ከወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የአማራ ተጋድሎ ግብ አይጠብቅም!
የሴቶች የፖለቲካ ዕውቅና ማግኘትን አንገት ማስደፋት ትልቅ የታሪክ ፍቀት ነው።
„አቤቱ ምህረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ
እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።“
መዝሙር ፹፭ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
05.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
የሴቶች የፖለቲካ ዕውቅና ማግኘትን አንገት ማስደፋት ትልቅ የታሪክ ፍቀት ነው። የኢትዮጵያ ሴቶች በማንኛውም መስከ ለዘመናት የአገር አንድነት እና ሉዑላዊነትን ለማስከበር ጉልህ ተጋድሎ ያደረጉ ናቸው።
የኢትዮጵያ ሴቶች ያልተሳተፉበት፤ ያልተሰዉበት አንድም የትግል መስክ አልነበረም። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የአገር ግንባታም የኢትዮጵያ ሴቶች ሁለገብ ተሳትፏቸው ቢልቅ እንጂ የሚያንስ አይደለም። የኢትዮጵያ ሴቶች ብልህነታቸውን፤ መክሊታቸውን፤ ጸጋቸውን፤ ስጦታቸውን፤ ጥበባቸውን፤ ብልህነታቸውን፤ ሁለመናቸው ሳይቆጠቡ ሳይሳሱ የሰጡ ድንቅ ፍጥረቶች ናቸው።
የኢትዮጵያ ሴቶች በማናቸውም መሰክ የግንባር ቀደሙን ድርሻ በመውሰድ እኩልነታቸውን በዬዘመኑ በዬምዕራፉ አስመስከረዋል። ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን ለሴቶች የፖለቲካ ዕውቅና በመስጠት አጤዎች የአንስት እቴጌዎችን ምክራቸውን በማድመጥ፤ ብልህነታቸውን በመቀበል የብዙ ዕድል ባለቤት መሆን መቻላቸውን ታሪክ ያስረዳል።
በ60ዎቹ የማርክስስት ሌኒኒስት ፍልስፍና ተጋድሎ ሂደቶች ውስጥም ሴቶች እኩል ተሳትፎ ቢያደርጉም ከፖለቲካ የተገለሉበት፤ እንዳሉም ያማይቆጠሩበት ለመስዋዕትነት ብቻ የሚፈለጉ የበይ ተመልካቾች ነበሩ። ከዚህም ሌላ የሰው ልጅ አቅርቦት ላይ ብቻ አትኩሮት ከማድረግ ውጪ ሴቶች ዜግነታቸውን በስልት የተነፈጉበት ወቅት ነበር። „እንዳያማ ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ ዓይነት ነበር።
አሁን ባለው የአማራ እና የኦሮሞ ተጋድሎ በተገኘው የለወጥ ሂደት ሰፊ አትኩሮት ተሰጥቶት ለለውጡ ጥበባዊ አቅም በመስጠት እረገድ ድንቅ የሆነ እርምጃ እየተወሰደ ነው በዶር አብይ ሌጋሲ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለሴቶች አቅም ልዩ ፈላስፋም ናቸው። ይህን ዛሬ ዓመት በስፋት ጽፌዋለሁኝ።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_26.html
