የአቅም ጥገትን መንገዱን ማንበብ ይቻላል!

የሚቀድመውን የመለዬት ጥበብ ለሁሉም መርሁ 
ቢሆን ምን አለበት?
„የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ
የእግዚአብሄርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ
አታውቁንም?“
ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር፲፮
ከሥርጉተ©ሥላሴ
15.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 


የአቅም ጥገትን መንገዱን እንደ መጸሐፍ ማንበብ ይቻላል።

·       ፍታ

አላዛሯ ኢትዮጵያ የ27 ዓመታት ግዞታዊ ኑሮዬ በቃኝ ብላ ማዕበል ውስጥ ኑሯውን ካደረገች ወደ ስድስት ሰባት ዓመት ሊሆናት ነው። ከድምጻችን ይሰማ ሉላዊ፤ ሰላማዊ ድንቅ አብዮት ጀምሮ ሲሰላ፤ በቃኝን ተከትሎ ያሉ ወጀቦች ሁሉ ተነሱም፤ ተቀመጡም ፍሬዎቿን ሲለቀሙ ኖረዋል። ለቃሚዎች ደግሞ አሁን ተለቃሚዎች ሁነዋል።

ወጀቡ እንደ አገር ለአላዛሯ ኢትዮጵያ እኩል ነው። አደጋውም ያን ያህል ሴንሲቲብ ነው። አሁንም አውሎ ላይ ናት እናት ኢትዮጵያ። ቀላል እርምጃ አይደለም የሰሞናቱ ውሳኔ እና ቁርጠኝነት። እጅግ ደፋር እና እጅግም ልብ የተሸለመው ልባም ድርጊት ነው።

አፈጻጸሙ እራሱ ተውኔታዊ ነው። ለነገሩ እኔ በመንፈሳዊ ስለማምን የአምላክ ስራ ነው። በቃችሁ ብሎናል አማኑኤል። ድፍን 50 ዓመት ሲባክን ለነበረው ተከታታይ ትውልድ እንደገና የመፈጠር ያህል ነው። ከአነጋገር ይፈረዳል፤  ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ።

·       ይን እስቲ ስጡበት።

አንድ ሙሉ ቤት በጉንዳን ቢወረር፤ ልብሱ ሁሉም ጉንዳን ቢወረው፤ ምግቡንም ሁሉ ጉንዳን ቢወረው፤ መኝታውንም ሁሉ ጉንዳን ቢወረው የቤቱ ባለቤት መጀመሪያ የቱን ቢያሰቀድም ራሱን አረጋግቶ ከጉንዳን እርግጫ እና ቁንጥጫ ወጥቶ ጉንዳኑ በቁጥጥር ስር ሊያውል ይችላል ብዬ ራሴን ፈተንኩት?

ውዴቼ ታዳሚዎቾቼ ግን የቤቱ ባለቤት የቱን መጀመሪያ ማጽዳት አለበት ትላላችሁ? የቱስ ቢቀድም አቅሙን አጣራቅሞ ቀጣዩን ርምጃ ሊያስወስደው የሚችል ችሎታ ወይንም የጥበብ መንገዱ ሊሆን ይገባዋል ብላችሁ ትበይናላችሁ?

ከመሃል፤ ከዳር፤ ከጠርዝ፤ ከላይ፤ ከታች ከዬት ይጀመር? ከልብሱ፤ ከቆመበት ወለል ከምግቡ፤ ከምኝታው፤ ከመቀመጫው ከዬት ይጀምረው? ማራገፊያ ስልቱ እና አጋዥ ድልድዩስ? ቤቱ ቲፍ ብሎ በጉንዳን ሞልቷል። ራስ እግሩ በጉንዳን ተውጧል። የጉንዳን ማዕበል ወይንም ሙላት ይባል። የሚገርመው ጉንዳኑ ደራሽ ሳይሆን መድምዶ ርስቴ ብሎ ተደላድሎ የተቀመጠ ነው።

