ጥርጣሬ ማምረት ለውጡን አይጠቅመውም።

የማይጠቅም።
„እንግዲህስ እነግርህ ዘንድ እንደ ባለ አዕምሮ ሰው ቁም አለኝ።“  
መጽሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፵፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
04.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ሳተናው ላይ ስገባ አንድ ጹሑፍ አገኘሁኝ። ጠቅላለ መንፈሱ ቢጠቅም መልካም ነበር። ግን የማይጠቅም አስተሳሰብ ስላለው ትንሽ ማለት ፈልግሁኝ። የሚጠቅመውን አልነካካውም፤ አይጠቅምም የምለውን ሐረግ ብቻ ነው የማነሳው። አግረ መንገዴን አብን ስለተነሳ አንድ ነገር አያይዛለሁ፤ መንፈሱ በቀጥታ ርስቱ አህቲነት ስላለው። መቼም በአብን ላይ  ያለው ማዕት ብአዴን/ አዴፓ ላይ ተሰውሮ የተያዘ መከራ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል አዴፓ/ ብአዴን። 

የሐዋሳው የኢህአዴግ ጉባኤ እና የለውጥ ሂደቱ ፈተና! – ኤርሚያስ ለገሰ
  • ·       የተከበረው ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እንዲህ ይላል…

 የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ከህውሃት ጋር በጠላትነት ከመፈራረጃቸው ባሻገር ጨዋታቸው ኢኮኖሚስቶቹየአውራ ዶሮ ጠብ (Chicken Games) መሆኑ በግልፅ ወጥቷል። ለህውሓት ከአዴፓ ይልቅ የአብርሃ ደስታ አረና ፓርቲ ወዳጁ ነው። ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው። ልዩነታቸው እኔ የወከልኩትን ሕዝብ የበለጠ የሚጠቅም አጀንዳ አለኝ የሚለው ላይ ነው። በሀሳብ መተጋገዝ ካየነው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሚቀርበው ዶክተር ደብረፂዮን ሳይሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነው። የህውሓት አመራሮችቲም ለማን!” ከምድረገፅ ለማጥፋት መጥፎ እልህ ውስጥ ገብቶ የቀበሮና ጃርት ጦርነት ( The Hedgehog Theory) ውስጥ ተዘፍቀዋል። በተለይ አቶ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶክተር አምባቸውን የመሳሰሉ የአዴፓ አመራሮችን ለማጥቃት ቀን ከሌት ስትራቴጂ ሲነድፉ እና በዙሪያቸው ሲያደቡ የምናይበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ቀበሮ እንዲህ ነው የሚያደርገው። እርግጥ ብዙ ጊዜ ቀበሮ አይሳካለትም።“

በጥቅሉ ሲታይ የግንባሩ ድርጅት አባላት እንደግል እና እንደ ድርጅት የሚከፍል ሃሳብ፤ ጥርጣሬን አብዝቶ የዘራ ሞገደኛ ሃሳብ ነው። በዚህ ውስጥ ለጸሐፊው ኦዴፓ ቅዱስ ነው። እሱ እና ኦዴፓ / ኦህዴድ ምን እና ምን ሆነው እንደባጁ ብራና ሳተናው ይመስክረው። የማናውቀው ሰው ሆኖ ነው የባጀው። አሁን አሸነፊው ሃሳብ ስላሸነፈ ብቻ ሳይሆን በወዳጅ በዘመድ የተገኜ ንጹህ አዬር እንዳለ እናውቃለን።
  • ·       ትንሽ እንፈታተሽ።

መጀመሪያ በጥቂቱ እንነሳ። ለህውሓት ከአዴፓ ይልቅ የአብርሃ ደስታ አረና ፓርቲ ወዳጁ ነው። ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው። ልዩነታቸው እኔ የወከልኩትን ሕዝብ የበለጠ የሚጠቅም አጀንዳ አለኝ የሚለው ላይ ነው።“

