የአቶ ዮናስ ደስታ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ስለመነፈግ።
እንኳን ደህና
መጡልኝ
የጠ/ሚር
አብይ አህመድ
ሦስተኛው … ው
መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ።
--- ምን ታደርጋለህ? አልኩት።“
መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ።
Seregute©Selassie
21.04.2019
ከእመ ብዙኃን ሲዊዚሻ።
·
ክፍል አንድ።
እንዴት ናችሁ ውዶቹ ክብረቶቼ። ደህና ናችሁ ወይ?
ዛሬ ሦሰተኛውን መዶሻ ደግሞ እናያለን። ሦስተኛው መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ ላይ የነተሰነዘረ ነው። የቀድሞው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፤ እኔ
ልክ እንደ ሁለት አገሮች ጦርነት የመከፈት ስሜት ነበር የተሰማኝ ዜናውን ሳነብ። መጀመሪያ ዜናውን ያገኘሁት ሪፐርተር ላይ ነበር።
እና እጅግ ደነገጥኩኝ።
የሚገርማችሁ ለአንድ ወዳጄ ዶር አብይ አህመድ
ለጠ/ሚኒሰተር እጩ ተወዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ በቅርበት አብሬው እሰራው ከነበረው ወድንዴሜ ጋር መልእክት ስንጻጻፍ ዶር አብይ አህመድ
ጠ/ሚር ከሆኑ ወደፊት ያመጧቸዋል ብዬ ካሰብኳቸው ወገኖች ፈላስማ ዶር ምህረት ደበበ፤ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ፤ አቶ ዮናስ ደስታ ሊሆኑ
እንደሚችሉ ጽፌለት ነበር።
ምክንያቱም ያን ጊዜ ኢትዮጵያዊ ራዕያቸው ትክክለኛውን
ሰው በትክክለኛው ቦታ ሪኮመንድ በማድረግ፤ እውቅና በመስጠት ምስክር በመሆን የጎለበተ አቅም አያ ብቻ ስለነበር እነዚህ ወጣት ሊሂቃን
የቲማቸው አካል የመንፈሳቸው ቤተኛ ያድርጓቸዋል የሚል እሳቤም ዝንባሌም ነበረኝ። የላኩለትም ኢሜል አለ ከእጄ ላይ እሱም የጹሑፌ
ታዳሜ ስለሆነ አይረሳውም።
ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋዋላ ግን ያዬሁት የጎላ
እርምጃ አልነበረም። ይባስ ብሎ አሁን በቅጽበታዊ ውሳኔ ያን የመሰለ ልምድና ተመክሮ ያለውን መንፈስ፤ የኢትዮጵያዊነት ብሩኽ የተስፋ
ጮራ፤ ድንቅ የሚያስብ፤ ብሄራዊ ተቆርቋሪነት ተቀላ።
እኔ እንደሚገባኝ ጥልቅ ኢትዮጵያዊ ተቆርቋሪነት
አሁን ዒላማ ላይ እንዳለ ነው እማስበው፤ በዚህ ውስጥ የእስክንድርን ንቅናቄ፤ በዚህ ውስጥ በርሃ በርሃ ሲንገላታ የነበረ ደመከልቡ
ቆመስ ስመኛው በቀለን ሰማዕትንት ማዬት ይገባል። ተቆርቋሪነት ከለውጡ መባቻ ጀምሮ በተለያዬ ስልት ደመ ከልብ እዬሆነ መሆኑን።
በሌላ በኩል ጸረ ኢትዮጵያ ትርኪ ምርኪዎች አቅም
እንዲያገኙ ጉልበት እንዲያገኙ ህግ እንዳይዳኛቸው በይፋ እና በ አደባባይ የተፈቀደው። ስንት ዓለም አቀፍ አህጉር አቀፍ መናህሪያ
አዲስ አባባ ላይ የጎረምሳ ስብስብ አዛዥ እና ናዛዥ ተፈሪ እና ነጋሽ ሆኖ የህዝብን ስብሰባ የሚያስተጓጉልበት፤ ደረቱን ነፍቶ የሚያምስ
የሚያተራምስም ለዛውም ኗሪ ሳይሆን መደበኛ የህሊና ኮንቤኒሽናል ጦርነት የሚፈቅድበት ሁኔታ እያዬን ያለነው።
አቶ ዮናስ ደስታ በዚህ ዘርፍ ሲሰሩ ንጹህ ኢትዮጵያዊነትን
