ይድረስ ለማከብረዎት ለብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ ።

ይድረስ ለማከብረዎት ለብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ
ባህርዳር።
„ወርቅና ብዙ  ቀይ እንቁ ይገኛል የእውቀት
 ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.01.2018
ከእማ ዝምታ - ከሲዊዝሻ።
                                                               
·        መነሻ።
ETHIOPIA - ''አርበኞች ግንቦት 7 የውሸት ፖለቲካ እየተጠቀመ ነው።'
'ቅሬታ አቅራቢ የግንባሩ ወታደር- NAHOO TV
Published on Jan 5, 2019



ጤና ይስጥልኝ የማከብረዎት ብ/ጄ አሳመንው ጽጌ እንዴት ሰነበቱ? ደህና ነዎት ወይ?እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰዎት። መታመን እንዳይደርቅ አስቸኳይ ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው ለጥያቄዬ ... ከዚህ ሩህሩህ ዘመን በላይስ ምን ይናፍቃል? ያላዩት አገር ካለሆነ በስተቀር? 

·       ምክንያታዊ ጥያቄ በትህትና … ግን የግድ መልስ ሊሰጥበት የሚገባ።
  
አንድ ቃለ ምልልስ አሁን አዳመጥኩኝ በናሆ ቲቪ። በግዳጅ ጊዜ ብዙ ፈተና ስላለ አብዛኛውን ጉዳይ እንደማንኛው ወታደራዊ ሥርዓት አዬሁት። እርግጥ የሚያሳዝኑ ነገሮች መኖራቸውን ሳስብ የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ይቆም ዘንድ ፈጣሪ ይህን አዲስ ሰውኛ ዘመን ስላመጣ ተመስገን ማለቴ የዘወትር ግዳጄ ይሆናል።

በሌላ በኩል ሃላፊነት እና ተጠያቂነት በዬትኛውም ደረጃ መቀበል እና መፈጸም ደግሞ የነገን የኢትዮጵያ መሪ የመሆን ዕድል ቢገጥም ብሎ ማሰቡም ስዕሉን እኔ የራሴ ግንዛቤ ስለላኝ፤ በገርነት ለሚያው ወገን የሚጠቅም ትምህርት ያገኜ ይመስለኛል። 

ቃለ ምልልሱን ደግሜ አዳመጥኩት ነገር ሃላፊነት እና ተጠያቂነት፤ ወገናዊነት፤ ቃል ኪዳን፤ የበርሃ ኑሮ፤ አርበኝነት፤ የእኔ የማለት የት ቦታ ላይ እንደሆነ፤ የማደራጀት፤ የመምራት፤ የማቀናጀት ነገር ብዙ እንደሚቀር አስተውያለሁኝ። ተስፋ አዬር ላይ የተንጠለጠለ ስለመሆኑ ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁኝ። አሁን በቤተኞቹ ሲገለጽ ግን አዲስ ሆነብኝ።

በዚህ ዕሳቤ ይህ ቀን ባይመጣ በሚለውም ሳሰላው ይህን የተመረቀ ዘመን ለማስቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ ቆርጦ መትጋት እንዳለበት አንድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ይመስለኛል። ተስፋ እና አቅም ካልተመጣጠኑ ቢያንስ አሁን የተገኘውን ለምለማዊ ዕድል እንዳያመልጥ ጠበቅ ማድረግ የሚገባ ይመስለኛል።

የበዛ ዝርክርክነት የሰው ህይወት ያህል ለሚገበርበት መስመር ለማድመጥ ይከብዳል። ይጨንቃልም። እንግዲህ ጋዜጠኛ ሆኖ የማንፌሰቶ ማህበረተኛ አለመሆን የሚጠቅመው ለዚህ ጊዜ ነው። ዕውነትን ፍለጋ ርትህ አደባባይ ሂሊና ፈተና ስለሚያስቀምጥ። ሌላውን አረመኔያዊ ድርጅት ነው ብለህ የታገልክበት፤ ያብጠለጠልክበት በራስህ / በራስሽ ባመንሸው / ባመንከው ቤት ስታደማጠው/ ወይንም ስታዳምጨው ጋራ ነው ውሃ ያዘለ … ለማመንም፤ ለመቀበልም ... ጦርነት በ እኛ ቢበቃ ምን አለ ፈጣሪ ቢማለደን። 

·       አፋጣኝ መልስ!

