የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለሰላም ዘብ መቆም ነው!

የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ
ተግባር ለክልሉ ህዝብ
ሰላም ዘብ መቆም ነው።

„አግዚአብሄርን የሚፈለግ ልብ ደስ ይበለው።“
መጽሐፈ መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲
03.11.2-18
ከሥርጉተ©ሥላሴ
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
አማራ ከዚህ መሪው ጎን መቆም ግድ ይለዋል።

 ጦርነት አውዳሚ ነው። ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ ቢኖር አመድ እና ቂም በቀል 
ብቻ  ነው። ቂም እና በቀል ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ጸር ነው። ጥቂት ሰዎች 
ለውጥ አልመጣም ይላሉ። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በቀና የሚዩት አንዳችም ነገር 
አለመኖሩ ሰው ከምን ተሠራ እስከማለት እደርሳለሁኝ። ፍጹምነት ከሰው 
መጠበቅ ዓይነት ነው። ግድፈት የለም ማለቴ አይደለም። ግድፈት ራሱ ሰውኛ
  እንጂ ሮበትኛ አይደለም። ብቻ ሁሉንም ድፍጥጥ ሲያደርጉት የትኛው 
ፕላኔት እንዳሉ ይገርመኛል። 

እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ግን የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ለውጤት የበቃ ነው
 ባይ ነኝ። ኮሽታ የማያሳማ፤ ዕወጁልኝ የማይል ለውጥ አለ። ቀውስ የለም ማለቴ 
ግን አይደለም። የግርግር ሙሽሮች በእጃቸው የሰሩት ቀውስ አለ። ያው ሁሉ 
የሥልጣን ጥመኛ አይደለ። ያ ያው ሁሉ የቤተመንግሥት ቀይ ምንጣፍ ምኞተኛ አይደለምን?

የአማራ የማንነት ህልውና ተጋድሎው መሰረታዊ ጥያቄዎች መፈታት ለመቻል 
የሥርዓቱ አዋራሪሶች ከሥልጣነ ገብታቸው በስልት ማስነሳት ነበር የመጀመሪያው
 ረድፈኛ ተግባር። ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ተከናውኗል። ርዕዮቱም ቢሆን ሞራው 
ነው ያለው። ይህ ስለተከናወነም በሁለቱ የአገር መሰረት ሃይማኖቶች ተፈጥሮ 
የነበረው የ27 ዓመት ስንጥቅ ተገጥሟል። ተቋም ለሚበላው ከኦርቶዶክስ 
ተዋህዶ እና ከእስልምና በላይ የሚኖሩት ለገሃድዋ ዓለም ዋናተኞች ሌላ 
ሊሆን ይችል ይሆናል። 

ለመንፈሳውያን ግን ከዚህ በላይ የመኖር ትርጉም የለም። ሃይማኖት አንድ ከመሆን
 በላይ ትውፊትን ማቆዬት የለም። ለጋህዳዊው ዓለምም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚቻል ይመሰለኛል። እኛ ዲዛይን ባደረግነው መልክ ሁሉን አፍርሶ በመገንባት 
ሳይሆን ምሶሶዎችን በመትከል መልካም ጥበባዊ ጅምሮች አሉ።

አንዱ የኤርትራ ችግር አፈታት ሲሆን ሁለተኛው የኢትዮ ሱማሌ ችግር አፈታት 
ነው። ሁለቱም የመካከለኛው አፍሪካን በተለይም የአፍሪካ ቀንድን ሰላም 
ለማስጠበቅ ወሳኝ እርምጃዎች ነበሩ። ስንቃወም ዕውነትን አብርን እምንድጥ 
ከሆነ እኛ ሰው የመሆናችን ሚስጢር ተዛንፏል ማለት ይሆናል። 

አሁን እኔ ይገርመኛል በቀደመው ጊዜ የህውሃት አንደበት ይባል የነበረው ድሬ ቱብ
 ዛሬ በቃ ጦር ሰበቃ ላይ ነው የሚገኘው። የተያዘ የተረዘዘውን ሁሉ ሲያብጠለጥል 
ነው የሚገኘው። አንድ ምሳሌ ባነሳ አሁን የፕሬዚዳንት ለውጥን በሚመለከት
 የተሄደበት መንገድ ይገርመኛል። ባይነግሩንም ሚስጡረን ደረስንበት ይለናል 
ድሬ ቱዩብ። ምን ሚስጢር አለው ይሄ ጠ/ሚሩ ኦሮሞ ፕሬዚዳንቱ ኦሮሞ 
ከባድ ነው በዞግ ፖሊሲ ለምትመራ አገር።

 ዜግነት ማዕክሉ ቢሆን በደርግ ጊዜ እንደዛ ስለነበር ትዝ የሚለው አይኖርም አሁን ሁላችንም ስስ ሁነናል። ስለዚህ መሆን የነበረበትን እርምጃ ደፍሯል የ ለማ አብይ 
ካቢኔ። ለዛውም በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ እናቷን አገኘች እስክንል ድረስ ወርቅ የሆነ
 እርምጃ ነው የተወሰደው። ድርብ እርካታን ያሰገኘ ነው።

ሴቶች ወደ ስልጣን በመጡ ቁጥር ደግሞ እናታዊ መንፈስ በካቢኔው፤ በቤተ-
መንግሥቱ አካባቢ ይነግሳል። መከላከያ ላይ ስናይ ቃለ ምልልሱ የአገር መሪነት
 ሙሉው ሃላፊነት ለመቀበል መሰናዶዎ ልዑቅ ነበር። ፍርድ ቤት ላይ ስንመለከት
 „በህግ አማላክ“ ሚስጢር መፍቻ ቁልፍ የተገኘበት ነው። ቀደም ብዬ እኔ 
ሳመለክት የነበረው አሁንም በኢህአዴግ ቢያዝም የኢህአዴግ ጽ/ቤት እና 
የዲሞክራሲ ግንባታ የሚለው በተወሰነ ደረጃ መነጣጠላቸውም የተሸለ 
እርምጃ ነው።

በ100 ቀናት ወስጥ ዋጋ ያልወጣላቸው፤ ተመን ያለተሰራላቸው ሐሴቶችን 
በምልሰት ስናስብ ህዝብ እና መንግሥትን ለማቀራረብ ሸጋ ተግባራት 
ተከናውነዋል። በዲፕሎማሲው ዘርፍም ቢሆን አንቱታን ያስገኙ መሰረቶች
 ተጥለዋል። ዕውነት የማይመስሉ ኪኖ የሚለስሉ የዳበሩ ተግባራት 
ተከናውነዋል። ክህደት የሰው ተፈጥሮ ስለሆነ ነው እንጂ። ከዛ ጥበቆ 
እስር ቤትም የወጣውም ለውጥ አልመጣም ይላል። የሚገርም ነው። 
ጸሐይ እስፈለጉ ድረስ መሞቁ ነጻነት አይደለምን? ውሃ ሲጠማ ብድግ
ብሎ መጠጣቱስ? መጻዳትን በፈቀዱት ሰዓት መከወኑስ። 

