርታንያ ...
"Theresa May says MPs have provided a clear majority against leaving without a deal. The legal default in EU law remains that the UK will leave without a deal unless something else is agreed, she says, noting the responsibility on everyone in the House is now to work out what that is."
no deal brexit 321 በ278 ድምጽ።
የዚህን ታሪክም የቀደመውን ታሪክ አክሎ ሥራዬ ብለው ይመርምሩት ዘንድ ጠ/ሚር ለማ መገርሳን እጠይቃቸዋለሁኝ። ብዙ ያስተምራል። ወደ ራስ ለለመለስ ጊዜ እራሱ የሚሰጠው ሽልማት አለና።
የቀድሞ የብርቴን ጠ/ሚር ዴቢድ ካሜሩን ነበሩ፤ ወ/ሮ ትረዛ ማይ ከመምጣቸው በፊት ሰፊ ተጋድሎ አድርጋዋል። ያን ጊዜ ጠ/ሚር አንጂላ ሜርክልም ሌት እና ቀን ሰርተዋል። ግን አልሆነም ነበር። አዲሷ ጠ/ሚር ወ/ሮዋ ሁለተኛዋ ሴት ጠ/ሚር ነበሩ ለአገሪቱ። ያን ውሳኔ ለማስፈጸም ነበር።
የቀድመዎን የእንግሊዝ ወጣት ጠ/ሚር እኔ አማያቸው እሳቸውን እንደ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ እንደ አቶ ደመቀ መኮነን ነው እማያቸው። ይህን ዕድል አሳላፈው የሰጡትን ሁሉ ክዳዋል። አብሶ የአማራ ህዝብ እና መንግሥት አደራ የካዱ ናቸው ፕ/ ለማ መገርሳ። ራሳቸውን ያፈረሱ። መፍረሳቸውን እሳቸውም አቶ አዲሱ አረጋም ገልጠዋል።
በዚህ ውሳኔ ሰሞናት እንደ አሁን ለገዳዲ ለገጣፎ ገማና የመግለጫ ጋጋታ በመሰል ነበር እንግሊዝ ስታተመስ የነበረው። አንዲት ወጣት የፖለቲካ ሊሂቅ ህይወታቸውን በአደበባይ አጥተውበታል። ይህን ደግሞ እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር አመሳስለዋለሁኝ። ሰምዕቷ ወ/ሮሮ Jo Cox ይባሉ ነበር። ከሰራተኛ ማህበር ነበር የመጡት። ፖለቲከኛ እና የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ነበሩ። ያን ጊዜ ልቤ ተነክቶ ነበር።
እኔ የፍቅራዊነትን ፕሮጀክት ስሰራ ነበር በሃሳብ ደረጃ ያን ጊዜ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንም እማዬው ልክ እንደ ወ/ሮ ጆ ነው። በዛ በጭንቅ ጊዜ አውሮፓ ምጥ ላይ በነበረበት ወቅት ነበር እሳቸውም የ አውሮፓን አንድነት ለማስጠበቅ የተጉት የተነሱትም። እናም ዘረኞች በአደባባይ የገደሏቸው። ሥርዓቱን በሰመጠ ሃዘን እከታታል ነበር። ጠ/ሚር የመሆን ዕድል ሁሉ ነባራቸው እኒህ ሰማዕት።
ህዝብ ነበር ያለቀሰው ለሰማዕቷ እኔም።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሲነሳ ደግሞ ለሽ ብሎ የባጀው ግንቦት 7 መግለጫ አውጥቷል። ያው ከቲም ለማ አስፈቅዶ ነው መግለጫውን ሊወጣ የሚችለው ብዬ አስባለሁኝ። የሻሸመኔው፤ የቡራዩ፤ የአዲስ አባባው ጭፍጫፋ ስለምን ይሆን የተዘለለው? አሁን ምን አተጋው ብዬ ራሱን ግንቦት 7 ሳስብ ያው እንደ ጠ/ሚሩ ቢሮ የ እስክንድ ንቅናቄ ስላሰጋው ነው። የራሱ አካል እኮ ይህን ሁሉ ብሎ ነበር? ስለምን እገታ አልጣለም?
የግንቦት ሰባት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበበ ቦጋለ የአዲስ አበባ ህዝብን የሚያፈናቅሉትን እነ ታከለ ኡማን ልክ ናቸዉ ማለቱ በምን ስሌት ይሆን?