እኔ ግልጽ እንዲሆንልኝ የምፍልገው ብ/ጄ/ አሳምነው ጽጌ የማን ናቸው? የሚለው ነውበዚህ ቃለ ምልልስ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ካንፕ ለገባው የሠራዊቱ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ተጠሪ ውክል አካላት፤ ሠራዊቱን የሚያደራጁ እና የበላይ ጠባቂ ሊሆኑ የሚችሉት ብ/ ጄ አሳምነው ጽጌ እና ሌላ አንድ ከፍተኛ መኮነን እንደሆኑ በግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች ለሠራዊታቸው ኤርትራ ላይ ተገለጸልን ነው የሚለው አርበኛ አምደማርያም ዙራ።

ሁለቱም መኮነንኖች የግንቦት 7 መንፈሶች ስለመሆናቸው እራሳቸው የሚመሰክሩት ሆኖ አሁን ብ/ ጄ አሳምነው ጽጌ ዬትኛው ድርጅት ናቸው ነው የእኔ መሰረታዊ ጥያቄ። የማንን ተልኮ ለማስፈጸም ነው የአዴፓ ማዕክላዊ ምክር ቤት አባል ሆነው የተመረጡት?  አሁን እርግጥ ነው ከፖለቲካል ድርጅት አባልነት ወጥተዋል ግን ሰፊ ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

 ይህ ዝንቅንቅ ጉዞ መጥራት አለብት ብዬ አስባለሁኝ። እስካሁን ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሁሉንም አዳምጫለሁኝ። በኢትዮጵያ አዲስ የለውጥ መንገድ አብዘተው መመሰጣቸውን ነው ያጠናሁት። ያመለጠኝ ቃለ ምልልስ ፈጽሞ የለም። ሲሾሙም እጅግ በደስታ ነው ህሊናዬ የተቀባላቸው። ወጣቶች „እኔም አሳምነው ነኝ“ ብለው የጸጥታውን ጉዳይ እንዲረዷቸው ሁሉ ተማጽኜ ነበር።

ነገር ግን በዚህ ቃለ ምልልስ ደግሞ የሰማሁት መንታ መንገድ ላይ አቁሞኛል። ስለሆነም ብ/ ጄ አሳምነው ጽጌ የኢትዮጵያ መንግሥት ወይንስ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚፎካከረው የግንቦት 7? ይህን ንጥር ያለ መግለጫ ሊሰጥበት ይገባል።

የግንቦት 7 አባል አካል የሆነ ማናቸውም የኢትዮጵያዊ ዜጋ ስለሆኑ በዬትኛውም ሃላፊነት ቦታ ተመድበው፤ ተሹመው ከፈቀዱ የመሥራት ሙሉ መብት አላቸው። ማንም ከልካይ የለባቸውም። እንዲያውም በመንግሥት ሥራ የማሳተፍ ተግባር ቢፈጽም ብዙ ነገር ማትረፍ ይቻላል። ነገር ግን ይህ በጠራ የፖለቲካዊ አቋም መሆን ይገባዋል።

አሁን ብ/ ጄ አሳምነው ጽጌ ዬያዙት ቦታ ከዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ነፃ የሆነ መሰለኝ መስፈርቱ። በተለዬ አማራው ላይ ያለ ቲያትር ከኖር ቁልጭ ባለ መልኩ መገለጽ አለበት። ብአዴንም /አዴፓም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል።

 የአማራ ክልላዊ መንግሥት ብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌን የሚያውቃቸው በግንቦት 7 ከፍተኛ መኮነንት ወይንስ ብአዴን/ አዴፓ በሚመራው በአማራ ክልላዊ መንግሥት ሥር ናቸው?
የዬትኛው የፖለቲካ አካል ውክል አካል ሆነው ነው አሁን አማራ ክልል ጸጥታውን በመምራት ላይ የሚገኙት ብ/ ጄ አሳምነው ጽጌ?  ይህን የአማራ ክልላዊ መንግሥትም ሆነ ብ/ ጄ/ ተፈራ ማሞም መግለጫ ሊሰጡበት ይገባል። የእስካሁን ይበቃል አቅም በቅይጥ መከራ ሲባክንበት የተኖረበት ሁኔታ አብሶ - ለአማራው።

