የእቴጌ #ብሪቱ ሰርግ እና #ቅልቅል ወይንስ #ኑዛዜ? ምጣኔ ሃብታዊ ተህድሶው እና ሥርዓቱ። • #ብሄራዊ ስሜት አድራሻው የት ይሆን? ሚናውስ? #ኢትዮጵያዊነት መርህስ #መሪስ ነውን???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
በኢትዮጵያ ገብያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በመሆን ላይ መገኘቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንታት ሙያዊ ትንታኔ እዬሰጡ ነው። በተጨማሪም ገዢው የኢትዮጵያ የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥትም የራሱን ባለሙያወች አሰልፎ ማብራሪያ እያሰጠበት ነው። በኢትዮጵያ ገለልተኛ ሚዲያ ስለለ በኢኮኖሚ ሙያ ለሌላቸው ዜጎች ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ብዬ አስባለሁ። ሁሉም በራሱ መሻት ዙሪያ ስለሚሠራ።
የመነሻ የሆነ ሃሳብ ያላቸውም ቢሆን የኢኮኖሚ ፍልስፍናው የማይደፈር ተርም ስለሆነ ሜቶሎጂው ከባድም ስለሆነ ለአማተር ፖሊሲውን የመረዳት የአቅም ስስነት ሊኖር ይችላል። ከሁሉ የሚከፋው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሁሉም ዓይነት እርምጃ #በደራሽ ዜና ስለሚያውጁ የበቃ እንኳን ባይሆን የነቃ የህሊና #ጉዝጓዝ አልቦሽነቱ ሽብር ነዢ የመሆን አቅሙ የዚያኑ ያህል ከባድ ነው። ሌላው ቀርቶ ለካድሬወቻቸው እንኳን በቂ ግንዛቤ፦ መረጃ በአግባቡ ስለማይሰጡ የተበጣጠሰ ግንፍል #ስሜት #ገዢ ሆኖ ይታያል። በግራ ቀኝ ያለውን ገለፃ አቅርቦ ህዝብ ህሊናው እንዲዳኜው ከማመቻቸት የመንግሥት ልሳንን ብቻ የደገፋ እሳቤወችን ይለፍ ሲሰጡ አስተውያለሁ። ኢኮኖሚ የህልውና #ህሊና ነው።
#በዘባጣ ሥርዓት የፈለገ ዓይነት ፖሊሲ ሥራ ላይ ለመዋል ዳጥ እና ምጥ ነው። ይህም ሆኖ ህዝብ ችግሩን ተረድቶ የተረጋጋ ተሳትፎ ያደርግ ዘንድ የግንዛቤ አድማሱ የሚያሰፋ መስኮች እገዳ ሊጣልባቸው አይገባም። ችግሩን ለይቶ አቅጣጫ ማሳዬት ወገንተኛ ያልሆኑ ሚዲያወች ሚና ነው። ኢኮኖሚ ኦኮ #ፋክት ነው።1+1= 2 ነው።
ኢኮኖሚ ፕሮፖጋንዳ መራሽ ሊሆን አይችልም። ቢፈለግም አይቻልም። ዲስፕሊኑ ለአማተር ካድሬወች አይሆንም። ስንዴ ለውጭ ያቀረበች፤ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ከኃያላን ተርታ ብቻ ሳይሆን #ጥገኝነቷ እንደሚቆም ተነግሯል። ፕሮፖጋንዳ ህልውናን ቢያሻሽል ዛሬ ካለበት ደረጃ ባልተደረሰ። ለወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው፥ የምሳ ጊዜያቸውን ተደብቀው የሚያሳልፋ ወገኖች ባልኖርን። ኢኮኖሚ #ፋንታዚም፦ የእርጎ ባህርም አይደለም። ለነገሩ የእኛ ነገር እንደ ኢኮኖሚው አስተሳሰቡም ያልተመጣጠነ ዕድገት ላይ ነው።
