የዕለቱ መልክቴ።
(መፅሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፲፯ ቊጥር ፩)
ከሥርጉተ ሥላሴ 28.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
የዕለቱ መልክቴ።
የኔዎቹ ቅኖቹ ግን ጥቂቶቹ እዚህ ዳምኗል። ተጫጭኖታል። ኢትዮጵያም ደምኖባታል። ነገም ሞት ስለሚጠበቃት። ዜግነት ከደመና አልፎ ጠቁሮበታል፤ ጠባቂ አልባ መሆኑን መስቀል አደበባይ ስላወጀለት። የዲሲውን የሥም፤ የዝና፤ የክብር ይገባኛል ግብግብ ልታደመብት አልፈቀድኩም።
በዚህ ጨለማ ቀን በሚለቀስበት ቀን አልወደውም ለተኖረበት ዝና መውደቅ መነሳቱን። በመከራ ቀን ራስን አጀንዳ እድርርጎ መውጣቱን ያቅለሸልሸኛል። ውሸተኞች መሆናችንም መግለጫው ይሄው ነው። „ነፃነት ነፃነት ነፃነት“ ግን የእውነት ነውን? አልነበረም?
ለነፃነት የሚደረገው ተጋድሎ አጠገብህ ያለውን ነፃነቱን ስትጠብቅለት ነው፤ ዘግተህና ቆልፈህ የያዝከውን በሩን ስትከፍትለት ነው። የምታውቀውን ንጥረ ነገር አውጥተህ ስትመሰከርለት ነው። ስለ አንተ ሳይሆን ስሌላው ብቃት ሞግተህ ስትረታለት ነው። ከአንተ የተሻለ ጀግና እና ብቁ ሲመጣ አፍነህ ወይንም አዳነፍነህ በመቅበር ጀግንነት ጸንቶ አይቆምም። ነፃነት ከአንተ በላይ ጀግና መፍጠር ስትችል ነው ታገልኩለት ማለት የምትችለው። ስተትተካ፤ ራሱን የተካ ሲመጣ ደግሞ ሳጥፈራው፤ ሳታገለው አጥፍህ ሳትይዘው ነው ...
ከዚህ አልፈህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ ብትል የምንታዘብ ሰዎች ስላለን ቢያንስ ዕንባችን ወደ እዬር እንልካለን። ሌላ አቅም ስሌለን። ከዘመነኛ ጋር ስለተጠጋህ የዘመንክ ሊመስልህ ይችላል፤ ግን ከዘመናኛ ጋር እንድትጠጋ፤ ተቀባይነት እንዲኖረህ ያደረከው ግን ያ በመንፈስህ ያገለልከው የእያንዳንዱ ስደተኛ የድምጽ ድጋፍ ታክሎ ነው።
ዛሬ ብሱ ሰው የራሱ ሚዲያ አለው፤ አንዳንዱ ራሱ ጮኾ እዛው የገደል ማሚቶው ውጦት ይቀራል። ስለምን? ደጋፊ ስሌለው። መልካም ነገርም ቢሆን ደጋፊ ከሌለው የአሮጌ ቆርቆሮ ጩኽት ሆኖ ነው የሚቀረው። ስለዚህ መንብር ላይ ያወጣህ ያን ህዝብ በላከው ልክ ካልተገኘህለት እዬዳጠህ ተረት ሆነህ ትቀራለህ ... መሸርሸር አለና።
አንተ እዬቀብርክ ሌላው ቀበረ ብለህ ብትጮህ፤ አንተ መንፈስ እዬገደልክ ሌላው ስጋ ገደለ ብትል ቀመሩ ያው ነው። ያው ከቀባሪው ያልተሻልክ ነህ አንተው እራስህ። ጀግንነቴን ላስቀጠል ካልክ ቅንነትን፤ ንጽህና፤ ከራስ በላይ ማሰብን፤ ተተኪ ማብቀልን፤ የበለጠን ማሰቅደምን እንጂ መቀብርን ጀግንነትን አያስቀጥልም። ለዚህም ያየየኸው ነው መረሳት እንደሚኖር ... የትናንቱን ላስቀጠል ቅንነት ይጠይቃል ... ስደት ላይ ያለ እስረኛህን አቋጥረው መጀመሪያ ልክ እንደ ጀግናዬ ዶር ጠበቃ ሼክስፔር ፈይሳ።