የቀረ ክፍት ቦታ የለም በጉንዳን መላ አካላቱ ተውጧል። ወደ በሩ ለመወጣትም፤ በመስኮት ልዝለለም ቢል የጉንዳን ቁንጥጫ ለሚያውቃት ፋታ አይሰጥም እና እናማ የቱ ይቅደም? እራሱ ወደ መስኮቱ ወደ በሩ የሚ ደርሱ መንዶች በጉንዳን ጡብ ተገንበተዋል። ጉንዳን እና ህብረቱ ደግሞ ይታወቃል። 

አሁን የአላዛሯን ኢትዮጵያ ወዘተረፈ ችግር እኔ እምመለከተው ከዚህ አንጻር ነው። ችግሩ የሥርዓት ነው። ለውጡ ደግሞ የጥገናዊ ለወጥ ነው። የጥገናዊ ለውጡ ዓላማ መርዛማ ደምን እያወጡ በአዲስ ደም መተካት ነው። ለዛ ደግሞ ስከንትን፤ ጊዜን፤ ሁኔታ እና ቦታን ማድመጥን በእጅጉ ያስፈልጋል።

ከዬትም ሊጀመር ይችላል - ከተመቸው፤ ግን ሂደቱን የሚገዙ ህግጋትን እና ማህበራዊ ንቃተ ህሊናውን አጣጥሞ ለመጓዝ ልዩ ጥበብ፤ ልዑቅ ስልት፤ የመጠቀ ብልህነት፤ ድርብ አደብ እናም የደህንነት ሙያዊ ሰው መሆንን ይጠይቃል። ዛሬ አላዛሯ ኢትዮጵያ ይህ አላት ብዬ አምናለሁኝ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ። ለዚህም ነው በጥዋቱ የዛሬ ዓመት እኔ ለማውያን የሆንኩት።

·       ድማጭነት የተጠዬቀበት ወቅት።  

ጊዜን፤ ሁኔታን፤ አቅምን፤ ክህሎትን ማድመጥ ያስፈልጋል። አሁን ከዜጋ የሚጠበቀው አደብ ነው። ተግባሩን ፈተናውን የገቡበት ቁርጠኞች አሉና። ብዙ እማዳምጠው ጠቅልሎ ስለምን እስር ቤት አያስገቡም የሚል ነው። ባላው ምሰሶው ከወለቀ እኮ ሥርዓቱ ይወድቃል፤ ሥርዓቱ ሲወድቅ ደግሞ ሁሉም አብሮ ይሰምጣል። ለዘር የሚቀር የለም። ማዕበላዊ ጦርነት ህግ የለውም እና።

እንደ ገናም አቅጣጫ የለሽ ፈተናም፤ መሪ የለሽ መንገድም፤ መርህ የለሽ መከራም ሊገጥም ይችላል። ስለዚህ በቀስታ፤ በዝግታ፤ በፀጥታ መራምድ በእጅጉ ያስፈልጋል። ሁሉ ከሆነ ደግሞ እጅግ ከባድ ነው። አለኝ ብሎ ቢሰገስገቱ መፈንዳት ነው። ጊዜ የሚጠይቁ፤ ሂደትን የሚፈትኑ፤ በወጉ መለዬትን የሚሹ የአርምሞ ጊዜ በእጅጉ ያስፈልጋል። ተደሞው መቻሉ በጥልቀት ማሰቡ ሁሉም በዬፈርጁ ባለቤት አላቸው። መሪ ማለት ይህን አቀናጅቶ እና አደራጅቶ ለግብ ማብቃት ነው።

ግብ ሲባል የመጨረሻው ብቻ አይደለም መነሻ እራሱ ግብ ነው። ከመነሻው ጀምሮ በዬሰዓቱ የታቀደው ስኬት ማለት ነው ግብ እንጂ የሰው ፍላጎት ማለቂያ የለውም። መጨረሻም የለም።

አሁን ጉግል ተፈጠረ ጉግልን በእጥፍ የሚያስንቅ ሌላ ፍልስፍና ደግሞ ይህን ያቀዱ ሰዎች ነገ አዲስ ይሠራሉ፤ የነገውም ቢመጣ ይህም የተነገ ወዲያው ፈጠራ ይቀጥላል። የሚያልቅ ተጨረሰ የሚባል የፍላጎት ቋት የለም።