ለሴቶች በፖለቲካ ተሳትፎ የተሰጠው ዕውቅና እና አክብሮት የለውጡን ተስፋ መሰረት በማስያዝ እረገድ ያለው ሰፊ ድርሻ ረቂቅ ስለመሆኑ ጠቀሜታው ነገ የሚታይ ይሆናል።
በዚህ የሰፊ ዘመን የተጋድሎ ውጤት በሆነው ዕድል በአግባቡ መጠቀም የሴት የፖለቲካ ሊሂቃን ድርብ ድርሻ ሊሆን ይገባል። ለህዝብ አገልግሎት መስጠት ለሴቶች አዲስ ባይሆንም በመንፈስ ድንግል እና
በእናትንት መንፈስ መከውን ይገባቸዋል ባይም ነኝ።
በዚህ የሴቶች አቅም ዕውቅና ድል እና የብሥራት ዋዜማ ጥቁር የሆኑ ድርጊቶችን በመፈጸም የኢትዮጵያ ሴቶች አንገታቸውን የሚያስደፋ ተግባር ለመፈጸም መትጋት በውነቱ የሚሊዮን የኢትዮጵያ ሴቶች የከፈሉትን መስዋዕትነት ተስፋ የተቃጠለ ካርቦን ማድረግም ነው።
እኛን በቁም የመግደልም ነው። ወጣትነታችን የገበርንብት የነፃነት ተጋድሎ እንዲህ መና ለማስቀረት መታተር የዓለም ሴቶችን ቁጣም የሚያስቀሰቅስ ነው። ምክንያቱም የሴቶች ተጋድሎ ዓለም አቀፍ ነውና።
በዚህ ዘርፍ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብርሂም በዞጋቸው መንፈስ ተመርተው የሚፈጽሙት ከአድሎዊ - ከአፈኛዊ - ከአግላያዊ - ከወረራዊ ከሌባዊ - ከዘራፊያዊ - ኪሰራዊ ዕይታ ሊወጡ አለመቻላቸው በውነቱ የኢትዮጵያ ሴቶች ያገኙትን ድል ለመቀበር የተሰናዳ ልዩ ሴራም ነው።
ይህ በኢትዮጵያ የተጀመረው ሴቶችን ከፖለቲካ ታስትፎ የማቅረብ ታላቅ ብሄራዊ ዜማ አህጉራዊው አቅም አግኝቶ አፍሪካን የሚያበራ ሆኖ ሳለ በዚህ ላይ መርዝ መነስነስም በውነቱ አለተመታደልም ነው። ለውጡንም በስልት የመሞገትም ሸርም ነው።
በዬቦታው የአብይ ቅብሉነት ያስበረገጋቸው ግብረ አበረቾቻው የአብይ ሌጋሲ ቀልብ ለመሳብ ያደረገው ነው እያሉ መንፈስ የመተርትር ዘመቻንም አጋዢ ነው። የወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በወልቃይት፤ በጠገዴ፤ በጠለምት በራያ ላይ የሚሰሩት የሽንክነት እሾኽነት አካሄድ ሴቶች አቅም የላቸውም፤ መምራት አይችሉም ከሚሉት ጋር አብሮ ተደምሮ የተገኘውን የሴታዊት ዕድልን ለመጨፍለቅ ሆን ተብሎ ታቅዶ የተሰራ በሴታዊነት የአቅም ክህሎት ላይ የተሰነዘረ ደባም ነው።
አማራ አማራ እንጂ ትግሬ አይሆንም። ትግሬም ትግሬ እንጂ አማራ ሊሆን አይችልም። ማንት አይቀናም አይሸመትም። አይሸጥም አይለወጠም። ማንነት በገብያ ህግም አይተዳደረም። የ43 ኣመታት የገዳዮች ማህበር ለወልቃይት ለጠገዴ ለጠለምት ህዝብ ምንጠራ ካሳ ያስፈልገዋል። እስከ አሁን ለተዘረፈው አንጡራ ሃብትም ካሳ ያስፈልጋዋል።
ይህ ሁሉ ቀርቶ ፍትህ ይሰጥ ዘንድ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በሰላም ሌቦችን ዘራፊዎችን ወራሪዎችን የወሰዱትን አንጡራ የማንነት ጥሪት እና እርሰት በክብር ማስከበር ሲገባ፤ ተጋዳሊት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ማጣፊያው ሲያጥራቸው አዳዲስ ሸፍጦችን እዬፈጠሩ የህዝብን ፍላጎት ማፈን መጫን ወቅቱ ያለፈበት ሴራ መሆኑ አበክሬ ላስገነዝባቸው እሻለሁኝ።