ግንቦት 7 በ10/03/2019 ስብሰባን 13.03.2119 የግንቦት መግለጫ የእስክንድር ነጋ ልክ እንደ ሰብዕዊ መብት ተሟጋቿ ጆ ሁሉንም ትብትብ ጥሶ መውጣት የህዝብ ተቀባይነት እና ኢትዮጵያም ሰው የማግኘቷ ሚስጥር ነው ይህን እርምጃ ያስወሰደው ግንበት 7ብዬ ነው እማስበው።
ፈጣሪ ይጠበቅህ ለድልህ ሳይሆን ለነፍስህ አስባለሁኝ!
እንደ ወ/ሮ ሰማዕት ጆ እንዳትሆን ስጋትም አለብኝ!
ቦይንግ ሥራውን ቀጥሎ በድንገት እንዲያቆም እስከ ቀጣይ ፕላኑ ያደረገ አምላክ ነው ግንቦት 7 አዲስ አቋም መግለጫ እንዲያወጣ ያደረገው። የራሱ ከኦሮሞ ወከልኩት የሚለው የግንቦት 7 ም/ሊቀመንበር እኮ አዲስ አባባን በሚመለከት አቋም ይዘዋል ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ አበበ ቦጋለ።
እሳቸውን የመገሰጽ አቅም አልነበረውም ግንቦት 7። የሆነ ሆኖ አልፎታል ግንቦት 7። እድሜ ልኩን እንዲህ ነው ካለፈ በሆዋላ ነው የሚባትተው። አቅም መጣ አቅም ወጣ በተባለ ቁጥር። ዕድሉን የጣሰው ደግሞ እንደለመደበት ኢህአዴግ የሰጠውን ሹመት የተቀበለ ዕለት ነበር።
ግዙፉን ህዝባዊ ሃላፊነት ሸብሽቦ ገና የኢህአዴግን ወጥ ፓርቲነት አንጋጦ ይጠብቃል፤ ወይንም ኩዴታ። ጠ/ሚር አብይ አህመድም ከግንቦት 7 ጋር ፍቅር ይዟቸው ሲወድቁ ሲነሱ አንቱ ብለው የተጠጉት መንፈስ ደግሞ ላጥ ወደ አለው ገደል አፋፍ ላይ አደርሷቸዋል። በፕ/ ለማ መገርሳ ቀልድ የለም ቀረቤታው የለብ ለብ ነው … ልብ የለማሻ እንዳሻ እምትኮንባት አይደለችም ...
ዶ/ር ብርሃኑ፤ ኦዲፒ እና አዴፓ (ሚኪይ አምሃራ)
February 15, 201
ግንቦት 7 ዕድለኛም አይደለም። የሚጠጋው ሁሉ ነው የሚናዳው። ለዚህ ነው እኔ ቅባዕን እሰቡ የምለው። እጅግ እሳሳለት ስለነበር ነው እንዲህ ከመሆኑ በፊት ይህን ጽፌ የነበረው። ቡድን ለማም ይህን ቢያነበው ፈቃዴ ነው። ራሱን እያዳመጠ እንዲህ ምስቅልቅሉን ራሱን ከሚያወጣ ...
ቁሞ ዬሚጠብቅ (stagnant) ዬሆነ ዬአመክንዮ ድንጋጌ – ዓለም አስተናግዳ አታውቅም! – ከሥርጉተ ሥላሴ
December 23, 2016
አንድነት ሃይል በሚባለውም በእስክንድር ንቅናቄ ምክንያት የመከፈል ዕሳቤ አለበት። ለፕ/ ብርሃኑ ነጋ የማያደግድግ ከሆነ መንፈስ እስክንድር። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ማዕቀብ በተደራጀ ሁኔታ ይጣልበታል - ከአንግዲህ። በ እኛ የተለመደው እገዳ እዛው መሬት ላይ ይገጥመዋል። እሱን የጠራ፤ ፎቶ ፓስት ያደረገ ሁሉ የፈተና ቤተኛ ነው።
አሁን ስጋቴ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከአለምንም ጠበቂ ስለሆነ የሚንቀሳቀሳው በህይወቱ አደጋ እንዳይደርስበት ነው። የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ርህራሄ የለውም። ደምስስ አስወግድ ነውና። ስለሆነም ብልህ ባለቤት ስላለችው አበክራ ትንገረው።
ሰው የሚጠቃው በሚያፍቀረው እና በሚያምነው ነውና። ከብዙ ነገር መታቀብ፤ መቆጠብ ይኖርበታል ከፈጣሪ በታች። በስተቀር የቆሞስ ስመኛው በቀለ፤ የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ተፎካካሪ፤ ተቀናቃኝ እነፈልጋለን የሚባለው ተረብ ነው።
