የነገው አስኳባ የከንቱ ውዳሴ ካባ።

እንኳን ደህና መጡልኝ
የነገው 
ብሄራዊ 
አስኳባ
ሠርግ የከንቱ ውዳሴ  ካባ።

„አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
 አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን።“
መዝሙር ፴፱ ቁጥር ፲፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


ነገ የአስኮባ ብሄራዊ የሠርግ ቀን ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ አስኮባቸውን ይዘው መንገድ ሲያጸዱ እናያለን። የነቀምቱ እግር ኳስ ቲምም እንዲሁ በተመደበለት ቦታ ሆኖ የአስኮባ ቀነኑን የፊሽካ ድምጹን ይጠብቃል - ለዛውም በጉጉት። ወይንም በታምራነት ትዕይነቱ ይከናዳል።

የካሜራ ርችት ይተኮሳል፤ እልልታ በስላቅ ትንግሩትን ይዘጋግባል፤ የመዲናዋ ንጉሰ ነገሥታት አብረው ይታደማሉ  … ሚዲያው ሁሉ ፎቶ ቀጭ ለማድረግ ይሰለፋል። ለዛውም በሽሚያ ...

እሁድ በሚካሄደው የጽዳት ዘመቻ ዙሪያ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር መግለጫ

Published on Apr 11, 2019

ካቢኔውም እንዲሁ። ከኪጋሌ መልስ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላማዊ የተረጋጋች፤ የህግ የበላይነት የሚከበርባት፤ የመኖር ዋስትና ያለባት፤ መኖር ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የተፈቀደበት፤ ተስፋ ያበባት ሚሊዮን ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉበት፤ ሚሊዮኖች ሜዳ ላይ የወደቁበት፤ ነፍስ የትም ቦታ እንደተርታ ጉዳይ የታዬበት፤ ርዕሰ መዲናዋን ልታጣ ሞት አፋፋ ላይ ያለች የመከራው ሲሳይ ከአፍ እስከገደፉ ስለሞላ ነገ አስኮባ ዲል ባለ ሠርግ ይዳራል፤ ይኳላል በመላ ኢትዮጵያ። ቅልቅሉ፤ ግጥግጡ ደግሞ መቼ ስለመሆኑ ቀን ተቆጥሮ ቢነገረን መልካም ነው። 
 
በዚህ ውስጥ እኔ እማስበው የተረጋጋ የሰከነ የመንፈስ ፍሬ ነገር እንደሌለ ነው። አንድ ቦታ ትሄዳለህ የሆነ ነገር ታያለህ በቅጽበት ትመጣለህ ያን እተገብራለሁ ትላለህ፤ ቀደም ባለው ጊዜ ተስፋ አድርግበት ነበር በጠ/ሚር አብይ ሁለገብ አቅም።

አሁን ግን እንደ እጸ በለስ ነው። እኔ እንዲያውም ዶር አብይ አህመድ ጠ/ሚር በሆኑበት ማግስት በወር አንድ ቀን የጽዳት ዘመቻ ይኖራል ብዬ አስብ ነበር። የከተሞች ባዕል በጎንደር ያደረጉትን ንግግር መሰረት አድርጌ ማለት ነው። ለዛም ነበር አብይ የጎንደር ጌጥ ብዬ የጻፍኩት። 

ያንጊዜ የነበራቸው ተነሳሽነትን ወደ ተግባር ለመለወጥ ሰከን ያለ የነፃ አግልግሎት ፖሊሲ እና ትግበራም ጠብቄ ነበር ግን በመና ተወራረደ። አሁን ኪጋሊ ባይሄዱ ኖሮ ይህን አያቅዱትም ነበር ማለት ነው?

የመጀመሪያ አረብ አገራትን የጎበኙ ጊዜም እዛው ወዛቸውን ሳያሰርፉ ፈላስማው ዶር ምህረት ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ለዚህ ዓመት ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ የምሥራች አብስረው ነበር አሁን ያ ቃል ምን ላይ እንዳለ አላውቅም።