ዘርፉ ይጠይቃል። ከዞግ ዘለለ ዕሳቤ ውጭ የሆነ። ለዚህ ደግሞ ዜግነታቸው ብቻ የሰጣቸውን መብት ብናስበው እንኳን ሃላፊነቱን ትተን
በ አገራቸው መንፈስ ውስጥ አሉ በመኖራቸው ውስጥ ላሉ አመክንዮች ሁሉ ባለቤት ናቸው። ይህ ነው ተጥሶ ያዬነው።
ይህ ጽኑ የዜግነት ተቆርቋሪነት ጉልህ የሆነ መንፈስ
እንዲህ እንደ አሮጌ ዕቃ አሸቀንጥረው ሲጥሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ በአቶ ሰዬ አብርሃም ላይ፤ አቶ ሃይለማርያም
ደስአለኝ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ ከውሰዱት እርምጃ የሚለኝ አልሆነብኝም። ይህ የማንአለብኝነት ይህ የበላይነት መንፈስ ለጨዋው የ
ኢትዮጵያ ህዝብ ፈጽሞ አይመጥንም።
አቶ ዮናስ ደስታ የ ኢትዮጵያ ምርጥ ልጅ ናቸው።
በቆዩባቸው ጊዚያት ሁሉ አንቱ የተባሉ ተግባራትን የከወኑ ዜግነታቸውን የዋጡ አብነትም ናቸው። ዜግነታቸው የተለጠፈባቸው ሳይሆን
በዜግነት መንፈስ ውስጥ ሰክነው የተፈጠሩ ወጣት ሊሂቅ ናቸው። ለ ኢትዮጵያ ቢቀርባት እንጂ እኒህ ዓራት ዓይናማ መሪ ለሳቸው ምንም
የሚቀርባቸው ነገር አይኖርም። እንዲያውም በጊዜ መገላገሉ ለመልካም ይሆናል። የፈጣሪ ጥበብ ልሁቅ ነውና።
·
የዜግነት
ሰጪም ነሺም የለም። ዜግነት መብትም ግዴታም ነው ህሊና ላለው።
እያንዳንዱ ዜጋ በአገሩ ጉዳይ፤ ቅርስ፤ ታሪክ፤
ትውፊት፤ ትሩፋት ላይ አኩል የመጠዬቅ፤ የማወቅ መብት አለው። ጊዜ እና ሁኔታ እንጂ እሳቸው ያላቸውን ሃላፊነት ያህል ሁሉም ዜጋ
አለው። ይህ ዛሬ የተመኩበት ስልጣን ነገ ሊያልቅ፤ ሊቀደድ፤ ሊያረጅ፤ ሊደረመስ እንደሚችል እሳቸውም በአንድ ወቅት ተናግረውታል ዛሬ እዚህ የተቀመጠው ሰውዬ ነገ ታች ይወድቃል
ብለው። በአንድ ሰብዕዊ ርህራሄ እና አስተዳደር ባጠመረው የቢሯቸው ሃላፊዎች ጉባኤ ላይ።
Ethiopia
- Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ
እኔ ይህን ቪዲዮ አይቼ ይህን ጽፌ ነበር።
እዮር ሰማይ ላይ ብቻ ሳይሆን በዚህ ቅዱስ መንፈስ ውስጥ አየሁ። ተመስገን።
„ችግሩ
ከስልጣን በፊትና
ቡሀላ ያለው
ወሬ እየተለያየ
ተቸገርን ነው“
ብለው ነበር አሁን እማዬው እኔ ያልኩት
ሳይሆን አቶ መሀመድ ጀማል ያሉትን ትክክል ሆኖ ነው።
ግን እኛ ቅኖች እንዴት ሊፈረድብን ይችል ይሆን በዚህ ንግግር ወስጥ ያሉ ሰብዕናዎችን ደግፈን ብንነሳ ዛሬ በምናዬው አውሎ ደግሞ ድጋፋችን ብናነሳም የተገባ ነው።
እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድን የማውቃቸው በመንፈስ
ለፍቅራዊነት እንቡጢጣ ፕሮጀክቴ በዬአህጉሩ መንፈስ ሳፈላልግ ነበር ያገኘሁዋቸው። ከዛ መንፈሳቸውን ስለተመቸኝ መከታተል ጀመረኩኝ።
በሳቸው ጉዳይ ጎርባጣ የሆኑ ነገሮች አሉ ሲባል ወደ ፖለቲካው መድረክ ሲመጡ ዕጣ ነፍሴን ሞግቸላቸዋለሁኝ። ጥሪት ነበረኝ። ጥሪቱ
ደግሞ አውሬዎ ያልሆነ ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ መንፈስን የተላበሰ ሰብዕና አላቸው የሚል ሙሉ እምነት ስለነበረኝ ነው።
Ethiopia
- Dr abiy ሚኒስትር ከመሆንህ በላይ ሰዉ ነህ!
