ኢራንን #በእግረኛ ጦር ……… እና ተስፋው በስሱ።

 

ኢራንን #በእግረኛ ጦር ……… እና ተስፋው በስሱ። 
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 May be an image of one or more people, people smiling and eyeglasses
 
ስጋትን ለማስወግድ ቁልፋ በእግዚአብሄር በአላህ #መታመን ነው።
1) ኢራንን የሚሰጉ አገሮች አሉ።
2) አሜሪካንን የሚሰጉ አገሮች ይኖራሉ።
3) ራሺያን የሚሰጉ አገሮች አሉ።
4) እስራኤልን የሚሰጉ አገሮች አሉ።
5) እንደ ቃልኪዳን የጦር አቅም ኔቶንም የሚሰጉ አሉ።
6) ተስፋን የሰጠ፤ ተስፋችን የሚጠብቅ፤ ለተስፋችን ተፈፃሚነት እርግጠኛ የሚያደርግ አምላክን፤ አላህን ከውስጥ ማመን ቢቻል #ስጋቱ አቅም እንዳይኖረው አድርጎ የማክሸፍ ሥልጣነ ክህሎቱ #የእዮር ሊሆን ይገባል።
 
የሰው ልጅ በአምላኩ ካለው መታመን ይልቅ #ለፖለቲካ ፍላጎቱ #መታመን ስለሚያደላ እንሆ ትውልድ ሁልጊዜ #በጦርነት ጢስ እና #ጭንቅ ይታመሳል። 
 
የሰው ልጅ #በመሸነፍ ውስጥ #ማሸነፍ መኖሩን ቢመረምር፤ በስክነት ስኬቱን ቢይ፤ ተሸንፎም ባለ ዕድል የመሆን አቅሙ ሊጎለብት ይችላል። በተለይ በጦርነት መሸነፍን ተቀብሎ የእግዚአብሄርን የአላህን ፍጡር መታደግ #የጽድቅ ጎዳናም ነው። 
 
ይህም ብቻ አይደለም ይህ መርዛማ ኬሚካል ምድርን #ይበክላል። ቀጣዩ ትውልድ በሙሉ የጤና ሁኔታ #ስለመፈጠሩም እርግጠኛ የሚደርግ ጭብጥ የለም። መሬትም #ተሰቃዬች። አዝዕርትም #ፍዳቸውን አዩ። ተፈጥሮ ተሳቀቀ። እግዚአብሄርም አላህም #አለቀሰ
#ኢራንን በእግረኛ ለመግጠም ባይሞከር ምርጫዬ ነው። ለምን? 
 
#መስዋዕትነቱ የከፋ ስለሚሆን። 
 
#እንዴት? #የገዢ መሬት እና #የሙት መሬት ዕጣ። 
 
1) የኢራን እግረኛ ዘገባወች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ነው ።
2) ሠራዊቱ ከኋላው ደጀን ህዝብ ስላለው በሙሉ አቅሙ ይዋጋል። ቢጎዳም የቅርብ ርዳታ ያገኛል።
3) የኢራን ጂኦ አቀማመጥ በእራሱ #ምሽግ ነው።
 
4) ኢራናውያን #ገዢ መሬቱን ይዘው ስለሚቆዩ ተፋላሚው ኃይል የሚጠብቀው #ሙት መሬት ብቻ ይሆናል። አደጋው ሰፊም ይሆናል።
5) ኢራን ላይ ውስጡ ሃይማኖታዊ ንጥረ ነገር ተሰውሮ የመገኜቱ አቅሙ፤ ተዋጊው ብስጩ ሊሆን ይችላል። ገፊ ኃይሉም የጨከነ መንፈስ ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ተፋላሚውን በአይበገሬነት ለመግጠም ሞተሩ ይሆናል።
 
6) የኢራን ላዕላይ መዋቅር፤ ወታደራዊ አቅሙ፤ ባህር ኃይሉን ጨምሮ መጎዳታቸው በሠራዊቱም ይሁን በህዝቡ በቀላዊ ስሜትን ስለሚያፋፋ የኢራን ተዋጊ በከፍተኛ ቆራጥነት የመግጠም አቅም ሊኖረው ይችላል።
 
7) ኢራኖች በሚያውቁት የአዬር ጸባይ፤ የመሬት አቀማመጥ ታግዘው ተፋላሚወች ደግሞ #በእንግዳዊ ሁነት ሚዛኑን ሲሰላ ዕድሉ ለኢራናውያን ሊሆን ይችላል።
 
የፔርሽውያን ስልጣኔ፤ ቀደምትነት "የታሪክ አባት ነን" ቶኑ በራሱ የሚፈጥረው በራስ የመተማመን አቅም ኢራኖች ወደ ፊት እንዲዩ ደጀናቸው ሊሆን ይችላል። ወዘተ ……
 
ስለዚህም እኔ እስራኤልም ሆነ አሜሪካ #በእግረኛ የሚሉትን ሃሳብ ደግመው፤ ደጋግመው ቢያስቡበት ጥሩ ነው ባይ ነኝ። በሌላ በኩል በኢራንም በኩልም ጦርነቱ በዘመናት ውስጥ በቀላሉ ላያገኟቸው የሚችሉ የሰለጠኑ መሪወቻቸውን ማጣታቸውን፤ የኢኮኖሚ ድቀቱን በማስተዋል መርምረው #ሰላምን ቢመርጡ ትውልድን የማትረፍ ብልህነት ይሆናል።
 
ይህ ጦርነት በሰፋ ቁጥር የዓለምን ሰላማዊ መኖር የህውከት ቴርሞሜትር ስለሚጨምር በተሟላ የማስተዋል አቅም እንደገና ቢመረምሩት ጥሩ ይመስለኛል። በሌላ በኩል የፖለቲካ ሊቃናትን እና የየአገሮችን ህዝብ ጉዳትም ግራ ቀኙ ተፋላሚ ኃይሎች ቢያስቡበት ጥሩ ነው። ይህ ጦርነት ግሎባሊ #ራህብን እያወጄ ያለ ጦርነት ነው። ብልህነት እና ዊዝደምን በእጅጉ ይፈልጋል።
 
#የገረመኝ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ግሎባል የእዮብ ትዕግሥት።
 
በዚህ ጦርነት እጅግ እየገረመኝ ያለው አመክንዮ የሰላጤው አገሮች ሙሉዑ ትዕግሥት ነው። እግዚአብሄር የእነሱን ታጋሽነት ያስቀጥል ዘንድ እለምነዋለሁኝ። 
 
ሁለት የአሜሪካ ፓይለቶች በህይወት መገኜታቸውን ሰማሁኝ። እግዚአብሄር በፍጹም ሁኔታ እረድቷቸዋል። ዜናው አስጨናቂ ነበር። እግዚአብሄር እንዲህም የማይቻለውን ያስችላል። ስለሆነም በእጅ በሚገኝ የመቻል አቅም ተፋላሚወች ወደ ቋሚ፤ ቅን፤ ዕውነተኛ ንግግር ይመጡ ዘንድ ፈጣሪ ይርዳ። አሜን። ትርፍ * ድል* ተስፋ * ከሰላም ዘንድ ማፈስ ይቻላል። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
05/04/926
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።