ዋናው አብይ ጥያቄ ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የወገራ የስሜን አውራጃ የጎንደር ክ/አገር እንጂ የትግራይ አይደለም ነው ወሳኙ ጉዳይ። በብሄረሰብም ሲመጣ አማራ ነን ነው። አዎን እኔም እደግማዋለሁኝ እኔ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለሁኝም።
ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ፋሲልን ትተው የት ይሄዳሉ? እሰኪ ከውጭ አገር የሄዱ ዲያስፖራዎች ከጎንደር ውጪ ትግራይ ሄደው ያውቁ እንደሆን ይነገረን። በመንፈስም ትግራይን አናስታውሰውም። እትብት ጎማ አይደለም። እትብት ደም ነው። የወልቃይት የጠገዴ የጠለምት የደም ሥር ጎንደር እንጂ የወልቃይት የጠገዴ የራስ ገዝነት አይደለም ጥያቄው። ማንነታችን ከማንም በችሮታ የሚገኝ አይደለም። ይህን የሰጠን ፈጣሪ እንጂ ሰው ለዛውም የፋሽስት አስተዳር ወያኔ ሃርነት አይደለም። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዶክተሬኑ ለአማራ ህዝብ ፋሽስት ነው።
ይህን ሸፍጥ ይህን ማባጫል ያሰናዱት በአማራ የህልውና ተጋድሎ የ20ሺህ ወጣቶች የካቴና እራት የሆኑ 50 ባህርዳር ህዝብ ሰማእትነት የፈጸሙበት፤ የአንባ ጊዮወርጊስ 26/27 ህጻናት የተጨፈጨፉበት፤ እነ አርበኛ ጎቤ ራሳቸውን ኑራቸውን የገበሩበት፤ የጎንደር መሰረት ቅዳሜ ገብያ የተቃጠለበት ደብረታቦርም እንዲሁ፤ ተባዕት የነጻነት አረበኞቻችን የዘር ማፍሪያቸው እንደ በግ የተሸለተበት፤ የዋልድባ ቅዱሳን አባቶች ያን ሁሉ ፍዳ ያዩበት፤ ሴቶች የነጻነት አረበኞቸችን ጥፈራቸው የወለቀበት በፍጹም ሁኔታ ናዚያዊ ተግባር የተፈጸመበት ታገድሎ ነው ለሳቸው የፌድራል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቦታ ያበቃቸው። እነ ዶር አረጋይ በርሄ እና እነ አቶ ግደይ ዘራጽዮን ለ እትብታቸው ያበቃቸው።
ትናንትም ቢሆን የአማራ ልጆች የከፈሉት መስዋዕትነት ነው ትግራይን ህይወት ሰጥቶት ያኖረው። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ውድቀትም አብረውት የታገሉት አንበሳ የአማራ ልጆች እነ ኮነሬል ደመቀ ዘውዱ ያመጡት ለውጥ ነው የወያኔ ሃርነትን የ100 ዓመት ህልም የናደው።
አሁንም ቢሆን ጥያቄው በወጉ ካልተመለሰ ለለውጡ ለራሱ መልካምነት ቀጣይነት አደጋ አለበት። ስለምን? ቢባል መንፈስ ቅዱስ ስላለበት። ዕንባ ሁልጊዜ እዮርን ያንኳኳል። ሌላም ሰማያዊ ቁጣም ያመጣል። የመሬት መገመስ ይሁን ከሰማይ ተባይ የመዝነብ ነበልባልም ያመጣል። ቁጣ የፈጣሪ ከሆነ በአዬር መቃወሚያም አይቆም እና።