Published
on Feb 17, 2018
Ethiopia: Dr Abiy ahmed speech at Gonder
abiy News
Published on Mar 16, 2018
Abiy
ahmed speech at Gonder part 2
Published on Nov 4, 2017
ከሁሉ በላይ ቤተሰባዊ አቀራረባቸው የሁሉም ሃብት
ሆነው አያቸው ዘንድ ብዙ አድክሞኛል። ዛሬ ደግሞ ሌላ ዥንጉርጉር ሰብዕና ላይ ናቸው። ቡፌ … ባህሬ፤ ቡፌ ሰብዕና፤ ቡፌ አቋም፤ ቡፌ ራዕይ። እዛናለሁኝ።
እኔ እውነት ተነገሪ ብባል የ አቶ ዮናስ ደስታን
ከዜግነት መነሳት ስሰማ ፋሲል ግንብ የተደረመሰ ያህል ነው የተሰማኝ። የሰው ልጅ መላዕክ አይደለም። ስህተትን ማድመጥ፤ ስህተትን
መቀበል ካልተቻለ መሪነት ከወንዝ ላይ የተንሳፈፈ ኩበት ነው የሚሆነው።
ጥያቄው እኮ እውነት ነው ወይንም ቢሮውን መዝጋትና
እሳቸው ደርበው መስራት ልክ እንደ ሰላም ሚ/ር የሰላም ሚኒስተሯን በተለያዬ ሁኔታ ጠምደው እሳቸው ግን የሰላም ሚ/ር ሆነው እዬሰሩ
እንዳሉ ማንም አላስተዋለውም። እንዴት ሆኖ ሳፎስትኬትድ ሆኖ እንደታዋቀረም አስቡት።
በፈለገው መልክ አንድ ሰው 100 ሚሊዮን ህሊና
ሊኖረው አይችልም። የባዛ ትምህክት ያፈነዳል። ባለሙያዎችን ማማከር ግድ ይላል። በነገራችን ላይ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
በሚ/ር ማዕረግ መሾማቸው ግድ ያልሰጠኝ ለዛ ነው።
እሳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሆነው እንደሚሰሩም ስለማውቅ።
በደጋፊነትም ማን አለባቸው የመከላከያ ሚ/ሩ ለማ መገርሳም ይደመራሉ። እኔ አሁን አሁን ሳስበው ጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ኦነጋዊ የሆነ
መፈንቀለ መንግሥት ነው የሚመስለኝ። የተካሄደው እኮ መፈንቅለ መንግሥት ነው። አሁንም እዬሠሩ ያሉት ያነን ነው።
ከዛም ጠብ ከዚህም ጠብ የሚአደርጉት ጠባጠቦሽ
ለማዛል ነው። ለዚህ ነው ገና በጥዋቱ የ አማራ ብሄርተኝነት ላይ ሙሉ አቅማቸውን ለማፈሰስ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የቅርብ ሰው
በማደረግ አልጋም ፈላስማውን ዶር ዳኛቸው አሰፋ እና ሰሞኑን የሾሟቸውን ፕ/ አበባው አያሌውን ያሰለፉት፤ አቶ ውብሸት ሙላትን አልደፈሩም
እነ አቶ ታዬ ደንዳአን ስንት ቦታ ላይ ሲያሻፍሩ …
የተነሱበት አላማ አሻም የሚል መንፈስ ላይ ነበር እርብርባቸው… አሁን የሰሞኑ
የ አንቦ ጉዞም የ ዓመቱ የልግጫ ዋንጫ ነው>.. ለነገሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ወደ ባህርዳር ልከው ነበር ደምጥማጡን አጠፋነው
እንጂ … ለውግ ለማዕረግ ሳናበቃ …
እኔ ሰው እንዴት እንደሚዬው አላውቅም እንጂ በይፋ
በአደባባይ እኮ ነገረውናል በጋዜጣዊ መግለጫቸው እኔ ኦዴፓን የምሰበሰብውን ያህል ስልጣን ብአዴን ውስጥም አለኝ ብለውናል። በህውሃት
ይህቺ አትደፈረም። ያ እኮ ቀልድ አይደለም።
አሁን እኛ በብሮድካስት ቦርድ ብዙ እንላለን ያ ለስሙ ነው እንጂ አዬር መቃወሚያቸው
ብሮድ ካስት ከሳቸው እጅ ይወጣል ተብሎ አይታሰብም።
የሜቴክ እስርን ለማጠናከር የወጣ አንድ የሰብዕዊ
መብት እረገጣ በዘመነ ህወሃት ለማጋለጥ እንደ ማካሄጃ ወጥቶ ነበር። የጹሑፉ ቅንብር የሳቸው ነው ብዬ በወቅቱ ጽፌ ነበር። እሳቸው ብዙ ናቸውና በኢትዮጵያ
የሚ/ መስሪያ ቤት ሳያስፈልግ በሁሉም ቦታ እንዳሉ ማሰብ ይገባል። የሚያምኑት ሰው የላቸውም። ሁሉም ማካሄጃ ነው።
አሻም የሚሉት
ደግሞ እንዲህ በብጣሽ ወረቀት ይገፈተራሉ፤ ዜግነታቸው ይቀማል። ከዚህ በላይ ዲስክርምኔሽን የለም፤፡ ከዚህ ያለፈ እሰጣ ገብ ሲመጣ