እንዲህ ዓይነት እርምጃ የሁሉም ጓዳ የሚፈታትሽ ጉዳይ የኢኮኖሚ ባለሙያወችን አገር ውስጥም ውጪ ያሉ፤ ኢኮኖሚ ተኮር ሚዲያወችን ለምሳሌ አገር ውስጥ #መሪ ሚዲያ እና መሰሉ፤ የባንክ እና የኢንሹራንስ ባለሙያወች፤ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ከዝቀተኛው እስከ ከፍተኛው ደረጃ የሚገኙ ባለሃብቶች፤ ዕጩ ወደ ንግዱ ሊሠማሩ ሂደት ላይ የሚገኙ ዜጎችን፤ ህዝቡን በሙሉ በዬደረጃው ሰብስቦ ማነጋገር፤ ማወያዬት፤ #አደጋውን እና #ትሩፋቱን ማገናዘብ ይችል ዘንድ #መድፈር ይጠይቅ ነበር።
ኢትዮጵያ ከዚህ አጣብቂኝ ውስጥም እንደገባች በግልጽ መንገር ይገባል። ትልቁ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ስውር ናቸው። ስውርነታቸውንየምናነግሰው፤፦የምንከበክበውም እኛው ነን። በዚህ ሂደት ትውልድም መኖርም ሲገበሩ ኑረዋል። በአደጋ ደራሽ ተቋም የሌላት አገር።
የሆነ ሆኖ ከአንድ ዓመት ደጅ ጥናት በኋላ ብድሩ ተገኝቷል። ቅድመ ሁኔታወች በአበዳሪወች ተቋማት ሲፈፀም የኢትዮጵያ መንግሥትም ያን ፈቅዶ ገብያው እንዲወስን ፈቅዷል። አበዳሪወች የኢትዮጵያን መንግሥት ሞጋቾች ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ የተቀበለ አይመስልም። አመክንዮው ከባሰው ችግር የተሻለውን ችግር የመረጡ ይመስላል። የ2024 የበጀት ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ለቀጣዩ ዘመን በጀት ለማግኜትም የታሰበም ይሆናል።
የዚህ ጠቀሜታ እና ጉዳቱን በሚመለከት አገር ቤት #የእኛ፤ #ሸገር 102.1 እና #አንድአፍታ ሚዲያወች፦ ውጪ አገር #አንከር፤ #ህብር እና #ኢኤምኤስ ከኢኮኖሚ ባለሙያወች ጋር ያደረጉትን ውይይትሁሉንም አዳመጥኩኝ። አንዳንዱን ያልገባኝን መለስ እያደረኩ ደገምኩት። ሁለት ጉልህ የተራራቁ ዕሳቤወችን ተገንዝቤያለሁ።
በተጨማሪም ሁለቱን ወደ መሃል የሚያመጣም ብቻ ሳይሆን በአቀራረቡም ቀለል ያለ የአቶ ክቡር ገናንም አዳመጥኩኝ እሳቸው ሁለት ሚዲያ በተመሳሳይ አጀንዳ ላይ ነው ማብራሪያ የሰጡት። ሁሎችም ሚዲያወች ይህን መሰል ውይይት ለሚዲያቸው መንፈስ ቀረብ ያሉ አመክንዮወችን ይዘው ተጠያቂወች ያቀረቡትን ዕይታቸውን አጋርተዋል። የኤኮኖሚ ሊቃውንታት ሙግት ግን ከጠያቂወቻቸው አልገጠማቸውም። ምክንያቱም በኢትዮጵያ አንድ ጋዜጠኛ ከሀ እስከ ፐ ባሉ የመኖር ክስተቶች ተንታኝም ጠያቂም ስለሆነ።