አብሶ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ያን የመሰለ ግርማ ሞገስ ያለው የቁራዕን ክብር ተላብሰው የቁራዕንን ህገ ደንብ በሚጥስ ሁኔታ የእስልምና ሴት ፖለቲካ ሊሂቃን ቅስም በሚሰብር ሁኔታ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ተስኗቸዋል። በሁለት በሦስት ዕጥፍ አንገት መድፋትን አውጀዋል።
ለዚህም ነው በቀድሞው ፕሬዚዳንት በዶር ሙላቱ ተሾመ አሸኛኘት ላይ ምርር ያለ መልእክት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያስተላለፉት። በሴቶች አቅም ላይ ያላቸውን የብልህነት ህሊና ስለተፈታታነው። ገና ፊርማው ሳይደረቅ ምስላቸው በአደባባይ የተወገዘ ዕለት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቅም ነበረባቸው። ሁላችንም ነው ያፈርነው። የሁላችንም ተስፋ ቅስም ነው እንኩትኩት ያለው።
ይህ ቪዲዮ ዓለም ዐቀፉ ማህበረስብም ሊያው ስለሚችል እጅግ አጥንትን ይሰነጥቃል። እኔ ሴቶች ጥበቦች ናቸው ብዬ ስለማምን እደነግጣለሁኝ በዚህ ጉዳይ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ታሪክን ጂኦግራፊን ፓኦቲካ ፍልስፋናዊ ጽንሰ ሃሳቡን ሳያውቁ ድብልቅልቅ ባለ መንፈስ የሚሰጡትን መግለጫ ሳዳመጠው አፍራለሁኝ። ሴት ነኛ እና። በሴትነት በነገረ ፆታዊ ጉዳይ እንገናኛለን እና።
ራያን በሚመለከት ወሳኞቹ እነሱ ናቸው። ወደ ቀደመው ግዛታችን ወደ ወሎ እንመለስ ሲሉ ነው ያዳመጥኳቸው። የቀድሞው ህይወታቸውን ነው የመረጡት ወደ ወሎ ነው ዝንባሌያቸው እንጂ ራስ ገዝነት ወይም ልዩ የዞን አሰተዳደርን አይደለም ፈቃዳቸው። መተከልም ጠዳፈነ ፈንጅ ያለበት ነው። ጎጃም አባይ እንጂ የክብር ሽራፊ አይደለም ርስቱ።
ይህን በመፈጸም እና በማስፈጸም እረገድ የወልቃይት የጠገዴ የራያ የጠለምት ጉዳይ ነፃነቱን ሌብነትን ዝርፊያን ወረራን ከሚያበረታቱት አንስት ሊሂቅ ፈጽሞ አይጠብቅም። እሳቸው እራሳቸው የሌብነት ፍልስፍና እስረኛ ናቸው። እሳቸው እራሳቸውን ገና ነጻ አላወጡም።
በተጨማሪም ይህን ጥያቄ መልሱን ለማስገኘት በጦርነት አይደለም። ምክንያቱም ሌብነት፤ ዘረፋ በጦርነት መፍትሄ አያገኝም። ሃቅ እና የታሪክ ማስረጃዎች ብቻ ይፈቱታል እና። ስለሆነም ትእግስት፤ ተደሞ፤ እዮባዊነት ሰንቆ አብሮ የኖረ ህዝብ ነገ አብሮነቱ ሊቀጥል በሚችል መልኩ መከወን አለበት።
አሁን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጦርነት ላንሳ ቢል ውደቀቱ የራሱ ነው የሚሆነው። ሽንፈቱም የታሪክ ይሆናል። ትውልዱን በአብሮነት በመቻቻል ለማስቀጠልም ከባድ ነው። በሌላ በኩል በሁሉም ክልል ቢዘጋ የትግራይ ህዝብ ጉሮሮው ይታነቃል። ትግራይ ከበለስ ሌላ ምን አለውና? ነፍሱን ቋጥሮ ያኖረው ትናንትም ዛሬም የአማራ መሬት ነው።