የተከበርከው አቶ ኤርምያስ ለገሰ ኦዴፓንስ ለምን አልደፈርከውም፤ ምን አስፈራህ ነው መሰረታዊ ጉዳዩ? አገር መሪ ስለሆነ ወይንስ ሌላ ውለታ ቢጤ ስላለ? ኦህዴድን/ ኦዴፓን ስታብጠለጠለው አደለምን የባጀኸው? „ለማማም ገዳይ ገዱም ገዳይ“ ብለህናል ሌላው ቢቀር። ይህም ብቻ አይደለም እናንተ ስለ ኢትዮጵያ ኦሮምያ ላይ  እዛው ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ ስለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ምቹ ሁኔታ ፍጠሩ መሪነቱን ለእኛ ተው ተብለዋል። አገር መምራት ለእናንተ አያምርባችሁም ነው ሲፈታ።

ይህም ብቻ አይደለም ለለማ ‚ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ መንፈስ እኮ 1% ነው የሰጠኸው። ሌላውንም ጆሮ ያለው፤ አቅም ያለው፤ ችሎ በዛ በጭንቅ ጊዜ ቢመርም ቢጎመዝዝም ያደመጠው ያውቀዋል። የሆነ ሆኖ ምነው ዛሬ እንዲህ እኛ ነን አውራዎ ደጋፊዎች ተባልን? ማተብ የሚባል ነገር አለ!
   
ይህም ይሁን ፊርማው ሳይደርቅ? በአብርሃሙ ቤት በብአዴን ቅናዊ አመራር ባህርዳር ጎንደር ወሎ ላይ ግንቦት 7 አቀባባል ሲደረግለት፤ ወጣቶችን እንዲያወያይ ሲፈቀድለት፤ ከኤርትራ ምድር በጭነት መኪና የጫነውን ግንቦት 7 አለኝ የሚለውን ሰራዊት ተቀብሎ ካንፕ ሲያስቀምጥ ያን ያህል ክብር ሰጥቶ የወርቅ ካባ ለሊሂቃኑ ሲያለብስ ብአዴን አብን ወግኖ ነበርን?

እስኪ ይነገረን ብአዴን ውጭ አገር ለነበረ አንድ የአማራ ድርጅት፤ ለአንድ የአማራ አክቲቢስት ይህን ያህል ክብር፤ ግርማ እና ሞገስ የሰጠው ከቶ ለዬትኛው ድርጅት ይሆን? ለእናንተው ነው ጉንብስ ቀና ሲል ነው ያዬነው። ከ14 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ሲደረግ እናንተው አላችሁበት።

በብአዴን ጉባኤ ላይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲገኙ እናንተ አላችሁበት። አሁን ለብአዴን / አዴፓ የሚቀርበው አብን ነው እዬተባለ እዬተከሰሰ ነው። ለነገሩ ይባለቸው ቁጭ አደርጎ አምላክ እያሳያቸው ነው። ፊርማው ሳይደርቅ? ይህን ኦዴፓ / ኦህዴድ ነው ያደረገላችሁን?  ነገ ደግሞ አብን ተከሳሽ ቢሆን የአዴፓ አባላት በአብን ምክንያት መታሰሩም መገረፉም መሳደዱም ይቀጥልላቸዋል ማለት ነው። ዕድሜ ለአቶ ኤርምያስ ለገሰ አሁን አዋህዷቸዋል እና አብን እና አዴፓን። 

ሰሞኑን አብን ከኤሌቲቪ ጋር ቃለ ምልልስ ነበራቸው፤ ሙግቱ ተመችቶኛል። ውስጥ የቋጠረው ፍቺ ተፈቷል። ጠንከር ባለ ሁኔታ የተጀመረው ሃርድ ቶክ እንደ አጀማመሩ በዛው ልክ ተጠናክሯል ተጠናቋል።