ቀድሞ ነገር ይህን ያህል አቅም ያለው መሪ በህልማችንም አስበነው አናውቅም። ለማንፌሰቶ ማህበርተኞች ሊኖራቸው ይችላል ግን ይህን ወዘተረፈችግር የመሸከም
 አቅም ያለው ግን በመብራት ስናፈላልግ ለኖርነው ሰዎች ዕድሉ እዮራዊ ነው ብለን እናምናለን። የወል ችግሩ አማራን በሚመለከት የተኖረበት ስለሆነ ብዙም ብርቅ አይደለም። የሚጠበቅ ነው። ከራስ ጋር መታደምን የሚጠይቅ ረቂቅ ስለሆነ። 
ለዛም መንፈስ ቅዱስ ካገዘ ነው። 

በጥቅሉ ሲታይ ግን አንገት የማያስደፋ ሁኔታ መኖሩን አሊ ማለት ከራስ ጋር መጣላት
 ነው የሚሆነው። በዞግ በተሸነሸነ በ9 መንግሥታት ሥር አሁን ወደ 10 እዬተሸጋገረ
 ነው የዜግነት ፖለቲካን ለማምጣት በምን ያህል ክህሎት ሲባል ውሃ ያዘለ ተራራ ነው። ይህም ሆኖ ስለምን ዘራፊዎች፤ በደለኞች፤ ገዳዮች በይቅርታ ሲለቀቁ እራሳቸው እኛን አላሳራችሁንም ብለው ሌት እና ቀን ሴራ ሲሸርቡ ውለው ያድራሉ። የሚገርመው 
ህልም የሚመስለው ነገር ለነተጋሩ ይህን የመሰለ ተደላድለው የመኖር ዕድል 
አያገኙም ነበር ለውጡ በዚህ መልክ በማስተዋል እና በጥበብ ባይመራ ኑሮ። 

ከሁሉም ተጠቃሚ የሆኑት እነሱው ናቸው። እነሱ ደግሞ አብሶ ሊሂቃኑ እንደ
 ለመደባቸው ኮሽ ባለ ቁጥር የሚያስደምጡት ሰው መሆናቸውን አደጋ ላይ
 የጠላ ነው። ስለምን ዋይታ ስለምን ኡኡታ አልሰማነም ባዮች ናቸው። ጭቆናው
 የወያኔ ሃርነት ትግራይ፤ አፈናው እና ረገጣው ስለምን ተነካ ባዮች ሆነዋል። ይህ
 ለእኔ እግዚዬሩን በጦር የመውጋት ያህል ነው። በደም የተነከሩት የትናንትም 
የዛሬም የህዋህት መሥራቾች እነ አቶ ግደይ  ዕድሜ ለአማራ ተጋድሎ እና ለኦሮሞ ፕሮቴስት ማለት ሲገባቸው ዛሬም ከበሯቸውን አብረው ከመታበይ ጋር ይደልቃሉ።
 አዴፓን እስከ መክስ ሄደዋል። ለዚህ ያበቃቸው አዴፓ እንጂ ህውሃት አይደለም።   

በሌላ በኩል በኦሮሞ ሊሂቃን በኩልም በዘመነ ደርግም የለመደባቸውም በአዲስ
 ካባ ለውጡን ተጥልለው አሁንም ሌላ አፍራሽ ትዕይንት ላይ እንደ አመላቸው
 እዬከወኑ ነው። ሌላውም የነበር ለምድ ለብሶ ቆዳውን አለስልሶ ይገዝግዛል። 
ይህን ሁሉ ተሸክሞ የተመጣጠነ ተግባር ለመፈጸም ያለው የመንፈስ አቅም ደግሞ የሚገርም ነው። 

ይህን ሁሉ ጉቶ ችሎ የ አብይ መንፈስ ወደፊት እዬገሰገሰ ነው። አብሶ የ60ዎቹ
 ትውልዱን ቢተውት ምን አለበት? አሁን አኮ ኢትዮጵያ ላይ የሚታዬው ወጣት
 ብቻ አይደለም ታዳጊ ወጣቶች ናቸው። እነሱን ሲታዩ አሁን ከልጅ ልጅ ልጅ ጋር ፖለቲካዊ ፉክክር ማድረግም እጅግ የሚገርም ነው። ምን አለ በቃን ቢሉ። ዘመኑም ማህበራዊ ንቃተ ህሊናውም አይገጥምም። ጨው እና ማርን የመቀላቀል ያህል ነው - ለእኔ። አክተር አይሞትም እናት ደግሞ አንጋች ታቀርባለች እንደ ብርንዶ ለዬዘመኑ ... 

ስላልኖርንበት ይህ የመፍትሄ አሰጣጥ ክህሎትን ልንለምደው አለመቻላችን
 ይመስለኛል ችግራችን። ብዙ ያልተለመዱ መልካምነቶች አሉ። ሲርቡን፤
 ሲጠሙን፤ ሰንሳሳላቸው የኖርን ርህርህናዎች አሁን ደግሞ ባልጠበቅነው ሁኔታ
 ከች ሲልልን ቸገረን። ሌላው የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ እንዲቀጥል የሚሹት
 ሴረኞች እንደ ተጠበቁ ሆነው። መልካም ነው እያሉ የሚመክሩት ነገር ደግሞ
 መርዝ አለ። መንፈስን የሚንድ። አብይን ከ ፍቅር የሚግጥ።

ለሲህ ደግሞ ደጉ ኮ/ጎሹ ወልዴ የጠ/ሚር አብይ አህመድ አማካሪ ከሆኑ፤ 
የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉዳይ ምሰሶ በቅጡ ከቆመ ብዙ ነገሮች ረብ ይላሉ ብዬ አስባለሁኝ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሆኑ ዶር ለማ መገርሳ ጽኑ አማካሪ 
ያስፈልጋቸዋል። አሁን እኔ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወህ ብያለሁኝ። ልባሙ
 ዶር ካሳ ከበደ ጉዳዩን በባለቤትነት ስለያዙት። እነዚህ ጉዳዮች ሰቅ ናቸው 
ለኢትዮጵያ አዲስ የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመፍጠር። 

ለነገሩ አልታዬን ብሎን ነው እንጂ የአንድ አገር የዴሞክራሲ ልኬታ ከመለኪያዎቹ
 አንዱ ያ አገር ለሴቶች በሰጠው ነጻነት ልክ ወይንም በፈጠረው መጠራቅቅ ይወሰናል የሚለውን እያዬን ነው። የመጀመሪያ የሰላም ሚኒስተር ሴት፤ የመጀመሪያ የመከላከያ ሚኒስቱር ሴት፤ እቴጌ ዘውዴቱ መርሃ መንግሥት ስለሆኑ ከአሁኑ ሹመት ጋር ማነጻጻር ባይቻልም ግን ባላሰብነው ሁኔታ የመጀመሪያዋ ፕሬዚዳንት ሴት፤ የመጀሪያዋ የሚዚና አዋራዊት ሴት፤ የመጀመሪያዋ መከለካያ ሚኒስተር ሴት፤ የንግድ ምክር ቤትም እንዲሁ ሴት መመረጣቸውን ሰምቻለሁኝ … ከሁሉ በላይ ውስጣቸው ጠረኑ ኢትዮጵያ 
ኢትዮጵያ ማለቱ ትልቅ የብሥራት መባቻ ነው። 