ደግሞ ቁርጢ ይከተላል።
ግጭት ላይ፤ ህወከት ላይ፤ ቀውስ ላይ ደግሞ እሳቸው
የሉም፤ በ አንዲት አሮጊት ቤት እደሳት ላይ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ አስልቶ የሚነሳ መንፈስ ምን ያህል ርቁቅ እንደሆን ማሰብ ይገባል
ለዚህ ዞግ ይፈለጋል ቤት ለማደሱም ማለት ነው>.. ካልቸገረ ቅይጥ ዝንቅ ቀለም አያፈለገም በወጥ ቀለም ውስጥ ያለው አራርሳዊ
ስለሆኑ በማስተዋል መርምሩት … በቅንነት ያየናቸው፤ ያስተዋልናቸው፤ የደከምንባቸው በፈጠሪ ዘንድ የከበሩ ናቸው፤ ለህሊናችም ለምለም
ግን በቀጣይነት ቅንነት ተገድሎ ተዝቅቅዝቆ ሲሰቀል እያዩ ዝምታን ግን ሌላ ርግማንም ያመጣል …
·
የኢጎ ቁልል።
የኢትዮጵያ መሪዎች ችግር ይህ ተመሳሳይ ነው።
ሲአስፈልጋቸው … የሰውም የእንሰሳም፤ የነፍሳትም የጉንዳንም የህክምና ባለሙያ፤ ኬሚስት፤ ባይወሎጂስት፤ የአዬር ንብረት ተንባይ፤
የሰማይም የምድርም መሃንዲስ፤ ከከርስ በታችን ከከርሰ ምድር ላይ
ያሉ ማዕድናት ኤክስፐርት፤ የምርምር የጥናት ሳይንቲስት፤ የጠፈር ተመራራማሪ፤ የቢዝነስ ማናጀር፤ የፍትህ ሚንስተር፤ የዳኞች ጉባኤ
ሰብሳቢ፤ የሃይማኖት ተቋማት እጬጌ፤ የዩንቨርስቲ ፈላስፋ፤ የመማክርት ጉባኤ ፕሬዚዳንት ወዘተ ወዘተ ወዘተ ፈጣሪ ሆነው ቁጭ ይላሉ።
የሚያዳምጡት እራሳቸውን ብቻ ነው። ጆሮ ለምስል
አልፈጠረላቸውም። ለዛውም ጠ/ሚር አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ የነበረውን የምልዕት ድጋፍ ደግሞ እሰቡት። ያ በራሱ ከአጤኔት በላይ አምላካዊነት
ቢፈጥር አያስፈርድም።
እና አሁን የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ስታስቡት አምላክ እንዴት በሰው ይመራል? ይህ ነው የሳቸው ችግር። በሌላ በኩል እኔ ሳስባቸው ጀርመኖች ፍጹማውያን የሆኑ ሰዎች
ከልክ፤ ከደንበር ሲያልፉ በሽታ ነው ይሉታል። ልክ በራስ መተማመን ሲያንስ የበታችነት፤ ሲበዛ እና ሲንር ደግሞ አንባገነን የመሆን
ጉዳይ እንደሚመጣው ሁሉ።
ስለዚህም አያዳምጡም እንደገናም ሁሉንም ቦታ ተክቼ
ልስራ ይላሉ … ይህ ነው የኮ/መንግሥቱ ሃይለማርያምን ዘመን የገደለ እነ የኮ/ ጎሹ ወልዴን የመሰለ የሉላዊው ዓለም የብቃት ልዑል
ያሳጣ፤ ስንት ምድር ልትገልጣቸው ልትተረጉማቸው የማትችላቸውን እነ ጄኒራልን ፈንታ በላይን ሰማዕትነት የመንፈስ ግዝፈታቸው እኮ
ከፕላኔታችን በላይ የሆኑ ከፍተኛ መኮነኖችን ያሳጣ ኢትዮጵያንም እንዲህ ከሚፈርሱ አገሮች ተርታ ያሰለፈው … ይህ የተለጠጠ ጉድ
ነው።
ማድመጥ ምን ያቅታል? ስህተትን መቀበልስ ማንን
ይገድላል? ስለምን በህጋዊ አካልነት
በዓለም አቀፍ መድረክ ሳይቀር አውቅና ያለውን ድርጅቱን ሳያማክሩ እድሳት ይጀመራሉ? እሳቸው
ፈራጅም፤ ዳኛም፤ አቃቢ ህግም፤ ተከላካይም፤ ከሳሽም ሆነው ይችሉታልን? እኔ የጤናቸው አልመስለኝ የማዬው ሁሉ ነገር።
እርግጥ ነው ኮከባች ንጉሥ ስለሆነ ሌሎች ኮከቦችም
በሚወለዱበት ሰዓት ቀንን ሁኔታ ተጽዕኖ ሊያደርጉባች ስለሚችሉም ልጠቅልል ቢሉ፤ ልበጥብጥ ቢሉም ባልፈርድም አሁን እኮ መሪ ናቸው።
እንዲህ በቃ ባንድ ብጣቂ ወረቀት የአንዳ አገር አንጡራ ሃብት መወርወር ኧረ ቀስ አድርገው ይያዙት … እኔስ ፈራሁላቸው የውነት
…
·
ያለበት።
በዚህ ሂደት ወስጥ እርግጡን ባላውቅም የተወለዱበት
ቀን ወር ግን ከመልክ ገፃቸው ሳዬው ደልዳላዋ ቀዳማዊት እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ካንሰር ይመስለኛል ኮከባቸው። አብሶ የዚህ ኮከብ ባለቤቶች
