#ህም። #እምም። #የፈንጅ እና #የቦንብ አደጋ የሙዚቃ ኮንሰርት አይደለም። #ማን #ይፈጽመው ማን??


ማህበረ ቅንነት እንዴት አድራችሁ፦ አርፍዳችሁ ዋላችሁ።
ትንሽ ቆራጣ ነገር ልል ወደድኩኝ። #የፈንጂ፤ #የቦንብ #ፍንዳታ ምኑ ያስፈነድቃል። ይህ ካስፈነደቀ የትኛውም ዓይነት የሰማይ በረራ፤ የምድር ጉዞ በሚደርስ ድንገተኛ አደጋ የፌስታ ኢቬንት ቤተኛ መሆን ማለት ነው። እንዴት ብሎ ነው በጦርነት ማህል፤ በግጭት መሃል፤ የእሳት አደጋ፤ የፈንጅ አደጋ ድንገተኛ አስደንጋጭ ክስተቶች የሰውን ልጅ #ሲቀጥፍ፤ የነዋሪውንም የአለምንም መኖር ሲያውክ፤ መኖር ሲስተጓጎል የህዝብ የኗሪው #የተረጋጋ መንፈሳቸውን ሲዘርፍ "ወሸኔ፤ ማለፊያ" ዜና የሚሆነው።
ምነው ሰውነታችን ከላያችን ላይ እንዲህ #እንዲፋቅ ፈቀድን? ማን ይሁን ማን ይፈጽመው// በዬትኛውም አግባብ ይፈጸም፦ ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ ንጹሃን መንገድ ላይ መቅረትን የሚነግር መርዶ #ፖለቲካ ተብሎ ሊቀርብ ፈጽሞ አይገባም። እራሱ የፈንጂ የቦንብ አደጋ ሞት ብቻ አይደለም። ዘመቻው #አካል #ይጎድላል፤ ጦሪ የነበረው ተጧሪ ይሆናል። ስቃዩ፤ የሞራል ድቀቱ፤ የተስፋ ማጣት ስቃዩ #ተመን ይወጣለታልን????
ልጆችስ ተብትነው ሲቀሩ፤ ሰርክ #በስጋት ሲናጡ ይህ እንደ ሸበላ ገጠመኝ ሊታይ ይሆን? አዝናለሁኝ። በየትኛውም ሁኔታ የምናጣቸው ወገኖች ሃዘን አይበቃንም? ከእስር ቤት በድብደባ፤ ከሥራ መልስ በባሩድ፤ ያልተነገረው በስውር #በምግብ #ብክለት፤ ስንት ወገን አጣን? ባልተገባ የመረጃ ፍሰት፤ ባልተጠና እና አቅምን ባልመጠነ #ኦፕሬሽን ቀንበጦቻችን አላጣነም።
እነኝህ ሁሉ እናት የላቸውንም???? እስር ላይ ያሉት ከእነ ደማቸው ከኦፕራሲዮን መልስ ወደ እስር ቤት መመለስን እንደምን ይታይ ይሆን? ቀጣይ ህይወታቸውስ? በአገር አንድ ነገር ቢፈጠር በሰው እጅ ያሉ ወገኖቻችን ምን ሊደርስባቸው ይችላል ብሎ ማሰብ ተስኖ የደራሽ ፈንጅ እና ቦንብን ፍንዳታ ላይ ጉጉት ማሳዬት ምን ይባል???? ሰባዕዊነትም፤ ተፈጥሯዊነትም ባለቤት አጣ። የጭካኔ ሃሳብን የሚያወግዝ ሰብ የፈንጅ ፦ የቃጠሎ እና የቦንብ ፍንዳታ ክፋ ሃሳብን ማውገዝ፤ ሃራም ማለት ይገባል። ስቃዩ አሰቃቂነቱ ሚዛን ሊወጣለት አይችልምና።
ሁሉም በተደላደለ ኑሮ ተቀምጦ፤ አገር የቀሩ ቤተሰቦቹን ልቅምቅም አድርጎ #ቤተሰቦቹን እያሸሸ "በሞኝ ክንድ ዘንዶ ይለካበታል" እንዲሉ ለአማራ እናት ግን #አንድስም እንኳን ተቆርቋሪ ማግኜት አልተቻለም። እያዳመጥኩ እኮ ነው እናት የትም ቦታ፤ በምንም ሁኔታ እናት ናት። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን የአማራ እና ቋያ ተሸካሚነት፤ የማህፀኗ ቄራነት ባለቤት የለውም። ሁልጊዜ በግራ ቀኙ #አንጋች አቅርቢ ነው።
እናት አንድ ሆና፤ አምሳያ የለሽም ሆና ማገዶ አሰናጂ የምትባለው የአማራ እናት ናት። አንዲት #እስክርቢቶ ያልገዛ፤ አምጦ ያልወለደ ሁሉ "የአማራ #ወጣቶች ምን ይሰራሉ ከተማ?" ሲል ይደመጣል። ለሌሎች እናቶች ከሚታዘነው 1% ለአማራ እናት አይታዘንም። ለሁሎችም አጀንዳ ፈጽሞ አይደለችም። ስለ እናት የሚታዘነው #ተባደግ ነው። ከእናትም #የክት እና #የዘወትር፤ የሚታዘንለት እና የማይታዘንለት አለ።
ማስተዋል ተሰደደ። አርቆ ማሰብ ዘበጠ። እኛነት ርቃኑን ሆነ። እናም ልብ ለልብ ተራራቅን። አዬሩ፤ ባዕቱስ ምን አለ ቢታዘንለት። እንዲህ የፈንጅ እና የቦንብ ጥቃት እንደ መልካም ነገር የሚታዬው። ይገርመኛል ዜናወቹ - እራሳቸው። የሰብአዊ መብት ታጋይ፤ ጋዜጠኛ የሚል የገዘፈ ሥያሜ ይዞ በፍጁት፦ በእልቂት በሰኔል እና ቹቻ ጉዳይ የክት እና የዘወትር ሲበጅለት። ሰውነት ደንበር አልባ ነው። ተፈጥሯዊነት ደንበር አልባ ነው። እንኳንስ የአንድ አገር ልጅነት። አምላካችን፤ አላኃችን ልብ ይስጠን አሜን። የጭካኔ ሃሳብ ማራመድ፤ መከብከብ ለጋዜጠኝነት ሆነ፤ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋችነት ምቾት ሊሰጥ አይገባም። #እርዕሶቹ እራሳቸው #ያስደነግጣሉ፤ ያንዘፈዝፋሉ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/02/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