·       የወግ ፍሬ ነገር።

አላዛሯ ኢትዮጵያ መንግሥት የላትም እያልን ስንጽፍ ነበር፤ መንግሥት አለ ከተባለ ሥርዓቱን የሚያስቀጥል እንጂ ለህዝብ ሃላፊነት የሚሰማው እንዳልነበረ ይታወቃል። እርግጥ ነው መንግሥት የለም የሚለውን አመክንዮ የሚያምነው ዕውነቱን ጥቂት ነበር።
እራሱ ኢህአዴግ በስብሻለሁ እያለ ግን መበስበሱን ጥሶ ለውጣት ያልቻለበት ዋናው ምክንያት ራስ እግሩ የዝርፊያውም፤ የሰብዕዊ መብት ረገጣውም ተዋናዩ ሁሉም መሆኑ ነው። እርግጥ ነው ጥቂቶች ሊኖሩ ይቻላሉ ግን ከላይ እስከታች ሥርዓቱ ከመገለ ችግሩ መዋቅራዊ ነው ማለት ነው።

አንዱን ሲነካ ሌላው ይናዳል፤ ሲናድ ደግሞ ተተኪ ተዘጋጅቶ መሆን አለበት፤ ተተኪ ብቻ ሳይሆን በዚህ ውስጥ የሚጠቁ የቤተሰብ አባላት ደግሞ ስላሉ የእነሱም ግብረ ምላሽ አሉታዊ ስለሚሆኑ እና ስላለመሆኑ ዋስትና ያስፈልገዋል። ይህም ብቻ አይደለም አሁን እንደ አዲስ መረጃውን ያዩ ሰዎችም አነባለሁኝ። የትኛው ፕላኔት ላይ እንደ ነበሩ ሁሉ ግራ ይገባል። እርግጥ ነው የመረጃ እጥረት በስፋት አለ። ሰው አያነብም፤ አያዳምጠም፤ አይከታተልም።

ቀደም ባለው ጊዜ ለእውነት የቆሙ ጸሐፈት እና ሚዲያዎች አገር ውስጥ እንዳይደመጡ ታግደው ነበር። አገር ያለው ሚዲያ ደግሞ ስለ 11 % እድገት እና ስለ ህዳሴ ግድብ እና የጠሐይ ቀናት ነበር ሲተርብ የነበረው። ስለዚህም ህዝብ አያዳምጣውም። ኑሮውን ያውቀዋል እና። 

ቀድሞ ነገር የወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ አስፈጻሚ ለነበሩ ሚዲያዎች አቅል አቅም አልነበረም ለማድመጥ እራሱ አስከ መጋቢት 24 ቀን 2010 ድረስ። ስለዚህ ገመናውን ሳናውቅ ቀረን ቢሉ አገር ቤት ያሉ ሰዎች ብዙም አይደንቀኝም። ውጭ አገር ያለው ግን የራሱ ድክመት ነው። ለመሆኑ ገና ምን ተነክቶ?

ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ የምታባል አገር እኮ በወራሪዎች ነበር ትምራ የነበረው። በሚጠሏት፤ በሚጸዬፏት። ወራሪ ደግሞ ወረራው እንዳይገታ ነበር ጭካኔን መርሁ አድርጎ ይንቀሳቀስ የነበረው። ሌላው ቀርቶ ለራሱም ለወጣበት ህዝብ እስከ ጠቀመው ድርስ ብቻ ነው ባሊህ የሚለው።

የዚህ ጥገናዊ ለውጥ ዋንኛ ግብ አዲስ ተጠያቂነት እና ሃላፊነት የሚሰማው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መፍጠር ስለሆነ ፈተናው ከባድ ነው። መንገዱም ጥልፍልፍ ነው። ምክንያቱም ጠቅልሎ አፍርሶ አይደለም የሚገነባው። አብዮት አይደለም እና። እራሱን እያፈረሰ እንደገና የመሥራት ሂደት ነው እኔ እያዬሁት ያለሁት። ለዚህም አጋዥ አካላትን ከዬትኛውም ወገን በማጥናት በጎ እርምጃዎችንም ጀማምሯል። 

