ኦነጋውያን ማቆላመጡን ማብቃት ይገባል።

ግርዝዝ።
„ይህ ትዕቢት ምን ጠቀመን፤ ከትዕቢት ጋር ያለ
የኦሪትስ ባለጠግነት ምን አመጣልን።“
መጽሐፈ ጥበብ ፭ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 29.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

በጠ/ሚር አብይ አህመድ የ100 ቀናት ክንውኖች ውስጥ ተካቶ ከነበረው የጉብኝት ቀጠና ወስጥ አንዱ ደንቢ ዶሎ ነበር። ደንቢ ዶሎ ላይ የነበረው ህዝባዊ ስብሰባ የኩርፊያ፤ የቁጣ የውጡል ነበርለምን መጣችሁብን ዓይነት ነበር። የሚገርመው እና የሚደንቅው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ ኢህአዴግ የሚያስጨፈረውም ከዛ ሰፈር ትውር አላለም ነበር።

በቦታው የተገኙት ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ነበሩ። ታዳሚዎች ግን ውስጣቸው ቅጥል እያለ ነበር ንግግሩን የተከታተሉት። ያቀረቡት ጥያቄ ሁሉ ወልደ ግራ ነበር። ፊታቸውን እንደ ኮሶ ኮስኩሰው ነበር አንግዶችን የተቀበሏቸው። ፊታቸውን እንደኮሰኮሱም ነበር የሸኟቸው። 

እና እኔ እህታችሁ ከልብ ስለሆነ ሁሉንም ነገር የእኔ ብዬ የምከታተለው ደንቢሻ የምትፈልገው የደንቢን ንጉሥ ብቻ ነው። እዛ ሰፈር ዶር መርራም አቶ ጃዋርም ቦታ የላቸውም ብዬ በተከታታይ ስቸከችክ ባጀሁኝ።

ይህም ብቻ ሳይሆን ግንባር ስለሚባለው ፍልስፍናም የጠብታ ያህል የሚያውቁት ስለሌለ እባካችሁ እዛ አካባቢ ትንሽ የሚላስ የሚቀመስ የህሊና ተግባር ፈጽሙ ብዬ ኦህዴዶችን ተማጸንኩኝ።

እርግጥ ነው የለማ ቡድን ሥራ በዝቶበታል። በዛ ላይ ልብ ለልብ የመሆንም አዳጋ አለበት። በተጨማሪም ጥድፊያ ላይም ነው የልቡን ለማድርስ ባገኘው የሥልጣን የበላይነት አጋጣሚ ለማስፈጸም። በዚህ 6 ወር ውሰጥ የሦስት አራት አመት ክንውኖችን ከውኗል።

በሌላ በኩል ለውጡ ገና ሳይጠናም ነበር ዶር መርራ ጉዲና እና አቶ በቀለ ገርባ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰው ሄደው ቀለበት ውስጥ ኦህዴድን /ኦዴፓን ለማስገባት ሙከራ አድርገው የነበሩት። በዛም የወለጋ አካባቢ መዋቅራቸው አደጋ ውስጥ ነበር። መንፈስም ተበትኗል። እኔም ከህግ በላይ የሆኑትን የኦፌኮን አመራሮች የወሰዱት እርምጃ ትክክል አይደለም ብዬ ጽፌ ነበር።

አሁን ደንቢሻ ኦነግ ትጥቅ መፍታት የለበትም ብላ በይፋ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥታለች። ዛሬ ደግሞ አቶ ለማ መገርሳ የልጆቻቸው ነገር አሳስቧቸው አንድ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከኢትዮጵያ ሪጂስተር አሁን አነበብኩኝ።

አቶ ዳውድ ኢብሳ ሠራዊቴ ሚሉት አገር ውስጥ ያለውን ነዋሪ ነው። የሚገርመው ለውጡ የቄሮ እና የእኛ ብቻ ነውም ባይ ናቸው። እውነት 
ለመናገር የኦሮሞ ፕሮቴስት እኮ ቄሮ እኮ ግንጫ እና እዛው አንቦ አካባቢ ሸዋ ላይ እኮ ነው የነበረው። ሌላው ቀርቶ እንኳስ አርሲ ባሌ ከፋ ወለጋ ሊሄድ ቀርቶ ገብሬ ጉራቻን እንኳን አልጨመረም። ይህ ሃቅ ነው። አርሲም ባሌም ሀረርጌም አልተሳተፉበትም። 

እንዲያውም አንድ ጊዜ አቶ ጃዋር መሃመድ ሲጠዬቅ እነዚህ አካባቢዎች ይቆዩ ብለን ብሎ ነበር። እኔ ደግሞ አቅም ስላነሳችሁ ነው እንጂ የተጋድሎ ድንበር የለውም ብዬ ተችቼም ጽፌም ነበር።

የሆነ ሆኖ ደንቢ ደሎ ቱክ ሳትል ነበር የባጀቸው። በሌላ በኩል ደግሞ ብቻውንም የአንቦ እና አካባቢው የቄሮ ትግል አይደለም ለውጡን ያመጣው። ምክንያታዊ የነበረው የአማራ የህልውና የማንነት ገድለኛም ተጋድሎም እንጂ። የአማራው በጎበዝ አለቃም የታገዘም ነበር። ሲሰነብት እዬተረሳ ካልሆነ። እንዲያውም ያን ጊዜ የአንቦ የኦሮሞ ፕሮቴስት ታጋዮች ባዶ እጃቸውን ተጎዱ ነበር የእኛ ጭንቀት።