ለሁሉም እንዲህ ቢሆን ምን አለ አሰኝቶኛል። ከዶር ገመቺስ ደስታን ጋር የነበረው ልስሉስ ውይይት ተከታትዬው ስለነበር። አወያይ እንዲህ ጠንከር ሲል ገፊ ሃይሉ ምን ይሆን በሚል ጠለቅ ያለ ብርታት ያለው መንፈስ በአድማጩ ዘንድ ይፈጥራል። ስለዚህ ለእኔ ማለፊያ ነው። ለሁሉ እኩል ነበር መሆን ግን ይጠይቃል።

 „የውሃ ልክነት“ ለሚለው ግን ትንሽ ነገር ላንሳ„ፊደል“ መቅረጽ ዕወቀት መፍጠር ነው። ዕውቀት ደግሞ አገር በማበጀት፤ ሰብዕና በመቅረጽ፤ ጥበብን በማጋባት ትልቅ ድርሻ አለው። ሌላው „ፈውስ“ መጸሐፍ እና የጀርመን የመዳህኒት ፍልስፍናንም ሐንቦርግ ዩንቨርስቲ ጎራ ማለት ይጠቅማል። ሌላው መስካሪ የሚታዩ፤ የሚዳሰሱ ቅርሶች ስላሉ ብዙም መድከም አያስፈልግም። ዛሬ ድርስ የምኸዋር ፈላስፋዎችን የሚሞግትም ቅርስ አለ በዛው መንደር። ይህ በጥቂቱ ነው ...   

ሌላው ያዬነው ውሃ ልክነት ደግሞ ጣና ኬኛ እና ዕድምታውን ሁላችንም ያዬነው የዘመኑ ገድል ነው፤ የ2010 የጠ/ ሚር ምርጫ ድምጽ አሰጣጡን ገባ ብሎ  መመርምር መልካም መሆኑን እግረ መንገዴን ለልዕልት ቤትሻ በአከብሮት ማብሠር እሻለሁኝ። ዕድለኝነቴ የአርሲን ገበሬንም እኔም ማወቄንም መግለጽ እውዳለሁኝ። ሙግቷን ግን አሁንም ወድጄዋለሁኝ። 

ልዕልት ቤቲ ታፈሰ ከራሷ ካቆሰላት ስሜት ጋር ባታነካካው፤ ሰው ከሰጣት ገፊ የቤት ሥራ መንፈስ ጋር የነበረው ቁርኝት ከመኖሩ፤ ሰብዕናን ከመተላለፍ አክብሮ የሄደ እንግዳ ክብር ነው ለዛውም ለሷ ለክርስትና ጽኑ አማኟ ከዚህ በስተቀር ሙግቷን ወድጄዋለሁኝ።

ይህን የአወያዮች፤ የጸሐፍት ሙግት የሚያርደው፤ የሚፈራ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ሊባል ከቶውንም አይችልም። እንኳንም ሞገተችልኝ። መንጠር ብቃት የሚመጣው ከዚህ ስለሆነ። የአብን መሪ ዶር ደስአለኝ ጫኔ ወጣት ናቸው፤ ጀማሪ ናቸው ያጠነክራቸዋል። በዛ ላይ ወጀቡ ሁሉም አሰፍስፎበታል አብን ላይ።

በሌላ በኩል የሰሞናቱን የ5ቱን  የኦሮሞ ፓርቲ ድርጅቶችን መግለጫም አቅርባ የማከብራት ቤትሻ ስትሞግት ማድመጥ ናፍቆኛል። ግን በአሪስኛ እንዳይሁን አደራ ቤቲሻ።
       