ጉዟችን ወደዬት ነው የሚለውን ቀያሽ የሆኑ እርምጃዎች እዬታዩ ነው … ከዴሞክራሲ አንዱ ፈተና ሴቶችን በ አቅማቸው ልክ ለማሳተፍ መፈቀድ ነው። እና ይህ የላዕላይ መዋቅሩ አውታር ነው። ዴሞክራሲ ሂደት ነው የሚባለው በዚህ የለውጥ እርምጃ 
ከሂደት የቀደመ ነው - ለእኔ። ዘመኔን ሁሉ ስታገልለት የኖርኩት መሰረታዊ አመክንዮ መሥመር ይዞልኛል።  ይህ የጎረበጣቸው ናቸው ቀልብ ለማሰብ፤ ትኩረት ለማግኘት 
እያሉ ሲያጣጥሉ የሚገኙት። እንዳሰቡት ጨለማ ሳይሆን ስለቀረ የተጋሩ ሴል ቤተኞች።  

ወደ ቀደመው ሃይማኖታዊ አመክንዮ ምልሰት ሳደርግ ለሰከንድ እኔ የቀደመውን
 ልዩነት አለሳብውም። እንደ ቅደስት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅነቴ ያን ባስበው
 ህሊናዬን ለዲያቢሎስ መንፈስ አሳልፌ ሰጥቻለሁኝ ማለት ይሆንብኛል እስከዚህ
 ድረስ እኔ በሙሉ ልቤ እና አቅሜ ልክ ውህደቱን ተቀብያዋለሁኝ። እኔ ብቻ 
ሳይሆን በትጋት የሚያገለግሉት ቤተሰቦቼም ሁሉ። እንዲያውም ሐሴቱ አሁንም
 ድረስ ወስጤን ያረስርሰዋል። 

ለዚህም ነው እጅግ የምሳሳላቸው የብጹዕ አባቴን የዕምነቴ ማተብ የሆኑት 
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ የአቡነ መርቅሪዩስ ፎቶ ፕሮ ፋይሌ
 ላይ ያደረኩት በተወለዱበት ዕለት አዲስ አባባ ቦሌ ላይ ሳያቸው ሙሉ ሐሴቴን ስላገኘሁኝ።

እርቁን ተቀብለው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያቀርቡላቸውን የአብሮ መጓዝ 
ጥያቄ ፈቅደው የተራዘመውን የጉዞ ቀጠሮ አሳጥረው እሺታን አስቀድመው
 መሄዳቸው የድሎች ቁንጮ ነበር ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። ለምድራዊ ዓለም
 ለተፈጠሩት እንኳን አይበጅም እንኳን ለመንፈሳዊ አለም እርቅን መግፋት

መስከረም 8 ቀን 2011 ነው ብለው አሻም ቢሉ እንኳን በምን ሁኔታ አቀባባሉም አትኩሮትም ሊሆን እንደሚችል አደጋው ስላልገጠመ አናውቀውም እንጂ እጅግ 
ከባድ ነበር። በሌላ በኩል የጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሞት መትረፍም በዛ ጉዞ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተከወነ የተከደነ እዮራዊ ሰማይ የዘመናችን የዕድማታ 
ሚስጢር ነው። ስለ ቡና ፖለቲካ አንድ ቀን ታሪክ ያወጣዋል።

አሁንም አጥር ቅጥር ሆኖ እዬጠበቃቸው ያለው ይኸው ነው። ከዛ ጉዞ በኋላም
ቢሆን  ሞቱም ኩዴታውም ቀጥሎ ጥበቡን ሰጥቷቸው ተርፈዋል። እራሱ የርዕሰ
 መዲናዋ የአዲስ አባባ ህውከት እና የተፈጠረው ሁኔታ ብዙ መንፈስን ያሸፈተ 
የበተነ ነበር እርምጃው የግራ ቀኙ። በሌላ በኩል የጅጅጋው የአብዬት 
ቤተክርስትያን እና የቅዱሳን ሰማዕትነት ጦስ ጦርነት የሃይማኖት ለመክፈት
 ነበር እሳቤው። 

የጎንደር የአማራ ታገድሎ አብዮት ድምጻችን ኢሰማ ሞቶው ነበር እና፤ ያን
 የታቀደውን አዲስ የቀውስ ሴራ የአከሸፈው የጎንደር የቅደስት ኦርቶዶክስ 
ተዋህዶ ሃይማኖት አማንያን የ44ቱ ታቦታ መንፈስ ቅዱስም ታክሎበት 
የሉላዊ የእስልምና እምነት ክብረ ባዕል በፋሲል ግንብ ቅጽር ግቢ አከባባር
 መሰናዶ ላይ ያደረጉት ከድንቅ በላይ የምርቃት ተግባር ነበር። ኢንሻአላህ!

የቡራዮ እልቂት እና የአርሲ የመስቀል ባዕል ወከባም ጎንደር የሚገኙ 
የእስልምና ዕምነት ተከታዬች የመስቀል ደመራን ባዕል መሰናዶ ራሳቸው
 በሃላፊነት ወስደው ፒያሳን ጽዳቱን ያጸዱት አንሱ ነበሩ። አቧራው ራሱ
 ገርሞኛል። ፒያሳ እኮ ንጹህ አስፓልት ነው የነበረው። ያን ያህል ጉድጓድ
 እና ድንጋይ ግርም ነው ያለኝ። 

የሆነ ሆኖ የተምሳሌት አናት ጎንደር የመሆን ርዕሰ መዲና ዓምድ! ወደፊትም
ጎንደር የለውጡን ሰለሙን ደስታውን ተስፋውን የመጠበቅ ርዕሰ ግዴታ አለበት።
 ጎንደር ሴረኞችን ሁሉ አክሽፎ ከለውጡ ጎን መቆም ቀደሚው ትልም ሊሆን
 ይገባል። ነገ የሚገኘው ዛሬ ሰላም ውሎ ሲያድር ብቻ ነው። ቅኔናው ዋርካው
 ጎጃምሻም እንዲሁ። ፈተናን ማለፍ የሚቻለው በተደሞ ሴሮኞች ባዘጋጁት ባቡር ባለመሳፈር ነው። 

  • ነገረ አማራ።

በአሁን ወቅት የአማራ ክልላዊ መንግሥት የጸጥታ ክፍል አላፊ ሆነው የተሾሙት
 የነፃነት አርበኛው ብ/ጄ/ አሳምነው ጽጌ ናቸው። በምርጫ ቢሆንም በህዝብ 
ድምጽ ከሳቸው የሚተካከል ከኮ/ ደመቀ ዘውዱ በስተቀር ለአማራ ማን 
እጬጌ አለውና በዘርፉ? 

ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል ይላሉ ጎንደሮች ብዙ ሰው ኮ/ ደመቀ ዘውዱን በሃሳቡ
 ሲያገል አያለሁኝ። ሆን ተብሎ ታቅዶ። ትልቅ ግድፈት ነው። ይህ ሰው ለዘመኑ
 ልዩ አይከን ነው። ለራሱ ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት መንፈሱ ጉልበታም ነው። ማስተዋል ላለው ሰው እቦታው አቤቱ ድረስ ተሄዱ ሊታይ የሚገባ የትወልድ ትውፊት ነው። ታሪክ ነው። የዘመን ግርማ ሞገስም ነው። 


የዚህ ሰው መንፈስ ዘመን የማይሽረው፤ ዘመን የማያገኘው፤ ዘመንን በልዩ ጥበባዊ
 ክህሎት የዋጃ ልዑቅ ነው። አሁን አሁን ሥሙን ለመጥራት የሚጠዬፉ ሰዎችን አዳምጣለሁኝ። እጅግ ይሰቀጥጣል። ለዚህ ሁሉ የምህረት ጉዞ እኮ የእሱ ተጋድሎ
 ያሰገኘው የመንፈስ ሃብት ነው። ማንም ሰው ማንም ሃይል የሱን መንፈስ ያህል ሞገድ የፈጠረ ትንግርት የሰራ የለም። ገናናነቱ የእርጋታው ጽሞና ልዑል እግዚአብሄር የቀባው ጸጋው ከቶውንም የሚደፈር አይደለም። ቅብዕ የእግዚአብሄር ነውና።

አማራ በዘመኑ ለትወልዱ እንዲህ ዓይነት መንፈስ አሰባሳቢ ድንቅ መሪ ለዛውም
 የመንፈስ ማግኘቱ እዮራዊ መሆኑን ማስብ ይገባዋል። ዛሬ እማናያቸው በአማራ
 ሥም ተከበሩ የሚባሉ፤ ዕውቅና አገኙ የሚባሉ ተንታይ የሚባሉ የሚሹሞ 
የሚሸለሙ ሁሉ የዚህ ጀግና ገናና መንፈስ ጥሪት ናቸው። 

  በዚህ ጀግና እንደ ገና አዎን እንደ ገና አማራ የመሰረዝ ውል ተቀዶ ዛሬ ኤርትራ
 ላይ ዛሬ ጅጅጋ ላይ መንፈሱን የሚጋሩ ቅኖች ቅዱሳኖች ተፈጥረዋል እንደ አቶ
 ሙስጠፋ ዑመር እንደ አቶ የማነ ገብርአብ ዓይነት። የኢትዮ ኤርትራ እርቀሰላም
 ከዚህ ለውጥ ጋር የተገኜ ሰማያዊ በረከት ነው። የለውጡ ጄነሬተር ደግሞ አማራ
 መሬት ነው። 

የዚህ መንፈስ ገናናነት ነው ብአዴን ከወደቀበት አዘቀት አገግሞ፤ የመስከረሙ 
ጉባኤው ከኢህአዴግ ጉባኤ በላይ በመላ ዓለም አትኩሮትን ስቦ አድማጭን 
አጓጉቶ እኩል የለውጥ አራማጅ ተብሎ እንዲታወቅ፤ እንዲደመጥ አትኩሮት
 እንዲያገኝ የሆነው። ዛሬ አብን ሳይቀር ኮ/ ደመቀ ዘውዱን ሥም ደፍሮ ለመጥራት ሲቸግረው አንድ ሁለት ጊዜ አይቻለሁኝ። አርበኛ ጎቤን ሲያነሳ እሰማለሁኝ። 

ጎቤ የተወለደው በጀግናው ኮ/ደመቀ ዘውዱ ነው። ያን ጥቃት ጠጥቼ አልተኛም
 ሲል ነው ሰማዕቱ ጎቤ በርሃ የወረደው። ጎቤ ባይሳዋም አብን አያነሳውም ነበር።
 ለቆመው ክብር ሳይሰጥ ለሞተው ክብር የታይታ ነው። ዛሬ አብን ይህን ያህል
 ድጋፍ ያስገኘው ኮ/ደመቀ ዘውዶ አማራነትን በጀግንነት ስናለጸው ነው። 
የመጋቢት 24 የተ/ሚር አብይ ንግግር እንዲት አድርጎ ነው መንፈስን 
የሰበሰበው። 

ለአማራርም የዚህ ሰው መፈጠር አማራነት ተቀብሮ እንዳይቀር ትንሳኤ ሆኗል።
 ይህ ሰው ባይፈጠር ዛሬ አማራ ስለ አባቶቹ ትሩፋት ተቆርቋሪነት እና ዘብ አደርነት
 ይህን የመሰለ ነፃነት አያገኝም ነበር። የዚህ ሰው መፈጠር ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል "የኦሮሞ የጋንቤላ ደም ደሜ ነው" እኮ ሚሊዮኖችን አሰባስቧል።
 የኦሮሞ ሊሂቃን አቅም አከርካሪ እንኩት ያደረገ ነበር። አልተደሰቱበትም ነበር። 

የ60ወ0ቹ ፖለቲከኞችም ትርክታቸው አፈር ድሜ ነው የጋጠው።  ጣና ኬኛ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እኮ የመጠው
 ከዚህ የ አማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ነው። ትናንትን እዬጣልን ዛሬን
 እናነጋለን ማለት አይቻልም። ለዚህም ነው ጎንደር ከማናቸውም መንግሥታዊ
 እይታ ውጭ እንድትሆን የምትፈለግበት ምክንያት። አሁን የ አብይ የድጋፍ
 ሰልፍ ከጉራጌ ዞን የላቀ ነበር ግን አስታዋሽ አልነበረውም። ያን መዘገብ ሲገባው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እስር ቤት ሄዶ ያን ነበር ያሳዬው። ድፍረት ባይኖርም 
ዕውነትን ከድኖ ነገን ማሰብ ራስን ማዋረድ ነው። 

Ethiopia -- Gondar people in support of Prime Minister Abiy Ahmed

| የጎንደር ሕዝብም እንዲህ ተደምረናል

Published on Jun 24, 2018

መነሻውን ያላወቃ መደረሻውን አያውቅም። ሺ ሚሊዮን ጊዜ ቄሮ የሚበላው 
ቄሮ ተጋድሎው የማስተር ፕላን ብቻ ነው የነበረው። ያም ቢሆን የአማራ መንፈስ ባይታከልበት የትም አይደርሰም ነበር። ወደፊትም። የኦሮሞ ፕሮቴስት በግፍ መከራ ከመቀበል ውጪ የትም አይደረሰም ነበር። ወደፊትም።