ውጪ አገር እንዲህ አይደለም። የፕሮሚ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ፤ የህግ፤ የፕሬስ ህግ፤ የጤና፤ የፍልስፍና፤ የፖለቲካ ሌላው ቀርቶ የማህበራዊ ሚዲያ ወዘተ በዘርፋ ስፔሻላይዝድ አድርገው ጋዜጠኝነቱን አክለው ተምረውት ይሠሩበታል። ስለሆነም ጠያቂውም ተጠያቂውም በሚያውቁት #የሳይንስ እና #የፍልስፍና ዕውቀት በተመጣጣኝ ዕውቀት ላይ ስለሚነሱ አድማጩ በእጅጉ ተጠቃሚ ይሆናል። የረጋ የሰከነ ግንዛቤም ለትውልድ መሠረት ይይዛል።
ተጠያቂው ለምን? እንዴት? መቼ? የት? ወደዬት የሚለውን ጥያቄም ከሙያ አንፃር ያቀርባል፦ ተጠያቂውም በድፍረት መልሱን ይሰጣል። ሌላ ቀረብን የምለው በገለልተኛ ሚዲያ ሁሎችንም በአንድ መድረክ አቅርቦ እርስ በርሳቸው ማሟገት ይቻል ነበር።
ተስፋ አፍላቂ የሚለውን /// ሞት ጠሪ የሚሉትንም እንዲሁም አቀራራቢ ሃሳብ ያለቸውንም በወል መድረክ ወላዊ የህሊናዊ መሰናዶ የሚያሟላ ሁነት መፍጠር ይቻል ነበር። ሊቃውንቱን የሚጫኑ መጠይቆችም ላይመጡ ይችሉ ነበር። ሊቃውንቱም ጠያቂውን ሊጫኑ የሚችሉበት መንገድ አይከፈትም ነበር። በተበተነ መስመር የተበተነ ፍላጎት። ኢትዮጵያን ማዕከል ያላደረገም።
ህዝቡን በሚመለከት ከተመቸው ይቀጥላል። መኖሩን ያለበት እሱ እራሱ ነው። ካልተመቸው ያምፃል። ቢያምጽ ጉዞውን ሊመራ የሚችል አቅም ያለው ተቋም አለ ወይ ሲባል የምናዬው ነው።
#የግል ዕይታ እና መጠይቆች።
1) ትልቁ አንኳር ጉዳይ ደግሞ ይህን አዲስ ጉዞ ለመምራት ብሄራዊ ስሜት ወሳኝ ጉዳይ ነው። ግሪኮች የገጠማቸውን ፈተና የተሻገሩት በብሄራዊ ስሜት ድልዳል ነው።
2) ቢሮክራሲው ዞግ ዘለል እንዲሆን ምን እርምጃ ተወስዶበታል?
3) ከሴክተሩ ጋር ቅርርብ ያላቸው አካላት በግዴታቸው እና በመብታቸው ዙሪያ ምን ኦሬንቴሽን ተሰጣቸው? ምንስ የቁጥጥር ሲስተም ተዘርግቷል።
4) ቀለጤወቹ እና ደልቃቆቹ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፕሮጀክቶችስ ማዕቀብ ይጣልባቸዋልን? ወይንስ እንደተሞላቀቁ ሊቀጥሉ ይሆን?
5) ይህ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ ለውጭ ኢንቨስተሮች ምን ደልዳላ የሰላም መሰናዶ አሟልቷል? ለመሆኑ በትግራይ፤ በአማራ፤፦በኦሮምያ ያሉ የገዘፋ የጦርነት ውጤቶች እና ሂደቶችን ችግር ለመፍታት ምን ዓይነት የስልት እና የስትራቴጂ ውህድ ውሳኔ አለ?
6) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ከውጭ ካሉ ሞጋቾቻቸው፤ ከአገር ውስጥ ካሉ የሳቸውን ቀለጤ ፕሮጀክቶች ከሚንቆላብሱላቸው የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንታት ጋር የዙም ውይይት ለማድረግ ምን መሰናዶ አላቸው? የወጣላቸው ፈሪ ናቸው እኮ። ከሁሉ የሚገርመኝ ተመሪም፤ ተማሪም ለመሆን ያለመፍቀዳቸው መራራ ጉዳይ። መማር እኮ ደንበር የለውም። ከአንድ ከብት ከሚጠብቅ ታዳጊም ለመማር መፍቀድ ብልህነት ነው። የሚቀስሙት ዕውቀት ከኖረም የራሳቸው አድርገው እንጂ እከሌ ከሚባል አገኜሁት አይደፍሯትም።
7) ላልታሰቡ ድንገተኛ ሁኔታወች ከዕቅድ ውጭ የሆኑ ክስተቶች ቢፈጠሩ ከፕላን ውጪ እንይሆን ላልታሰቡ ወጪወች ምን ታስቧል? እኔ የምኖርበት ከተማ ቪንተርቱር ይባላል።
የተፈጥሮ የአዬር መዛባትን ቀድሞ ለመመከት ከእያንዳንዱ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ሳይሆን በፈቃድ የሚወሰን ወርቅ፤ ብር፤ ብሮንዝ የሚል ደብዳቤወች ተላኩ። ከመብራት እና ከውኃ ከመደበኛው ወጪ የሚጨመር ታሪፍ ማለት ነው።
ያ ታሪፍ በመራጩ ፈቃድ ልክ ይከፈላል። ወርቅ ከሆነ የወርቅ ብር ከሆነ የብር። ከዛ በፊት ከዓመት በፊት ገብያቸው ላነሰ የተወሰነ ድጎማ ተደርጓል። ይህ ማለት መንግሥትም ነዋሪውም ሳይጎዳዱ ተደጋግፈው መጪውን አደጋ የመቋቋም ብቻ ሳይሆን አደጋን የመቅደም ብልህነት ተከናወነ። ለምን? የማያረገርግ ሲስተም ስለተዘረጋ። የኮረናጦርነት ዓለምን ሲንጥ፤ የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት ተጽዕኖንም ሥርአቱ ስኩን ስለሆነ በተለመደው ሁኔታ ፀጥ ብሎ ቀጠለ። ሳይረገርግ ኢኮኖሚው የሥነ ልቦና ህሙም ሳይሆን። ለምን? ሥርዓት ስለተዘረጋ።
8) ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ምንጩ ሲስተም ይመስለኛል። ሁሉም ችግር ከጠሚር አብይ አህመድ በላይ ነው። ከጨከነው ችግር ለስላሳው ጭካኔ ይሻላል ተብሎ እንደተገባበት ባለሙያወቹ ሲገልፁ አዳምጫለሁ። ቢያንስ ጠሚር አብይ አህመድ አሊ ፌካዊ ያልሆነ ቲም አደራጅተው ይህን ፈተና ይሻገሩታል ወይንስ ማስቲካ እያደሉ ይዘልቁታል? ቀልድ እና ቁምነገር ተቀላቅሎባቸዋል። በዚህ ማጥ ውስጥ ተቀምጠው እሳቸው የሳይክል ሽርሽርቸውን እንደ ልዩ ስኬት የ120 ሚሊዮን ህዝብ ድሎት አድርገው ስለሚገምቱት። አገር መምራት እና እራስን ማዝናናት ለዬቅል ስለሆኑ።
9) ግብረ ሰላሙ፤ የሆቴል ሽርሽሩ እና ወጪው፤ ክልሎች እንኳን ተቀምጠው እንዳይሰሩ ሞናትነስ የሆነው የወል ጉዞ እና ወጪውስ ይታቀባል? ይገታል? እርምጃ ይወሰድበታልን?
10) ነገስ ዓለም እንደ ኮቢድ ዓይነት፤ እንደ መካከለኛው ምስራቅ እና አውሮፓዊ ጦርነት ቢገጥማት አፋፍ ላይ ያለችው ኢትዮጵያ ዕጣዋ ምን ይሆናል?
11) ለህወሃት ዲል ያለ እርዳታ ተደርጎለታል። ዕዳው ተከፍሎ ሳይጠናቀቅ በጠሚ አብይ አህመድ መንግሥት እና በህወሃት ጦርነት፤ በአማራ ክልል እና በፌድራሉ ጦርነት፥ ተፈቅዶ ኦሮምያ ላይ የነደዱት መንግሥት ሰራሽ ቀውሶች እና ውድመቶችን ለማስቆም ምን የህሊና ብቃትስ? መሰናዶ አለ? ምንስ ዋስትና አለ ለአዳዲስ አትራፊ ፕሮጀክቶች?