የሆነ ሆኖ ስለምን እዛ ኤል ቲቪ ላይ „አብን“ እንዲቀርብ የተደረገበት ምክንያት ልክ አቶ ጃዋር መሃመድ አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት አልጀዝራ ጋር ቃለ ምልልስ እንዲያደርግ የተደረገው ድራማ ነው የተደገመው። ስለምን ከእንቶኔ በፊት ቀድሞ አልተደረግም ቃለ ምልልሱ። የተፈለገው የተጠነሰሰው - የተቀመመው አቅጣጭ የተቀመጠው በማን ስለመሆኑ ልብ አለን እናውቃለን። የቤቲሻ ሙግት ግን የማልክደው ጉዳይ ተመችቶኛል። ምን አንገት የሚያስደፋ ጉዳይ ይኖራል በነገረ አማራ ጉዳይ። ምዕራባውያንም ይመሰክሩታል እኮ፤ የፕሮፌስር ልቅና የተገኘው በምን ሚስጢር እንደሆነ ታሪክን ማንበብ ነው።   
  • ·       ሌላው

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ወደ ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ዕይታ „በሀሳብ መተጋገዝ ካየነው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሚቀርበው ዶክተር ደብረፂዮን ሳይሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነው:። ይህ ፈንጅ ነው። ፈንጅ የሚሆነው በሁለመናው በግንባሩ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው የለውጥ መንፈስም ደጋፊም ፍቅር ለጋሽም ጭምር ነው። ለዛውም ዛሬ ድምጽ በሚያስፈልግበት ጊዜ። የሃሳብ መሰባሰብ በሚያስፍለግበት ወቅት።

ይህ እንግዲህ አደገኛው አስተምህሮ ነው። ለዶር አብይ አህመድ፤ ለአብይ ሌጋሲ፤ ለኦዴፓ ጠቃሚ አይደለም። ህዝብ በጥርጣሬ እንዲያቸው ያደርጋቸዋል። ሲደግፋቸው የነበረው ሰውም ድጋፉን እንደ ገና ሪባይዝ እንዲያደርግ ይጋብዛል። አብሶ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ጮማ የሆነ ፍንጭ ነው። „እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ“ ዓይነት ነው። ለዛውም የኢህአዴግ ጉባኤ ምን ይወስን ምን በማይታወቅበት ሁኔታ ላይ።

ለወደፊትም እንዲሁ መሰናክል ያመርታል። ተፎካካሪ መሆናቸውን ሁሉ የሚደጥ ነው ይህ ሃሳብ። ኢህዴግ እና ግንቦት 7 እኮ ተፎካካሪዎች ናቸው? በዚህ አገላለጽ ተዋህደዋል ወይ ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን። ምክንያቱም የቀደሙ ውልብሊቢቶች ስላሉ። ለእኛ ችግር የለውም ግን ኦዴፓ እንደ ድርጅት ዶር አብይን እንደ መሪ የሚፈትን ይሆናል። አንድ የፖለቲካ ድርጅት ካለደጋፊ ከባህር የወጣ አሳ ነው። ኦዴፓ ሙሉው ከሳቸው መንፈስ ጋር ስለመቆሙም የሚያውቀው አባሉ ብቻ ነው።

በፍጹም ጠቃሚ መንፈስ አይደለም። መንፈስን ይሰነጥቃል። የአብይ ሌጋሲ ያለውን በራስ የመተማመን መንፈስም ይፈትናል። ደፍሮ ለመንቀሳቀስ የሚያንቀው ነገር ይኖራል። ከዚህ ቀደም እንዳሻው ሃሳቡን ሲገልጽ ለነበረ መንፈስ እንዲህ ማነካካት አያስፈልግም ነበር። ቃላት መምረጥ ግድ ሊለው ነው የአብይ ሌጋሲ። 

