ልጥፎች

አሜሪካኖች „ምን እንርዳችሁ“ ማለታቸው ተደመጠ።

ምስል
አሜሪካኖች የመከላከያ አቅማችሁን ለመገንባት „ምን እንርዳችሁ“ ማለታቸው ተደመጠ።  ድንቅ ውበት። "የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤  እግዚአብሄር  ግን አካሄዱን  ያቃናለታል" ምሳሌ ፲፮ ቊጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=h-tSeJBvBho #EBC   እንደዘገባው። „ኢትዮጵያና አሜሪካ በወታደራዊው መስክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ“ ·       መቅድም። ውዶቼ ጭብጡ ላይ አይደለም የእኔ ጉዳዬ። ጉዳዬ የአብይን ሌጋሲን ለማስቀጠል የአሜሪካ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት የሚገልጸውን ክፈል ብቻ ለማዬት ነው እምሻው።   ስለዚህም በዚህ ዘገባው ውስጥ ቀልቤን የሳበው ታማኝነትን ለማስቀጠል ታማኝ ሆኖ መገኘት ስለመጠዬቁ ፍሬ ሃሳቡን ማግኘት ይቻላል። ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ በባዕለ ሲመታቸው ካደረጉት አንኳር ቀልብ ሳቢ ጉዳይ ላይ ስለሴቶች ያላቸው ልዩ ምልከታ፤ ውጭ ስለምንኖረው ኢትዮጰውያን ያላቸውን ናፍቆታዊ ራዕይ እንዲሁም በኢትዮ ኤርትራ የፍቅራዊነት ሂደት ላይ ያላቸውን የተስፋ ጥሪ ገልጠው ነበር።   ይህን ሦስት ማዕቀፍ አትኩሮት የሰጠ ልዑክ ነው አገረ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የላከው። አሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵውያን ፈቅደው እና ወደው አዲሱን የኢትዮጵያ የተስፋ በር በክብር ጥሪ አድርገውለት አቀባበሉን በአማረ እና በሰመረ ሁኔታ ከውነውታል። ይህ ደግሞ ፈሶ አለመቅረቱን ነው የዛሬ መረጃ የሚጠቁመን።   በሌላ በኩል ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደ ትውልዱ የዘመኑ ቤተኝነታቸው ሴቶችን ወደ ፖለተካው መድረክ በአቅማቸው ልክ ወደፊት የማምጣትንም ል

የዶር. ደብረጽዮን "አንጠልጥለን እንሰጣለን?"

ምስል
የዶር ደብረጽዮን „አንጠልጥለን እንሰጣለን“ ከምላስ        ወይስ ከአንጀት ተረቡ? „ከቁጣው ጢስ ወጣ ከፊቱም የሚባላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።“ መዝሙር ፲፮ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ  16.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                               ዘመን ሲሰጥ። እንዴት አላችሁልኝ ውዶቼ? ትናንት አንድ ዜና ሽው አለኝ እና የውነት ይሆን ብዬ ስፈታትሽ እውነት  ነው ተባለ። ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ከህግ በላይ ማንም ስሌለ አንጠልጥለን እንሰጣለን በእነሱ ሥማችን አይጎድፍም ማለታቸው ነው የተደመጠው እድምታው በትርጉም ሲቃና። ግን ይህ የአፍ ወለምታ ነው ወይንስ የልብ? እኔ አኮ እውነት ተናገሪ ብባል ዶር ደብረጽዮን በራሳቸው ፈቃድ ራሳቸው ጠይቀው አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀሪዮስን ሄደው በአካል ሲጠይቁ ከህሊናቸው ጋር ምህረት አውርደዋል ብዬ ነበር። በረከት ይዘው ተመልሰዋል፤ ተባርከዋል፤ ተቀድሰዋል፤ ምርቃታቸውን ሳያባክኑ እንደ ሰው ተፈጥሮ ይሆናሉ የሚል ሙሉ ዕምነት ስለነበረኝ በሐሴት ራሱን አስችዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ታዲያ ምን ይሆናል ከዛ ከተባረከው ተግባራቸው ማግስት እትጌ ትግራይ ጎራ ሲሉ ያው የለመደበዳቸውን ፉከራ ቀጠሉ፤ ይባስም ብሎም በራያ ሌላ ደም ፈሰሰ። እናም ደነገጥኩኝ። በወቃይትም ሌላ ርግጫ ቀጠለ። በውነቱ እኔ ነገሮችን በቅንነት ስለማይ እግዚአብሄር ፈቅዶ ነው ይህን መልካም ነገር ሊያደርጉ ያነሳሳቸው ብዬ አስቤ ሰልነበር ከዛ ከቀደመው ትዕቢታዊ ጭካኔ ጋር ይፋታሉ የሚል እምነት ነበረኝ። የወሰዱት እርምጃ ደፋር ነበር። ብፁዕን አባቶቻችን እንኳን አገር ገባችሁ ለማለት ካለምንም ገፊ ሃይል ራሳቸው ጠይቀው ነበር አብረው ከጠ/ ሚር

