አሜሪካኖች „ምን እንርዳችሁ“ ማለታቸው ተደመጠ።

አሜሪካኖች የመከላከያ አቅማችሁን ለመገንባት „ምን እንርዳችሁ“ ማለታቸው ተደመጠ። 
ድንቅ ውበት።
"የሰው ልብ መንገድ ያዘጋጃል፤ 
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን 
ያቃናለታል"
ምሳሌ ፲፮ ቊጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
17.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

·       መነሻ።

https://www.youtube.com/watch?v=h-tSeJBvBho

#EBC  እንደዘገባው።

„ኢትዮጵያና አሜሪካ በወታደራዊው መስክ

ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ“

·      መቅድም።

ውዶቼ ጭብጡ ላይ አይደለም የእኔ ጉዳዬ። ጉዳዬ የአብይን

ሌጋሲን ለማስቀጠል የአሜሪካ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት የሚገልጸውን ክፈል ብቻ ለማዬት ነው እምሻው።

 

ስለዚህም በዚህ ዘገባው ውስጥ ቀልቤን የሳበው ታማኝነትን ለማስቀጠል ታማኝ ሆኖ መገኘት ስለመጠዬቁ ፍሬ ሃሳቡን ማግኘት ይቻላል። ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ በባዕለ ሲመታቸው ካደረጉት አንኳር ቀልብ ሳቢ ጉዳይ ላይ ስለሴቶች ያላቸው ልዩ ምልከታ፤ ውጭ ስለምንኖረው ኢትዮጰውያን ያላቸውን ናፍቆታዊ ራዕይ እንዲሁም በኢትዮ ኤርትራ የፍቅራዊነት ሂደት ላይ ያላቸውን የተስፋ ጥሪ ገልጠው ነበር።

 

ይህን ሦስት ማዕቀፍ አትኩሮት የሰጠ ልዑክ ነው አገረ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የላከው። አሜሪካን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵውያን ፈቅደው እና ወደው አዲሱን የኢትዮጵያ የተስፋ በር በክብር ጥሪ አድርገውለት አቀባበሉን በአማረ እና በሰመረ ሁኔታ ከውነውታል። ይህ ደግሞ ፈሶ አለመቅረቱን ነው የዛሬ መረጃ የሚጠቁመን።

 

በሌላ በኩል ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደ ትውልዱ የዘመኑ ቤተኝነታቸው ሴቶችን ወደ ፖለተካው መድረክ በአቅማቸው ልክ ወደፊት የማምጣትንም ልዩ ተልዕኮ ሰንቀውት የነበረው የህሊናቸው የቤት ሥራ ስለነበር፤ ይህንም ድርጊት ላይ ድርጊት ላይ አዋውለውታል።   


ይህም የአሜሪካ መንግሥት ልዩ ግምት ከሰጠው ሌላው አንኳር ጉዳይ ነው። በተጨማሪም በባዕለ ሹመት ንግግራቸው ላይ ኤርትራን በፍቅር  ነይልን በማለት ብቻ ሳይሆን የአልጀርሱን ስምምነት ወደ ተግባር ለመተርጎምም ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ደፋር እርምጃ ወሰደዋል። እንዚህን አንኳር ጉዳዮች ልብ ያለው የአሜሪካ መንግሥት ምን እንርዳችሁ እስከ ማለት እንዳደረሰው የኢበሲ ዘገባ ይገልጣል።


በሌላ በኩል ዶር አብይ አህመድ ከሳውዲ እና ከአረብ ኢምሬት 

ጉብኝት ማግስት ፈላሳማው ኢትዮጵያዊ ዶር ምህረት ደበበ ባዘጋጁት የመልካምነት ጉባኤ ራሳቸው እንደ ነገሩን „እኛ አንድ ስንሆን እኛ ስንጠንክር እረዳቶቻችን ወደ እኛ እራሳቸው ይመጣሉ፤ ምን እንርዳችሁ ይሉናል“ ያሉት ትንቢት ይፈጸም ዘንድም ነው።

 

·      ወግ።

 

አሜሪካ አገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆኑ  የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ፍቅርን አቅንተው ፍቅርን በገፍ የሸመቱበት ወቅት ነበር ከሀምሌ ከ19 ጀምሮ የነበረው ድባብ። ድባቡ እጅግ መሳጭ እና በውንም ኢትዮጵያዊነት ከፍ ብሎ ልዕለ ሃያል ሆኖ የወጣበት ወቅት ነበር። የአብይ ሌጋሴሚ በህሊና እንዳሻህ ሁንበት የተባለበት ነበር።

 

በፕሮፓጋንዳ እና በቅስቀሳ ሞገድ ሳይሆን፤ ወገን በህሊናው ፈቅዶ እና ወዶ እንዲሁም ወስኖ በዬስብሰባው በልዩ ጥሞና እና ፍቅር የታደመው ወገን  ኤርትራውያንንም ጨምሮ  ሙሉ ቀን ተሰልፎ ነበር ከተስፋው

ጋር የተገናኘው። ትንግርት ነበር ሁኔታው ሁሉ።

 

በጠ/ሚር አብይ አህመድ የተመራው ሉዑክም ደከመኝ ሳይል ሌት እና ቀን የወገኖቹን አገራዊ ፍቅር በአግባቡ አክብሮ በተጠራበት ሁሉ በመገኘት አንቱ የሆነ ተግባርን ካለ በቂ እንቅልፍ ከውኗል። የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እርቀ ሰላማዊ ሂደትም በታምር የተጠናቀቀበት ወቅት ነበር።