የግንቦት 7 ከሆኑ ፌድራል ላይ ነው መሾም የሚገባው፤ ክልል ላይ ከሆነም በግልጽ ሊነገር ይገባል። „አለባብሰው ቢያርሱት“ እንዳይሆን …  እንዲህ ዝንቅ በሆነ ባልጠራ ፖለቲካ ሰዉ መንፈሱ ሊበተን አይገባም። አፋጣኝ በሆነ ሁኔታ መግለጫ ሊሰጠብት ይገባል። ሌላ መናድ እና ሁከት ሳይፈጠር። ናሆ ቲቢም መሰሉን ተግባር በፍጥነት መከወን አለበት። ከብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ ጋር ቃለ ምልልስ ማድረግ ይኖርበታል።

ሌላው አሁንም አርበኛ አምደማርያም ዙራ አንደሚገለጸው ከሆነ ግንቦት 7 ከተማ ውስጥም የታጠቀ ሠራዊት እንዳለው እንደገለጸላቸው ነው። ያ ሠራዊት እስካሁን ካንፕ አለመግባቱን ነው የጠቀሰው። ይህ ደግሞ የፌድራል መንግሥት ጉዳይ ይሆናል። ዝም ብሎ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። ይህም ወሳኝ ጉዳይ ነው። ለፕሮፖጋንዳ ከሆነም ግንቦት 7 ጠይቆ ማረጋገጥ ይገባል የጠ/ሚር ቢሮ ሆነ የሚመለከተው አካል።

የት ነው ይህ ሠራዊት? አርባምንጭ? አዲስ አባባ? አሰብ? የት? ይህም በውል መታወቅ አለበት። በዚህ መሰል ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት በተዘናጋ ቁጥር አብሮ መስመጥ ስለመሆኑ ሊገነዘበው ይገባል። ከሁሉ በግራ በቀኝም የእኔ ጉዳዬ የድምጽ አልባዎቹ እናቶች ዕንባ ጉዳይ ነው። ዛሬም ሌላ የተመሰጠረ የውጊያ ሁኔታ ትልም ከኖረ ከባድ ነው። ዙሮ ዙሮ የሚጎዱት እናቶች እና ልጆቻቸው ናቸው። እስከ አገለገለ ድረስ ነው በፖለቲካ ህይወት  … ከዛ በኋዋላ አሮጌ አካፋ እና ዶማ ነው ማንም አያስተዋሰውም። 

 … አሁን ሁለቱ የግንቦት 7 መኮንኖች ናቸው የሚባሉት እስር ላይ በነበሩበት ወቅት በአንድ ዓለም አቅፍ ሚዲያ፤ በአውሮፓ ህብረት የእኛ ናቸው ተብሎ ትግል ሲደረግላቸው ሥማቸው ሲጠሩ ሰምቼ አላውቅም። ሲከበሩ ሲወደሱ ሲቀደሱም ሰምቼ አላውቅም። ቢያንስ በአውሮፓ ህብረት ሪፖርት? 

ለነገሩ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ እኮ እዬተረሱ ነበር እንኳንስ ሌላው? ሌላው ቀርቶ እኔ ለኮፕን ሀገኑ ጉባኤ ያዘጋጀሁት ፓስተር እንዳይለጠፍ ታግጄ ነበር በአዛጋጆች። እኔ የማላውቀው ነገር ይኖራል ብዬ በክብርት ዳኛ ብርቱካን ጉዳይ ላይ ብቻ ነበር ተጋሁኝ።

በመጨረሻ ግን አርበኛ አምደማርያም ዙራ እና አርበኛ ጥላሁን አበጀ ለህይወታቸው ከፍ ያለ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። አብሶ በምግብ ብክለት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል። አሁን የገቡበት መጠራቀቅ ቀላል አልመሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል። መረቡን ማግኘት አይቻልም። በነፃ አገር ታስረን የምንኖረው ዕውነት ፈቅደን ግን ሞትን ደፍረን ነው።

ግንቦት 7 ተቃውሞ ወጥቶ በግዴለሽነት ህይወትን ማስቀጠል ፈጽሞ አይቻልም። ፍጹም ጠንቃቃ መሆን ይኖርባቸዋል። ብዙ ነገር ላይ መታቀብ ይኖርባቸዋል። አርበኛ ጥላሁን አበጀ በጣም ወጣት ስለሆነ ቤተሰቦቹ የተለዬ ጥንቃቄ ሊያደርጉለት ይገባል። እራሱ በሞራላቸው የሚደረሰውን መከራ ለመቋመቋም መሰናዳት ይኖርባቸዋል - ሁለቱም።

