ኮራ ኮራ ብላ ለቀጣዩ ራሺያ ደግሞ በቀዩ የበይ ተመልካች...
ኮራዝያን
ኮራ ያለ ቡድን ነው ለካንስ ዋው! ለዋንጫም እድሉ ሰፊ ነው።
„በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች
እንደዚሁ ክፉ ነገርም ለኃጢያተኞች ተፈጠረች።“
(ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፳፭)
ከሥርጉተ ሥላሴ 08.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
- ዜና ስፖርት።
ትናንት እንደግዳ ስለነበረብኝ ቁጭ ብሎ የማደር ያህል ነበር። እናም በዛለ ሰውነቴ ነበር ዛሬ
የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን ሳቅ ትንሽ ረፋድ ላይ የጫርኩት እና የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክትም የላኩት። ከዛ በኋዋላ የተለመደው
ተግባር ተከውኖ በቂ እረፍት ወሰድኩኝ። የትናንቱ ምሽት ዕንቅልፍ በፍቅር ተወራረደ።
ከዛም ትናንት ከእንግዳዬ ጋር በጨረፍታ ብቻ የተመለከትኩት ያለዬሁት የራሺያ እና የኮራዚን የቅዳሜ
ምሽት የኳስ ጉግስ በጥሞና ተመለከትኩኝ። የፊፋ የ2018 የእግር ኳስ ማራኪ ጨዋታ የመጀመሪያው የራሺያ እና የግብጽ ነበር። የፋይናል
የሚመስል ፉክክር ነበር የተከወነው።
ዘንድሮ ዕድሜ ለአብይ መንፈስ እንጂ ሙሉውን ስላልተከታተልኩኝ ኮራ ይህን ያህል ጥንካሬ እንደአላቸው
ስላላዬኋዋችው አለውቅኩም ነበር። እርግጥ ነው በ2016 አውሮፓ የፊፋ ዋንጫ ውድድር
ላይ ሲወድቁ ቅር ብሎኝ ነበር።
ዛሬ ሳያቸው ግን ካለፈውም የሚገርም ብቃት አይቻለሁኝ። ቀጣዩ ተጋጣሚያቸው እንግሊዝ ነው። ያለምንም
ጥያቄ ይረቱታል። ዋንጫውን ለመወስደም ቀጣይ ብቁ አቅም አላቸው። ለዋንጫ ወይ ከፈረንሳይ ወይ ከቤሌጄም ጋር ይገጥማሉ። የትናንቱ
ጨዋታ እጅግ ማራኪ ነበር በጣም ማራኪ። ኪኖ ነበር።
የአስልጣኛቸው እርጋታ እና ስክነት ትውልድ ይገነባል። የኮከቦች ኮከብ ተጨዋቻቸው
10 ቁጥሩ ነው። ኮከብነቱ እኔ በ አውሮፓ ሊግ ሁልጊዜም ስለምከተታለው ስፖርታዊ ጨዋነት አይበታለሁኝ። ተሳክቶለት ዋንጫውን ቢቀናው
አይከፋኝም። አሁን ከቀሩት ቡድኖች የትኞችም ቢወስዱት እኔ እኩል ነው ደስ የሚለኝ። ሴራ የሌለበት ጨዋታ ደስ ይለኛል።
የሰከኑት አስልጣኛቸው።
- · እንዴት ደስ የሚል ነበር …
የመጀመሪያው የ90 ደቂቃ ጨዋታው አንድ ለአንድ ማለት እኩል በኩል፤ ከዛም ተጨማሪው 30 ደቂቃ
ሁለት ለሁለት፤ የፔናሊቲውም ሁለቱም ተመሳሳይ ግብ ማጣት መጀመሪያ ላይ ገጠማቸው፤ በእኩልነት ይህን ሁለቱም አስተናገዱት፤ ሁለተኛ
መሳት ራሺያ ሲገጥመው ድል ወደ በኮራ ከራ ብሎ ኮለል አለ።
ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች እጅግ በሚገርም ብቃት እና ልብን በሚማርክ ሁኔታ ተፈጸመ። ዘንድሮ
አዳዲስ ቡድኖች ብቅ አሉ፤ ነባሮቹ ደግሞ ወደ ባዕታቸው ምልስት ሆነባቸው። ስለሆነም ከወትሮው የተለዬ የልብ መንጠልጠል ስሜት እና
ፍቅር አለኝ። ቀሪዎቹን እንግዲህ በሙሉ ጊዜ እከታተለሁኝ።
ለዋናጫ በአንድ ቁጥር ኮራ ሙሉ ብቃት ላይ መሆኑን ዛሬ በምልስት የትናንቱን ጨዋታ ስመለከት
ተገንዝቤያለሁኝ። ፈረንሳይ እና ቤልጄም ጠንካሮች ቢሆንም ኮራ ግን የበለጠ ጠንካራ ነው።
ብርቅዬው የኮከቦች ኮከብ የኮራ አይናቸው።