 

ይህን በአደብ፤ በተደሞ፤ በተመስጦ የተከታተለው የአሜሪካን መንግሥት አንድ ልዑኩን ሰሞኑን በኢትዮ አፍሪካ መዲና ወደ አዲስ አባባ ልኳል። ልዑኩ የመከላከያ ጉዳይን የሚመለከት ነው።



የልዑኩ መሰረታዊ ጭብጥ መነሻ እና መድረሻ ያን ያህል የህዝብ ፍቅር እና ተቀባይነት የተናኘለት የአብይ ካቢኔን በመከላከያ ዘርፍ በአቅም ግንባታ እና አቅሙን ሙያዊ አድርጎ ለ21ኟው ምዕተ ዓምት ጋር እንዲመጥን አድርጎ ለመገንበት፤ ለማዘመን በራሱ ፈቃድ በራሱ ተነሳሽነት ልዩ መስህብ ያለው ግብዣ አቅርቧል።

 



እንደ መከለካያ ሚኒስተር ሚንስተሯ ኢንጂነር አንሻ መሃመድ አገላላጽ ይህን መሰል እርምጃ አሜሪካ ወስዳ አታውቅም ባይ ናቸው፤ ማስልጠኛቸውን ፕላናቸውን፤ የተግባር መስኮቻቸውን በተንቀሳቃሽ ተቋምነት ኢትዮጵያ ድርስ አመጥተው እንደሚከውኑት ነው የገለጹት።

 

የመከላካያ ሚኒስተር አካሉ የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄ/ ብርሃኑ ጁራ አገላለጽም ለመከላካያ ሪፎርም ስልጠና ላይ፤ አቅም ግንባታ ላይ ለመሳትፍ ምን እንርዳችሁ ግብዣ መቅረቡን፤ የመከለካያ አካልም ለልዑክ ቡድኑ ያቀረበለትን ጥያቄ ሁሉ በሙሉ ሁኔታ መቀበሉን ተገልፆል።

 

በዚህ ውይይት ላይ ያስደሰተኝ መደምደሚያው የባህላዊ ትሩፋታችን ስጦታ ነው። አገር ባህል ልብስ። ፍቅር፤ አክብሮት፤ ታሪክ፤ ትሩፋት፤ እሴታዊነት ቀን ወጣላቸው። ዘመን ሲሰጥ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ በአንድም በሌላም ጎልቶ እና ጎልብቶ ይወጣል። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና።

 

ጉዳዬ እኔ የቃላ ምልልሱን የቡድኑን ተልዕኮ አይደለም እሱን እናንተው ውዶቼ ሂዱበት። የአብይ ሌጋሲ ዓለም እንዴት እየታደመበት ስለመሆኑ ለማዘከር ነው።

 

ይተዋቃል በስሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስቲባል ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ መጥቼ ላግኛችሁ ማለታቸውን ተከተሎ ኮሜቴው ጥያቄውን ተቀብሎ ከፈቀደ ወዮ ተብሎ ነበር። እኔም ያን ጊዜ ቅናት እና ምቀኝነት ነው፤ ፈቀዱ ከሆነ ይሳካ ካልሆነም ይቀር ብዬ ጽፌም ነበር። በዛ ወጀብ ምክንያትም ኮሜቴው ውሳኔው አሉታዊ ሆነ። ፉክክር ስለተያዘ። መቼም ኢትዮጵያ ከፍ ብላ መታዬት ያለበት በዬስሜታችን በተከተመው የወረቀት አምልኮት ነውና።

 

ሌሎች ቅኖች ደግሞ እኛም የማድረግ አቅም አለን ብለው ያን የግርዶሽ እና የክትር ግንብ አፍርሰው ሲነሱ በወዘተረፈ ዘመቻ ያን ቅናዊ፤ ፍቅራዊ ልባዊ ጥያቄ ማሰናከሉ ሲቀር፤ ቢችሉ አተራምሰው ለማስቀርት ተሞከረ፤ ሲጠንክር ደግሞ ባለሟል ሆነው ተገኙ። ሽርክቷ ዓለም

 እንዲህ ናት።

 

ብቻ ከአሉታዊነት ወደ አዎንታዊንት ሽግግሩ  ምክንያታዊነቱ ለጋህዱ ዓለም ሰዎች አይደለም ትናንት ዛሬም ሊገለጥል አልቻለም። ያን የህዝባዊ ፍቅር ሞገድ የሚያግደው ማንም ምንም ሃይል አልነበረም

 እና ተሳካ። ስለምን? የአብይ ጥሪው እዮራዊ ነውና። ለዚህም ነው የተቃጣበትን የሞት ሰይፍ ሁሉ እራሱ አማኑኤል መክቶ ዛሬን የሰጠን። ተመስገን። የአውሮፓ ሃያላን መንግሥታትንም ጉዳይ በሚመለከት ያላፈው ወር ጭብጥ ያለውን ብሎናል፤ መልካም ዜናውን ጀባ ብሎናል እንደ ማለት።  

 

ቢስ አይይብን እንጂ ተስፋውስ እዬራዊ ነው ተመስገን።


ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን 
አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።