 በሌላ በኩል ዛሬ ላይ „ጣና ኬኛ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ለመንፈሳችን 
ያደረገው ጥበቃ ምን ያህል ነው ብሎ ሚዛን ውስጥ ለማስገባት ቢቸግርም
 ግን የሁሉም መሰረት የኮ/ ደመቀ ዘውዱ የአማራነት ተጋድሎ ገናናት
 የፈጠረው ህብር ህላዊነት ነው። ይህም ኮነሬል ቅብዕ ስለተሰጠው ብቻ 
ነው። ቅብዕው ሰዋዊ አይደለም።

ግርማው እራሱ የተለዬ ማህባ አለው። እርጋታው ተመስጦ ነው። የእሱን 
ክብር ለማስተጓጎል አሁንም እንደ ዘመነ መይሳው የሚታትሩ እኩዮች
 ቢኖሩም ዛሬ አማራ ታሪኩን የሚጽፉ ለልጅ ልጅ የሚያስተላልፉ ልጆች
 ስላሉት ችግር የለበትም። ፎቶውም  በዓለም ዓቀፍ መድረክ ተልኳል። 
የእሱ ይሁን የወ/ረት ንግሥት ይርጋ። 

ምን እምንሰራ ይመስላቸዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ከጀርመኗ 
ካንሰለር ጋር ቆይታ ምክክር አደርገዋል፤ ዶር መራራ ጉዲና ከእስር ሲፈቱም 
በኢንባሲው ክብር ተሰጥቷቸው ነበር፤ ቆሼ ላይ የደረሰው አደጋም ቀድሞ 
ሰንደቅኑን ኢንባሲው ዝቅ አድርጎ አውሎብለቧል፤ እሰረኞችንም ጉዳይ 
ክብርቷ እዬደወሉ ይጠይቁ ነበር። ይህ በችሮታ የተገኘ አልነበረም በተጋድሎው
 የተገኜ ውጤት ነው። 

በጣም በእርግጠኝነት እኔ እምናገረው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሉላዊ
 የመቻቻል እናት ክክብርት መራሂተ መንግሥት አንጂላ ሜርክል ጋር ሲገናኙ
 የነበረው ግላዊ የውይይት መንፈስ ባዕዳዊ እንግዳዊ ሳይሆን ልዩ የሆነ 
ቤተሰባዊ እና የተመቸ ጊዜ ሊሆን እንደሚችል ደፍሬ መግለጥ እሻለሁኝ።
 ልባዊ እንደ ነበርም አሳምሬ አውቃለሁኝ። ስለምን? ቀድሞ ደልዳላ 
ጉዝጓዙ ተሰርቷል። ዛሬ ሚሊዮን አብይ ኬኛ ሳይል በቅጡም 
ዕውቅናቸው እንደዛሬው ሳይገኝ። ሁሉም ማዕቱን ያወርድባቸው 
በነበረ ጊዜ። 

ወደ ቀደመው ነገር ስመለስ አማራ ክልል አንድ ጥሩ ነገር ያደረገው ሜ/ጄ/
 አሳምነው ጽጌን የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ አድርጎ መመደቡ ነው። እሳቸውም
 ማንም በተኛበት ወቅት ማንም ባላስተዋለበት ወቅት፤ ችግርን ቀድመው
 በማዬት ራሳቸውን የማገዱ ብሄራዊ ጀግና ናቸው። እኒህ ብሄራዊ ጀግና
 መሪ በሆኑበት ቦታ ላይ አማራ ጸጥታን ቢያደፈርስ ውርዴት ነው።
 ውርዴም ነው።

ከማንም ከምንም በላይ አማራ ክልል እያንድንዱን ሁኔታ ዘብ ሆኖ ክልሉን
 መጠበቅ አለበት። ለውጡን አምጥቷል ራሱን ገብሯል። ራሱን ገብሮ 
ያመጣውን ለውጥ ደግሞ ራሱ ተቃራኒ ሆኖ ማፍረስ፤ ማቃጣል አይገባውም።
የጎደለ ነገር፤ ያልተሟላ ነገር ሊሟላ የሚችለው አገር ሰላም መሆን ስትችል
 ብቻ ነው። አገር ሰላም መሆን ካልቻለች ሰው የራሱንም ልጁንም ማዳን 
አይችልም።

ጥያቄዎችን በሥርዓት ማቅረብ ማለት ህውከት በመፍጠር መሆን አይገባውም።
 አማራ ስንት ጠላት እንዳለበት ማወቅ ይገባዋል። እንኳንስ አጥፍቶ ሳያጠፋ እንኳን መከራውን ኑሮበታል። በዬከተሞቹ ብጥብጥ እንዲነሳ ያለሙ ወገኖች እንዳሉ አማራ ማወቅ ይኖርበታል። ስለዚህም አማራ ከአዴፓ ጎን በመቆም ጸጥታውን የራሱ መሆኑን ተገንዝቦ መጠበቅ ይኖርበታል። 

ልባሙ ጎጃም ቅኔነቱን መወጣት ይኖረብታል፤ ርዕሰ የለውጥ ሐዋርያው ጎንደርም
 እንዲሁ፤ አቤቱ ሸዋም እንዲሁ፤ ደጉ ወሎም እንዲሁ። ነገ የተሻለ ቀን የሚሆነው
 ዛሬን የተሸለ ለማድረግ የጸጥታው ዘብ አደር መሆን ሲቻል ብቻ ነው።

አማራ መሬት ላይ የሚንቀሳቀሱ የአማራ ድርጅቶችም ቢሆኑ ለለውጡ እነሱ
 ራሳቸው ዘብ ሊቆሙሉት ይገባል። ለውጡ ሊያደርግ የሚገባውን ከግቡ 
የሚያደርስው ተጨማሪ የቤት ሥራ፤ ተጨማሪ ራስምታት የሆኑ ነገሮችን 
ካልተፈጠሩ ብቻ ይሆናል። በጥሞና፤  በአርምመሞ ሆኖ ቢታሰብ ይህ ለውጥ
 ቢቀለበስ ምን ይኮናል ብሎ መመርመር ያስፈልጋል። 

ምርቃት ካልተጠቀሙበት፤ ካላከበሩት፤ ካልተንከባከቡት ይነሳል። አሁን 
የምርቃት ዘመን ነው። ከታወቀበት። የ50 ዓመት ችግር በማሽን አይወገደም።
 ቅዱሳን መላዕክት አይደሉም አገር እዬመሩ የሚገኙት። እኔ አማስበው ለውጥ
 የሚለው ሁሉ ቤተሰቡን እንኳን ማሰተዳደር ተስኖት ሲበትነው የኖረ ሊሆን ይችላል። ለመሆኑ የትኛው ህብረት እና ቅንጅት ነው ሰንብቶ የሚያውቀው?

