እኔን።
እኔን።
እባካችሁ ግፍን ፍሩ። እባካችሁን በቀል ይብቃችሁ። ስንት ዘመን ልትኖሩ ይሆን?
ይህ ግፍ ኢትዮጵያን ስንት እርግማን ያመጣባት ይሆን??
"ፃድቅን መቅጣት፤
ጨዋ ሰውንም በፃድቅነቱ መምታት፦
መልካም አይደለም።"
ጠቅላይ ሚር አብይ ፓስተር ናቸው ይባላል። ወሮ ዝናሽ ታያቸው ቀዳማዊ እመቤቷም ዘማሪ ናቸው። በዚህ ግፍ ውስጥ ዘማሪነትስ ሆነ ፓስተርነት በፈጣሪ ዘንድ አገልግሎቱ ተቀባይነት ይኖረው ይሆን?
ሁልጊዜ በተቋማት ግንባታ በትቤት የሚተጉት ቀዳማዊት እመቤት ይህን ግፍ እና ግፍ ህሊናቸው ችሎ ያራምዳቸው ይሆን? ከቤተሰብስ በዚህ ዕድሜ ያለ አጎት አይኖር ይሆን? አዛውንቷ ኢትዮጵያስ እንደምን ይከፋት? ዛሬ ነገ ስንብታችን አናውቀውም። ለፀፀት ይቅርታ ለመጠዬቅ ቀጠሮ አያስፈልገውም። ዛሬውኑ ባለ ዕድል እኒህ አዛውንት አባት ከእስር ተፈተው በክብር ተከብረው እንዲኖሩ ያለስጋት ሊደረግ ይገባል።
ውቦች እንዴት አደራችሁልኝ። ደህና ናችሁን?
ኑሩልኝ።
ሥርጉትሻ 2024/05/20
ጊዜ ራዲዮ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