ኦባንግሻን የት አደረሱት???

 

 May be an image of 5 people
 
 
እዚህ ዙሪክ በሰባዕዊ መብት ዙሪያ ይሠሩ የነበሩ ትጉኃን ነበሩ። እነሱ ስብሰባ ጠርተው ቅድስት ፀሐይ አለችኝ እራሷ ኢትዮጵያ ናት እሷ ጋብዛኝ እሷ ከፍሪቦርግ እኔን ከዙሪክ ለዙሪክ ሰብዓዊነት ጉባኤ። ኦባንግሻን በአካል ያገኜሁት ያኔ ነው። በሥራ አብረን ነበር። ደወል የምትባል ርዕሰ አንቀጽ ነበረቻቸው። በፀጋዬ ራዲዮ በመደበኛ አቅርባት ነበር። አዬ ዶር አብይ ያን ሁሉ ድካም ካለ ሰናፍጭ ታክል ጥረት ጠቀለሉት። ይገርማል።
የሆነ ሆኖ ኦባንግሻን የት አደረሱት??? የት ነው ያለው ጠይሙ ዕንቁ??? ዕንቁአችን መልሱ ማህበረ ኦነጋውያን። ግዞትም ከሆነ ይነገረን። ቁርጥ ያጠግባል እንዲሉ።
ሥርጉ በህዝባዊ ተሳትፎም ጀርመን ሙኒክ እና ፍራንክፈርት አማይን፤ ዴንማርክን ያካተተ፤ እዚህ ዙሪክ፤ ጀኔባ፤ በርን ጉልህ ተሳትፎ በዘጋቢነት በነጣ አገልግያለሁ። የደጉ ዘሐበሻ እና የሩህሩሁ ሳተናው ድህረ ገጽም ቁጥር የማይወጣላቸው ቋቯሚ አምደኛ፤ ሞጋችም ነበርኩ። ፌቡ እኮ አራት ዓመቴ ነው። ለዛውም በእምዬ ቸርነት ገፋፊነት።
የእኔ ጠሐይ። የእኔ ቅን፤ የእኔ ደግ። የእኔ ለጋስ ኑሪልኝ። በራሷ ወጪ በጋዬን ታሳምረዋለች። ከ400 መቶ በላይ ፎቶወቼ የጠሐዬ ነው። የአዲስዬ ዕንቁ ጌጥም።
ኑሩልኝ።
ሥርጉ14/06/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።