መቼውንም ዘመን፤ መቼውንም የለውጥ ዓይነት ቢመጣ ይህን የመሰለ ታሪካዊ 
ለውጥ የአማራን የአባቶቹን ሌጋሲ ያሰጠበቀ ድል አይገኝም። ይህን ለውጥ 
የእኔ ሊለው የሚገባው ከሁሉም በላይ አማራ መሆን አለበት። እዮባዊነትን
 በመሰነቅ። ሙያን በልብ በማድረግ።

አማራ የሚባል ማህበረስብ ኢትዮጵያ መሬት የለም። የሌለ ነገር ሊወከል አይገባም፤
 በባዶ መሬት መባሉን የጣሰ ገደል ነው የተፈጸመው። ይህን ገደል ያለፈው ሳምንት
 ሰላማዊ ሰለፍም በህብራዊነት አትሞበታል!

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም አንዲት ባለሥልጣን ሴት ናቸው፤ የሰላም ሚነስተሯ፤ 
የመከላከያ ሚነስተሯ፤ ፕሬዚዳንቷ፤ የጠ/ፍርድ ቤት ሚዛኗ ሁሉም ለእውነት
 አይቆሙም ብሎ ማሰብ ጅልነት ነው። በእውቀትም፤ በልምድም በተመከሮም
 የት እና የት ይደራረሳሉ እና። አብሶ ፕሬዚዳንቷ እና ፍትኽዋ ሊሂቅ ሉላዊ 
ናቸው እኮ። በሰብዕዊ መብት ዙሪያ የደባረ ተመክሮ ዕውቅና እና ክብርን 
የተጎናጸፉ። ሰው ነኝ አማራነቴም ሰዋዊ ነው ጥያቄ የሰብዕዊ መብት ጉዳይ ነው። 

እናንትነት እውነትንት ስለሆነ አሸናፊው ዝርፊያ ወረራ ሌብነት ሳይሆን ሃቀኝነት
 ብቻ ነው። እናትነት ነፃነት ስለሆነ ለነጻነት ኢትዮጵያ የልቧን አግኝታለች። 
እናትነት እዬራዊ ሽልማትነት ስለሆነ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆናለች ትሆናለችም። 
ስለዚህ አማራ የዚህ ሁሉ የዚህ ዘመን የለውጥ አስመጪ፤ አስገኝ ሃይል መሆኑ 
ከልቡ ሊያስተውለው ይገባል። 

አማራ እኔም እራሴን ገብሬበታለሁኝ ብሎ ማሰብን ማስቀደም ይኖርበታል። 
ብአዴን/ አዴፓ ባያደመጥው እኮ ለውጡ እንደ ግብጽ ባክኖ ነበር የሚቀረው። 
ይህ እኮ ትልቅ ልቅና ነው። ማድመጥ እኮ ልዩ ሥጦታ ነው። ክህሎትም ነው። 
የምትማሩት። በንግግር ጥበብ የትህርት ክ/ጊዜ ማድመጥን ትማሩታላችሁ።

ይህ እኮ ትልቅ ጥበብ ነው የተካፋን ማድመጥ። ዕድሜ ለአቶ ደመቀ መኮነን፤ ዕድሜ ለዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ዕድሜ ለዶር አንባቸው መኮነን፤ ነፍስ ይማር ለቆመስ ተስፋዬ ጌታቸው በማለት አማራ ለለውጡ ባላ እና ወጋጋራ ማገር መሆን አለበት። ፈቅዶ፤ ወዶ። 

ግንቦት 7 ቢያሽንፍ የአማራ ታሪክ ሊሆን አይችልም ነበር፤ ኢህአፓ ቢያሸንፍ
 የአማራ አይደለም፤ ሰማያዊ ቢያሽነፍ የአማራ አይደለም። ስለምን? ህብረ 
ብሄራዊ ስለሆኑ። ለዚህም ነው የአማራን ተጋድሎ „የነፃነት ሃይል“ በሚል
 እንዲጠራ የተፈለገበት ምክንያት ከልብ ሆኖ አማራ መመርምር ይገባል። የታሪክ ሽሚያው፤ የኮፒ ራይት ሽሚያ ሁሉ የመጣው ከዚህ ነው። የ አማራ ሥም መጠራት ስሌለበት። ለውጡ ሂደቱ ተጋድሎው የአማራ ህዝብ አካል ነው። ታሪክን አሳልፎ 
የሚሸጥ ባንዳ ብቻ ነው። ለታሪኩ ዘብ መቆም ደግሞ የ አያት ቅድመ አያቶቻችን
 ትሩፋት ነው።  

ታሪኩ አማራ ጎልቶ እንዳይወጣ የተወሰነበት አመክንዮ ነበር። ግን ምርቃቱ የፈጣሪ ስለነበር የሆነው ሆኗል። ከሆነም በኋዋላ ደግሞም ይህን በሸፍጥ ለመደለዝ ብዙ መንገድ ተሂዶበታል። አማራ የሚባል ሥሙ ራሱ እዬኖራችሁበት ስለሆነ ታውቁታላችሁ። ሌላው ቀርቶ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ማለትን ደፋሪ የለም። አብን እራሱ ይህን ደፍሮ አይናገረውም። እንኳንስ ሌላው።

ስለዚህ አማራ የራሱን ታሪክ ራሱ ላለመብላት፤ ላለማስበላትም አደብ እንዲኖረው
አበክሬ እመክራለሁኝ። አማራ በራሱ ጊዜ ልዑል እግዚአበሄር የሰጠውን ችሮታ፤ 
ጸጋ፤ በረከት መጋፈቱን ማቆም አለበት። 

ነፃነት ጀመርኩኝ የሚለው ሁሉ ማገዶ እያደረገ የራሱን አክተር ሲያወጣበት የኖረበት ዘመን እንዲያከትም አማኑኤል እራሱ የታደመበት መሆኑ አማራ አውቆ እና መዝኖ ለሰጠው አቅም ሁሉ ለፈጣሪ / ለአላህ ምስጋና ማቅረብ የሚችለው አማራ ለውጡን በመጠበቅ፤ ለውጡን በመንከባከብ፤ ባገኘው ጥሩ ነገር ፈጣሪን ተመስገን በማለት 
ይሆናል።

አዴፓ ቢሆን ያደረጋቸው መልካም ነገሮች ስላሉ ጥያቄውን አዳምጦ ሰፊውን የለውጥ እውራ ድርሻውን ተውጥቶ የአማራ ስለሚባል ጎልቶ እንዲወጣ ባይፈለግም ግን እራሱ የአማራ ህዝብ የእኔ ሊለው ይገባል። "ባለቤት ያቀለለውን ባላሞሌ አይቀበለውም" እንዲሉ። እያንዳንዱ በዬዕለቱ የሚፈጠሩ አስደማሚ ክንውኖችን የአማራ ተጋድሎ
ክፍለ አካላት መንፈሶች ናቸው ብሎ መቀበል ያስፈልጋል። ኤደፓም ለውጡ
የአማራ ስለመሆኑ አብክሮ ሊታገልበት የሚገባ ነው። ታሪክን፤ ትሩፋትን፤ ትውፊትን አስልፎ ሌላ መሸለም አይገባምና።  