አሁን የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ጎዳይ ዶር ካሳ ከበደ እንዲይዙት መደረጉ ትልቅ እረፍት ነው። አሁን እኔ ብግሌ እኔ አርፌያለሁኝ። የሱማሌ አማራር ከተለመደው ውጪ የሰብዕዊ መብት ተሟጋችን ወደ አገር አስገብቶ ማድረግም ደፋሩ ርምጃ ነው አቶ ሙሱጦፋ ዑመርን። እነኝህ የብልህነት ጥልፎች መስተጋብራዊ ጥረቱን ንጥረ ነገሩን ያፋፉለታል። እንደ አጋዥ ሳይሆን እንደ ወሳኝ የመፍትሄ አካል ይሆናሉ። 

ሌላው በጉልህ ዛሬ ሊታይ የማይችለው ሴቶችን በፖለቲካ ድርሻ እንዲኖራቸው የማድረግ ደፋር እርምጃ ያልተጠቀምነበት፤ ያልተነካ ድንግል የአቅም መስክ ነው። አብዛኞቹ ሴቶች ጥበቦች ናቸው። ሴትነት ስኬታማነትም ነው። ይህ በስጋት ሥነ - ልቦናው ለተጎዳው 100 ሚሊዮን ህዝብ እናታዊ ረድኤትና በረክት አለው። እርግጥ ረቂቅ ነው። 

የጥገናዊ ለውጡ ሂደት እኔ እንደምረዳው የቆዬውን መርዛማ ደምን ልክ እንደ ኩላሊት አጠባ እያደረገ በመጥረግ ብክል ደሙን ማስወጣት ነው። ለዚህ ሂደት ደግሞ ተበዳዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ከኖረው ጊዜ ስለማይበልጥ ሰፊ የትዕግስት ማሳ በልቡ ውስጥ ሊኖረው ይገባል። በዚህም ውስጥ ተመስገንን ማስቀደም ማጣጣም ይኖርበታል። መተንፈስ ቻለ። የተቃጠለውን አዬር አስወጥቶ ንጹህ አዬር ለማስገባት አንጻራዊ መረጋጋት ተፈጠረለት።

በማስተዋል ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ግን አዲስ የተሠራ መጠባባቂያ ቤት ሳይኖር ነበሩን ማፈረስ አውላላ ሜዳ ላይ መቅረት ነው። በእያንዳንዷ ደቂቃ 100 ሚሊዮን ነፍስ ሁሉንም የመኖር አስፈላጊ ነገሮች ይጠይቃል። ያን ለማድረግ ደግሞ ቤቱን ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ ህዝብን አውላላ ሜዳ ላይ እዳሪ አፍሶ ሊሆን አይገባም። መቆያ ቤት የግድ ያስፈልጋል ቢያፈስም፤ ቆርቆሮው ቢበሳሳም።

ይህን ብልህነት ሲነሱ ነው እነዚህ የለውጥ ሐዋርያ የሚባሉት ሃላፊነት የሚሰማቸው ወገኖቻችን የጀመሩት። በሚናገሩት ልክ መሆን ለመቻል፤ በሚያደርጉት ጥረትም በዬቦታው የተለኮሰው እሳት ተመልክተናል። ያግዛሉ የተባሉት ከውጭ ወደ አገር የገቡት እንኳን በምን የትርምስ ዓውድ ላይ እንደ ነበሩ ሁላችንም ታዝበናል። ተጨማሪ ችግር ፈጥረው ሌላ የቤት ሥራ ነበር የደረቱት።

ራሱ ነፃነት እፈልጋለሁ የሚለው ወገን በፈረሰ ቤት አዲስ ቤት ለመስራት ምንም መሰናዶ ሳይኖር ነበር ሥር ነቀል ለውጥ የሽግግር መንግሥስት፤ የተጽዕኖ ፈጣሪ የአንድነት መንግሥት ሲል የነበረው። „ራስ ሳይጠና ጉተና“ ይሉታል ጎንደሬዎች ይህንን።