ሴቶች ከሆኑ እናትነት በጥልቀት፤ ሚስትነት በጥልቀት፤ ፍቅር እና ሰላም ፈላጊነት፤ በጥልቀት የሚታይባቸው በመሆኑ ባለቤታቸውን እናታዊ፤
ፍቅራዊ፤ ሚስታዊ በሆነ ሁኔታ ቀስ እያደረጉ ሊገሯቸው የሚገባ ይመስለኛል። መንገዱ አላመረኝም …
የሚበልጠኝ ሰው አለ ብለው ማሰብ ይኖርባቸዋል
ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ የሚቀድመኝ ሰው አለ ብለው መቀበል ይኖርባቸዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ኢትዮጵያ እኮ ስንት እንቁ የመንፈስ
ዲታ ሊቀ ሊቃውንታት አገር ናት። ተዘርዘሮም ተነግሮም ተብራርቶም በማያልቅ ሁኔታ ኢትዮጵያ በመንፈሳቸው የለሙ የዳበሩ የላቁ ልጆች
እናት ናት።
አቶ ዮናስ ደስታ ለውጭ ጉዳይ ሚኒሰተር የሚመጡን ሰው ናቸው። ይህን ደፍሬ ነው የምናገረው። መሬት ቢይዙ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጥሩ ነው። አዬር መንገድ
በፈቃዳቸው ቦርዱን አቋቋሙ፤ የ ንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክን ቤተመንግሥት ለማድስ ሲነሱ መንግሥት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሥልጣኑን የሰጠውን አካል ሳያሳውቁ፤ ሳያማክሩ በራሰቸው ተነሳሽነት ነው።
ቀድሞ ነገር ይህ እኮ አገራዊ ጉባኤ ተጥርቶ ሊመከርበት፤
ሊዘከርበት፤ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነበር። ራሱ ካቢኔው ተሰብስቦ ሊወያይበት የሚገባ ጉዳይ ነው ኢትዮጵያ እራሷ የምተገለጥበት
የጥቁር ህዝቦች የድል ማማ የሆነ የታሪክ አውራ ጭንቅላት ጉዳይ እኮ ነው ይህ ጉዳይ። ይህ እድሳት የኮንደንዬም እደሳት አይደለምና
… ቀድሞ ነገር ፋሲል፤ ላሊበላ፤ አክሱም፤ ለሰራ ምን ቻይና ድረስ
ያስኬድ ነበር? ጥልቅ ኢትዮጵያውነት መንፈስ ውስጥ ከሴሉ ቢኖር።
ይህ ቤተ መንግሥት ለውጭ አገር ጉብኝት እንጂ
ውስጣዊ አቅሙ፤ እምቅ ሃብቱ፤ አደረጃጀቱ፤ ፓተንቱ ለውጭ አገር ባለሙያዎችም
የሚሰጥ አልነበረም። ቤተ መቅደስ እኮ ነው ተከፍቶ የተረከቡት ቻይናዎቹ። መታሰብ እራሱ አልነበረበትም። የጥበብ ግድፈትም ነው። የአድዋ ህሊና ነውና። አድዋ እና አለም ደግሞ ምን እና ምን እደሆኑ ይታወቃል። ያው
እዳ ስትሸከም እራስን በስውር ቅኝ ግዛት አሳልፎ የመስጠት ቅደመ ድርድርም ታሳቢ በማድረግ ይታይ እንደሆን አላውቅም።
አባት እና እናቶቻችን አነ ንግሥት ማክዳን፤ እነ
እቴጌ ጣይቱን፤ አነ እቴጌ ሰብለወንጌልን ብናነሳ ጥሩ ለማኝ ሳይሆኑ ብቁ ንጥር ዲፕሎማቶችም ነበሩ፤ ይህን አላይም ነው ዮሖንስ
መተማ ላይ፤ መይሳው መቅደላ ላይ ሰማዕት የሆኑት። ልመና ውርስና ቅርሳችን አይደለም። ድህነታችን የሴራው ባለባት እነ አቤቱ ተሰማ
ናደው የተከሉት ነቀረሳ ነው እንዲህ ራሳችን ችለን መቆም ተስኖን ከፈራሽ አገሮች ተርታ ያሰለፈን … እንጂ ጥበብማ ይቀዳል … የ
አውሮፓ የሥልጣኔ ምንጭ እኮ የግዕዝ የመንፈስ ሃብታት ነው …
የሚኒሊክ ቤተ መንግሥት አገር እንመሠርታለን የሚሉት
የራሳቸው መንፈሶች አረንቋ ዕሳቤ መሰረቱ ጽንሰቱ ከዚህ ጥላቻ ላይ ስለምን ተቸከለ ብሎ በግልብ ሳይሆን በጥልቀት ሊታይ ይገባል
…የሚስጢሩን ናዳ ማማም የግልብ መንፈስን ሁሉ ያርደዋል …
ስለ ንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት
እድሳት ጉዳይ እኮ የአንቀጽ 17 ወሳኝ የመለከት ሚስጢር ያለበትት ጉዳይ ነው።
አመክንዮዎች የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ፤
