ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም። 25.11.2020 የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት?

የበህግ አምላክነትን ጥሳ እናት ወደ ዬት? 
 


ኢትዮጵያዊነት በጉልት አውጫጭኝ አልተፈጠረም።
ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተው የሚማሩት ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያዊነት የዓለም መድህን የሆነ የምርምር ማዕከል ነው።
ኢትዮጵያዊነት አናባቢም ተነባቢም ቅዱስ በረከት ነው። ኢትዮጵያዊነት ተዘርዝረው በማይዘለቁ ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ምጥን ማንነት ነው።
ኢትዮጵያዊነት በጉልት ገብያ አውጫጭኝ አልተመሰረተም።
ኢትዮጵያዊነት በውስጥህ ከኖረ ክህደት፣ ዝቅጠት፣ ስላቅ፣ ዝንፈት፣ መስቃ፣ ትዕቢት፣ ፀረ ሰውነት አያሸንፋህም። ኢትዮጵያዊነት ተፈጥሯዊነትም፤ ሰዋዊነትም ነው።
ኢትዮጵያዊው ሰው ፀጋው ዝልቅ ነው። ተማረ አልተማረ። ሰማዩን አይቶ የአዬሩን ባህሬ ይነግርኃል። ዛፍ ቆርጦ ዕድሜውን ይነግርኃል፣ የሰውነት ዛላህን አይቶ ውስጥህን ያነበዋል። ያብራራዋል እንደ ዘመንኛው ራዲወሎጂ በለው።
ኢትዮጵያዊነት መርኽም ነው። ኢትዮጵያዊነት መንገድም ነው። ኢትዮጵያዊነት በህግ አምላክነትም ነው። ህግ ነው።
ኢትዮጵያዊነትን በውስጡ ለፈቀደ ብርኃን ነው። ከፍ ቢል ዝቅ ቢል መጥኖ በቁጥብነት መኖርን ያኗኑራል። ሊቀ ሊቃውንቱ ፕ/ ኃይሌ ላሪቦ ኢትዮጵያዊነትን "ረቂቅ ሚስጢር" ይሉታል።
አባ ትሩጉም አቶ እስክንድር ነጋ ደግሞ "የኢትዮጵያዊነት አፈጣጠር ኦርጋኒክ" ነው ዬሚል ጥልቅ ፍልስፍና አለው። ውስጡን ላጠናው ዕውነት ነው።
ይህን የሚሸከም መሪ ማግኜት ግን አልተቻለም። ለዚህ ነው የአፍሪካ አገር መሪዎች እዬተሸማቀቁ ያሉት። አፍረውብናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ኢትዮጵያዊነት ቅኔ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።