የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት።

 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት። ግልፍተኝነቱ ደግሞ ሥልጣን ላይ ሆኖ የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡን እንደምን መያዝ እንደሚገባው እንኳን አያውቅም። ለዘርፋ ደም የሚያፈላ እርምጃ፤ ደም የሚያፈላ ንግግር ይደረጋል። ከዛ ፀጋ ይደፋል። ፀጋ ከተደፋ በኋላ ደግሞ ልምምጥ ይመጣል። አብሶ #ካድሬወቹ #በዲፕሎማሲ #ጉዳይ ላይ #እንዳይዘነቁሉ #በህግ #ሊታገዱ #ይገባል። ፓን አፍሪካኒስት ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ደረጃ የማይመጥናት ላይ ናት። በሌላ በኩል #በዘርፋ #ሙያ #ጠገብ #ኢትዮጵያውያን #በነፃነት #እንዲሠሩ #ሊፈቀድ #ይገባል። ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ። በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ አመጣሽ ሰብዕና ረቂቁን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንዲታቀቡ ሊደረግ ይገባል። ኢብን ሙሁራን ቢሆኑም። ኢትዮጵያ በትርፍ ተናጋሪወች ልትለካም አይገባም። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ ለሁላችን ከብዳናለች የምለው። ለአገር ክብር ብርቱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ተቋም አለ። ውጭ ጉዳይ ሚር። የዳበረ ልምድ ያለው። በነፃነት ይሠራ ዘንድ ይፈቀድለት። ከዞግ እሳቤ ተወጥቶ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/2

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።