 ጅማ ዩንቨርስቲ የሥራ ማቆም አድማ ላይ እንዳለም አዳምጫለሁኝ ሽልማቱ ቀርቶ የመኖር ዋስትናችን ይረጋገጥ በሚል ማለት ነው …  

እኔ ውስጣቸውን ቀደም ብዬ በመረመርኩበት ልክ ሊሆኑ አልቻሉም ዶር አብይ አህመድ። ሳይንስና ቴክኖሎጂ በነበሩበት ጊዜ የኦነጋውያኑ እገታ ውስጥ አልነበሩም ነበር። አሁን በማዬው ሁኔታ ግን ልባቸው ሩቅ ያልማል ያን ያልሙትን ለማሳካት በመዳፋቸው ያለው ነገር ደግሞ ምንም ነው። 
ራሱ ሥልጣኑ ምስል በፍሬም ያለ ክቡር እቃ ሆኖ ነው የማዬው። 

ህልመኝነታቸውና ሁኔታው ሊመጣጠን አልቻለም። አንድ ቦታ ሂደህ አንድነገር ስላዬህ ሳይሆን በአገረህ በባዕትህ ያለውን ችግር አጥንቶ ጊዜያዊና ዘላቂ ትልም ነድፎ አቅም የመጠነ ተግባር መከወን ነበር የሚበጀው።

ለመሆኑ የመደመር ፖለቲካ መርሃ ግብር አለውን? የአጭር የረጅም ጊዜ። የረጅም እና የአጭር ጊዜውን የሚያያዝስ የመካለከኛ ጊዜ አለውን? 
ሊኖረው ይችላል ብዬ አላስብም። ምክንያቱም አንድ ነፍስ ስብሰባ ሲያዘጋጅ የጠ/ሚር ቢሮ ሌላ ስብሰባ ያዘጋጃል፤ አንድ ነፍስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲያዘጋጅ ያን አሳግዶ የራስን ጋዜጣዊ ለመስጠት የጠ/ሚር አብይ መንፈስ ይጣደፋል።

ስለዚህ አዬር እዬተከተሉ መንጎድ የአኒሞ ሜትር ያለህ እንደማለት ነው እኔ እማስበው። ራሱ ወንበሩ ተቀምጦ የሚሠራበት ጠ/ሚር አላገኝም። ስለዚህም እያለቀሰ ነው ያለው ... ወንበሩ እራሱ፤ መርፌ የተሰካካበት ነው የሚመስለው።  ለነገሩ በህልሜ መሰረት ባዶ ነው ... 

የሰከነ ትልም መከራ።

ህወሃት ከቤተ መንግሥት ከተሰደደ ወዲህ አማራ ክልል የራሱ ፕሮግራም ነው አለኝ ያለን፤ ኦሮሞ ክልል የራሱ ፕሮግራም ነው ያለው ያው ፌድራሉን ጨምሮ እሱ አውራ ስለሆነ ኦሮማማን አፍሪካዊ የማድረግ ባለትልም ነው፤ ትግራይ ክልል የራሱ ፕሮግራም ነው በቀደመው ፍልስፍና እና ባህል ጸንቶ። ደቡብ አይታወቅም። ያው ቀዝቃዛ ነው።

ሌሎቹ ግዞተኛ ናቸው በባርነት የተከነዱ 27 ዓመት ሙሉ። አፍ እያላቸው የማይናገሩ፤ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ፤ ህሊና እያላቸው ልብ የተገጠመላቸው ልጉምት የሰፈነባቸው። 

ግን በዓመት አንድቀን ለጭፈራ ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን ይታደማሉ … ለዛ መፈቀዱም ዕድለኞች ናቸው ይህንስ ማን ክፉ ብሎት፤ በሁለተኛ ዜግነት መመዝገቡን ... አሁን ደግሞ ኦዴፓ ሻታ እዬዞራቸው ነው። 

ጠንከር ያለውን ደቡብን በፌድራል ምክር ቤቱ የነበረውን ልዕልና ተርትር አድርጎ እሱ ገኖ ለመውጣት ልዩ ስልት ቀይሶ እዬተንቀሳቀሰ ነው። የዋዛ ... 
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በደቡብ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ማቋቋሚያ የሚውል የዐሥራ ስምንት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
April 13, 2019

የኦዴፓ ንጉሥነት የተረጋጋጠበት የዘንድሮ የባዕል አከባባር ላይ ከጎን ሻጥ የተደረገው ደቡብ ነበር። የጠ/ሚሩ ስኬት ላይም ልዩ ትንተና ሰጩ ደቡብ ነበር፤ የኦሮቤኒ የልቤ የተባለውም ደቡቡብ ነው። በሌላ በኩል ልዕል አቅሙን የሚፈትኑ እጮኛማ ድርጊቶች ደግሞ መሳ ለመሳ ይከወናሉ ክልል ዞን ምንትሶ ቅብጥርሶ... የዋዛ ... ምህንድስና እንዲህ ነው በአንድ በኩል ራቁት በሌላ በኩል ደግሞ ተክሊል ....

የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነው

Published on Apr 9, 2019 


ስለዚህ ወጥ ፕሮግራም ከሌለ ፖሊሲ ለማውጣትም፤ መርሃ ግብርም ለማውጣት ይችግራል። ከግንባሩ መሰረታዊ ሰነዶች ነው መርሃ ግብርም ፖሊሲም ሊወጣ የሚችለው። 

ተዚህ ላይ አንድ ነገር ለመሆኑ ግንባሩ እንደ ግንባር መተዳደሪያ ደንብ አለውን ነበረውን? ወይንስ ዝም ብሎ በቡና ፖለቲካ ጣሊያን ላይ በገጠመው የአደራዳሪ ሃይለ ቃል በግጥምጥሞሽ በሄሮድስ መለስ ዜናዊ ዳንቴል የተሠራ?

ግን ራሱ ግንባሩ በመንፈስ ደረጃ አለ ወይ - ተዛሬ ላይ? ነው ደንቡም፤ ፕሮግራሙም በአንድ ሰው ልዩ ፈቃድ ነው አሁን ተሆነ የሚንቀሳቀስው?

የግንባሩን የቀደመ መርህ በኦሮማማ ኦፌሻሊ መተካቱተስ ታውጇልን? ዝብርቅርቅ -- ድብልቅልቅ --- ቅይጥይጥ ...  ዝብጥጥብ ያለ ነገር ነው ያለው። ሰርቴቴ ይሁን ጠፍጣፋ፤ ጠፍጣፋ ይሁን ሞላላ፤ ሰተቴ ይሁን ምንምኔ ሁለመናው ውሎጉዞ የሌለው ነገር … ይህ የማነሳው ስለ ኢህአዴግ ግንባርነት ተጨንቄ አይደለም የኢትዮጵያ ጉዳይ መንፈስ የሚያርፈበት ዕውነት ፍለጋ እንጂ

ከራውንዳ ለመማር ዘፍጥረትን የጣሱትን፤ የተመድን ምሥረታ የተፃረረውን ኢ-ሰብዕዊ - ኢተፈጥሯዊ የበቀለ ትዕዛዛትን በህግ አቅርቦ በመጠዬቅ፤ ከማንኛውም ይህን መርዝ እሳቤ እንቅስቃሴውን በማገድ፤ ጸረ ሰው የሆነውን ማን እንደሚረዳው የማይታወቀውን ሚዲያ በህግ በመከርቸም፤
የችግሮች ምንጭ የሆነውን ህግ መንግሥት ላይ ሰፊ ተግባር ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መወሰድ እንጂ በነጋ በጠባ ንፋስ ላይ እዬተንጠለጠሉ በኮቢ እና በቀሰማ ኢትዮጵያን ያህል አገር እመራለሁ ብሎ ማሰብ ረግረግ ነው … 

እያለቀ ያለ ቀን ነው እኔ የሚታዬኝ … እያለቀሰ ያለ ማዕልት ነው እኔ እሚታዬኝ ... ድለላ ስለላ ንሁላላ ለተወሰነ ጊዜ ሊያስኬድ ይችላል ግን አቅም የለውም ዕውነትን ሞግቶ ቀጣይ ለመሆን።

የበደሉ አፍ እላፊ የሄዱ የሚዝቱ በተንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ፤ ወይንም ቃለ ምልልስ በሰሩበት ማግስት እንዲህ ህዝብ ከቀዩ እዬተነቀለ አገር እዬፈረሰች ኬክ፤ የፈረስ ጉጉግስ፤ ጭፈራ እና አጥቂና ጎል አግቢነት ጎንድ ያሰኛል … …
ዘመነ ተረትተረት።

ዝም ብሎ ህዝብን የእርጎ ባህር እያሳዩ አብሮ ለመስመጥ እና ለማስመጥ መሰናዳትም እንደ አገር መሪ ሲታስብ ያቅራል። አሁን የዛሬ ወር ያን ያህል ሉላዊ ነፍስ በምድርህ ያለቀ፤ በዬአካባቢው በዬዕለቱ ነፍስ ከዶሮ ባነሰ ሁኔታ እያለፈ ስለነገ ማሰብ ቀርቶ እያንዳንዱ ደቂቃ የስጋት ቀጠና በሆነበት ባዕት ላይ ተቀመጠህ ኳስ ሜዳ ገብቶ መዳነስ በውነቱ የቆሙበትን መሬት አለማወቅ ነው።

