መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል።
የፈጠረውን አቅምም በቅጡ ለመምራት የራሱን የምምራት #አቅም፦ #ክህሎት ማሰልጠንም ይገባዋል።
ይህን አዋዶ ህዝብ ጠቀም ማድረግም ሌላው የመሪነት የጥበብ ዘይቤ ነው።
ሥርጉትሻ 2024/07/17
መሪነት፦ #ተጠናቆ #መፈጠርን ይጠይቃል። እንዴት ነው ሪኮመንድ የሚደረገው? እራስን #በመምረጥ? የራሱን ከተንቆናጠጠ በኋላ ሌላውን እንደ ሥልጣን #ጥመኛ በማዬት? ለምን? ሌላው እኔ #እመጥናለሁ ወይ ተብሎም እራስ አይጠየቅም። #ፕሮቶኮሉንስ እችለዋለሁን ብሎ ማሰብም ይገባል። አሁን ጠቅላይ ሚር አብይ ንግሥናውን ሲመኙ #ፕሮቶኮሉን ጭራሽ አላሰቡበትም። ለዚህ ነው ብዙ ነገር #ልቅ የሆነው። ይህን የሚከታተል አካልም ያላቸው አይመስለኝም። #ሲነሪቲም አለ ሥርዓት ባለው መንግሥታዊ አወቃቀር። ይህን ጠሚር አብይ ልብ ያሉት ይመስለኛል። #ቀደምቶችን #ይሸኛሉ። የሳቸውን ተሿሚወች መርጠው #እንዲያመልኳቸው ያደርጋሉ። አዲስ ነገር ፈጥረው። " #ፊልድ ማርሻል" እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ልቅና በልዕልና የነበራቸው ቀደምት የኢትዮጵያ ጀግና መኮንኖች መ እንኳን ያልተሰጣቸውን ነው የተከወነው። የሆነ ሆኖ መሪነትም እራስን፦ አቅምን እመጥናለሁ ወይ? ብሎ መጠዬቅን ይጠይቃል። ተያያዥ ጉዳዮችም። ሥርጉትሻ 2024/07/20
መሪነት #በችሮታ ወይንም #በይሉኝታ ወይንም #በቤተሰባዊ ትስስር ወይንም በማህበራዊ ኑሮ #ቅርበት እና #ርቅት አይቸረቸርም። መሪነት #በሥርዓት - ጥልቅነት፤ በሃሳብ - #ብሩህነት፤ በተመክሮ - #ብቃት እና #ስኬት፤ በማድመጥ እና በማደራጀት ልዩ #ስልታዊ አቅም፤ በችሎታ እና በሃሳብ ግልፅነት እና #ጥራት ልቅና የሚወሰን ነው። ሚሊዮን ህዝብ ለመምራት ምራቁን የዋጠ ሰብዕና በልምድ በከበረ ልቅናን ይጠይቃል። መሪነት #ግጥግጦሽ ወይንም የመልስ #ቅልቅል የፌስታ መተግበሪያ #ቱል አይደለም። ከሁሉም ተሽሎ መገኘትን ይጠይቃል። በዚህ ውስጥ የመርህ ሰውነት እና የተግባራዊነት ደረጃንም ማጣጣም ያስፈልጋል። ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ከህግ አክባሪነትም ጋር ውህድነትም ያስፈልጋል። ምኞትም ፋንታዚም መሪ ሊያደርግ አይችልም። ሥርጉትሻ 20/07/024
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