ዶር አብይ አህምድ የእኔ የሚሉት ሰብዕና፤ የእኔ የሚሉት ፍልስፍና ያላቸው ሰው ናቸው። ይህን ደግሞ ባጅቼበታለሁኝ። የፖለቲካ ፍልስፍናቸው ሆነ ሃሳብ የማፍለቅ መንገዳቸው አይገናኝም ከግንቦት 7 ጋር። ሃሳብ ጥገኛ አይደለም የአብይ መንፈስ። ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው አይሻም። ወይንም ተጽዕኖ ፈጣሪ መንፈስ ሲለቅም አይገኝም። ሃሳብ አያልቅበትም። በሃሳቡ ውስጥ ነው ትልሙ የሰከነው። በሌላ በኩል ትናንት እኮ አትመጥንም አትወደዳርም አልነበረም ሙግቱ ስለምን ዛሬ ማጠጋጋት ተፈለገ ይሆን? የትናንቱ አብይ እኮ ነው ዛሬም ያለው። እስኪ „ህሊናን“ አንብቡት ውዶቼ። በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮች እዮዋቸው። ቋሚ የሆነ ጽናት ጠፋ። በፍላጎት ውስጥ መዝለቅ ተራቆተ።    

ESAT Efeta 5 Jan 2107 (2018)

ይድረስ ለአቢይ አህመድ (/  (ለኦህዴድ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በኤርሚያስ ለገሰ)

ሌላው ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል እና ዶር አብይ አህመድ እኮ በአንድ ርዕዮት የኖሩ ጓዶች ናቸው ቢያንስ። አሁንም እሰከ ዛሬዋ ቀን ድረስ በአንድ ግንባር ውስጥ ነው ያሉት። ሃሳቡ መልዕክቱ ለዶር ደብረጽዮን አብይ ከእኔ ይልቅ የግንቦት 7 ሊቀመንበርን ያቀርባል፤ የእኔን ሃሳብ አያቀርበውም እንዲል ወደዛ ይገፋል። ይህ ደግሞ ጥሩ አይደለም። ብዙ ሰው በጣም ስሜቱ ስስ ነው። በዚህ ላይ ግንቦት 7 በጥርስ የተያዘ ንቅናቄም ነው። መቼውንም ቁስሉ ይሸራል ብዬ አላስብም። ምክንያቱም የግራ ፍልስፍና ጠጠር ነው ወደ ፍቅር ለማምጣት። ፈተናው እኮ አሁን ይህ ነው።

ሌላው ያን ያህል በዶር አብይ አህመድ ላይ በተገኘው ሚዲያ ሁሉ በአሉታዊነት ተዘምቶ አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ መንፈሳቸው ቅርብ ሰው እንደ ተፈለገ እና እንደ ተገኘ ይታወቃል። አቀራራቢ ሰው። ያ አቀራርቢ ሰው ከሦስቱ ሥላሴዎች አንዱ ነበሩ። ማናቸው በምን አመክንዮ ተገናኙ አስፈላጊ አይደለም። ግን ተልዕኮቸውን በሚገባ ተወጥተዋል። የፖለቲካ ሰው ግን አይደሉም። ይህን በብልህነት ክድን አድርጎ መያዝ ያባት ነበር። ግን አልሆነም። ማሸነፍ እኮ ሚስጢርን መጠበቅ ነው። 

የሆነ ሆኖ ቢያንስ በረጋ ሁኔታ ላይ ላለው የአብይ ሌጋሲ በግራ በቀኝ ጥርጣሬ ማምረት የተገባ አይደለም። ትናንት በተቃውሞ ሥም ዛሬ ደግሞ በድጋፍ ሥም? ? ? ሌላ ተጠራጣሪ ማህበረሰብ መፍጠር ምን ይባላል? ማንን ይጠቅማል?  ለውጡን? እእ ...
  • ·       ፍርድ ሲሰጥ።  

አቶ ኤርምያስ ለገሰ ፈርዷል፤ ወስኗል በአዴፓ ላይ። አዴፓን ወንጅሏል። „ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው።“  ዘረኛ ነው አዴፓ እያለን ነው። ኢህዴግ እኮ ህብረ ብሄር ፓርቲ አልነበረም፤ ህብረ ብሄር ፓርቲ ቢባል ብአዴን/ አዴፓ ነው። መሪዎቹ በሙሉ እነማን እንደ ነበሩ ዓለም የሚያውቀው ሃቅ ነው። ራሱ የአሁኑ ጤና ጥበቃ ሚ/ር ተጋሩ ናቸው የዶር ቴወድሮስ አድህኖም ቤተሰብ ናቸው። ውክልና ያገኙት በብአዴን/ በአዴፓ ነው።