ስለሆነም ከለውጡ ከጎኑ ሊቆም ይገባል - አማራ። እነሱንም አይዟችሁ ሊላቸው 
ይገባል። ሁሉ ነገር በአንድ ጀንበር አይሳካም። የ50 ዓመት ሙሉ የአማራ ጸር 
ጉዳዮች ጥቅልል ብሎ ከባህር ከገደል በአንድ አፍታ አይገባም። ይህ በድግምት 
በ አዚምም የሚቻል አይደለም። ተበክሏል አዬሩ ራሱ። ብዙ የመንፈስ ተግባር 
በስክነት መከወን አለበት። ከሁሉ ግን አማራ በተፈጥሮው ልክ መሆን ከቻለ
ካለ አስተማሪ ነገሩ እልባት ያገኛል። በመሆን ውስጥ ነው ዳኝነት የሚገኘው። 

እራሱ በለውጡ ውስጥ ያሉት በህሊናቸው ውስጥ የከተመውን የጥላቻ እከክ
 እስኪድን፤ ከመንፈሳቸው እስኪያስወግዱት ድርስ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። 
እንዲድኑ ደግሞ አማራ በተፈጥሮው ውስጥ ሆኖ አብነቱን ሊያሳያቸው 
ይገባል። ህግን በማክብር። ህግን ሳይተላለፍ ለህግ መከበር ዘብ አደር ሲሆን።
 ደስታን በልክ በመያዝ፤ ቀጣዩን ትግል በተደራጀ ሁኔታ በመከወን ከግቡ 
አማራ ይደርሳል። አማራ ዜጋ የመሆን ትልቅ ጎል ነው ያለው። 

የአሁን ዜግነት የለበጣ ነው "እንዳያምም ጥራው እንዳይበላም ግፋው" ዓይነት ነው። ስለዚህ ተጋድሎውን በቁንጽል አይቶ ትጥቅ መፍታት አያስፈልግም። ረቂቅ ፈተናዎች
 አሉ። በጊዜያዊ ሸብ ሸብም አብሮ ከበሮ መምታት አያስፈልግም። አማራ አገር
 ሊኖረው ይገባል። አገር ቢኖረው ለዚያ ቢያበቃውም የአባቶቹም የተደሞ የማስተዋል ሌጋሲ ለማስቀጠ መትጋት ይኖርበታል።   

ለምሳሌ እንዲለውጥ የሚፈለገው ፓሊሲ ሊለወጥ የሚችለው በፖለቲካ ድርጅት ተደራጅቶ አመራር አካል ሆኖ ድምጽ መስጠት እና መንሳት ካልተገኘ ከሰማይ 
የሚገኝ ችሮታ የለም። ማንም ፈቅዶ ለ አማራ ቁልፍ ቦታ አይሰጠውም። 

ይህን ውል የሚንድ መንፈስ ቅዱስ መሬት ላይ የለም። ለዚህ ነው ዶር አንባቸው 
መኮነን መገለል የሚያርመጠምጠን። የመወስን አቅሙ ስለተነፈገው። ከትልቁ 
የፖለቲካ ልቅና ወርዶ ተንሳፋፊ እንዲሆን ስለተደረገ አሁን የሚ/ምክር ቤት አባል አይደለም ያ ትንታግ ይህን ቀን እንዲመጣ ራሱን የገበረ አንበሳ ነበር። ለነገሩ በህይወት 
መቆዬቱ ነው ለእኔ ቁም ነገሩ። የሚሆነው አይታወቅም። 

እሱ ብቻ አይደለም ፌድራል ላይ የአማራ ውክል አካላት ወደ ማህበራዊ ጉዳዮች ነው የተገፉት፤ ይህም ሌላው አደጋ ነው። ለዚህ ደግሞ አዴፓ ይህን ካለ ይሉኝታ መዋጋት ይኖርበታል። ምክንያቱም ለውጡን እዚህ በማድረስ ረገድ ወሳኙን ሚና የፈጸመው ያለጥርጥር አዴፓ ስለሆነ። ዕውን አዴፓ አማራዊ የመሆን ፈተናውን ካለፈው።

 በሌላ በኩል የፖለቲካ ሥልጣን በማግኘት እና በመጣት መከካል ያለውን ልዩነት ህብረተሰቡ በውል ማወቅ አለበት። ይህ ከሆነ አቅሙን አያባክንም። አቅሙን የትም አይበትንም። መንፈሱን ላልተገባው ቦታ አይገብርም። ወኪሉ ነው ለእሱ ሊሟገትለት የሚቸለው። መብት በስማ በለው አይገኝም። ስለሆነም ተደራጅቶ መታገል ለይደር 
ሊቀጠር አይገባም። አንድ አመት ከመንፈቅ ነው የቀረው። ዛሬ ያልተሰናዳበትን ነገ
 ከዬትም አይገኘም። አማራ ትንታግ ሊሂቃንን ወደፊት ማምጣት ይኖርበታል።

የቀድሞው ኦህዴድ የዛሬው ኦዴፓን እኮ በመታመን ረገድ ብዙ ችግር እንዳለበት
 እኛ ሳንሆን ምዕራባውያንም ይህንኑ ስለማለታቸው ራሳቸው ነገረውናል። 
መታመመን እንዲኖር ያደረገው አዴፓ እና የአማራ ልጆች በሁለም መስክ 
እንቅልፍ አልባ ለአንድ ሙሉ ዓመት ሌት ተቀን ተግተን በመታገላችን ነው። 
ኦዴፓዎች ይሆኑ ከዛ የተገኙት አብይ ለማ መንፈሳቸው ማተቡ ከኖራቸው አንደ 
ሰው ማሰብ ከቻሉ ሃቁ ይህ ነው። የእነሱ ሰዎችማ እኛ የገነባንላቸውን መታመን
 በአንድ ሆነው ንደውላቸዋል። ዓለምም ጉድ ብሏል። ያ እነሱን ሲፈርስ ለኖረ 
ሚዲያ ሁሉ አጥር ቅጥር ሲሆኑ ይደመጣሉ። አልፈው ተርፈውም ሚዳያቸውን አስረክበዋል። 

ለዛሬዋ ለውጥ አማራ እጅግ ደክሞበታል። የእነሱ ሰዎች አሁን በሸራተን የሞሸሯቸውን ዕውቅና እንዲያገኙ የተጉላቸው ምን ሲያደርጉ እንደ ነበር፤ አሁንም ምን እያደረጉ እንደ ሆነ አገር ያውቀው ጠሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። እዚህ ላይ ነው ፍትሃዊ ሰውነት የሚጠይቀው።