በአንድ ድርጅት በሜቴክ ብቻ ያለው እኮ የአንድ አንስተኛ አገር አጠቃላይ ችግርን ይሸፍናል። ግዙፏን ኢትዮጵያ ስናስባት የመዋቅሩን ስፋት እና መጠን ስነሰላ ስንቱ የመገለ እንደሆን ማሰብ አይሳንም።

ለዚህ ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሥራ ሲጀመሩ የአገር ውስጥ ነዋሪዎችን እና የጎረቤት አገር መንግሥታትን ለማግኘት አጣምረው አቀናጅተው የሠሩት። መጀመሪያ የህዝብን ድጋፍ አቅሜ ብሎ ለመነሳት ያ ተፈላጊ ቀዳሚ ልባም ምራቁን የዋጠ እርምጃ ነበር።

በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ያወያያሉ፤ ውጭ አገር ደግሞ ከጎረቤት ጋር የዲፕሎማሲ ተግባር ይከውናሉ። ዲያስፖራውንም አትኩሮት ሰጥተውል። በሌላ በኩል መሬት ላይ በመንግሥታዊ አካላት እና በግንባር ድርጅታቸው ያለውን ችግር ፈልፍለው ሊያጠኑ፤ ሊመረመሩ የሚገባቸውን ደግሞ አግባብ ያለው አካል ያደራጃሉ።

 ከዋዜማው ጀምሮ አቅም ስናባክን እኛ የፈበረከነው ችግር፤ የፈጠርነው ጫና ሲደመር የወያኔ ሃርነት ትግራይ የአለቀም የገነገነ የሴራ ተልዕኳቸው ጋር በግራ በቀኝ ተወጥሮ፤ ግድያውም፤ መፈንቅለ የመንፈስ እና የመንግሥቱም ሙከራ ታክሎ ማለት ነው እዚህ ላይ የተደረሰው። 

ብዙ ጊዜ ሳስበው የእነዚህ ቅኖች መንገድ ካለመረዳትም የመነጨ ነበር።
ይህን አያይዞ ለማስቀጠል የአቅምን ልክ በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ ሆነ በኢትዮጵያዊ ዜጋ በጎረቤት አገር መንግሥታት መሰረት ማስያዝ ይገባ ነበር። አንድ ምሳሌ ብጠቅስ ከእትጌ ኤርትራ ጋር የሰላሙ ሂደት ባይሳካ አሁን ከምናያቸው በከፋ ሁኔታ ችግሩ ያይል ነበር። ይህን እንኳን ተመስገን አላልነውም። ትልቅ እርምጃ ነበር የአልጀርሱን ውሳኔ ወደ ተግባር ለመወጥ የተሰጠው ወሳኔ። ደፋርም ነበር። "የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ" ብታነቡት ፍሬ ሃሳቡም ይኸው ነበር። እጅግ ጠቃሚ እርምጃ ነበር።

የሱማሌ የአማራር አካላት ለውጥ ሌላው ትልቁ ዕጹብ ድንቅ ነበር። የጋንቤላውም በተወሰነ ደረጃ መልካም ነው። ከሁሉ በላይ ደግሞ የቅኑ ኮ/ ጎሹ ወልዴ አገር መግባት ታላቅ ስኬት ነው።  በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በእስልምና ሃይማኖት የነበረውን ውጥረት መልክ ለማስያዝ የተሄደበት መንገድ፤ የተሰጠው ህሊናዊ አትኩሮት እና አክብሮት ቢያንስ አሁን የአብይ ካቢኔ መተንፈስ አስችሎታል። ታሪካዊ ጉዞው እና ቅደመ ተከተሉ ልብ ላለው መሳጭ ነው። መጸሐፍም ነው የትጋት ድርሳን! ያልታሰበ ሲሳይ ነው ሰማይ ላይ ዱብ ያለልን። በፖለቲካ ህይወት ለቆዬ ሰው አቅም ማለት ምን ማለት እንደሆን ለመረመረ፤ የክህሎቱ ቤተኛ። ልግብግብ አይደለም አቅሙ። 

·       ንሹ!