ሌላው አዴፓ ወደፊትም ማንኛውም ዜጋ ደንቤን ከተቀበለ አባል ይሆናል ነው የሚለው። ይህም የቆዬ ባህሉ ነው። ይህ ማለት አባል ሆኖ ግዴታውን የሚወጣ አቅም ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ አመራር አካል ይሆናል ማለት ነው። ይህን የእሱ የፖለቲካ ድርጅት ግንቦት 7 አይደፍረውም።  ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው።“ ይህን ካለን በኋዋላ ደግሞ እንደ ገና ያመጣ እና ከቲም ለማ ጋር ያጋባቸዋል፤   

የህውሓት አመራሮችቲም ለማን!” ከምድረገፅ ለማጥፋት መጥፎ እልህ ውስጥ ገብቶ የቀበሮና ጃርት ጦርነት ( The Hedgehog Theory) ውስጥ ተዘፍቀዋል። በተለይ አቶ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶክተር አምባቸውን የመሳሰሉ የአዴፓ አመራሮችን ለማጥቃት ቀን ከሌት ስትራቴጂ ሲነድፉ እና በዙሪያቸው ሲያደቡ የምናይበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ቀበሮ እንዲህ ነው የሚያደርገው። እርግጥ ብዙ ጊዜ ቀበሮ አይሳካለትም።“ ማዋዥቅ። 

እኔ ሌላው የንድፈ ሃሳብ ፖለቲከኛ ቢናገር ፍጹም አይከብደኝም፤ እሱ ግን ንድፈ- ሃሳቡን ብቻ ሳይሆን የድርጅት አባል፤ አካል ሆኖ ኑሮበት መሬት ላይ ሠርቶበታል። ያልፉት ጊዜያቶች የባከኑ መንፈሶች አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ በዚህ መሰል መፈረጅ እና መንፈስን መክፈል የተገባ አይደለም። ምን አለ ትዕግስቱ ቢኖር። ይህ አገላላጽ በግንባሩ ውስጥ ያለውን ቅራኔውን ቢያባብሰው እንጂ አያረግበውም።

ራሱ ግንቦት 7 አሁን ማንሳት አይገባም ነበር። እረፈት ቢሰጠው ምን አለ። የሚጻፉ፤ የሚሰጡ መግለጫዎች፤ ውይይቶች ሁሉ ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል። ምክንያቱም ሙሉው አመራሩ መሬት ላይ ነው። ደጋፊዎቻቸውም መሬት ላይ ናቸው። ከሁሉ በላይ የአብይ ሌጋሲ የማስቀጠሉ ነገር ከስሜታችን፤ ከፍላጎታችን ጋር ንክኪ እዬፈለግን እያውራረስን ከሆነ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው። ለሁሉም ሳይጠቅም ባክኖ ይቀራል። ለውጡ እንደ ግብጽ ባክኖ ተበትኖ ከስሎ ይቀራል። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም።

አላስተዋላችሁት ካለሆነ በቡራዮ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መግለጫ ሲሰጡ አቶ ነዕምን ዘለቀን አቋቋማቸውን አይቼ አዝኛለሁኝ። በአካል ባላውቃቸውም ንግግራቸውን ዩቱብ ላይ እከታተላለሁኝ። የአንበሳ ግልገል ነበሩ ሲናገሩ ስብሰባ ላይ። እዛ ላይ ግን ኦቦ በቀለ ገርባ እዬተናገሩ እሳቸው በምን ሁኔታ እንደ ነበሩ አቋቋማቸው ፈጽሞ አይረሳኝም። ረመጥ ውስጥ ነው ያሉት።