በስተቀር የሥነ - ልቦና ህሙማን የመሆን ዕጣ ሊገጥማችው ይችላል። እንዲያውም ጥላ ከለላ ስለሚያስፍለጋቸው ብአዴንን ቢጠጉ የሚያወጣቸው ይምሰለኛል። አገር መልቀቅም የሚያወጣ አይመስለኝም። የግንቦት 7 ሠራዊት እንዲህ ቀላል አይደለም። 

መረቡ ክህወሃትም በላይ ነው። እንዲህ ዘው ተብሎ ተገብቶ ዘው ተብሎ ተወጥቶ ኖርማል የሆነ ህይወት የሚመራበት አይሆንም። በተፈለገው ጊዜ እና ሁኔታ ፈንጁ አይቀሬ ነው። አንደበትን እና ብዕርን መሰብሰብ ወይ ደግሞ ገድሞ መኖር። እውነት የሆነውን ነገር ነው እኔ የምናገረው።  

አርበኞቹ በጣም ነው ያሳዘኑኝ። እራሳቸውን ነው እሳት ውስጥ የማገዱት። የግንቦት 7 ማንኛውም ልብ ፍላጎት እና ራዕይ እኔ ነኝ ያለ የደህንነት ሙያተኛ ሊውቀው ፈጽሞ አይችልም። ግንቦት 7 መንካት ሲጀመር ገዳም ለመግባት ወስኖ ነው። ከባድ ድርጀት ነው። በቅንነትም ራስን ለመገበር ካልተፈለገ ጸጥ ረጭ ብሎ እያዩ ዝም ነው። 

እራሱ ሳይደርሱባቸው እንኳን አያስቀምጡም እንኳስ ተደርሶባቸው። የሰው ሰላማዊ ኑሮ አያረጋጋቸውም። ሽክፍ ብሎ ለመቀመጥም ሆነ ነካካቶ ለመቀመጥ ሁለቱም መንገድ አደገኛ ነው። አደናቸው ውስብስብ ነው … ከምን እንደተሠሩ ራሱ ይገርመኛል።

ውዶቼ አጥኗቸው እና ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለ ዕጣ ቢሆኑ  ብላችሁ እሰቧቸው … በታማኝነት፤ በሰውኛ፤ በተፈጥሮኛ፤ በእኛዊነት ዙሪያ ፈትሿቸው። ኢህፓንም፤ መኢሶንም፤ መድህንም መሪዎችን አዋቃቸዋለሁኝ በአንድም በሌላ። አይከታተሏችሁም እነሱ። ነፃነታችሁን ተጋፍተው በስጋት እንድትዋጡ ቀርቶ ከተወሰነው ተልዕኮ በኋላ ትዝ አትሏቸውም። ይረሷችሁዋል፤ በግንቦት 7 ግን አፈር ተስመሶ እስትቀበሩ ድረስ በዛው ልክ ነው ክትትሉም፤ ጥላቸውም፤ ውግዘቱም ጥቃቱም የሚቀጥለው ... ዘመን አይለውጣቸውም። 

ለዘር ሳይበቃ የቀረውንም የራሴን የኢሠፓንም  አደረጃጃት አመራር አውቀው ነበር ግን ግንቦት 7 መተርጎም አልችልም። በዛ ውስጥ ያሉ ቅኖችን ሳሰባቸዋ ደግሞ  በእጅጉ ያሳዝኑኛል። ጥሩ ጥሩ ሰዎች ደግሞ አሏቸው። እነሱ በማያውቁት ዓለም ውስጥ በበዛ ቅንንት አገልግሎት እንደሚሰጡ፤ እንደሚደክሙ፤ እንደሚባዝኑ … አዳምጣለሁኝ። ግንቦት 7 ዝግ የሆነ ድርጅት ነው። ይህን መሰል ተፈጥሮ ለትውልድ በምን ያህል ጥልቀት ሊጠቅም እንደሚችል አላውቅም?

ፖለቲካ መከራ ነው ግማድ። በዚህ ቃለ ምልልስ ከሳሽም ተከሳሽም፤ በዳይም ተባዳይም ከህወሃት አንጻር ለመመዘን እጅግ ይክብዳል „ማሰቃያ ቦታ፤ መረሸን“ ከባድ ነገር ነው። እውነትነቱን የሚያውቀው ፈጣሪ ቢሆንም ዛሬ እንዴት እንቅልፍ እንደምተኛ ፈጣሪ ይወቀው … ግንቦት 7 የተቃላቀሉ ጋዜጠኞችንም ይህ ጉዳይ የሚፈትን ይመስለኛል ... 
  ሰውኛ ከሆኑ ... 

ዕውነት ደፋርን ትጠይቃለች!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።