መንገዱን ማንበብ ይቻላል። ከምን እንደተነሳ? ወደ ዬት አቅጣጫ እንደ ተጓዘ፤ አሁን የትላይ እንዳለ፤ ቀጣዩን ወደ ዬት እንዳደረገ ታቅዶ፤ ታልሞ በሙሉ መሰናዶ ስለሚከወን ሁሉ ነገር በቱማታ የሚሉ ዕሳቤዎች ሂደቱን አላጠኑትም የእኔም አላሉትም ማለት ያስችላል። 

እርግጥ ነው ተፎካካሪዎች የራሳቸውን የቤት ሥራ መቀመር እንጂ  ኢህአዴግ ፍኖተ ካርታ ላይ አጀንዳው እንዲህ እና እንዲያ እያሉ አቅም ማባከን አይገባቸውም። ካላቸው ይህን መንፈስ እና ልቅና በልጦ ለመገኘት ፉክክር ነው እና መትጋት ሊሆን ይገባል ተግባራቸው። 

እንደ እኔ ላለው ባለቤት እከሌ አለኝ የማይለው ባተሌ ዜጋ ግን ነፍስ ያለው ተግባር የአብይ ሌጋሲ እዬሠራ መሆኑን ከመቅድሙም በአጽህኖት ስለማምንበት በአብይ አክቲቢዝም ላይ አጠንክሬ እቀጥልበታለሁኝ። ግድፈት ሲኖር ደግሞ ያው በተለመደው መልክ ... 

ያልተሰናዳ ሰው እኮ በተመረጠ ማግስት ጉዞ አይጀምርም። በሚገባ ተሰናድተውበታል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ። ስንዱ ናቸው ማንጠግቦህ።

አሁን አንድ ዶክመንተሪ ዘገባ ቀርቧል ስለሜቴክ። አቅራቢውም ጸሐፊውም በቀደመው የOBN ሚዲያ ላይ በልዩ ዶክመንተሪ ዝግጅት የሠሩ ወገኖች ናቸው። ቅንብሩ፤ ሥንኙ ድምጹ ስታዩት በዚህ ሁሉ ማህል ያ ህሊና በምን መሰናዶ ልክ፤ በምን ብቃት እና ጥበብ ልክ፤ በምን አቅም ላይ ሰክኖ እንዳለ ያሳዬናል - የጸሐፊውን ተክለ ቁመና በግሌ ስመረምረው ሁለገብነቱ የሚዋሰው ነገር አለመኖሩ ራሱን አስችሎ መንገዱን ለመምራት አስችሎታል።

ምን ለማለት ነው? ዕለታዊ ያለሆነ፤ ዘላቂ ዓላማን የያዘ፤ የእናት አገሩን ውሰጧን ውስጥ ያደረገ፤ ችግሯን የእኔ ብሎ ያጠና፤ ማናቸውንም መስዋዕትንት ከፍሎ እሷን ማዳን ብሎ ከቆረጠ፤ ከወሰነ የድርጊት መንፈስ ስለሆነ ጉዳዩን በባለቤትነት የያዘው አደብ ሸመታ ወደ እዮብ ጎራ ቢባል መልካም ነው።

„የቸኮለ አፍሶ ለቀመ“ አይደለም የተያዘው። በዚህ ሂደት የጨበራ ተዝካር የለም። እኛ ለምዶብናል አፈስን ስነለቅም ለቅመን ስናፈስ፤ እንዲያውም የራሱ አጋር በፈጠረው ዝብርቅ ሻሸመኔ እና ቡራዩ ባይታከሉ ኖሮ የትርፍ ወቄቱ ተዚህም ይብልጥ ነበር። የሆነ ሆኖ በሰከነ ህሊና፤ በዳበረ ብቃት፤ በተሟላ ክህሎት፤ መዳፍ ላይ ባለ ሙያዊው ክህሎት ስለሆነ አላዛሯ ኢትዮጵያ እዬተመራች ያለው ተመስገን እና ጸሎትን አደራጅቶ መምራት ደግሞ የእኛው ፈንታ ይሆናል። 