ይህም ብቻ አይደለም ኢህአዴግ ውስጥ ያሉ ኦህዴድ እና ብአዴን ድምጹን ለማድመጥ መድፈራቸው ነው ለዚህም የተደረሰው። አቶ ዳውድ ኢብሳማ ስንት ዓመት ሙሉ አንዲት መንደር መቆጣጠር አልቻሉም። ይህ ደግሞ እኛ ብቻ ሳንሆን  የዓለም ሚዲያ ሁሉ ያውቀዋል። ትምክህታቸው ግን እንደ ታላቁ እስክንድርያ ያክል ነው።
  
የሆነ ሆኖ ደንቢ ደሎ የነበረው ኦዲዬንስ ቁጡ ነበር በዛ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሰበሰቡት ህዝባዊ ጉባኤ ላይ። ስለሆነም ነበር ለዛ ህዝብ የተገባውን አያያዝ እና የህሊና መሰናዶ እንዲደረግለት ነበር እኔ አበክሬ ሳስገነዝብ የባጀሁት። 

አፋር ላይም ይህንኑ ተናግሬያለሁ። አፋር ላይ የነበረው ጉባኤ የወያኔ ሃርነት ጠረን የነበረው ነው እና በጊዜ አንድ ይባል ብዬ 7 ክፍሎችን ርትህ በሚል 
ጽፌ ነበር። አድማጭ ከዬት ይገኝ?

የደንቢ ደሎ ልቅ መለቀቀ መከራው ብዙ ነው። በወቅቱ እንደዛ የመሰለ 
አቀባበል ሲያደርጉ በተለዬ ሁኔታ ህሊናቸው በመደበኛ ሊገራ ይገባ ነበር። 
ያ አልሆነም። ይህ ጉዳይ ምን አልባት ኦሮሞዊ ብቻ ተደርጎ ሊታይ 
ይችልም ይሆናል። ሃይማኖታዊ መስመርንም ሊከተል ይችላል። አቅጣጫው በውል ያልተወቀ ነው። ሰው እዬተሸነፈ ሲመጣ፤ ሰው ተስፋ እያጣ ሲመጣ የመጨረሻውን እርምጃ ነው የሚወስደውየመጨረሻው እርምጃ ደግሞ ከሰው እሳቤ መውጣት ነው። ችግሩ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድም ሊሆን ይችላል። መጠኑም እያደር እዬጎለበተ ሄጅ ነው። በዛ ላይ ቤንሻንጉል እና ትግራይም አለ። ብሄር እና ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች እንደ ቤንዚን ተቀጣጣዮች ናቸው - በቀላሉ።፡ 

የሚገርመው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አቶ ዳውድ ኢብሳ የሚያሳስቡት ህዝቡን እንዳትጎዱት የሚል ነው። ሥርዓት እዬተዳፈሩ። ይህ መቼም ሆኖ የማያውቅ ጉዳይ ነው። አዲስ አባባ ላይ መብታቸውን ያቀረቡ ንጹሃን እኮ በጥይት ሩማታ ነው የተጨፈጨፉት። ሺዎችም ታስረዋል ለእነሱ ክብር ልዕልና ሲባል። ዘመኑም የእነሱ ስለሆነ።

አቶ ዳውድ ኢብሳ አበክረው የሚገልጡት እኛ አሁን እንዲህ ማሽሞንሞኑ መቆላመጡ ሙሽርነቱ ይቀጥልልን እኛ የልባችን ደርሶ መውጫ መግቢያ እስክናሳጣችሁ ጊዜ ነው የሚሉት፤ እና አቤቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬውስ ምን ይለን ይሆን?

ገና በጥዋቱ ነበር እኔ የደንቢደሎ ነገር አላመረኝም ብዬ ስናገር የባጀሁት። ግን ማን ይሰማል። አሁንም እንደ ትናንቱ የደንቢ እናት ታንባ፤ የሰው ብርንዶ ቤትም ትክፈት። እኔ እማዝነው ለድምጽ አልባዎቹ እናቶች ብቻ ነው። 
  • ·       መነሻ።

ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ ስህተት ነው/ ለማ
October 29, 2018
አቶ ለማ መገርሳም ጭላጭ የኢትዮያዊነት ብናኝ ጠረን የሌለበትን የሚዲያቸው ባለሙሉ ባለስልጣን አውራ ካደረጉ፤ አክቲቢስቶቻቸውን ክብር እና ሞገስ ካቀዳጁ በኋዋላ ይህን ማለት የሚያስፈልጋቸው አይመስለኝም። ከኦነግ ጋር የነበረውን ድርድሩንም እሳቸው ነው ያደረጉት። የቡራዩ መከራም የቅርቡ ጉዳይ ነው። ወንጀለኞችን ጠዬቅን ይበላል ግን እኔ አላምናቸውም። 

እራሱ የኦዴፓ መዋቅር ስንቱ ከእነሱ ጋር ስለመሆኑ ማጣሪያም የላቸውም። ዝም ብሎ የጀምላ ጉዞ ነው ያለውብቻ የቆዬ ሰው ይዬው „ወትሮ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ“ የሚባለውም ይሆን ይሆን ያሰኛል።  

እኔ የሚያሳዝነኝ የወይዘሮ ታደሉ የዕንባ ማህበረተኞች አሁንም ተረኛ መሆናቸው ብቻ ነው። ለአራት እግር ወንበር ሲባል የኦሮሞ እናት 50 ዓመት ሙሉ ልጅ ትውለድ ለሞት። ደግሞ የሚገርመው በከሸፈ ፓለቲካ ሁልጊዜ መታመስ። 

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።