የጥቁር ህዝቦች የታሪክ የኖኽ
ኖታ መርከብ የሆነው ታላቅ እጬጌ ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስተሩ ህሊናዊ
ንድፍ ብቻ ሊተዳደር ሊሻሻል እንደገና ሊበጅ ከቶ አይገባም ነበር። ቅንነት ቢኖረውም ግን ሃብትነቱ የብዝሃን ነው። ህብርነቱ የሁሉም
ሰለ ሆነ ድምጸ ውሳኔ ሁሉ ያስፈልገው ነበር። ቤተ መንግስቱ የ ኢትዮጵያ ሰማይ እና ምድር ህገ መንግሥታችን ነውና።
ሲመሰረትም ብዙ አገራዊ መዋለ መንፈስ ፈሶበታል፤
ሂደቱ በራሱ ራሱን የቻለ አምክንዮ አለው፤ ጠቅላላ ይዘቱ የሚስጢር ቋት ነው። ልባችን ያለበት ጉዳይ ነው። ባልድርሻ
የመንግሥት አካላትን ጨምሮ የባህል፤ የቅርስ፤ የታሪክ፤ የህግ፤ የሃይማኖት፤ የቋንቋ ሙሁራን ሁሉ ተገኝተው መክረው ዘክረው ሊወስኑበት
የሚገባ ጉዳይ ነው። ንድፉ ሆድ ዕቃው ተዘፈርግፎ ሊታይ ሊፈተሽ፤ ሊመረመር፤ ሊታይ ይገባው ነበር።
ይህን ስል ጠ/ሚር አብይ አህመድ
እንደ መሪም እንደ ዜጋም እንደ ዞግ ድርጅት መሪነታቸውም መንፈሳቸው፤ ራዕያቸው ለመነሻነት አያገልግል ማለቴ አይደለም። የመነሻ
ሃሳቡ መፈተሽ፤ መመርመር ያስፈልገው ነበር። ጊዜ ወስዶም ማጥናት ይገባ ነበር። ላልጠፋ ቀን የምን ጥድፊያ ነው. .. ያው እንሟማታለን
የመከላከያ ሚኒስተሩ ቃለ ምህዳን ለቀጣይ ምርጫም መዳራሻ መላሾ ለማድረግ። የኦነግን መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ለማስፈንም ነው።
…. ቀድሞ ነገር ይህን የመሰለ አገራዊ ጭንቅላት ጉዳይ በአንድ ቀንጣ መንፈስ፤
በአንድ በጎ ፈቃደኛ ተነሳሽነት ወይንም በአንድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነፍስ ብቻ ሊፈትል የሚገባው ገዳይ አይደለም። አልነበረም።
ቅርስ ትውፊት ነው። ቅርስ ታሪክ ነው። ቅርስ
ነፍስ ነው። ቅርስ ህልውና ነው። ቅርስ ትናንት ነው። ቅርስ ነገ ነው። ቅርስ ከነገ ወዲያ ነው። ቅርስ ጊዜ ነው። ቅርስ ትውልድ
ነው። ቅርስ ማንነት አለው፤ ቅርስ ብሄራዊ ዜግነት ያለው ነው። ቅርስ ምዕት ነው። ቅርስ አለምአቀፋዊ ዜግነት ያለው ነው። ቅርስ
ሃይማኖትም ነው። ቅርስ ታማኝነትም ነው። ቅርስ እውነትም ነው።
ስለዚህ ለዚህ ሁለገብ አቅሙ ሁለገብ ክህሎት ያለው
የብዙሃን የሃሳብ ቅምረትን ይጠይቃል። ይህን አለመፍቀድ ለዚህ አለመሰናዳት ትርፉ ኪሳራ ነው። ዛሬ
እሳቸው ስልጣን ላይ ስላሉ ሊያደርጉ የፈቀዱትን ያድርጉት ግን እሳቸው ቋሚ ስላልሆኑ ነገ ደግሞ ሌላው እንደሚሆን ያደርገዋል።
ባለድርሻ አካላትን በገፉ በገፈተሩ ቁጥር መከራን
በራስ ላይ መቆለል ነው። ትርፍ ሳይሆን ኪሳራም ነው። እኔ እውነት ብናገር በመንፈስ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሰረዋል፤ ተሸንፈዋልም።
የሚገርመው ለቀጣዩ ፕሮጀክታቸው እንኳን በዚህው
ቤተ መንግሥት አዳራሽ ላይ ለማሳካት ሲያስቡ የቤተሰቡን ማዕከል መናህሪያ ከተማ አዲስ አባባ ማለት ተስኗቸው ሸገር ሲሉ ነው የሽንገላ ጥሪያቸውን
ሰነድ ያዘጋጁት። ንደቱ በዚህ መልክ እያባበለ፤ እያቆላመጠ ነው
የሚከወን። በዬስብሰባውም ፊንፊኔ እያሉ ይደመጣሉ …
ይህ መቼም የውደቀት መጀመሪያ ነው። የሚኒሊክን
ዙፋን ላይ ለመቀመጥ ከዚህ ቁምጽላዊነት ጋር መደመር ሳይሆን መቀነስ ያስፈልግ ነበር። ይህን መሸከም ያልቻለ ራዕይ በቀንጣ እሳቤ
እደሳት መጀመር በራሱ ታሪኩን ያፋልሰዋል።
እኔ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም በሆነው የኖኽ
መርከብ ምስል ባለው ጥንታዊ፤ ታሪካዊ፤ ሉላዊ፤ አዳም ሰገድ እያሱ ታቦቱን ለተሸከመለት ከዛ እጬጌ ገዳማዊ የቅኔ መንደር ደብረ
