ምራቅን መዋጥን ....

 ከተንከለከለ ፖለቲካ ጋር መንከልከል አይገባም። #ከሚንቦጀቦጅ ፖለቲካ ጋርም አብሮ #ማረግረግ ተገቢ አይመስለኝም።

 ፖለቲካ ለሰው ነው። ለሰው የሆኑ አመክንዮወች ደግሞ ርጋታን ይጠይቃሉ። አመክንዮ በራሱ #ስኩን ነው። 

የአመክንዮ ርጋታ ቢስ የለም። ለረጋ አምክንዮዊ ጉዞ የሰከነ፤ የረጋ፤ ለህግ የሚገዛ፤ አንደበቱ የታረመ ሰብዕና ይሻል። #አቅልየለሽ#አደብዬለሽ ሰብዕና ፖለቲካ ልኩ አይደለም። በፍፁም። 

ፖለቲካ ሳይንስም ፍልስፍና ነው። ያ ደግሞ ምራቅን መዋጥን፦ መጨመትን፦ ከሌላው የተለዬ የማስተዋል ልኬታን ይጠይቃል።

ፖለቲካ ከቅጽበታዊ ሰብዕና መዳፍ ከገባ ሲሰራ እና ሲፈርስ ውሎ ከማደር ሌላ ዕጣ ፈንታ የላውም። ችግሩ የመስዋዕትነቱ መግዘፍ እና እና #ኩርምትምት የሚለው የተስፋ ጉዞ አብሮ መታወኩ ነው። አይጣል ነው።


ሥርጉ2024/07/17

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።