እዚህ ያለነውን ምንዱባን የማያቋጥር፤ ያላቀፈ ሚደዲያ በላው የፖለቲካ ድርጅት ይሁን „የነፃነት ሃይል“ ሥሙን በፍሬም አድርጎ ግድግዳ ላይ ለመለጠፍ ካልሆነ ሰው የሚለውን ታላቅ ፍጡር ያቀፈ እንዳልነበር አለን መስካሪዎች። በተለመደው ሴራ እስክንሰናበት ድርስ።
እኔ ከንጽህና የሚነሳ እና የሚዘመር ለዛም የሚቀልጥ እንጂ ለሰው ሰራሽ ወረቀት እና ማንፌስቶ አምልኮ ሲያደገድግ ለኖረ ማናቸውም መንፈስ „ሰው“ ከሚለው ማዕቀፍ የወጣ ነው እና ሙላቴ አይደለም።
ይልቅ አዲስ አበባ ጎጃም ጎንደር ዳስ ጥሎ ላለቀስለት በርሃ ለበረሃ መከራውን ሁሉ ታግሶ ልጆቹን በትኖ ከአለ አንድ አይዞህ ባይ፤ ካለ እንድ ከለላ እንደባከነ ባክኖ ለቀረ ለዛ የመይሳው፤ የዘለቀ፤ የዘራይ ደረስ፤ የአብዲሳ አጋ ልጅ ለኢንጂንር ስመኛው በቀለ በጥቁር ልብስ ሰሞናቱን ባሳልፍ ምርጫዬ ነው።
ፍዳውን ችሎ ነፍሱን እረስቶ ሳይሰደድ፤ ለነፍሱ መጠለያ ዛኒጋባ ሳያበጅላት በበርሃ ለተቀቀለ፤ ግን በአገሩ ዜጋ ሳይሆን ነሽ የእኔ ብሎ እንደ ከፋው ሁሉን አምቆ ላለፈው ላዛ አልባሌ ሰው ግን ድርብ ንብርብር ጭንቅላት ለነበረው የቀራንዮ አባወራ ለእሱ ሰሞናቱን ልገበር።
ለማንፌስቶ ማህበርተኞች እና የአደባባይ ሰዎች ነጭ ለባሾች እጬጌው ሳይበር ያደግድግ …
ቅኖቹ ... የኔዎቹ ይህን ሥነ ግጥም ስለምን እንደጻፍኩት ገና እራሴን መመርመር
አለብኝ። ለእኔም እራሱ ስላልገባኝ። ያን ስሜቴን በምልሰት ልመልሰው ልል አልችልም ከ1000 በላይ ግጥሞችን በጸጋዬ ራዲዮ፤
በጸጋዬ ድህረ ገጽ፤ በተለያዩ ሚደያዎች ዛሬም ስለሚታታሙ … ለህትም የበቁት 613 ለአዋቂዎች ወደ ከ50 የሚሆኑ እጅግ አጭር
ቆራጣ የሚባሉ ዓይነቶች ከስድ ንባቦች ጋር ተዳብለው የታተሙ፤ ለልጆች ደግሞ „በፊደል“ በርካታ ግጥሞች ስለሆኑ ስጽፍ የነበረኝን ስሜት በፍጹም
በምልሰት ልቃኝህ ብል አልችልም …
ህመም
ህመምም
ህመምምም ሳ
ህመምምምም ላ
ህመምምምምም ገ
ህመምምምምምም ግ
ህመምምምምምምም ም
ህመምምምምምምም ልበል
ለዳግም። ዘ
ሳላገግምምምምምምምምምምም መ
ዘመም ም!
ምምምምምምምምምምምምምም!
ሳዘግም
በጅል ዘንጋም - እንዳልል ዕልም።
- · ተፃፈ ግንቦት 23 ቀን 2002 ዓ.ም ቪንተርቱር - ሲዊዘርላንድ። ቪንተርቱር ገዳም ናት።
- · ተስፋ መጸሐፌ ላይ ለህትምት የበቃ ገጽ 26 ላይ ጎጆውን የቀለሰ።
- · እርዕሱ ሳለገግም ዘመም።
· መስቀል አደበባይ? አብዮት አደባባይ? ሰኔ 16.2010? ሐምሌ 19 2010?
· ዕለተ ሐሙስ ለተፈጸመው የጠራራ ጸሐይ ሽፍትነት እና ሽብራዊ ርምጃ መጥኖልኛል።
- · ስጦታው መኖርን የገደለው ከንቱ ድካም … በከንቱ ድካምም ተባዝቶ ጠበቂ አልባ እንደ አልባሌ ወድቆ ለቀረው የግማድ ቤተሰብ ወገኔ ይሁንልኝ። በተጨማሪም ሲታገል ቆይቶም አሜሪካን አገርም አንድ ነፍስ ተሸኝቶ ህቅታው በስደት እንዲሆን ተወስኗል። ሁለቱም የአብርሃም በጎች ናቸው። ድርብ መከራን የጫነ የሰማይ ቁጣ ደም አዝሎ ይታዬኛል።
ከሞት የሚቀር የለም!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