ያማ ባይሆን በምሰራቁ ያገራችን ክፍል 700 ሺህ ወገኖቻችን ሲፈናቀሉ ያን ጊዜ ነበር ይህ አቅም ትጥቁን የሚፈታው ወይንም ሞያሌ ላይ 50 ሺህ ወገኖቻችን በድጋሚ ሲፈናቀሉ። የደበቡ ሰቆቃ እና መፈናቀል፤ የቤንሻንጉሉ መከራ፤ የሰኔ 16ቱ፤ የሐምሌው ዝምታ፤ የመስከረሙ ኩዴታ፤ የጥቅምቱ ፍጥጫ ሁሉንም አስተናግዶል ባለድርብ አደበኛው ውርስ የጽናት መንፈስ። የሚፍረከረክ አይደለም። ፈተናዎቹ ጥልቅ ግን የአሱ አቅም ደግሞ ምጥቅ ነው። ፈተናውን የመሸከም ብቻ ሳይሆን መፍትሄ የማመንጨት አቅሙም አንቱ ነው።

 ስለሆነም መሬት እና ሰማይ ቢደባለቅ ይህ ጥምር አቅም ማደረግ ያሰበውን ከማስቀጠል ውጪ የእናቴ መቀነት ጠለፈኝ እያለ በዬፌርማታው ጎማ የሚቀይር አይደለም። ይህን ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሴራ ባንዶች ያልገባቸው። ሌላውም ሴረኛ ያልተረዳው ይህን ነው።
በጣም ጠንካራ የማይበገር፤ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ፤ በራሱ የሚተማመን ጽናት እና ሃሳብ ያለው መንፈስ ነው አሁን የኢትዮጵያ መሪ ሃይል የሆነው። ይህ ደግሞ ለትውልዱ ታላቅ ተምሳሌት ነው። ተቋምም ነው። እያንዳንዷ ቀን እና ዕድማታዋ የመደበኛ የትምህርት ቀን ናት። ላወቀበት።

·       ስለመሆን።

ከእኛ የሚጠበቀው በሆነው ሁሉ ነገር በማድነቅ፤ በማድመቅ፤ በማጮኽ፤ ወይንም በማንኳሰስ፤ ወይንም እልህን በማቀጣጠል፤ ወይንም ብሶትን በማራገብ፤ ወይንም የቁጭት ቤተኛ በመሆን፤ ወይንም በተንጠራራ የአሸናፊነት ስሜት ላይ ተላይ በመተንፈስ ሳይሆን በዝግታ ሁሉም ነገር መያዝ ያስፈልጋል። 

መርከቧ ሹፌር አላት፤ ሹፌሩን ከሚያውኩ ወጆቦች በመቆጠብ ማድመጥን አብዝቶ የእኔ ማለት ያስፈልጋል - ቢያንስ።

በጥዋቱ ጹሑፌ እናዳሳውቁኩት ዘመናይ የሆኑ ጥያቄዎችንም ተግ ማድረግ በእጅጉ ያስፈልጋል። ሰባራ ሰንጣራ እዬፈለጉ ማብጠልጠሉ እና ተጨማሪ ጫና መፍጠሩም በውነት በዳዮች ከፈጸሙት የሚተናነስ አይደለም። 

ትውልድ ከብክነት የሚድነበት መንገድ ተጀምሯል፤ ስለዚህም የማጠናከሪያ የመንገድ ጠረጋ ከእኛ ይጠበቃል። ይህ እንደለመደብን እከሌን በካቴና ተጥርንፎ ማዬት እሻለሁኝ የጥድፊያ መንገድ የተገባ አይደለም። ለሁሉም ጊዜ አለው። ፈጣሪም አይረሳ የ እሱም ፈቃድ አለበት በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ። መሪ አለው ለሁሉም ጉዳይ። 
ስለሆነም ተግ እንበል …

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ክብረቶቼ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።