የሆነ ሆኖ ብአዴን ላደረገው መልካም ነገር ሁሉ የተበላበትን ወጭት ሰባሪነት ግን የተለመደ ስለሆነ አይደንቀንም። መልካም ማድርግ ለሰው ሳይሆን ለፈጣሪ ይመቸዋል። ከመልካምነት ቢያንስ የህሊና ትርፍ ይገኝበታል። ብአዴን እንደለመደበት የአብርሃም ቤትነቱን ይቀጥልበት ... አገር አለኝ ማለት ይህ ነው። አክቲቢስት ቶሎሳ የምገባበት አገር ሌላ የለኝም ጎንደር እና ጎጃም ካልሆነ ይላል። 
  • ·       ሦስቱም አይጠቅምም።

. 1 የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ከህውሃት ጋር በጠላትነት ከመፈራረጃቸው ባሻገር ጨዋታቸው ኢኮኖሚስቶቹየአውራ ዶሮ ጠብእግዚኦ!

. 2„ለህውሓት ከአዴፓ ይልቅ የአብርሃ ደስታ አረና ፓርቲ ወዳጁ ነው። ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው።“

.3.              „በሀሳብ መተጋገዝ ካየነው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሚቀርበው ዶክተር ደብረፂዮን ሳይሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነው።“ 

ሃሳብ የማፍለቅ አቅም ሲኖር ነው መተጋገዝ የሚቻለው። በሌላ በኩል አዴፓ አይጠቅምህም የኦዴፓው አብይ ከግንቦት 7 ጋር ተወዳጅ ነው ሃሳቡ …. ለወያኔ ሃርነትም መንፈሱ የአብይ ሌጋሲ ከግንቦት 7 ሊቀመንበር ጋር ስለሆነ ቀበቶህን አጠባብቅ ነው። 

ሌላው ሰሞኑን ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እሰቡት - ክብረቶቼ። የ5 የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጀቶች ክስ እና አሁን የተሄደበት መንገድ ለአብይ ሌጋሲ ምን ያህል አደጋ ውስጥ እንደሚጨምረው። እራሱ የአቶ ጃዋር መንፈስ አብይን አይፈልገም፤ በዛ ላይ ይህን መሰል ማዳበሪያ ማከል ምን ያህል ጥላቻውን እንደሚያከረው ተመልከቱት።
  • ·       ቁርጥ ያጠግባል።

እኔ መሬት ላይ እያለ ግንቦት 7 ሥሙን ባለነሳ ደስ ይለኝ ነበር። ግን ምን ይደረገ። ግንቦት 7 አይደለም „ጣና ኬኛን አባይ ኬኛን“ ባህርዳር ላይ ያስተናገደው። ግንቦት 7 አይደለም ደብረብርሃን ላይ ኦሮማራ ሊሂቃን ውይይት ያደራጀው። የዚህ ሁሉ የውሃ ልክ እሱ ነው። ፈቃጁም ብአዴን / አዴፓ ነው።  

„ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውንም“ ፕሮ ግንቦት 7 አይደለም ግርማ ክብር የሰጠው ለኦህዴድ / ኦዴፓ ይህን ብራናው የሳተናው ይመስክር። ራሱ ጽንሰቱ ጣና ዘገሊላ ግዮን ላይ ነው። ድልዳሉ ደግሞ ብአዴን/ አዴፓ ነው። ብአዴን  ለኦህዴድ/ ለኦዴፓ የጀርባ አጥንት ነበር። የዛሬን ስለማላውቅ ነው "ነበር" ያልኩት … የሥማቸው መመሳሰል ፍንጭ ቢሰጥም ... 