በሌላ በኩል የራሽያ ቡድን የግብጽ ጋር ካሳዬው የጨውታ ብቃቱ ጋር የእሱ ብቃት ተጋጣሚዎችን
ብቁ ተፎካካሪ የማድረግ እቅም እንዳለው ተረድቻለሁኝ። ይህ ማለት የባለቅኔው ጠ/ ሚር የአብይ አህመድ ጥንካሬ ለአፍሪካ ቀንድም
ሆነ ለኢትዮጵያ ለሚገኙት የተፎካካሪ ፓርቲዎች የአቅም ምንጭ ይሆናል ማለት ነው።
አሁን ተፎካካሪዎች ከእንጉልቻሙ ፓርላማ ጋር አይደለም
ፉክክራቸው በጥዋቱ ቡናን ፉት ከሚለው፤ ቀንንና ሌሊቱ ወደ ሥራ ሰዓት ወደ ቀዬረው ሊቀ ትጉሃኑ የአብይ መንፈስ ጋር ነው።
በሌላ በኩል ከታታሪው ከሩስላንዱ በተፃራሪው የነበረው የሲዊድን ቡድን ነበር። ከሲዊዲን ቡድን
ጋር ለማፏሸክ ብቻ ነው። ላምጣም በሌለው በበረደው እትት በሚያሰኝ የጨዋታ ትከዛ
ነው እስከ ተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ የሜዳን ዕድለኝነት በለብታ አስፈርሸው የባጁት።
ውዶቼ ...የድንቡልቡለት ፍቅር እንደ እኔ ክንፍ ለሚያደርጋችሁ በቀጣይ ቀናት እጅግ የላቀ ፉክክር ይታያል ብዬ
አስባለሁኝ።
የኢትዮጵያ አዬርም ከተለመደው ውጪ እዬሆነ ነው አብይ ኬኛ ኤርትራም ላይ እንደ ሰደድ እሳት
መንፈሱ እዬተመመ ነው። ቅናተኞች ዛሬ ጨርቃቸውን ጥለው ያብዳሉ!ወደ ጎንድ ቢላክም ያ ክፉ መንፈስ መልካም ነው።
የ ኤርትራው አብይ ኬኛን እያደመጠች ተዚህ ከኮሽ እንሏም እልልል ብላለች ሥርጉትሻ። ዲያቢሎስ ከንክፍነቹ የደቀቁበት ቀን ነበር። ከ6 ወር በላይ እንቅልፍ አጥታ የተጋችበት የብዕር ሰብሏ አሰበለ … የሥርጉትሻ።
ዛሬ ፕ/ ኢሳያስ አፍወርቂ ወደዚህች
ምድር የመጡበትን ቀን ያከበሩበት ቀን ይመስለኛል። እንደገና የተወለዱባት ማዕልቲ ናት ዛሬ። ከእጃቸው ወንዳማቸው እንዳያመልጡ ጥብቅ
አድርገው ይዘው ደስታቸውን ሲገልጡ ሳይ በጥዋቱ እንደነገርኳችሁ ያ የማላውቀው አዲስ ስሜት እያስቸገረኝ ከፈለጉ ይሄዱ ብዬ ፍል
ነጠብጣቦቼን ፈቀድኮላቸው … ቀጣዩ በዚኸው ይሆናል … መጪ እምንለው።
- · ስፖርታዊ ጨዋነት ሥልጡኑነት ነው።
ሥርጉትሻ የፓን አፍሪካኒስቱ የአፍሪካ የእግር ኳስ ብርሃን የታላቁ ሰው የአቶ ይድነቃቸው ተሰማም
መንፈስ ማህበርተኛም ናት ልክ እንደ ሎሬቱ።
ተይቅርታ ጋራ … ያው የትናንትም ቢሆን ከብሎጌ ታሪክ ጋር ኮራዝያን እንዳይቀሩብኝ ብዬ ነው
ትንሽ ብዘገኝም ይሁነው ያልኩት። እናንተም ይሁንብኝ ማለት ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ጨዋታዎች እንዳያመልጧችሁ ለማሳሰብ ነው …
አንደኛው ቤልጄም እና ፈረንሳይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኮራዝያን እና ብርታንያ ናቸው። አራቱም
ግጥሜ ናቸው። የራሞስ ሴራ ባለመታደሙ ከማንም እና ከምንም በላይ ደስተኛ ነኝ። ተናካሹ ስዋርስም ጥርሶቹን ይዞ አገሩ ገብቷልኝ።
አሁን የቀሩት ጨዋዎቹ ናቸው። ስለሆነም ለሁሎችም መልካም ዕድልን በእኩልነት እመኝላቸዋለሁኝ።
ዋንጫ ግን የኮራዝያን ይሆናል የሚል ግምት ነው ያለኝ። አቅማቸው የጉድ ነው። የግል እና የጋራ
ሃላፊነትን በመወጣት እረገድ የላቀ ጥበብ አይቻለሁኝ። በመጪው ማክሰኞ ምሽት ላይ ፈረንሳይ እና ቤልጄም እሮብ ምሽት ላይ ደግሞ ኮራዚ እና
ብርቴን/ እንግሊዝ ይጫዋታሉ። እንዳያመልጣችሁ …
ስፖርታዊ ጨዋነት ሥልጡኑነት ነው።
የኔወቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