ለነገሩ እነ ቦኮሃራም በፈለጉት አቅጣጫ ሁለመናውን እዬመሩ የአብይን ሌጋሲ ዘነዛና የማስቀረቱ ተልክዕ ከ100% በላይ ተሳክቶላቸዋል።

"አምነዋለሁኝ ያሻግሩኛል ሦስቱ የሲኦል መንገዶችን" በድፈረት እና በኩራት ያሉት የፕ/ብርሃኑ ነጋ የፖለቲካ ፍልስፍና እንግዲህ መናነቱ በዚህ ይለካል። እኔ ይልቅ የናፈቀኝ ነገር አለ። ግንቦት 7 ውጭ አገር ተመልሶ መቼ ነው ደግሞ ዴያስፖራውን በአዲስ ስልት እና ቅዬሳ ለመማጸን የተለመው?ያው እንደ አልያነሱ ነገር ማለት ነው ...  

እኔ በግሌ የአብይወለማ መልካም ትትርና የነበረው ከመጋቢት እስከ ሰኔ መጨረሻ ብቻ ነበር። ከዛ በኋዋላ ወንበሩም ባዶ ነው፤ መንፈሱም ባዶ ነው ተስፋውም ባዶ ነው ሁሉመናውም ወና ነው። ቅጥፍጣፊ ቅርንጭፍጫፊ ነገሮች ናቸው ልክ እንደ ውሃ ላይ ኩበት ተንሳፈው እያንሳፈፉን ያሉት ... 

አሁን እኮ ቁልቁል ያልወረደ ነገረ ለናሙና አንዲት ቅንጣት ማግኘት አይቻልም … ጃዋርውያን፤ በቀላውያን፤ ንጉሱጥላሁናውያን አዲሳውያን፤ አራራሳውያን በሚገባው ተልዕኳቸውን አሳክተዋል። በቀላቸውንም በሁሉም መስክ አሟልተዋል። ለዛውም በሚሊዮን የፍቅር ሙላት። ራስን ለማፈረስ የተለገሰ የፈቃድ ዕብንነት ነበር እኔ ጨምሮ ... 

አይደለም ሰው የዱር እንሰሳት ሰላማቸውን አጥተው እንዲህ በእሳት በሚጋይበት አገር ቁጭ ብለህ ጎል እና መረብ መሳቂያነት ነው። ከእንዲህ አይነት የእገታ መሪነት ይልቅ መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ የለት ጉርስ የሚለምን የእኔ ቢጤ በስንት ጣሙ … ነገ እንደ እኔ አስኮባ ይዘው ባይወጡ ይሻላቸዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ ... የውነት ያማል ... 

ኦነጋውያን ይህን የሚያስደርጉበት መሰረታዊ ምክንያት በህጋዊ የመንግሥት ጥበቃ ዓላማቸውን ለማሳካት የመረጡት በአብይ ተቀባይነት ህዝብን አነሁልለው ባሪያ ለማድረግ ነው፤ በሌላ በኩል መሰረት በያዙ ቁጥርም እንዲህ ያልሆነ ትወና በማሰራት የአብይ ሌጋሲን እራቃኑን ራቁቱን ማስቆም እና ህልሙ ተንሳፎ ሹፌር አልባ ማድረግ ነው … በዚህ የተንሻፈፈ መከራ ውስጥ ራስን ለመስጠት መሰናዳት በራሱ እብደት ነው ለእኔ። 

ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል። አማራጮችን ማዬት በማስተዋል ይገባል። ንደት ላይ ስለመሆናች መቀበል ያስፈልጋል። እንደዚህ ዘመን ስልበት ገጥሞንም አያውቅም። ተሰልበናል። 

ስለዚህ አቅም ለማን? አቅም ለምን? አቅም እንዴት? አቅም መቼ? አቅም የት? አቅም ወዴት? አቅም እስተምን የምርምር ማዕከል ማድረግ ህሊና ያለው ዜጋ ተግባር ሊሆን ይገባል። አብሶ በዚህ ግርግር ህዝብን ከህዝብ የሚነጥሉ ዲስኩሮች ታቅቦ አንቴና ከኦነግ አገር አጥፊ ትልም ላይ ማድረግ ይገባል። ኦነግ በስል ገብቶ አገር እዬገዛ ነው ያለው ... በዚህ ውስጥ ግብጽን ማሰቡም አይከፋም። 