እዛውም አማራ ክልልም የሚኖሩ በሺህ የሚቆጠሩ ተጋሩም አሉ። በዚህ ውስጥ ህጻናት፤ አዛውንታት፤ ነፍሰጡር ታገሩ አሉ። የእነሱም ሰላም ሊጠበቅ የሚችለው ከዚህ የትግራይ ሊሂቃን መታባይ ሲቆም ብቻ ነው። መሸነፍን ፈቅዶ መቀበል። ስርቆትም፤ ዝርፊያም፤ ገዳይነትም ጀግንነት አይደለም። ይልቁንም ውርዴት እና ውርዴ ነው።
ወሎ የተጀመረው መንገድ መዝጋት ጎንደር ከቀጠለ፤ አፋርም ቋፍ ላይ ስለሆነ የትግራይ ህዝብ አብሶ ህጻናቱ ምን ይሆናሉ? አብሶ አልጋ ላይ ያሉ ድውያን ምን ይሆናሉ? አርቆ ማሰብ ይገባል። ነገስ ትውልዱ እንዴት ይቀጥላል? ሌላው ከጣና የታሰበው የኤሌክትሪክ መስመርም አለ። እሱ ቀጥ ቢል ጸጥ ትላለች ልዕለት መቀሌ እና የኢንደስትሪ ከተማይቱ ዘመን ፊቱን ያልነሳት ቀዳማይ ልዕልት ትግራይ።
ችግሩ በአግባቡ ካልተፈታ አደጋው ሰፊ ነው። ያ ሁሉ ህሊና የማይችለው በደል በአማራ ላይ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ተፈጽሞ ይቅርም ተብሎ አሁን ደግሞ እንቀጥላለን ከተባለ የትም ጣልቃ ገብቶ ተጋሩን ሊያድን ስለማይችል እጅግ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። አቅምን በውል ማወቅ። አብሶ ጎንደር ላይ የሚነሱ ማናቸውም የእንቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ችግሩን በቀላል መፍታት አይቻልም።
የጎንደር የአማራ የህልውና የማንነት ታገድሎ ሲነሳ የትም አይደረስም መታበይ ነው ከዚህ ደረጃ ያደረሰው። ሁሉንም ነጻ ያወጣው ያ ተጋድሎ ነው። የኦሮሞም የጋንቤላም ደም ደሜ ነው ብሎ ነበር የተነሳው ተጋድሎው። ድምጻችን ይሰማ ብሎ ነው ነበር የተነሳው። የተጋድሎው ግቡ ደግሞ በወራራ የተያዙ መሬቶችን እርስቶችም ማስመለስ ነው። የአማራ የህልውና ተጋድሎ አይቆምም። የአማራ ፖለቲካ ውክልና ጥያቄም ቀጣዩ የተጋድሎ ምዕራፍ ነው። አንገት ደፍቶ ተዘቅዝቆ መኖር ከእንግዲህ ተቀብሯል።
ውሸት አያሳድርም። ውሸት አያነጋም። ውሸት አያስቀጥልም። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እንዲያውም ይህ የለበሱት የቁራዕን ክብር እዬተዳፈሩት ስለሆነ ለእስልምና እምነት ታማኝነትም ቀይ መስመር ነው። በስንት ዘመን የተገኘውን የእስልና የሊሂቃን የአንስት የፖለቲካ ተሳትፎ አረም እያበቀሉበት ነው። አልባሳቱ እራሱ ሃይማኖት ነው።
ለዚህ የእስልምና ዕምነት የክብር አልባሳት ከመወሰን በፊት ራስን ለቁራዕን ዶግማ እና ቀኖና ለማስገዛትን መፍቀድ ያስፈልጋል። ከውሳኔ በኋላ ደግሞ ሆኖ መገኘት ይጠይቃል። ሃይማኖት ሲሞቅና ሲቀዘቅዝ በቁጭ ብለህ ቆዬኝ የሚከላ አይደለም እና።፡ ይህን እያዬን አይደለም በወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በኩል። … ሸፍጥ ለእስልምና ዕምነት ባዕድ ነው። ሌብነትም ሃራም ነው።