12) ይህ በስንት ጣር፦ በስንት ደጅ ጥናት የተገኜ ብድር እናም በብዙ ግዴታወች በታጠረ ክስተት የተገኜ ዕዳ ወለዱንም ዋንኛ ዕዳውንም ለትውልድ እንዳይሻገር አትራፊ በሆኑ፤ ህዘበ - ጠቀም በሆኑ ፕሮጀክት ላይ ለማዋል ጥናት ተካሂዷልን? ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው ህዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በሚመለከትስ፦ በውጭ ምንዛሬ ምክንያት ተጀምረው የተቋረጡትን ጨምሮ ሁሉን ያካተተ የመለዬት ተግባር ቀድሞ ተከናውኗልን?
13) የሥራ ባህልን በማሻሻል እረገድስ ምን ታስቧል? አንድ ሰው ሁለት ሰዓት ብቻ ይበቃኛል ብሎ ለአንድ ጉዳይ ከቢሮው ሲወጣ የእሱ የሥራ መስክ ይስተጓጎላል፤ ገንዘብ ነው ያ። ከሄደበት ቦታስ በ2 ሰዓት ያለው ሳምንት ቢያመላልሰው? ተጨማሪ ጉቦ ቢጠዬቅበት ዬዙሪያ ገባው ብክነት እንደምን ማመጣጠን ይቻላል? አሁን ላለው የአደጋ ጊዜ ሁኔታ የሚመጥን የሥራ ዲስፕሊን ምን ያህል ድርጁ ነው? ለመሆኑ ታስቦበታልን?
14) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ይህን ዕዳ በሚመለከት አፈፃፀሙን በሚመለከት ከባለሙያወች የሚሰጣቸውን ምክር ለማድመጥ ትልቅ ጆሮ ከሚገዛበት ገብያስ ጎራ ብለዋልን???
15) ይህ ዕዳ ከቅንጦት፤ ከቅልጣን ፖለቲካ፤ ከሞድ ትዕይንት ወጥቶ ትርፍ ተኮር ፕሮጀክቶች ላይ ተመስጦስ፦ ጥሞናስ ይኖራዋል ወይ?
16) ከደራሽ ኢንፍሌሽን ለመዳንስ ምን ታስቧል? እያንዳንዷ ሰከንድ የከፍ እና ዝቅ ትዕይንት ባለቤት ናት። ከፍ እና ዝቅ ብቻ ሳይሆን የተስፈነጠረ ከቁጥጥር የወጣ ገጠመኝም ሊኖር ይችላል? አቤቱ ብልጽግና ይህን ለመምራት ዲስፕሊኑን ይቋቋመው ይሆን?
17) የለውጥ ፈላጊው ወገን የሥርዓት ለውጥ ይሻል፤ የህዝብ እምቢተኝነት ይነሳ ዘንድም ይታትራል፦ የሥርዓቱ ዕድሜ ማጠር ብቻ ለኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሄ ያስገኛል ወይ? በዬጓዳው፤ በዬህሊናው ያለውን መሻት የሚያሳካ የአካታችነት መስመር አለ ወይ? እኔ አይቼ አላውቅም። ተስፋዬ ሩቅ የሚሆነውም ለዚህ ነው። ከ8 ዓመት በፊት የነበረው አግላይ ሥነ - ልቦና ዛሬ ደርጅቶ እና ተጠናክሮ ነው እማዬው።
የተወሰኑ ዜጎች ምርጦች ሌሎች ደግሞ ትርፎች። የእኔ ዕምነት የዜግነት እርቦ እና ሲሶ የለም። እንዲያውም አህቲ የነበረው መንፈስ የግል ጎጄውን ቀላልሶ በሚያስማማው ብቻ እዬተገናኛ የሚያሻውን በአሻው ሚዲያ፤ ወይንም ስብስብ ጋር ማህበር መስርቶ በዛ ሲመክር፤ ሲዘክር ነው የማስተውለው። ለውጥ ከሩቅ ሳይሆን ከቅርብ ነው ሊጀምር የሚገባው። ከሁሉም በራስ ላይ የሚወሰድ እርምጃ ቅንነት መር ሲሆን።
18) ጠቅላይ ሚር አብይ ሌግዠሪ ህይወት ህልመኛ ናቸው። ሌግዠሪ ህይወታቸው እንዳይሳጣም የክልል መስተዳድሮች፤ ከንተባዋን ጨምሮ ሪዞልት ነው ውሎ አዳራቸው። ጥበቃው፤ ፕሮቶኮሉ፤ መስተንግዶው፤ መጓጓዣው የዘመነ ነው። ይህ የጊዜ፤ የገንዘብ፤ የመንፈስ ብክነትን ለማረም ምን ፈቃደኝነት አለ? ኃላፊነቱ ተጠያቂነቱ ጓጉሎ እና ተስተጓጉሎ ስለምመለከት። የብክነቱ ጣሪያ ተመን የለውም። ይህ የሚሆነው በዬጊዜው ነው።
19) ከጠቅላይ ሚሩ ጀምሮ የክልል መስተዳድሮች፤ ከንቲባዋ ወንበራቸውን ለጨረታ ወይንስ ለሥራ ያውሉት ይሆን። ብሪት ሰርግ ላይ ትሁን ኑዛዜ ላይ ቀጣይ ወራት ይነግሩናል። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና።
#እርገት ይሁን አይደል???