የአቅም ጥገትን መንገዱን ማንበብ ይቻላል!

ምስል
የሚቀድመውን የመለዬት ጥበብ ለሁሉም መርሁ  ቢሆን ምን አለበት? „የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁንም?“ ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 15.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ  የአቅም ጥገትን መንገዱን እንደ መጸሐፍ ማንበብ ይቻላል። ·        እ ፍታ አላዛሯ ኢትዮጵያ የ27 ዓመታት ግዞታዊ ኑሮዬ በቃኝ ብላ ማዕበል ውስጥ ኑሯውን ካደረገች ወደ ስድስት ሰባት ዓመት ሊሆናት ነው። ከድምጻችን ይሰማ ሉላዊ፤ ሰላማዊ ድንቅ አብዮት ጀምሮ ሲሰላ፤ በቃኝን ተከትሎ ያሉ ወጀቦች ሁሉ ተነሱም፤ ተቀመጡም ፍሬዎቿን ሲለቀሙ ኖረዋል። ለቃሚዎች ደግሞ አሁን ተለቃሚዎች ሁነዋል። ወጀቡ እንደ አገር ለአላዛሯ ኢትዮጵያ እኩል ነው። አደጋውም ያን ያህል ሴንሲቲብ ነው። አሁንም አውሎ ላይ ናት እናት ኢትዮጵያ። ቀላል እርምጃ አይደለም የሰሞናቱ ውሳኔ እና ቁርጠኝነት። እጅግ ደፋር እና እጅግም ልብ የተሸለመው ልባም ድርጊት ነው። አፈጻጸሙ እራሱ ተውኔታዊ ነው። ለነገሩ እኔ በመንፈሳዊ ስለማምን የአምላክ ስራ ነው። በቃችሁ ብሎናል አማኑኤል። ድፍን 50 ዓመት ሲባክን ለነበረው ተከታታይ ትውልድ እንደገና የመፈጠር ያህል ነው። ከአነጋገር ይፈረዳል፤  ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ። ·        ብ ይን እስቲ ስጡበት። አንድ ሙሉ ቤት በጉንዳን ቢወረር፤ ልብሱ ሁሉም ጉንዳን ቢወረው፤ ምግቡንም ሁሉ ጉንዳን ቢወረው፤ መኝታውንም ሁሉ ጉንዳን ቢወረው የቤቱ ባለቤት መጀመሪያ የቱን ቢያሰቀድም ራሱን አረጋግቶ ከጉንዳን እርግጫ እና ቁንጥጫ ወጥቶ ጉንዳኑ በቁጥጥር ስር ሊያውል ይችላል ብዬ ራሴን ፈተንኩት? ውዴቼ ታዳሚዎቾቼ ግን የቤቱ ባለቤት የቱን

