ዋ! #መራዊ ስለአንቺስ?

 ዋ! #መራዊ ስለአንቺስ?

 


ስንት ሰው ነው #የተጎሳቆለው? ስንቶችንስ #አጣን? ስንቶቹ #ለካቴና ተሰጡ? ስንቶች #ተሰደዱ? ስንት የመኖር ዓይነት #ተስተጓጎለ? ስንቶች ከባዕታቸው #ተነቀሉ? አሁን ለዓመት የተለያዬ በናፍቆት የሚገናኝበት ጊዜ በሆነ ነበር። ስለአጣናቸውም ዝክረ -መስዋዕትነት ልናደርግ ይገባ ነበር። የሃዘን ቀን ሊኖረን በተገባ።

 አቅም ያለውም የተጎዱትን በጎጥ፤ በመንደር ሳይሸነሸን ተጠንቶ የሚችሉ እንዲረዷቸው ዳታ ማጠናቀር ይገባ ነበር። ያ ግራጫማ ወቅት፤ ያ #ደመመን የተጫነው #ጨጎጎት ወቅትን ለተቋቋመው ህዝባችን ብሩህ ተስፋ እንዲሰንቅ ማድረግ በተገባ ነበር።

 በድንጋጤ አደጋ ላይ የባጁ ወገኖችም አሉን። የአባቶቻችን ዊዝደም የተሰጠው ባለ ቅባዕ ቢገኝ ዛሬ የሲቃ ቀን ነበር። 

በመገናኘታችን ትንሽ እፎይ፤ ስለተለዩን ሃዘን፦ እንዲህ ከአንድ ፍጥጫ ወደ ሌላ ፍጥጫ ሽግግር የሚደረግበት ባልሆነ ነበር። የደብረ ኤልያስ ቅዱሳን ሰማዕትነትንስ፤ የመራዊን ሰቆቃ ዋይታስ በምን 

ይካስ?????

 ሥርጉትሻ2024/07/17

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።