ብፁዑ አባ ልቅና ማዕዶተ - ዕውነትን ተመገቡት። ጠጡት።

 

ብፁዑ አባ ልቅና ማዕዶተ - ዕውነትን ተመገቡት። ጠጡት።
 
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"

 
"ዬኦሮምያ ህብረት ባንክ የቤተክርስትያኗን ቅምጥ ሃብት በካዝናው አስቀምጧል። እንሸነፍ ብለን። አዋሽ ባንክ፤ ዬኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ድርሻ አላቸው። ብዙም የረባ በንጠቀምም። አባይ ባንክ ግን ተወዳድሮ በገብያ ህግ አሸንፎ ነው። ከአማራ ባንክ ጋር ምንም ዓይነት ውል ዬለንም። ከእሱ ይልቅ ከሌሎች ተጨማሪ ባንኮች ጋር ዬጠበል ያህል አብረን እንሰራለን። የተሻለ ዬሚጠቅም ተወዳዳሪ ከመጣ ደግሞ ውላችን ይቀጥላል። " ………
ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር ስለነበረው ውይይት ተጠይቀው ሲመልሱ ከመሄዳቸው በፊት እንደምን እንደ ተሰናዱ፤ ከዛም ከሞት ጋር ፊት ለፊት ቆመው እንደምን እንዳስረዱ ገልፀው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ትዕግሥት አድንቀው ጠቅላይ ሚሩ ሊያወያዮዋቸው እንደጠዬቁ እና ጠቅላዩ ማዕከላዊ ይሆኑ ዘንድ፤ መንግሥታቸው ያለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ በትህትና ገልፀው የቤተክርስትያኗ ጉዳይ አወያዮዋም፤ አነጋጋሪዋም ውል አስፈፃሚውም ዶግማና ቅኖናዋ ስለመሆኑ እንዳስረዱ፤ በዚህም እንደተስማሙ ከገለፃው ዕድምታ ተረድቻለሁኝ።
የእግር እና የጭንቅላት አስተዳደርን ፍልስፍናም ባርከውልናል። ሰላማዊ ሰልፍ የገኃዱ ዓለም እና የሰማያዊውንም ፍንትው አድርገው ገልፀውታል። በዚህ እንደ ተረዳሁት ሰማያዊው ሰልፍ በሚያስደምም አኳኋን መከወኑን አብሥረዋል። የአንድም ሦስትም ሆኖ የመምራት ዬማስተዳደር ክህሎትን፤ ዊዝደምን ሲገልፁም የእጬጌው የብፁወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ልዩ ስክነት እና ዬረጋ ብስለት እንዲሁም የበታቾች አባ ትምህርት ብፁዑ ዶር አቡነ ጴጥሮስ እና የአባ ልቅና ዬብፁዑ አቡነ አብርኃም አህቲ መስመር ዕውነት ስለመሆኑ በአጽህኖት ገልፀዋል።
ሰሞኑን አላረፍኩም። እጅግ ደክሞኛል ዓይኔን መግለጥ አልቻልኩም። ጭንቀታም ነኝ እና። በሁሉም ቦታ እዬተዘዋወርኩም ሙግቱን ተያይዤዋለሁኝ። ግን ይህን የመሰለ በዬዕለቱ የዕውነት፤ ዬሃቅ፤ ዬፋክት ዩንቨርስቲ አምላኬ ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁኝ።
ያለው፤ ዬበቃ፤ ክህሎቱ የተሰጠው እንዲህ ሆኖ አስብሎ ማዬት ትናንት አባቶቻችን ኢትዮጵያን አበዷትን ዘመናችን አመሳጥሮልናል። ተመስገን።
እንዴት ነን? እንደምን አደራችሁልኝ። ተመገቡት ጠጡጥት። ታድለናል።
አባ ዕውነት፤ አባ ልቅና በዬቀኑ ዩንቨርስቲ ከፍታችሁልናል ዘመነ ብፅዕና በልዕልና። መታደላችን ማስተዋልን ያበራልን ዘንድ አጋይስት ዓለሙ ሥላሴ ይርዱን። ሰማዕትነት በተመስገን እንሆ ጸደቀ። ይፍቱኝ አባ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በወቅታዊ ጉዳይ የሰጡት ማብራሪያ
ወስብኃት ለእግዚአብሄር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/02/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።