አቶ ያሬድ ዘሪሁን ወደ ኬኒያ ሊሸሹ ሲሉ

ምስል
የአቤል እንባ ወደ እዮር ይጮሃል … „ማንም እራሱን አያታልል ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበባኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ነው።“ ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፱ እስከ ፳   ከሥርጉተ ሥላሴ 15.11.2018  ከገዳማዊቷ፡ሲዊዘርላንድ። የቀድሞው የመረጃ እና የደህነንት ሃላፊ እና የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጄኒራል አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢቢሲ ዘገበ። የአቤል ዕንባ ባክኖ መቼም አይቀረም። የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች የ27 ዕንባም ፈሶ አይቀርም።  እሳቸው ኬኒያ ሌላኛው አቶ ክንፈ ዳኘው ወደ ሱዳን ሌላው ደግሞ ወደ ጁቡቲ ይቀጥላል እንዲህ እያለ ማለት ነው … ቢያንስ  የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃውን የጨረሰውን ተጠያቂዎች መቅደም ካልቻለ ሾልከው ይሄዳሉ፤ መሄዳቸው ሳይሆን ክፋቱ እዛም ሆነው ማነኮራቸው አይቀሬ ይሆናል።  ስለዚህ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ዳታ ብዙ ከእንግዲህ አዋጪ አይመስለኝም። እራሱ ግብረ መልሱም የከፋ ሊሆን ይቻላል፤ እንዲህ ዓይነት ሰው ከጭካኔ ስለማይመለስ በዬቦታው የፍንዳታ የቦንብም ሊሆን ይቻላል ሊከሰት ይችል ይሆናል። አጥፍቶ መጥፋት ተስፋ ከቆረጡ ሰብዕናዎች ስለሚመጡ። በሌላ በኩል ብዙ ዜናውን አለማሟቅ እና በተደሞ እና በትእግስት ሁኔታውን መከታተል በእጀጉ ያስፈልጋል። በተለይ ከተሞች አካባቢ በጊዜ መግባትን ጨምሮ ሁሉም ዘብ መቆም ይኖርበታል ለዬአካባቢው ደህንነት።   ዘመን ያሉ ጥያቄዎችንም ተግ አለማድረግ፤ በመንግሥት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ሁኔታዎችንም ማስታገስ ያስፈልጋል። ከባድ ሁኔታ ነው አሁን ያለው ሃላፊነት። ሃላፊነት የሁሉም ነውና። በመንፈስም በጸሎትም መንግሥትን መርዳት የዜግነት ግዴታችን ነው።

ኤርትራ እና የአማራ መሬት ጥሪኝ የምሥራች ብስራታዊ ዜና።

ምስል
እርጥቡ የአማራ መሬት ጉብኝት ስኬትን ለኤርትራ እንሆ አበሰረ።  ፍቅርንም በቅንነት  አስከበረ! „ምህረት እና እውነት ከአንተ አይራቁ  በአንገትህም እሰራቸው።“ መጽሐፈ ምሳሌ ፫ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ© ሥላሴ  114.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ  ባላፈው ሰንበት ላይ የኤርትራው መሪ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና አቻቸው የሱማሌው ፕሬዚዳት ሙሐመድ አብደላሂ በጎንደር እና በባህረዳር ይፋዊ ጉብኝት ማደረጋቸው ይታዋቃል። በዚህ ውስጥ ቅንነት እና ድንግልና ስለነበረ እንሆ የኤርትራ ምኞት ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰለምና አንድነት ሊያጠናክር የሚችለው በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው ጥረት እና ልፋት ለውጤት ደርሶ ዛሬ ኤርትራ በተባበሩት ምንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት  ተጥሏበት የነበረው የኢከኖሚ ማዕቅብ የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ደምጽ ማጽደቁ ተደመጠ። እትጌ ኤርትራ እና መንግሥቷ እንዲሁም ህዝቧ እንኳን ደስ አላቸው፤ ጉልህ ሚና የተጫወቱት ጠ/ ሚ ር አብይ አህመድ እንኳን ደስ አላቸው። የሱማሌው ፕሬዚዳንትም በጎ መንፈስ በዚህ ውስጥ ስላለ እንኳን ደስ አለው። ደስታው የአፍሪካ ሰላም ነውና። ኢትዮጵያዊነት መንፈሱን ሲያቀርቡት ረቂቅ ጠጋኝ መንፈስ አለው።  ጥረቱ የተሳካው ቅንነት እንጂ የትርፍና የኪሳራ የብልጠት ስሌት ስላልነበረው ብቻ ነው። ይህን ማዕቀብ ለማስነሳት ብዙ ተሞክሮ „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር ሆናና“ ዛሬ የምሥራቹ ተደመጠ፤ እርጥብ እግር እና እርጥብ መሬት እንዲህ ሸክምን ያቃልላል። ለአብይ ካቢኔ ሉላዊ የዲፕሎማሲያው ዕውቅና እና ክብርም ደረጃውን በዚህ ውስጥ ማዬት ይቻላል። ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ መንገድ ጀምራለች። ኢትዮጵያን አፍሪካን ቁምነገር የማድ