ይህም ብቻ አይደለም አቶ ደመቀ መኮነን እጩ ጠ/ ሚር ቢዋዳደሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ነበር ጠ/ ሚር የሚሆኑት። ድምጽ ይከፋፈላል። ደቡቦች እና የወያኔ ሃርነት ትግራይ እሳቸውን ነበር የሚመርጡት። ይህም ብቻ አይደለም ሙሉ ድምጹን ለኦህዴድ/ ለኦዴፓ የሰጠው ብአዴን / አዴፓ ብቻ ነው። ያሸነፉትም በዚህ ነው። ደቡብ እኮ 8 ደምጽ ብቻ ነው የሰጠው ለዛውም። ይህም አንድ የመሰረት ድንጋይ አማራን ያደርገዋል። 

ይህም ብቻ አይደለም የአብይ ሌጋሲ እንዳሻው የሚዘናከተው አማራ መሬት ብቻ ነው። የትም ቦታ ዬዬድርጅቶችን የወያኔ ሃርነት ትግራይን፤ የደቡብን፤ የኦህዴድን ከታች እስከ ላይ ያሉትን አመራር አካላት አላነጋገሩም ዶር አብይ አህመድ። ኦህዴድ ላይ እንኳን አልቻሉም። የቻሉት አማራ መሬት ብቻ ነው። አማራ መሰረት ነው የሚባለው የትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ያለው ዕውነት ይህ ስለሆነ ነው። 

ከራሳችን ቢወረድ ሁሉም ራሱን ችሎ ቢቆም ምንኛ መልካም በሆነ ነበር? ግን አልተቻለም? ተወቃሹም፤ ተገላዩም፤ ተወርዋሪውም እሱ ነው አማራው። ርካቡም እሱ ነው አማራው እና ድርጅቱ።   

/ አብይ አህመድ  2100 የብአዴን አመራሮች ጋር በባህርዳር ተወያዩ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
አሁን በአቶ ኤርምያስ ፍልስፍና ብአዴን/ አዴፓ ከአብይ መንፈስ ይልቅ፤ ከግንባሩ መንፈስ ይልቅ የዘውግ ድርጅቱ ለዛውም ተፎከካሪውን አብን እንደሚቀርበው አድርጎ ይነግረናል። አይጠቅመም ይህ ለኦዴፓ …. መፈራቅቅ፤ መጠራጠር ነው የሚፈጥረው …  ለለውጡም አደጋ ነው። አዴፓን ለወያኔ ሃርነት ትግራይም ተላልፎ እዬተሰጠ ነው። በእርግጠኝነት እንዳይሰሩ ጫና ለመፍጠርም ነው።

ከሁሉ በላይ ለውጡ ቢቀለበስ የመጀመሪያ ረድፍ ተጠቂ ግንቦት 7 ነው። ተስፋ የሚባለው ነገርም ይቀበራል። የዚህ ሁሉ መፈናቀል መሰረቱ እኮ እልሁ - ቁጭቱ - መጠቃቱ የተሰማው አፈንጋጭ ቡድን ያደራጀው ያበጀው ቀውስ ነው። ወንበርም የቀረባቸው። ማስተዋል ያስፈልጋል። ተመክሮ የሚባለው ነገር ለዚህ ካልረዳ ለመቼ እንደሚሆን ግራ ይገባኛል። ቢያንስ አገር የገቡትን ወገኖቻችን እንሰብላቸው። እዛው የነበሩትማ የለመዱት ነው። ጀግኖቻችንም አይደሉም። ክብር ለመስጠት እንኳን አለመደፈሩ እዬታዬ ነው። 
  • ·       ምርኩዝ በጥቂቱ … ማተብ ያላቸው ይህን ጹሑፍ

#EthiopianPatrioticGinbot7 Welcome CeremonyAt Bahir Dar  ለአርበኞች ግንቦት7 በባህርዳር የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገ

Ethiopia:/ ብርሃኑ ጎንደር ላይ ታሪክ ሰራ ኢትዮጵያዊነት ነገሰ !!

 

ይህ ሁሉ ግን መና ቀርቷል ዛሬ፤ ነገማ ሲወሳ ወንጀል ይሆናል።

 

ትዕግስት ቢኖር ተስፋ ይለማ ነበር።


የኔዎቹ ኑሩልኝ፤ መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።