ንጹህ ያለተበረዘ ኢትዮጵያዊነት በእሱ መንፈስ ውስጥ አያለሁኝ። አዲስ አባባም ብርቱ ሰው አግኝታለች ብዬ አስባለሁኝ። ብቻ ህይወቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሰጋኝ። ቀደም ባለው ጊዜ በጋዜጠና ተመስገን ደሳለኝ ነበር እምሰጋው አሁን ግን የበለጠ ስጋቱ ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ሆኗል። እርግጥ ፈጣሪ አለ። ለንጹሃን ፍቅር ብቻ ነው ጋርድ።
ያን ጊዜም ለወ/ሮ ጆ ህልፈት የጻፍኩት እንዲሁ ነው። ለዚህ ነው እኔ ፍቅራዊነትን እንማራው ዘንድ ካሪክለም ይቀረጽለት የምለው። ሰው በመሆን ውስጥ አይደለም የእኛ ፖለቲካ። ብዙ ነገር ነው የሚጠፋው። የሰው አፍቅሮት ለሌለው ሰው ከቁስ በታች ነውና ሰው የሚታዬው።
· መቋጫ።
በመጨረሻ የምለው ጸበል መጠመቅ ንሰኃ መግባት ያስፈልጋል። ክህደት የምድር ቋያ ነውና። መታመን ለራስ እንኳን አለመሆን በሽታ ነው። ከበሽታ ለመዳን ደግሞ የራስ ወሳኝ እርምጃ እና ውሳኔ ይጠይቃል።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ላሊበላ ላይ „ማስተዋልና ጥበብ“ ከአባቶቻችን ዘንድ እንደነበር ገልጸዋል። ምን ፈለጉ እሳቸው? ጠ/ሚሩ ቦታ እኮ ይዘዋል። ያን ሌጋሲ በቅጡ ማስኬድ ነው። አንድ ሰው ሁለት እግር አለኝ ብሎ ከሁለት ዛፍ አይወጣም። ወይ ለኦሮሞ ታላቅነት አገርነት እና ሉዕላዊነት ወይንም ለኢትዮጵያ ታላቅነት እና ሉዕላዊነት። ለምን ተረሳ ያ ሁሉ የሚሊዮን ፍቅር … ከዚህ በላይስ ምን ይሰጣቸው?
ሌላም ጋዜጣዊ መግለጫ ከፕ/ ኢማኑኤል ማክሮን ጋራ በጋራ ሰጥተው ነበር። "ህገወጥነትን ለመከላከል አቅቶን አይደለም የታገስነው። በጭካኔ ብዛት ለተበሳጩ ወጣቶች ብስጭታቸው እንዲወጣላቸው ለመታገስ ነው" ብለዋል።
እና ይህ ዕድል ስለምን መስከረም ላይ ለአዲስ አባባ ወጣቶች አልዋለም? እሁድ እለትስ አስረው አልነበረንም? ለዛውም ዓለም መከራ ውስጥ ታድማ?!
ለነገሩ የትኛው ጋዜጠኛ አለና ይሞግታቸው? ብክትና በሲሶና በእርቦ ዜግነት ህዝብ እዬተከተከ ራሱ ሞራሉም የለም ይህን ጥያቄ ለመመለስ። የደህዴን አመራሮች እኮ ተደብድባዋል በስብሰባ አዳራሽ። የሦስት ቀን የሥራ አድማም ድርጅታቸው ኦዴፓ የሚተባበረው ቡድን እዬፈጸመ ብቻ ሳይሆን ንቅንቅ ለሚል እገድላለሁ ብሎ ዝቷል።
አቅም ከኖረ ስለምን ይህ ይሆናል? አቅም ቢኖር ትግራይ ላይ ስላሉትስ ተጠርጣሪዎች? ባዶ ስድስት ስላሉት ንጹሃንስ? ለነገሩ በትናንቱ የአቶ ጌታቸው እረዳ ከጋዜጠኛ ስሜነህ ባይፈርስ የመቀሌው ቃለ ምልልስ አዲስ አባባ ወይንም „ፊንፊኔ“ ሲሉ አዳመጥኩኝ … አብሮ የታደመ መከራ እንዳለ ውልብልቢቱን አዳምጫለሁኝ ለብአዴን መጪው ጊዜ ጥላሽት ነው … ክህደቱ በፈርጁ በፈርጁ ሲለካ … የ እኔ የሚለው አዴፓ ሥሙን አስወርሶ ጉዳዩን ደግሞ ክህወሃት ጋር? ጊዜ ይመልሰው ...
እንደ እኔ እንዲያውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ ቢያደርጉ ይሻላቸዋል። … የሚታዘዝም የሚመራም የለም። የሠራዊት ጌታ ነው እዬጠበቀ ያለው አገርን። በዛ ባባደ በከነፈ በስሜት በሚጋለብ ደመነፍስ የጃዋርውያን መንፈስ ነው ኢትዮጵያ እዬተገመሰች ያለችው?
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