ሽብልል በሽብልል ቃለ ምልልሱ ከፖለቲካ ሳይንቲስቱ ጋር - በዋልታ።

ምስል
ሽብልል በሽብልል። „ስለ ራዕይ ሸለቆ የተደገረ ሸክም። እናንተ ሁላችሁ ምን ሆናችኋዋል?“ ትንቢተ ኢሳያስ ፳፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ  14.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                                                          ·     መነሻ። ሽብልል የሚለው ቃል አንዲት ሴት የገብስ እንጀራ ካሰኛት በወፍራሙ ትለውሰዋለች፤ ለረጅም ጊዜም ይቆይላታል። አገልግሎቱን ውጤቱን ሳያሳውቅ። እዬገነፈለም አያጨናናቃትም ቀኑ ሲደርስ አቅጥና ከሙገጎ ጋር ታገናኘው እና እንጀራ ይሆናል፤ እሰከዚህ ድርስ ግን ሽብልሉ የዳቦ ይሁን፤ የጠላ አብሽሎ ይሁን የእንጀራ ይሁን መለዬት አያቻልም። ያው ሽብልል ነው። እንደተሸፈነ ተሸብልሎ ይሰነባብታል። ቀኑ ሲደርስ ግን ተቀጥኖ ሲጋጋር የገብስ እንጀራ ይሆናል።  ሌላው ግምል የሚባል ደግሞ አለ። ግምል ደግሞ የማሽላ ነው። የደበር፤ የወድ አራባ፤ የወዳከር የቡሌ ወይንም የባህር ማሽላ ሊሆን ይችላል። ገምላ አስንብታ ልታጋግር ስታስብ ሴት ባለሙያ አቅጥና ትጋግራዋለች ማለት ነው። የጤፍ የቦካ በሌላ ዕቃ ከኖራትም አብራ አዋህዳ ትጋገረዋለች። የገብስ እና የማሽላ ልወሱ ለብቻ ነው የሚዘጋጀው። እንዲያውም በሰፊ ገበታ ነው የሚቀመጠው። የ ጤፉ ግን በማንኛውም ቡሆዕቃ ይሰናዳል፤ በቅልም በ እንስራም ትልቅ ቤተሰብ ካለም፤ ድግስም ከኖረ በጉርድ በርሚልም ሊሆን ይችላል። የማሽላው እንጀራ ፍርክ ፍርክ የሚል ሲሆን የገብሱ ግን ለስላሳ እና ዘንጣፋ ነው። ግን ማሽላው በግምል ገብሱ በሽብልል መሰንበቱ አይቀሬ ነው።     ·        ሥሜ። https://www.youtube.com/watch?v=9Ck5Y9I42lA Professor Merera Gudina