ብርሃን ነው የተወለደኩት፤ እትብቴም የተቀበረው፤ ክርስትናም የተነሳሁት፤ ቤተሰቦቼም ያገለገሉት።
ግን እዛ እደሳት ሲኖር በልጅነት እማስተውለው
ነበር። ጣሪያው እሳር ነው። እሳሮች ያረጁት እንዴት እንክብካቤ ይደረግላቸው እንደነበር ሁሉ አውቃለሁኝ። ያረጀ ቅልጥሙ፤ የወላለቀው
ሁሉ በጥንቃቄ ተገጣጥሞ ተፈጥሮውን ሳይስት ሲጎዘጎዝ አይቻለሁኝ።
በልጅነቴ ማለት ነው። ቅርስ ሱቅ ሄደህ የምትሸምተው ሸቀጥ ወይንም
ስለተመቸህ በጀምላ እና በችርቻሮ የምትቸበቸብው አይደለም። ቅርስ ሰው ነው። ሰው አይቀናም፤
እኔ እንደማስበው ጠ/ሚር አብይ አህመድ አቶ ዮናስን
ደስታን ያነሱበት አገባብ በዚህ እርምጃቸው ከሰሩ እንጂ አላተረፉም። የሳቸው
በዬሦስት ወሩ፤ በ እለታት በሚቆጠሩም ነቀል ተከል ሹመት ቀርቶ በረጉ፤ በሰከኑ አገሮች ያለው ሥልጣን እንኳን ይህን ያህል አያስመካም።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በተመሳሳይ ሙቀት
ነበር ሁለቱንም የመመረጥ ዕድል አሳልፈው ሥልጣናቸውን ያስረከብቱ፤ ሌላው ቀርቶ የማይሞቃትም፤ የማይደንቃትም ሲዊዝ እንኳ እስከ
ቤተሰባቸው ስትዘክራቸው አለች እንዳለች።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ግን የሚከተሉት ፈለግ የሚሄዱበት
መንገድ መልካም አይደለም። የጥዋት ጤዛ ሆነ ሥራ ነገራቸው። የድሮው
ሰብዕናቸው ነው የሚሻላቸው … ለገሃዱ ዓለምም ለመንፈሳዊ ዓለምም …
በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ያላቸው ጠናና አቋም
ምን ሊያስከትል እንደሚችል አላስቡበትም፤ አሁን ደግሞ ይህን አክለዋል ነገ እና እሳቸውን ያያ …
በዚህ ዘመን መከራ ለመቀበል መቁረጥ፤ መወሰን
ቢያስከበር፤ ጀግና ቢያደርግ እንጂ የሚያወርድ ቅስም የሚሰበር፤ የሚሰቀጥጥ አይሆንም። እኔ ሥፈርጉተ ሥላሴ ምን ያኮራሻል ብባል
በህወሃት ዘመን ጫካ መውረዴ እና መታሰሬ መዳሊዬ ኒሻኔ ነው። እጅግ የምደሰትብና የምኮራበት።
ስለሆነም አቶ ዮናስ ደስታ ከሥልጣናቸው መነሳታቸው
ለ ኢትዮጵያ ቢቀርባት እንጂ ለሳቸው ታሪካዊ ድላቸው ነው። ዘመን ሲነሳቸው፤ ሲዋሳቸው የሚኖር ገድል ነው የፈጸሙት። ዛሬ ትውልዱ
ላይታዬው ይችል ይሆናል ግን ነገ ይህ ደማቅ ብርሃን ይሆናል። ታሪክን አበጁት። የ አባት እናቶቻቸውን መንፈስ ክብር ሲጣስ ስለምን
ብለው ጠዬቁ … እናም ሰማዕት ሆኑ። ለ እኔ የቁም ሰማዕት ናቸው።
ክብር ማዕረግ የቀረበት የጠ/ሚር ወንበሩ ነው።
ለነገሩ እኔ ወንበሩ ባዶ ሆኖ በህልሜ ያዬሀት ሀምሌ ላይ ነው። ለራሳቸው ነው የቀረባቸው። ከብራቸውን፤ ግርማቸውን፤ ሞገሳቸውን
ቀስ እያደረጉ እዬሸኙት ስለሆነ እኛም በሳቸው ላይ ያለን ተስፋ ቀስ እያደርገን ፈቅደን፤ ወደን፤ ደስ ብሎን እንሸኘዋለን …
ውል የለብን … ውለታ አንሻም፤ ቅርጥምጣሚ ወድስ
አንሻ … ቀድሞም እውነት
ነው ዛሬም እውነትን ተመርኩዘን ነው እምንናገረው … ወደ እውነት ሲመጡ ይደገፋሉ ከአውነት እዬራቁ፤ ከ ከእውነት እያፈነገጡ፤
ከእውነት እያዳለጡ እና በእውነት ላይ ደባ እዬሰሩ ሲመጡ ደግሞ ልባችንም
ይሸፍታል …
እንዲህ ማስከፋቱን ሲያነባብሩት ሸጋ ነው፤ ስለምን
ብትሉ መቁረጥን ሲለምሸልም። መወሰንን ሰለሚያጎናጽፍ … መቆረጥ እና መወሰን ሲሸለም ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ለሙሉ ነፃነት መትጋት
ይቻላል። „የበሰሰበሰ ዝናብ አይፈራም“ የሚባለውም ለዚህ ነው።
የሚገርመው አቶ ዮናስ ደስታ በጠ/ሚር አብይ አህመድ