የሆነ ሆኖ አማራ በትናንቱ የውሃ ልክነት እሰጣ ገባው መነሳቱ ግድ ቢልም ኮንፕሊክሱ ስላል የአሁን የሚታይ የሚዳሰስ የሚጨበጥ ሃቅ ደግሞ ወለል ብሎ እዬታዬ ነው። 
አማራ ለዬዘመኑ አይከን ነው። ይህ ግን ለመኩራራት፤ ለመመካት፤ ተቆልሎ ለመታበይ ከሆነ ተግባር ከሌለበት ተረት ሆኖ ይቀራል።

ስለዚህ አብሶ በአማራ ክልል የሚኖሩ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ ደስ ብሏቸው በተረጋጋ ሁኔታ፤ በሰከነ ሁኔታ የተለመደ ኑሯቸውን ይመሩ ዘንድ ዋልታ የአማራ ልጅ ሊሆን ይገባል። ዜጋ ኢትዮጵያ አገሩ ናት። ማንኛውም ዜጋ በአገሩ ኢትዮጵያ የመኖር የመሥራት መብቱ ሊከበርለት ይገባል። ለዚህ ደግሞ እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ተግቶ ከአዴፓ ከሜ/ጄ/አሳምነው ጽጌ ጎን ሆኖ ሰላሙን፤ ደህነንቱን ማስከበር ይኖርበታል። 

ሁሉም እኔም አሳምነው ነኝ ማለት ይኖርበታል። ጎረቤቱን መጠበቅ፤ ለጎረቤቶቹ ልጆች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት። ለዜጎች ሃብት ንብረትም አኩል ጥበቃ ማድረግ ግዴታ አለበት። ይህ የምርቃት ዘመን እንዳይነሳ አማራ በተፈጥሮው ውስጥ መስከን ይኖርበታል። ረብ ማለት። አማራ ቂም እና ቁርሾን መጸዬፍ ይኖርበታል። አማራ የዛሬውን የተባረከ
ቀን አክብሮ ፍቅር ሰጥቶ፤ ፍቅር ሆኖ ፍቅርን ማስበል ይኖርበታል። 

ማሰብ ያለበት አማራ ያልተጋባው፤ ያልተዋለደው፤ አበልጅ ያልተነሳው፤ ማህበር ዝክር አብሮ የማይታደምበት፤ በክፉም በደጉም አብሮ የማይኖረው አንድም ወገኑ የለም። አባቶቹ ከውጭ ዜጎች ጋር እንኳን ጋብቻ ፈጽመው ልጅ ወልደዋል። የአጼ በካፋ ባላቤት እቴጌዋ እኮ በግማሻቸው የውጭ ዜጋ ናቸው። ሌሎችም እንዲሁ። ሥልጣኔ ማለት እንዲህ ነው።

ስለሆነም ሰላምን ለመጠበቅ የገዛ መንፈስን ሰላም ማድረግ ይፈለጋል። መንፈስ ሰላም ከሆነ ለህውከት ቦታ አይኖርም። እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ህውከትን ተጸይፎ፤ ልዩነትን ተጸይፎ፤ ማዕከላዊ መንግሥትን ማጨናናቅን ተጸይፎ፤ ለራሱ ለውጥ ራሱ ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባል። ቀን አብረው ሲገነቡ ማታ ሲፈርሱ ከሚያድሩ የራስ 
ተሰማ ናደው ሴረኞች አድማ ጋር አማራ መተባበር አይገባውም። እነሱ እሱም
 ቀና እንዲል እንደማይፈቅዱለት ሊገነዘብ ይገባል - አማራ።

የትም ቦታ የአማራ ልጅ ለአንጣፊና ለጎዝጓዥነት ወይንም መንገድ ጠራጊነት እንጂ
 ከዛ ያለፈ ተግባር አያገኛትም። ሲደላ ሲደላደል የራሱን ዞግ ነው አትኩሮት፤ እውቅና እንዲያገኝ የሚተጋው ሁሉም። ይህን ተኑሮበታል። ጥገኛ አለመሆን የሚቻለው መንፈስን የራስ ጌታ በማድረግ ላይ ብቻ በማማከል ይሆናል።

ሙያ በልብ በመሆኑ አማራ በሁሉም መስክ የራሱን ድርጅት የማደራጀት አስፈላጊነት
ቸል ማለት የለበትም። ከዚህ በተጨማሪ የአባቶቹን የሚስጢር ሌጋሲ ለማስቀጥል እያንዳንዱ የአማራ ልጅ ግዕዝን በህይወቱ ውስጥ አንደ አንዱ የህይወት መርሁ አድርጎ ማጥናት ይገባዋል። ግዕዝ ሚስጢር ፍልስፍና ሳይንስ ምኸዋር ነው።

የእስልማና ዕምነት ተከታዮች የሆኑ የአማራ ልጆችም የራሳቸው የሆነውን ሃብትን
ግዕዝን ማጥናት ይኖርባቸዋል። በግዕዝ ስለ ቁራዕንም የሚያገኙትን ሚስጢር ገባ
ብለው ይዩት። ጀርመን ልጆቿን ግዕዝ ታስተምራለች። በዩንቨርስቲም ታሰመርቃለች። በሃይድልበርግ፤ በሃንቩርግ እና በበርሊን ፍሪ ዩንቨርስቲዎች ግዕዝ ንጉሥ ነው። 
መጽሐፈ ፈውስን ሃንቡርግ ዩንቨርስቲ ሙለውን ታገኙታላችሁ ክብርና አጤ ሆኖ። የመዳህኒት ቅመማ ተወዳዳሪነቱ የጀርመን ምንጩ ይኸው ነውና።

ይህ ሁሉ ሃብታትን ማስጠበቅ ማስቀጠል የሚቻለው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው። 
አማራ ክልል ከልማት ተገድቧል እያሉ በሌላ በኩል ያሉትን በማቃጣል፤ በማንደድ
 ነገን ማንገሥ አይቻልም። አሮጌ ነገሮች ሁሉ ሙዚዬም ተስርቶላቸው ጥሪት ይሁኑ
 ዘንድ፤ ቅርስ ይሆኑ ዘንድ ተከብረው መቀመጥ ይኖርባቸዋል። ለዛ ደግሞ አደብ ሲኖር ሰላም ሲኖር ነው። ከማቀጠል አመድ፤ ከማኖር ትውፊት ይገኛል።

 የእኔ ቅኖች የኔዎቹ አዱኛዎቼ ማለፊያ ሰንበት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁኝ። ፌስ ቡክ ያላችሁ ሸር ብታደርጉልኝ አመስግናችሁ አለሁኝ። ኑሩልኝ።

ግዜው ላላችሁ ስለፍቅራዊነት የቃላት ፓስተር ቪዲዮ ለማዬት ለምትፈቅዱ ትሁቶች ቻፕተር 5 ስለተጀመረ ሊንኩ ይኸውና።

Chapter five, Love Nature Delegations ( Part one 10.28.2018)

Chapter Five, Love Nature Delegations Part Two (02.11.2018)





                                   ሰላም የሚፈለግ ሰላሙን ይጠበቅ!



    

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።