ልጥፎች

ሰላሞች የተጎዳውን መንፈሳችን አከሙለን። ይባረኩ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ሰ ላሞ ች ! „ከቸር ሰው ጋር ሆነህ ቸር ሆነህ ትገኛለህ“ መዝሙር ፲፯ ቁጥር ፳፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·          መነሻዬ። መጣሁላችሁ ውዶቼ? እንዴት አላችሁልኝ። ስለ ሰላም ትርጉም ያለው ተግባር እንዲህ በኢትዮጵያ ህብራዊት ከተማ በነበረችው አዋሳ የሰላም ሐዋርያት ፈጠሙ። እሰቡ „በነበረችው“ ነው ያልኩት። አሁን ኦነጋውያኑ አዲስ የሰላ ቢላዋ ይዘው ደግሞ በአቶ ሌንጮ ለታ ፊታውራሪነት እዬሸነሸኗት ነው። መንፈሷን እያወኩት ነው አዋሳን፤ በሲዳማኛ ዜማ። የሆነ ሆኖ ዝርዝሩን ከጉዳዩ እንብርት ከፋና ቴሌቪዥን ዝግጅት እንድታዳምጡ በትህትና ጋብዤ እኔ ስለተሰማኝ ትንሽ ወግ ቢጤ ላዋጣ። https://www.youtube.com/watch?v=_15hZr_3BpE ሰላም የፋሺን ፌስቲቫል በሀዋሳ   „ሰላም“ ደስ ይላል። ይማርካል። ቢጠጣም፤ ቢበላም፤ በአፍ በአፍ በጉርሻ ቢያጣደፍም ተፈቅዶለት ነገረ ሰላም ሲፈጠር ታጥቦ ስለሆነ የተፈጠረው አይሰለችም - ለአደለው። እኮ ሰላም ድንቅ ነገር። የሰላም ሚኒስተር በማቋቋምም ከዓለም የመጀመሪያ ሆነናል። ይህን ስል መዋቅራዊ ይዘቱን ሳይሆን „ የሰላም ሚኒስተር “ የሚለውን ስንኙ መደፈሩን ማለቴ ነው። አዕመደ ማዋለ ምኸዋር ቃሉ ራሱ እንዲሆን መታሰቡ፤ መታጨቱ ድንቅ ነው። መዋቅራዊ ይዘቱማ የታጨቀ ነው።  በርካታ ጉዳዮች ተነባብረው ካልልክ ተወጥሮ በአንድ ሚ/ር ሥር ነው የወደቀው።  ነገር ግን „ሰላም“ የሚለውን ሃይለ ቃል እንዲህ አጉልቶ በማውጣት አረገድ ግን ዓለምን ሊያስተምር የሚችል ትልቅ ተምሳሌነት ተፈጥሟል። ቃል ሃይል አለውና።

ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ሊከፈትለት የሚገባ ገናና ማንነት ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዘመን ኢትዮጵያዊነትን ይከሳል - ይፈውሳልም! „ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፤ መንገዴን የሚያቃና፤ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ፤ በኮረብቶች የሚያቆመኝ፤ እግዚአብሄር ነው።“ መዝሙር ፲፯ ከቁጥር ፴፪ እስከ ፴፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                                      መካሻ! ·        ወግ ቢጤ በሲቃ … እኔዴት ናችሁ ክብረቶቼ? ዛሬ ወግ ወግ ብሎኛል … እንዲህ …  እኔ ውጭ ስወጣ ከገጠመኝ ፈተና አንዱ የኢሠፓ መደበኛ ሠራተኛ መሆኔን እንድደብቅ ነበር ምክሩ እና ዝክሩ። እኔ ደግሞ ምንም የማፍርበት፤ አንገቴንም የሚያስደፋ አንዳችም ጸያፍ ነገር ስላልሰራሁ በአደባባይ የኢሠፓ ቋሚ መደበኛ ሠረተኛ እንደ ነበርኩኝ አወጅኩኝ።  የሚገርመው ይህን የሚሉት በዘመነ ኢሠፓ የገበሬ እና የሠራተኛ ልጅ እዬተባሉ፤ ወይንም በራሱ በ ኢሠፓ ለከፍተኛ ትምህርት የተላኩት አውሮፓን ያጥለቀለቁት በስኮላርሽፕ ተልክው የተለያዩ ሙያ ሊቀ - ሊቃውንት የሆኑት ናቸው።  የበሉበት እጅ የሚቆረጥሙ … ደርግም እንደ ብአዴን እጁ አመድ አፋሽ ነው … ተጠቃሚው እራሱ አያመሰግነውም እኮ … ተጠቃሚው ስል በገሃዱ ዓለም ጨርቅና ወርቅ አይደለም ሙልጭ ያለ ድሃ ነው የ ኢሠፓ ይሁን የደርግ ሠራተኛ ፤ ግን በመንፈስ ልዕልና ጽናቱ አነቱ ነበር …  ሰብ በመቀረጽ ሂደቱም እጬጌ ነበር። ፍጽምና ከማንም ባይጠበቅም ለዛ ዘመን የሚመጥን የሚልቁ ብቁዎች ነበሩበት አበረው አመድ ለብሰው አይሆኑ ሆነው ባከነው ቀሩ እንጂ …  እማዝነው አሁንም ትውልዱ ለአዲስ ብ