የአብይ መንፈስ መዘረፉን እኔ ዛሬ ሳይሆን ሀምሌ ላይ በተከታታይ ጽፌበታለሁኝ። ፌክ የሆኑ ነገሮችን አምኖ መቀጠል ዬዘመኑ የልማታዊ ካድሬዎች ተልዕኮ ሆኖ ሳለ ያን እጸ በለስ በገፍ አድሎ ወይንም እያቀኑ ህልውናን ማስረክብ ግን እብደት ነው ለእኔ።

ለዛውም የአገር ኢትዮጵያ ሥህነ - መንግሥት የሚፈታተን ተግባር ህጋዊ ሆኖ እዬተከወነ እያለ … አሁን እኮ እኛ በቀጨሬ መጨሬው እምንሟገትበት ጊዜም አይደለም። ስለምን የውስጥ ሰላማችን እንዲስተጓጎል ተፈለገ ብሎ ማሰብ ይገባል። 

ህጋዊ እውቅና ያገኘ ሉዓላዊነት ተፈቅዶለት ሙሉ የሎጅስቲክስ፤ ሙሉ ድጋፍ  በአይነት እዬተደረገለት አቅም እዬተገነባለት ሽፋን እዬተሰጠው የኦነግ ፖለቲካ ነው አገር እዬገዛ ያለው። ችግሩ ማቆሚያ የሌለው መሆኑ ነው። አፍሪካንም አካታች ነው በቀጣይነት። 

ናዚ ካደረገው ውጭ አይደለም አሁን ያለው አዬር … ለዚህ ኦነግ ችግር ይፈጥርብኛል ብሎ ያሰበው አማራውን ነው። ይህንም ለማሳካት በስልት ከማናቸውም ወሳኝ የፖለቲካ፤ ወሳኝ ኢኮኖሚ ተቋማት፤ ሚዲያ ቀስ እዬተደረገ ተከልቷል። በአማራ ሥም የተደራጀው ብአዴን አንድ የጉሮሮ አጥንት ተሰክሎት በዛ ቧንቧ ነው የሚተነፍሰው - አቶ ንጉሱ ጥላሁን። ዓመቱን ሙሉ እንሱ ይህን ሲያደራጁ ክልሉ እንግዳ በመቀበል እና በመሸኜት ተጠምዶ ነበር የባጀው። ያ ሲያልቅ ደግሞ እልቂት ... መፈናቀል፤ እሳት ታዞለታል ... 

የአማራን ህዝቡን ሰላም ማወክ ነበር በባዕቱ ሳይቀር ወደ 90 ሺህ ህዝብ ተፈናቅሏል በመተባባር አንዱ እንጨት ሲያቀብል ሌላው ቤንዚን በመሆን። 

እያዬ እዬሰማ … አሁን ማህል አገርን ሸዋን ለመጠቅለል ታክቲክ እና ስትራቴጂው ተጠናቆ በለበጣ ነገር ዓለሙ የውሽማ ሞት እንዲሆን ተደርጓል። የቀረ ያላሰናዱት ነገር ስላላቸው… ለጊዜው ይበቃችሁዋል የያዛችሁን ይዛችሁ ሂዱ የተባለው ... ግን ምልክት ነው ... ልብ ላለው። 

 … አብዩ ያለ ግን የሌለ ነፍስ ነው። ህልም ህልም ነው እኔ የሚመስለኝ የመጋቢት 24 ቀን 2010 ንግግር እና ዛሬ ...

በመጨረሻ ጽዳት ጥሩ ነገር ነው አካባቢን ማጽዳት ጤና ነው። ም ነገሩ ግን የህዝብን ሥነ - ልቦና በዲሞግራፊ ፍልስፍና እዬጨፈላላቅክ አስፓልት ማጽዳት? እእ ...

ይልቅ ይህን እየከፈሉት እዬሸነሸኑት ያለውን መንፈስ አንድ ለማድረግ  ህሊናቸውን፤ ልባቸውን፤ ኩላሊታቸውን መሪዎቻችን ለመጥረግ ቢያስቀድሙ መልካም ነበር ይህን የታይታ የካሜራ እንድርቺ እንድርቺ ነገር ከሚያቅለሸልሹን  ቢተውን ምን አለ?... ግልምት ነው ያለኝ እኔ ... 

ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።