ጥያቄው ወልቃይት ጠገዴ ራያ ጠለምት የአማራ ክልል ናቸው ነው። ራስ ገዝ ልዩ አስተዳደር ከባርነት ወደ ባርነት ነው። ከታሪካዊ ማዕቀፋቸውም መውጣት ነው። በምንም ሂሳብ በምንም ቀመር ይህን ተጋድሎ ከግብ ሳያደርስ የሚተኛ የነፃነት አርበኛ አይኖርም። ተጋድሏችን ተጠናክሮ ይቀጥላል። መተከልም ቀደ ቀደመው እርስቱ ይመለሳል፤ የታዳጊ ወጣት አበጠር ዕንባ የአቤል ነውና።
ዝማታችን የአብይ ካቢኔ ችግር ውስጥ እንዳይገባ በማሰብ እንጂ እንደለመደብን የማይደፈረውን ጉልበታም አቅም ያለውን የተጋድሎ ሉላዊ ድርሻችን ለመወጣት አቅም ጠፍቶ አይደለም።
በዚህ ውጣ ውረድ ግን በአማራ ክልል የሚኖሩ ተጋሩ ከለመዱበት የስለላ ተግባር መቆጠብ አለባቸው። ለሃቅ ለዕውነት መታመን ያስፈልጋል። የአማራ ክልል ነዋሪዎችም ከሁሉም ጊዜ በላይ ወገኖቻቸውን፤ ቤተሰቦቻችን የተጋሩ አባላትን ሰላም መጠበቅ አለባቸው። የመኖር ዋስተናቸው ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው ሊከበርላቸው ይገባል። ይህ ደግሞ በችሮታ ሳይሆን መሆን ያለበት የተገባም ነውና።
ከጦርነት ከግጭት ከቋሳ የጸዳ ቤተሰባዊ ግንኙነት ቀጣይነት ዋነኛው የአማራ የማንነት የህልውና የተጋድሎ ግብም ሊሆን ይገባል። ሰላም ለሁሉም ነው መሆን ያለበት። ሰላም ነው የጥያቄ መፍትሄ አስገኝ ሃይል። ይህን ለውጥ ያስገኘው ምክንያታዊ አመክንዮ የአማራ ሰላማዊ ታገድሎ ስለሆነ ለውጡን የመጠበቅ፤ የማስቀጠል፤ የመንከባከብ ግዴታ አለበት ተጋድሎው። ወጀቦችን አብዝቶ መታገስ! ስንጥቆችን መድፈን።
ቁጣዎችን ማብረድ። ጥድፊያዎችን ማስከን በ እጅጉ ያስፈልጋል።
ከዘመናት ጦርነት ምን አተረፍን? ትውልድ ባከነ፤ ትውልድ መቅኖ አጣ አንጡራ ሃብታት ተቃጠሉ ወደሙ። ቢያንስ አሁን አቧራ የለበሱ ከተሞች፤ መንገድ ያላገኙ ቦታዎች ተዛማው ኤሉሄ ኤሉሄ የሚሉ የስልክ እና የመብራት እንጨቶች ሁሉ ቅርስ ናቸው እና ሰላማቸው ሊታወክ አያስፈልግም። ቢያንስ ዘመው ታመው እንኳን መቀጠል ይኖርባቸዋል።
በምንም መስፈረት ሁለቱ ህዝቦች ለውጊያ፤ ለጦርነት ነጋሪት መንፈሳቸውን ማሰናዳት አይገባቸውም። ማን ማንን ሊወጋ? ማን ማንን ሊያሸንፍ? ማን በማን ደም ላይ ድል ሊያደርግ? ወንድም እህት ተገድሎ ጉሮ ወሸባዬ? ወገን ተገድሎ ጉሮ ወሸባዬ ሰውነት አይደለም በፍጹም። አይበቃም ወይ የ50 ዓመቱ ማገዶነት? ሰው መሆን መቻል ማለት ዝርፊያን ወረራን ተጸይፎ ከእውነት ጎን መቆም ነው።
ሰላም ነው የህዝብ ዋስትና አስገኝ እንጂ ጦርነት አይደለም።
ሰላም ሊናፍቀን ይገባል!
ሰላምን አክብሮ የተነሳ ታገድሎ ለትውልድ በረከት ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