ኤርትራ እና የአማራ መሬት ጥሪኝ የምሥራች ብስራታዊ ዜና።

እርጥቡ የአማራ መሬት ጉብኝት ስኬትን ለኤርትራ እንሆ አበሰረ። 
ፍቅርንም በቅንነት 
አስከበረ!

„ምህረት እና እውነት ከአንተ አይራቁ
 በአንገትህም እሰራቸው።“
መጽሐፈ ምሳሌ ፫ ቁጥር ፫
ከሥርጉተ© ሥላሴ
 114.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 



ባላፈው ሰንበት ላይ የኤርትራው መሪ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና አቻቸው የሱማሌው ፕሬዚዳት ሙሐመድ አብደላሂ በጎንደር እና በባህረዳር ይፋዊ ጉብኝት ማደረጋቸው ይታዋቃል።

በዚህ ውስጥ ቅንነት እና ድንግልና ስለነበረ እንሆ የኤርትራ ምኞት ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሰለምና አንድነት ሊያጠናክር የሚችለው በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው ጥረት እና ልፋት ለውጤት ደርሶ ዛሬ ኤርትራ በተባበሩት ምንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት  ተጥሏበት የነበረው የኢከኖሚ ማዕቅብ የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ደምጽ ማጽደቁ ተደመጠ።

እትጌ ኤርትራ እና መንግሥቷ እንዲሁም ህዝቧ እንኳን ደስ አላቸው፤ ጉልህ ሚና የተጫወቱት ጠ/ ሚ ር አብይ አህመድ እንኳን ደስ አላቸው። የሱማሌው ፕሬዚዳንትም በጎ መንፈስ በዚህ ውስጥ ስላለ እንኳን ደስ አለው። ደስታው የአፍሪካ ሰላም ነውና። ኢትዮጵያዊነት መንፈሱን ሲያቀርቡት ረቂቅ ጠጋኝ መንፈስ አለው። 

ጥረቱ የተሳካው ቅንነት እንጂ የትርፍና የኪሳራ የብልጠት ስሌት ስላልነበረው ብቻ ነው። ይህን ማዕቀብ ለማስነሳት ብዙ ተሞክሮ „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር ሆናና“ ዛሬ የምሥራቹ ተደመጠ፤ እርጥብ እግር እና እርጥብ መሬት እንዲህ ሸክምን ያቃልላል።

ለአብይ ካቢኔ ሉላዊ የዲፕሎማሲያው ዕውቅና እና ክብርም ደረጃውን በዚህ ውስጥ ማዬት ይቻላል። ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ መንገድ ጀምራለች። ኢትዮጵያን አፍሪካን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ ያለው በትረ ሙሴ እንደ አሮን በትር በሄደበት ሁሉ ለምልም ነው። ተመስገን!

Ethiopian news ዛሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰበር ዜና Ethiopian special amahric news
የጸጥታው ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ አጸደቅ

የኔዎቹ ዝርዝሩን ትከታተሉት ዘንድ በትህትና እገባዛለሁኝ።  የኢህአዴግ አዲስ መግለጫም እሱንም እስኪ አዳምጥቱ። እኔ መግለጫዎችን ማጥናት ስለምሻ በጥሞና አዳምጬ የሚባል ከኖረው የምለውን እላለሁ፤ ከሌለው ደግሞ በልብ ሙዳይ ይቀመጣል። መግለጫ በጥሞና መጠናት አለበት። ጊዜም ይሻል። ኑሩልኝ።፡



ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሽንፎ 
የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።