አክቲቢዝም ላይ የጎላ ድርሻ እንደነበራቸው ነው እኔ እማስበው፤ ስለምን ብትሉኝ በዛ ቤተሰባዊ በሆነ „ከርምጃ ወደ ሩጫ“ ፕሮጀክት
ላይ የነበረው ሥልጡን፤ ውብ፤ የተሟላ ጤናማ መንፈስ ውስጥ የታደመ ነፍስ አብሮ እያለ ቀርቶ እኛን በሩቅ ያለነው ኢህአዴግ የሚባል
ጨካኝ ግንባርን ያሰረሳን እውነት ስለነበረው እኒህ ነፍስ በሳቸው ጉዳይ ላይ በተገኙበት ቦታ እና አጋጣሚ ሁሉ ነፍሳቸውን ከነፍሳቸው
ጤናማ በሆነ ሁኔታ ያሰተሳሰሩ የአዎንታዊ አርበኛ ይሆናሉ ብዬ ነው የማስበው።
ብቻ ስንት ዓይነት አብይን ወደን፤ ስንት አይነት
አብይን አክብረን፤ ስንት አይነት አብይን ተስፋ አድርገን፤ ስንት ዓይነት አብይን ሃሳባችን ጥለንበት እንደነበር አሁን ቡፌው ቀርቦልናል
… መርጦ መከተል ወይንም መርጦ መነጠል ነው ምርጫው።
ከሁሉ በላይ ግን አሁንም ደልዳላዋ ቀዳማይት እመቤት
ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ተስማሚ ጊዜ እዬፈለጉ ዶር አብይ አህመድን ሰብዕና ላይ አሁን እያዬናቸው ያሉ ግድፈቶችን ከሥር ከሥር እንዲገሩት
በሚስትም፤ በእናትም፤ በእህትም፤ በጓደኛም መንፈስ ሆነው እንደ አንድ መደበኛ ሥራ ቢይዙት መልካም ይሆናል። ከሰሟቸው ማለት ነው።
እቴጌ ሰብለ ወንጌል፤ እቴጌ ተዋቡ፤ እቴጌ ጣይቱ፤
እቴጌ ዘውዲቱ፤ እቴጌ ምንትዋብ ሥነ - መንግሥታዊ ሁነት ከደምም ያለ መንፈስ ስላለ ይህን ጥምር ሃላፊነታቸውን በመወጣት ጠ/ሚር
አብይ አህመድ ወደ ቀልባቸው ተመልሰው የተረጋጋ ሥነ - መንግሥታዊ አመራር እንዲኖራቸው ማድረግ የሚገባቸው ይመስለኛል። ቁጣ እን
ብስጭት አገር መርቶ አያውቅም። መጨረሻው ውድቀትም ነው።
ሴት ብዙ ናት፤ ሴት ደግሞ ጥበብ ናት፤ ሴትም
ብልህ ናት፤ ሴትም አማካሪ ናት። እኔ የሳቸው የንግግር ለዛ ራሱ ደስ ነው የሚለኝ። ዓመቱን ሁሉ ዜናውን ሰርቸዋለሁኝ ወድጄው ማለት
ነው። ስለዚህ ድርብ ብቻ ሳይሆን እጥፉ ሃላፊነት አለባቸው ብዬ አስባለሁኝ ከጭፍጫፊ ጋደፊነት ወደ ጠቅላዩ ጋዳፊነት ጠ/ሚር አብይ
አህመድ ከመሸጋገራቸው በፊት።
አሁን እያዬን ያለነው አዳዲስ ባህሪ በቅጡ ሊገራ
ይገባዋል። ለአማላካዊ መንፈስም መመቸት ይገባል። ዘማሪነት ካህንነት ከቤት መጀመር ያለበት ይመሰለኛል። አሁን እኔ ሳስበው የባለቤታቸውነ
ብርቱ ድጋፍ የሚያስፈልገበት ጊዜ ነው። አይ የሚላቸውን መንፈስ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደው
ፈቅደው ደስ ብሏቸው ሊያስተናግዱት ይገባል።
በሰተቀር „የናቁት ይወርሳል“ እንደሚሉት ጎንደሮች
ሆኖ ሌላ ማዕበል ይነሳል … የዝምታ መስፈን ይታያል። ይህ ደግሞ ረቂቅ ነው ልብ መሸፈት ብዙ ነገር ያመጣል የዓለሙ ዕወቅና ራሱ
ጤዛ ጎርፍም ነው … እንኳንስ ወዘተረፈ አሉታዊ መረጃ ቋቱ ሞልቶ ተርፎ።
ሌላ አዲስ ተሿሚዎችን በሚመለከት ምክትል አድርገው
የሾሟቸው ፕ/ አበባው አያሌውን በሚመለከት ብዙ ጹሑፎችን በአንድም በሌላም በአዎንታዊነት ገልጫለሁኝ። ሚዛናዊ የሆነ እሳቤ ያላቸው
ናቸው፤ ትርፍ ነገር ለመናገርም የማይደፍሩ ዲፕሎማት የሆነ ሰብዕና አይቸባቸዋለሁኝ። የታሪክ ተመራማሪ እንደመሆናቸው በታሪክ ቀናይነታቸውም
እሳቸውም ከ ከአቶ ዮናስ ጋር በተመሳሳይ አቋም የሚገኙ መሆኑን ነው እኔ የማስበው ስለምን ምክትል እንዲሆኑ እንደተፈለገ ግን ግልጽ
አልሆነልኝም። የተፈራ ነገር ስላለ ይመስለኛል። ያ አይ ቀጣይነቱም ስለ አለ፡፤
ብቻ ያው ባለተራ እንደሚሆኑም አስባለሁኝ። ምክንያቱን
የጠ/ሚር አብይ አህመድ የሹም ዶሮ ነኝ መንገድ ብዙም ለዚህ ትውልድ መንፈስ አይመጥንም። ሥልጡን አይደለም ዱካክም ነው …
ይቀጥላል …
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