የውድድር ተሳትፎ ነው።

 

 May be an image of 6 people
 
የውድድር ተሳትፎ ነው። በቴክኒካል ችግር ምክንያት ባይሳካም የአገሬ የኢትዮጵያ ሥም፣ የባዕቴ የሲዊዝሻም በዛ ታሪክ ውስጥ አሻራ አለው።
የሚገርመኝ ፈጽሞ እምለው ነገር አለመኖሩ። ኦ! ትዝ ካለኝ ትናንት አንድ ትሁት ሩህሩህ ወጣት ጋር ቻት ሳደርግ ትጥቅ እንዳልፈታ ሲያበረታታኝ ነበር። ቃል ገብቼለት ነበር።
ሰባተኛ "ርግብ በር" መጸሐፌ ጀርባ ሽፋኑ ላይ የተፃፈ ነው።
ማንነት ያለው ተስፋ ስላለኝ የመንፈስን እስር የመፍታት አቅሙ ፈተና ላይ አይወድቅም። ይልቁንም ማንነት ያለው $መፍትሄ የመፍጠር አቅሙ ጉልበታም ነው። ጉልበታሙ ማንነቴ ወደፊት የሚፈጥረው ግፊትና የሚጨበጥ ራዕዩ ደግሞ ትጥቅ እና ስንቄም ነው። በተሟላ #ስንቅና #ትጥቅ የተሰናዳ ማንነት ደግሞ ጉልህና - አሸናፊ ነው። ከዚህ በኋላ ወይንም ከእንግዲህ ወዲያ በቃኝ ብሎ፣ ለስንፍና እና ለፍርኃት #እጁን #አይሰጥም እና #ፈጽሞ!
ይላል። እና ሰኔል እና ሳጥን ብቻ ነው እኔን የሚያስቆመኝ። በብዙ የጤናም የሀዘንም የፈተና ድባብ አልፌያለሁ። ወጁብም ቁርም ፈትኖኛል። ግን ንፁሁ ቅንነቴ ጠግኖ ይዞኛል። ተመስገን።
ሥርጉ14/06/024
ቅንነት ዓራት ዓይናማው መሪዬ፣ የእብዬ የእናቴ ውርስ ስጦታም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።