1) እያንዳንዱ ሠራተኛ ጡረታ ያጠራቅማል። ያም ስጋት እንዳዣበበት አዳመጥኩኝ። የማይሰማ ነገር የለም በጣም በርብር የሆነ ሥርዓት ነው ማለት ልቻል ይሆን??? ገርሞኛል።
2) ዛሬ በአውቶብስ ጉዞ እዬራቀ ነው። የቻለ በአውሮፕላን ነው። እሱም የታሪፍ ጭማሪ ለቀበጡ የጠሚር አብይ ልዩ ፕሮጀክት ታስቧል። ደጉ፤ ቻዩ፤ ሩህሩሁ፤ አዛኙ፤ ቅኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መከራው እንደምን ይዘልቁ ይሆን???? ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው። እንደ እኔ ዕይታ ግን ዕንቁ ፖሊሲ ሥርዓት ካልደገፈው ተንሳፋፊ ነው። ለኢትዮጵያ የሥርዓት ብቻ ሳይሆን የአሰተሳሰብ ለውጥ + ቅንነት በእጅጉ ያስፈልጋታል።
የእኔ ክብሮች ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
#ሊንኮቹ እኒህ ናቸው። ዳኝነቱን አዘግይቶ መድረኩንም ጆሮውንም ለኤኮኖሚ ሳይንቲስቶቻችን መለገሱ የተገባ ነው ባይ ነኝ። ለመማር መፍቀድ ከግብታዊነት ይታደጋል። ዕውቀትም አይጠገቤ ነው።
«የተወሰነው የፖሊሲ እርምጃ በጣም የዘገየ ቢሆንም መድሀኒት እንጂ መርዶ አይደለም “ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ክፍል 1 ምጣኔ ኃብት @ShegerFM1021Radio
https://www.youtube.com/watch?v=bZ4EesMb78E&t=916s
“የማውቀውን እውነት እናገራለሁ ዋጋም አስከፍሎኛል” Ermias Amelga Interview Part 2 ምጣኔ ኃብት
EMS Eletawi አዲሱ የኢኮኖሚ ማሻሻያና አንደምታው Mon 29 July 2024
“አብዮት ሊቀጣጠል ይችላል” | “መኖር የተከለከለ ሕዝብ አለ”| የተለቀቀው ዶላር እና ጦርነቱ ! | Ethiopia
Anchor Media «ፖሊሲው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሞት አዋጅ ነው። የበለጠ መከራ ከፊቱ እየመጣ ነው።»
"ህዝቡ ይሄንን ሁኔታ ቀበቶውን ጠበቅ አድርጎ ያሳልፈው!"አቶ ክቡር ገና | Kibur Gena| Dollar | Macro Economy
Yegna Tv የኛ ቲቪ
Anchor Media ''የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው ራስን በራስ ማጥፋት ማለት ነው። የህዝብ አመጽ ሊቀሰቀስ ይችላል'' ዶ/ር ዮናስ ብሩ
«የቀድሞ የዓለም ባንክ አማካሪ በትግሉና ሕዝቡን በጎዳው ውሳኔ» | Hiber Radio with Dr Akelog July 29,2024
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/08/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